Monday, June 28, 2010

ዲ/ን ተስፋዬ መቆያ ለምን ተቆጣ?

ውድ እህትና ወንድሞቻችን እኛ በምኖርበርት በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሰሞኑን “የተከፈተው” ቤተ ክርስቲያን ላይ መነጋገሪያ እየሆነ ነው። በምድረ አሜሪካ ቤተ ክርስቲያን “መከፈት” አዲስ ነገር ባይሆንም፤ነገር ግን ይሄኛው ለየት ያደርገው በደጀ ሰላም የቤተ ክርስቲያን አመሰራረት በተመለከተ የሀሳብ ልውውጥ መጀመሩ ይመስለኛል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ሁለት ጎራዎችም በተለያየ መንገድ አቋማቸውን ፍንትው አድርገው እያሳወቁም ነው ። አንደኛው ወገን በማንኛውም መንገድ ቤተ ክርስቲያን “ይከፈት” እንጂ “የእግዚአብሔር ቃል ለምዕመን ከደርሰ ችግር የለውም” የሚል ሲሆን፤ሌላኛው ወገን ደግሞ ቤተ ክርስቲያን መመስረት ያለባት “ሐዋርያዊ ትውፊት ጠብቃ የቀደሙት አባቶቻችን ባስቀመጡልን ህግ መሰረት መሆን አለበት” የሚል ነው። ታድያ የትኛው ነው ትክክል? መልሱን ለአንባብያን እንተወው።

በመጀመሪያው ወገን የተሰለፈው በአከባቢያችን ካሉት ታላላቅ ሰባኬ ወንጌል አንዱ ዲያቆን ተስፋዬ መቆያ በ06/10/2002 ዓ.ም በዕለተ ሰንበት ስብከቱ አውቆም ይሁን ሳያውቅ አቋሙን ገልፆዋል። “ቤተ ክርስቲያን የሚከፍተው ማን ነው”? የሚለውን በደጀ ሰላም የቀረበልን ፅሁፍ “ቤተክርስቲያን መስፋፋት ያለባት በህጉና በሥርዓቱ መሠረት መሆን አለበት”፤ በሚሉ ወገኖች ተባዝቶ በአካባቢያችን ላሉት አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት መሰራጨቱን ይታወሳል። ከላይ ሥሙን የጠቀስኩት ሰባኪ ወንጌል በተሰራጨው ጽሑፍ  ተቃውሞ ያሰማበት ትምህርቱ ላይ “እንግዲህ የእግዚአብሔር ቃል ሲነገር ደስ የማይላችው አሁን ስትወጡ በር ላይ ይጠብቋችኋል፣ቤተ ክርስቲያን ብትመሠረት ምን ችግር አለው? የምዕመኑ መብዛት ለምን አላስደሰታቸውም?” በማለት በይፋ አቋሙን አሳውቆዋል። “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩዋችሁ ዋናዎቻችሁን አስቡ” ይህ በቅዱስ መጽሐፋችን የተቀመጠልን ቃል ነው። ታዲያ የእኛ ዋናዎቻችን ሐዋርያት፣ 318ቱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እና ከዚያ በኋላም የተነሱት ዋናዎቻችን አበው ስለ ቤተ ክርስቲያን አመሠራረት ያስረከቡን ህግ ለምዕመናን ማድረስ ወንጀሉ ምንድ ነው?። የቤተ ክርስትያን አመሠራረት ታሪክ ለሰባኬ ወንጌል ማስረዳት “ለቀባሪ አረዱት” ስለሚሆንብን ትተነዋል። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ወንጌል እንዲያዳርሱ ለምን ፲፪ቱ ሐዋርያትን መረጠ? ሁሉንም ነገር በሥርዓት መሆን አለበትና እሱ ራሱ የቤተ ክርስቲያናችን መስራች ጌታችንና መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶ ሥርዓት መስርቶልናል። ሐዋርያት እንዲሁም በሐዋርያት እግር የተተኩ አበው ቤተ ክርስቲያን እንዴት መመስረት እንዳለባት ሥርዓት ቀምረው አሰምጠውልናል። እንግዲህ ሥርዓቱን መጠበቅ እንኳን ባንችል ቤተ ክርስቲያን ሥርዓቷ ይጠበቅ ብለው የሚጮሁትን መቃወም ግን “የመውጊያውን ብረት መቃወም” እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

ዲያቆን ተስፋዬ በተሰራጨው ወረቀት ላይ ለምን የተቃውሞ ድምጽ አሰማ? መብቱ ነው እንዳንል ሃይማኖት ነው። ምክንያቱም በሃይማኖት ስንኖር መብቶች እንዳሉን ሁሉ ግዴታዎችም አሉብን። በዚሁ በዕለተ ሰንበት ትምህርቱ “እኛ የምንጨነቀው የሰዎችን ወንበር ለማስረዘም አይደለም” ሲልስ ምን ለማለት ፈልጎ ነው? መልሱን እሱ ይመልሰው። የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕጓ ጠብቄ እጓዛለሁ ካልን በመንበሩ የተቀመጡትን የመቀበል ግዲታ አለብን:: ይህ ስንል ግን በመንበሩ ያሉ ሰዎች ቅዱስ ወይም ፃድቅ ናቸው ማለታችን አይደለም። የተቀመጡበት ቦታ ወይም መንበሩ ግን ቅዱስ ነው፤ በማለት ቤተ ክርስቲያናችን ታስተምራለች። እንግዲህ ሰሙኑን እየተንሸራሸረ ያለው ውይይት የሥልጣን ወይም የወንበር ጉዳይ አይመስለንም:: ክርክሩ ሃይማኖታዊ ነው። በእኛ ዘመን በመንበሩ ወይም “በወንበሩ” ያሉ ሰዎች መንበሩን እንደ ስልጣን እንኳ ቢጠቀሙበትም፤ እኛ ደግሞ የቀደሙት አስተዋዮቹ አበው ያስቀመጡልን ድንበር ሳንጥስ የተጣለብን ኃላፊነት መወጣት አለብን ብለን እናምናለን። መንበሩን እንደ ስልጣን የተጠቀሙበት ሰዎች ነገ ይጠየቁበታል። በሃይማኖት እኔ እሻላለሁ የሚል ትምህርት የለም፤ በአካባቢያችን ግን ሁሉም እኔ እበልጣለሁ ወይም እኔ እሻላለሁ እያለን በራሳችን ፈቃድ እየሄድን ነው። በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ትልቁ የስልጣን አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ሆኖ ሳለ፤እኛ እንበልጣለን ወይም እኛ እንሻላለን የሚሉ ወገኖች “ቦርድ”ትልቁ የስልጣን አካላቸው ነው። ሰባኪያኑም “ለቦርዱ” ወንበር እውነትን ሲቃወሙ እያየናቸው ነው። ይህ ግን በታሪክ የሚያስወቅስ ሥራ መሆኑ ልብ በሉ፤አንድ ቀን እውነት መውጣቱ አይቀርምና።

ቤተ ክርስቲያን መካከላዊነቷን ጠብቃ እዳትስፋፋ ለምን ተቃውሞ ገጠመው? ለክፍፍሉስ ተጠይቂው ማን ነው? የራስ ገዝ አስተዳደር አስተምሮው የማን ነው? የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የራስ ገዝ አስተዳደር ወይም ገለልተኛ አስተዳደር ትምህርት ትደግፋለችን? በእነዚህ ጉዳዮች ዙርያ መወያየት መጀመር አለብን ብለን እናምናለን። እንግዲህ ሰሞኑን በአካባቢያችን የተጀመረው የመወያያ አጀንዳ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት “የራስ ገዝ አስተዳደር” ወይም በተለምዶ አጠራሩ “ገለልጠኝነት” ይቻላል ወይስ አይቻልም? ወደሚለው ጥያቄ እያመራ ይመስላል። እዚህ ላይ የወገንተኝነት ወይም ደግሞ ፖለቲከኞች እንደሚሉት ጎራ ለይቶ መሰለፍን መነሳት ያለበት አይመስለንም። በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ የቀደምት ትምህርቱ ምንድ ነው? የመካከላዊ አስተዳደር መስራችሁስ ማን ነው? የመካከላዊ አስተዳደር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ታሪኩ ምን ይመስላል? በቤተ ክርስቲያን ታሪክና እውነታዎች ላይ ተመርኩዘን ብንወያይ መልካም ይመስለናል።

እንግዲህ እንደ ዲያቆን ተስፋዬ አባባል ከሆነ ምዕመናን ቤተ ክርስቲያን የገጠማት ፈተና መስማት የለባቸውም:: የእግዚአብሔር ቃል በማንኛውም አካሄድ ተኬዶ ከተሰበከ በቂ ነው፤ የሚል አቋም ከተያዘ አካሄዱ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት አደገኛ ነው። ለዲያቆን ተስፋዬ አንድ ጥያቄ መጠየቅ እንፈልጋለን በዚሁ ዕለት ስብከትህ ላይ “ጭንቀታችን የቤተ ክርስቲያን አንድነት ነው” በማለትም ተናግረሀል። ይህ የሁሉም የተዋሕዶ ልጆች ጭንቀት ይመስለኛል፤ጥያቄያችን ግን የአንድነት መሠረት መሆን ያለበት ምን ላይ ነው? አንድነቱስ ሊመጣ የሚችለው የቤተ ክርቲያን መንፈሳዊ አስተዳደራዊ መዋቅር ጠብቀን መኖር ወይስ በሌላ? መልሱን እንጠብቃለን። አባቶቻችን እኮ ለ1660 ዓመታት መንበረ ማርቆስ ስለተመቻቸው አይደለም መዓከላዊነትና መንፈሳዊ አስተዳደርን ጠብቀው የኖሩት። “አሌክሳንደሪያ አካሄዷ ትክክል አይደለምና እንገለል” በማለት የአመፃ አድማ አውጀው ከአሌክሳንደሪያ አልተለዩም፤ በጥበብና በአስተዋይነት ሐዋሪያዊ ትውፊት ጠብቀው ኖሩ እንጂ። እዚህ ላይ ማለት የምንፈልገው ሥህተቱ ለምን ተፈጠረ? አይደለም። በተለያዩ ምክንያቶች በአካባቢያችን ሥህተቶች ተፈጽመዋል። ጥፋቱም እንደ ሥህተት ተቀብለነው ለመፍትሄ ግን ሩጫ መጀመር አለብን ብለን እናምናለን። ነገር ግን የተፈጠረው ጥፋት ትክክለኛ አካሄድ ነው፤ በማለት ትምህርት ፈጥረንለት የምንጓዝ ከሆነ ተልኮው ለቤተ ክርስቲያን አንድነት አስጊ ነው።

15 comments:

Unknown said...

as far as i know he hase got a posetive view towards our church but that country called America can chage anyone i hope he is not one of them

Anonymous said...

I attended one Wednesday Gubae and Iwas so disappointed when Kidist Mariam Betekristian advertises Drama. The advertisement has been going on for a while what really upsets me is showing clip of peple pushing each other to watch that drama in Ethiopia.I don't know what got in to them /bete ye tselot bete tebalalec/ yemilewun tiks yeresu yemeselal. I don't know where to go. Who to talk to. Please tell me if there is any thing tod to stop this kind of crime of yeabat bete

Anonymous said...

ከእነዚህም አንዳንዶች ስተው፥ የሚሉትን ወይም ስለ እነርሱ አስረግጠው የሚናገሩትን ሳያስተውሉ፥ የሕግ አስተማሪዎች ሊሆኑ እየወደዱ፥ ወደ ከንቱ ንግግር ፈቀቅ ብለዋል።

Anonymous said...

ለመሆኑ እዚህ እየተመላለሰ ሲሰራ ታክስ ይከፍላል::

Anonymous said...

everyone should have pray for ortodox tewahido!

Anonymous said...

diakon .pls chose only one religion.even is not god for you .waw ametsegna tiwlid,,,,,,,,,,?

Dagneslaveofmary said...

wey sewu anadin wey erasachin anidin tilina kirikir. huligize, min yihonal yihen kemititsifu sile Amalakachin, Sile Kidist Enatachin Feker tsifachu libonachin befekrwa bimeset. Egzihabiher yimiyastewul libona yadilen.

Unknown said...

WE NOW HIM

asbet dngl said...

everyone should have pray for ortodox tewahido!

asbet dngl said...

everyone should have pray for ortodox tewahido!

Esachew said...

መቼ ተለመደና ከቀበሮ ዝምድና ቀሲስ ለቡኬ

Unknown said...

lebetecrstiyan melchamun temegnulat enge yerasachhun hasab becha lemarramed atmokeru

Anonymous said...

Ι dо accept аѕ tгuе with all the concepts уοu hаνe prеsentеԁ for yοur post.
Theу aгe very cοnvincіng and cаn сertainly worκ.
Stіll, the рοѕts аre vеry quicκ for novicеs.
Coulԁ you please eхtеnd thеm a bit from ѕubsequеnt tіmе?
Thanks for thе ροst.

Here iѕ my ωеbpagе :: what is the best way to lose weight, diet exercise log, cumin lose weight, over weight
Feel free to visit my web site weightloss goals, body weight, diet tips, how many calories should i eat to lose weight, weight loss vancouver, weight loss surgery

Anonymous said...

Heya і'm for the primary time here. I found this board and I find It really useful & it helped me out much. I'm hoping to
give οne thing bacκ and аid othеrs suсh as you helped me.


Feеl frеe tо surf to my page chatroulette online users
My site ; chatroulette online

Anonymous said...

Hello there, ӏ diѕcovered your web site by mеanѕ
of Gοoglе whilst seаrching foг
a relаted ѕubject, yοur sіte camе up, it appеarѕ great.
I have boοkmarked it in my google bookmаrks.

Hі theгe, simрly becаme alert to yоur blοg via Google, and located that it's really informative. I am gonna watch out for brussels. I will be grateful when you proceed this in future. Lots of other people shall be benefited out of your writing. Cheers!

my web page ... Pubic hair
My blog post ; ways to remove acne