Friday, July 2, 2010

“ገለልተኛ ”፣ "ስደተኛ” ፣ ”እናት” ቤተ ክርስቲያን

“ገለልተኛ” ፣"ስደተኛ"፣ “እናት” ቤተ ክርስቲያን የሚሉ በወቅቱ እየተዘወተረ የሚነገሩ በቤተ ከርስቲያናችን ላይ ተቀጽላ ሥያሜዎች ናቸው። ቤተ ክርስቲያን ያለችበት ነባራዊ ሁኔታ ለውይይት ሲቀርብ የማያስደስታችው ወገኖች አሉ፤ እንደውም "ሚስጥራቸን በአደባባይ ማውጣት ይሆናል" ብለውም ያስባሉ። ሚስጥርነቱ  ምን ላይ ነው?የተለያየ ቅዳሴ መቀደሳችን እንደሆነ ያመኑት የተርዋሕዶ ልጆች ቀርቶ ያላመኑትም ቢሆን አውቀውታል። ተቃውሞው ይህ ብቻ አይደለም ቤተክርስቲያን ስላለችበት ሁኔታ መነጋገር "ልዩነትን መስበክ ነው"፤ በማለትም የሚያስወሩ ወገኖችም አልጠፉ። ተለያይተናል እኮ ፤ከዚህ በላይ ልዩነት ምን ይመጣል? ጥያቄው “ምን ብናደርግ” ወደ አንድነት መምጣት ይቻላል?የሚል ነው። መለያየታችን ግን የአደባባይ ሚስጥር ነው።

በአንዲት ቤተ ክስቲያን የምናምን የተዋሕዶ ልጆች ቤተ ክርስቲያናችን በተለይም እዚህ ባለንበት አካባቢ የገጠማት ፈተና  የምንወያይበት መድረክ ያስፈልገናል ብዬ አምናለሁ። እውቀቱ ባይኖረኝም ሀሳቡ ሥላለኝ ታላላቅ ወንድሞቼን በማማከር ለቤተ ክርስቲያኔ ይጠቅማል በማለት ይህ የጡመራ መድረክ ተጀምሮዋል። በዚህ የጡመራ መድረክ ላይ በአካባቢያችን ሥላለችው ቤተክርስቲያን ችግሮች እና የመፍትሄ ሀሳቦች ለማቅረብ ይሞከራል።
የጡመራ መድረኩ ዓላማ፦
1.    ጥንታዊትና ሐዋሪያዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአካባቢያችን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ እኛ ልጆቿ ተመሳሳይ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖረን የተለያዩ የመወያያ ሀሳቦችን ማቅረብ።
2.    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማዋ፣ መንፈሳዊ የአስተዳደር መዋቅሯ፣ቀኖናዋ በአካባቢያችን ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ጥረት ማድረግ።

6 comments:

desa said...

yes it is! the gap is_______________________!

Anonymous said...

THE usa ORTHODOX CHURCH IS KNOWN ORGANIZATION FOR PROFIT.THOSE HODAM "FATHERS" AND FEW BOARD MEMBERS ARE ACTIVELY INVOLVED IN THE DRAMA.lUCRATIVE SOURCE OF MONEY TO PAY THEIR PERSONAL MORGAGE!!! IT'S TIME TO STOP GIVING PENNY!.ONCE THEY DON'T HAVE THE FINANCE THEN NO MORE NONSENSE DRAMA AND DIVISION.I WOULD RATHER CONTINUE HELPING THOSE RURAL CHURCHS IN ETHIOPIA.

Anonymous said...

I have seen this page many times. but, No one who gives, any comments

what do you think about ?

Anonymous said...

THE BEST SOLUTION TO COME TO UNITY IS FINANCIAL SANCTION TOWARDS SOME usa ORTHODOX CHURCHS.SAY NO EVEN TO PENNIES!!!AND THEN THOSE HODAM PEOPLE WILL COME BACK TO THEIR MINDS.nooooooooo EVEN TO PENNIES

Anonymous said...

በቅድሚያ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድነት በማሰብ ይህንን ብሎግ ላዘጋጁ ሰው
የእውነት አምላክ ሁልጊዜ በእውነት ሥፍራ እንዲቆሙ ያግዞት እላለሁ፡
ለተነሳው የቤተ ክርስቲያኗ መለያየት ችግር ምንጩ እራስ ወዳድ የሆኑ ጳጳሳትና
ካህናት መነሻ ሆነው እስከአሁንም ጥርጊያውን እያቀኑ መጓዛቸው አይናችን እያየ
ጆሮአችን እየሰማ ነው እንዲህ አይነቱን መጥፎ ታሪክ በእውነት ላይ ቆመው
እውነትን የሚመሰክሩ እና የሚቀበሉ ጳጳሳት፤ ካህናት፤ ዲያቆናት (ሰባክያን)
እስከሌሉ ድረስ ሐሰቱ እውነት እስኪመስል
በበሽታው የተጠቁ ጥቂቶች አይደሉም፡ ከዚህም ባሻገር ቫይረሱን የሚያሰራጩ ሰባኪያን ነን ባዮች
በእውነት ቦታ እስከአልቆሙ እና እውነትን እስካልመሰከሩ ድረስ ሐሰት በተባለው በሽታ
ተጠቂዎቹ እየበዙ መሄዳቸው አይቀሬ ነው ፡ በአንፃሩም “ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ”
እንደተባለ እውነትን በመፈልግ እናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት ሐዋርያዊት እና ኦርቶዶክሳዊት
መሆኗን አምነው የሚጓዙትን ስንመለከት ደግሞ በእጅጉ እንኮንራለን፡፡ ሁላችንንም በእውነት ቦታ
ስለ እውነት ያቁመን፡፡

Anonymous said...

ስለ እውነት እንጂ ስለውሸት ስለፖለቲካ አንመስክር ቤተክርስቲያናችን የአውነት መነገሪያ ናት ክርስቴር የሞተላት ስለእውነት የመሰከረላት ናት እባካችሁን እጃችሁን ከቤተክርስቲያናችን ላይ አንሱ ገዳማችንን አትንኩብን እኛ ብንደክምም እኛ ብንተኛም አምላክ ለቤቱ አይተኛም፡፡