Friday, July 9, 2010

የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በዲሲ ምን ይመስላል?

በተለምዶ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ብላ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሀገረ ስብከት ያዋቀረችው ወደ ፲፭ (አሥራ አምስት) ክፍለ ግዛቶችን (እስቴቶች) ይደርሳሉ ። ነገር ግን በሀገሩ መንግስት ስያሜ መሰረት ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚባሉት ዲሲ፣ ቨርጂኒያ እና ሜሪ ላንድ ናቸው። ይህ ጽሑፍም የሚዳሥሰው በተዋቀረው ሀገረ ስብከት ሁሉ ሳይሆን በሀገርሩ መንግስት ስያሜ መሰረት በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ብቻ ይሆናል።

በዚህ አካባቢ የሚኖሩ የተዋሕዶ ልጆች ብዛት በእርግጠኝነት መናገር ቢያዳግትም፤ በግምት ግን ከመቶ ሺህ በላይ እንደሚሆን ብዙዎች ይናገራሉ ምክንያቱም አጠቃላይ የኢትዮጵያውያን ብዛት ሩብ ሚሊዮን ይሆናሉ ተብሎ ይገመታል። ስለዚህ ከመቶ ሺህ የተዋሕዶ ዕምነት ተከታዮች መሀከል “ምን ያህሉ ወደ ቤተ ክርሲያን ይሄዳሉ”?  የሚለውን ጥያቄ እርግጠኛ ሆኖ ለመመለስ ያስቸግራል፤ነገር ግን ባሉት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሚሳለም ሰው ቢደመር ግን ከ፲፭(አስራ አምስ) ሺህ አይበልጥም። ይህ እንግዲህ ምንም እንኳ በጥናት የተደገፈ ሳይሆን በእይታ የተገመተ ሲሆን በየ ሳምንቱ ዕለተ ሰንበትን ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚሄድ የዕምነቱ ተከታይ በመቶኛ ሲሰላ 15% ብቻ ነው።

ታዲያ 85% የዕምነቱ ተከታዮች ወደ ቤተክርስቲያን የማይሄዱበትስ ምክንያት ምንድ ነው? ይህ ትልቅ ጥናት የሚያስፈልገው ጥያቄው ቢሆንም አንዳንድ ምዕመናን ግን የራሳቸው ምክንያት ያስቀምጣሉ።  አንደኛው ምክንያት በተለያየ የእድሜ ክልል ልጆች ያሉዋቸው ወላጆች ልጆቻቸውን የሚያካትት ተገቢውን አገልግሎት ስለማያገኙ በሰንበት እቤታቸው ለመቀመጥ እንደሚገደዱ ይናገራሉ። እነዚሁ ወላጆች ሲናገሩ “እንደውም ልጆቻችንን ይዘን ስንሄድ አገልግሎቱን ስለማያውቁት ወይም ቋንቋውን ስልማይገባቸው ይሰላቻሉና በቅዳሴ ሠዓት ቤተ መቅድስ ውስጥ መነጫነጭ፣ ማልቀስና መሯሯጥን ይመርጣሉ። በዚህም ግዜ ካህናቱ ልጆቻችን እንድኒዝ መመሪያና ማስፈራሪያ ያስተላፋሉ ስለዚህ ልጆቻችንን ይዘን አንድ ክፍል ውስጥ ተቆልፎብን እንድንቀመጥ እንገደዳለን፤ ሥርዓተ ቅዳሴውም ቆመን ማስቀደስ አንችልም” በማለት አምርረው ያለውን አገልግሎት ይተቻሉ።  ይህ እንግዲህ ቤተ ክርስቲያናችን በ፵ (በአርባ) እና በ፹(በሰማንያ) የተጠመቁት ልጆቿን በአግባቡ ለመያዝ በዚህ አካባቢ ምንም የተሰራ ሥራ አለመኖሩን ያስገነዝበናል። ቤተ ከርስቲያን ዘመንን እየዋጀች እንደውም  ከዘመኑም ቀድማ ትውልድ የሚያስፈልገውን አገልግሎት መስጠት እንዳለባት አበው ሊቃውንት ያስተምራሉ። ነገር ግን በአካባቢያችን ይህ ዘመንን የመዋጀት ሥራ እየተገበረ አይደለም እጅግ በጣም ኋላ ቀር ሆነናል። ሌሎች በዕምነት የሚመስሉን አሐት አቢያተ ክርስቲያናት ግን ከኛ ተቃራኒ ናቸው፤ ከእነሱ ከተወለዱትም በተጨማሪ ለሌሎች ዜጎች የማዳን ሥራ እየሰሩ ክርስትናን እየሰበኩ እያየናቸው ነው። እንደውም ለልጆቻቸው መማሪያም በየ እድሜ ደረጃቸው ሥርዓተ ትምህርት ቀርፀው እስከ ኮሌጅ ድረስ የካፓስ ሚኒስትሪ (የግቢ ጉባኤ) መስርተው ልጆቻቸውን ይከታተላሉ። የእኛ ቤተ ክርስቲያን ግን በተቃራኒው እንኳን ሌሎችን አሳምኖ ለማምጣት ቀርቶ ስመ ክርስትና የሰጠቻቸው የራሷ ልጆች የሚደርስላቸው ስላጡ ከቤተ ክርስቲያን እየራቁና መጨረሻም እየጠፉ በዝምታ እየተመለከትን ነው።

ሌላው ሁለተኛው ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ያለው ሥርዓት አልበኝነት ያልጣማቸው ወገኖች የሚያቀርቡት ጥያቄ ስላልተመለሰላቸው ከቤ ተክርስቲያን ርቀው እቤታቸው ለመቀመጥ የተገደዱ ናቸው። እነዚህ ወገኖች ሲናገሩ “ሄዶ የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት ከማየት ቤት ውስጥ ውዳሴ ማርያም ማድረስን እንመጣለን” ይላሉ። እንደውም “በየ ቦታ የሚታየው የቦርድ ሥርዓት አልበኝንትና ፈላጭ ቆራጭነት ከማየት እቤታችን ብንቀመጥ ይሻለናል” በማለት ይናገራሉ። ይህም ብቻ አይደለም “በዚህ አካባቢ ያሉት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እኮ ሚስጥረ ቤተ ክስቲያን ከማፋለስም አልፎ ቀኖና ቤተ ክርስቲያይንም የሚጥሱ ናቸው” በማለት አጥብቀው ተቃውሞም ያቀርባሉ። በዚህኛው ምክንያት እቤት የተቀመጡ ወገኖች ግን በቁጥር ከመጀመሪያው ጋር ሲነፃፀር በጣም አናሳ ናቸው።

ሶስተኛውና የመጨረሻ ደግሞ በሥራ ጫና ምክንያት ከቤተ ክርስቲያን የራቁ ወይም ወደ ቤተ ክርስቲያን  የማይሄዱ ናቸው። እዚህ አካባቢ ያሉት አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት በአጠቃላይ ከአንዱ ወይም ከሁለቱ በስተቀር አገልግሎት የሚሰጠው ዕለት ሰንበትን ጠብቆ ብቻ ነው። እንደው የሰንበቱም አገልግሎት አብዛኛዎቹ በኪራይ ቤት ሥለሆኑ በሠዓት ይገደባሉ። በዕለተ ሰንበት ጠዋት ሥራ ላይ ሆነው ከሠዓት በኋላ ለመገልገል እንኳ ቢፈልጉ በዚህ ሠዓት የሚሰጥ አገልግሎት ሥለማያገኙ ከቤ ተክርስቲያን ለመራቅ ይገደዳሉ። አሁንም ምሳሌ የሚሆኑን ሌሎቹ በእምነት የሚመስሉን አሐት አቢያተ ክርስቲያናት ግን በዕለተ ሰንበትም፤ እንዲሁም ከዕለተ ሰንበት ውጪ ባሉት ቀናት የቤተክርቲያኒቱ አባላት እንዳመቺነቱ የሚፈለገውን አገልግሎት ይሰጣሉ። የእኛ ቤተ ክርስቲያን በተቃራኒው በአንድ ቀን ያውም በተወሰነ ሠዓት የተገደበ አገልግሎት ብቻ በመስጠት ላይ ሥለሚገኙ፤ ብዙዎቹ የእመቱ ተከታዮች በሚያመቻቸው ሠዓት ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት ባለመቻላቸው ከቤተ ክርስቲያን ርቀዋል። 

እንግዲህ ቤተ ክርስቲያን እዚህ አካባቢ የ፴(የሰላሳ) ዓመታት እድሜ አስቆጥራለች ቢባልም፤ ነገር ግን  ዘመኑን ዋጅታ ልጆቿን እየጠብቀች አይመስልም። ለዚም ምክንያቱ ቤተ ክርስቲያን በዚህ አካባቢ ማዕከላዊ አስተዳደር ባለማጠናክሯ እንዲሁንም ልጆቿም በጊዜያዊ ጥቅምና በዘር ተለያይተው መተያየትና መነጋገር አለማቻላቸው ለአገልግሎቱ  ትልቅ እንቅፋት መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ።

5 comments:

Anonymous said...

It's a big"hit and run" private business.The church seems not to have a clear long term plan.I see churchs divided by administration,ethnicity,chronicity etc.I don't buy the idea of having such volume / number of churches.What we lost is unity and peace in our church, not the flourishing number of churches in every corner.Therefore all the services are waste ,nonsense which ultimately result in "resistant strains/follower".

ሲላስ said...

ውድ ቀዳማዊ ኣቤል በተመሰገነ ስሙ ሰላምታዪ ይድረስህ።
ይህንን ጉዳይ ኣንስቶ መወያየቱ መልካምነቱ ኣጠያያቂ ባይሆንም ኣሳዛኙ ጉዳይ ግን በኣካባቢው ያለነው የአምነቱ ተከታዮች ስህተቱ ምኑ ጋ አንደሆነ ጠንቅቀን ከተረዳነው ኣመታትን ኣስቆጥረናል።
መጀመረያዉኑ ቤተ ክርስቲያኒቱን ይመራሉ ተብለው በቦርድ ስም ውስጧን የሚያተራምሷትን ግለሰቦች አስቲ በጥሞና አንመልከታችው ወይ የወደቀው መንግስት ጋሻ ጃግሬ የነበሩና አጃቸው በንፁሃን ደም የታጠበ ፣የህዝብን ንብረት ዘርፈው ከህግ ፊት ያመለጡ ፣ሌሎቹ ደግሞ ራሳቸውን አንደ ቁጥር ኣንድ የፖለቲካ ተቃዋሚ (የሚቃወሙት ነገር ምን አንደሆነ ሳያውቁት ማለት ነው) አንግዲህ አነዚህ ሁሉ ስብስቦች ናቸው በየኣብያተ ክርስቲናት ውስጥ ተሰግስገው አንደመያዣ ኣንቀው የሚጫወቱባት። ኣማኙ ይህንን ኣያውቅም ወይ ? በትክክል ያውቃል። ታድያ ችግሩ ምንድን ነው ካልን የቤተ ክርስቲን ሥር ኣት ለምን ይፋለሳል ብሎ ጥያቄ ለሚያነሳ ኣማኝ ወድያውኑ ወያኔ የምትለዋ የዘመኑ ምርጥ ስም ትለጠፍለታለች።ይህች ታድያ ማሽማቀቂያ መሆኗ ነው ይህን ተቁቁሞ ለሞገታቸው ሰው ደግሞ የነሱን ለቅሶ የሚያለቅሱ የነሱን ጩኅት የሚጮሁላቸው አንካን ጋዜጠኛ መሆን ኣይደለም ጋዜጣ አንብበው የማያውቁ ኣላዋቂዎች ከኛው በሚወረወርላችው ፍራንክ ሚዲያውን ይዘው አኛኑ መልሰው ሲያበጣብጡን ይህንን መቆጣጠር አስክንደክም ድረስ ኣሽመድምደውናል።
ጎበዝ የወንጌሉን ቃል አንደመሻር ኣይቆጠርብኝ ለኣብቶቻችን ልንፀልይ ይገባናል። አንሱን መከተል ሳይሆን አኛን መከተል ሳይኖርባችው የቀረ ኣይመስለኝም ከኣማኙ ውስጥ የሚያስቀና የዥፀሎት ህይወት ያላችው ብዙዎች ኣሉና። ለኣንድነት አንፀልይ በመለያየታችን የተጠቀምነው የለም። ገንዘባችን ለወንጀልኞች ኑሮ መግፊያ የሆነው።ቤተ ክርስቲያናችንን ከፖለቲከኞች አናፅዳ ። ወስብሃት ለአግዚኣብሄር።