Wednesday, July 14, 2010

በእውነት የፓትርያርኩ ሥርዓት አልባ መሆነ እኛን ከእውነተኛ መንገድ እንድንወጣ አስተዋፆ አለውን?

 “እናንተ እኮ ዝም ብላችሁ ነው የምትለፉት፤ የእኛ አባቶች ይሄንን አውቀው ነው ገለልተኛ የሆኑት” በማለት አንዲት እህቴ በምታገለግልበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉትን ካህናት እያመፃደቀች፤ እኔም በቤተ ክርስቲያን ላይ ያለኝን አቋም እንድቀይር ሽንጣን ገትራ ተከራከረችኝ።ይህ እንግዲህ ሰሞኑን በዜና  እየተሰራጨ ያለው የፓትርያርክ ጵውሎስ ሥርዓት አልበኝነት ምክንያት በማድረግ ነው ክርክሩ የመጣው። በእውነት የፓትርያርኩ ሥርዓት አልባ መሆነ እኛን ከእውነተኛ መንገድ እንድንወጣ አስተዋፆ አለውን? የሚለው ጥያቄም ተደጋግሞ ይነሳል።   ምንም እንኳ ፓትርያርኩ ከህግ ውጪ ሆነው ቢንቀሳቀሱም እኛም የእርሳቸው ፈለግ ተከትለን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያን መጣስ ተገቢ ነውን? እንግዲህ ከላይ የጠቀስኳት እህቴ “የእኛ ገለልተኛ አባቶች ትክክል ናቸው” አለችኝ። እውነት ትክክል ናችውን? መልሱን ለአንባቢው ልተወው።

በቤተ ክርስቲያናችን የአባ ጳውሎስ ሥርዓት አልበኝነት የተጀመረው ዛሬ ባይሆንም፤ሰሞኑን የተፈጠረው ግን እስከ ዛሬ ድረስ ከነበረው የከፋ መሆንኑን ግልጽ ነው። ይህን ተመርኩዛ ነው ልጅቱ “ገለልተኛ” ካህናትን  መርጣ እኔን የተቃወመችኝ። የፓትርያርኩን ተግባር መቃወሟ ትክክል ናት ምክንያቱም ብዙኋኑ እውነተኞች የተዋሕዶ ልጆች  እየተቃወሙት ያለ ጉዳይ ነውና። ተቃውሞው ግን “ገለልተኝነትን” የሚያጠናክር መሆን የለበትም።

የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች ተፈጻሚ አለመሆን፣ የፓትርያኩ ሥርዓት አልባ መሆን እና እንዲሁም ደግሞ አንዳንድ የቅዱስ ሲኖዶስ አባለት ሥርዓቱ ከሚያዘው ውጪ እኛ አካባቢ እየመጡ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት እና መንፈሳዊ አስተዳደር እንዳንናገር ከፍተኛ ፈተና እየሆኑብን ነው። እኛ ግን የምንከተለው “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩን ዋኖቻችንን” ስለሆነ የፓትርያኩ ሥርዓት አልበኝነት ሆነ የሌሎችም እንቅስቃሴ ቢሆን ከእውነት መንገድ ሊያስወጣን አይችልም። አቡነ ጳውሎስ እያደረጉት ያለው በደልም በመሸሽ  የየራሳችን ጎጆ ቅየሳ “ገለልተኛ” ሊያደርገንም አይችልም። የፓትርያርኩ ተግባር ግን ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይጠበቅ፣ ቤተ ክርስቲያናችን አስተዎቹ የቀደሙት አባባቶቻችን እንዳስረከቡን እኛም ለልጆቻችን መንፍሳዊ የአስተዳደር መዋቅሯን ጠብቀን እናስረክብ ብለው ለሚጮሁ ወገኖች ከፍተኛ ፈተና መሆኑ መሰመር ያለበት ጉዳይ ነው።

እግዚአብሔር ተዋሕዶ  ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን

12 comments:

Anonymous said...

Rule is already broken . it is almost 18 years. as loong as EPdRF in power , Abbaw will stay for ever until he dye or ?

Anonymous said...

Those independent or Geleltegna Churchs are among the worst place to practice religion.It's a lucrative and big buisness in western worlds.That's why U see a number of private owned churchs by different names all over the corners. The board members and those synthetic Abatoch who run the buisness don't care about the rules and regulation of ortohodox churche.As long as they get money(HODAM HULA!!!) they don't care about christianity .Of course some of the HODAMs are capable of getting pocket money to send their children to private school,paying personal morgage and to the extent building other private buisness.It's not only Abune Paulos who should be blamed at this point .We all should start questioning how those independent church people managing our money!!!Please ask where your money is whenever U go to Church.No More Silence!LEBA HULA!!!

Anonymous said...

I think it has wreten by oner (himself)of site

Anonymous said...

I think it has wreten by ouner of site

Anonymous said...

በጣም የሚገርመው ነገር የዚህ ብሎግ ባለቤት ማን ይሆን እያልኩ ራሴን እየጠየኩት ለነበረው ጥያቄ ጥሩ እና በቂ መልስ አገኘሁለት። ወንድሜ ሆይ ይህንን በማድረግህ ባላዝንብህም አዝኘልሀለሁ ደግሞም ታዝቤሀለሁ። ያልተናነጽበትንና ጉንጭ አልፋ የነበረውን ወሬያችንን እዚህ ላይ እንደ ደህና ነገር ቆጥረህ እዚህ ላይ ታወጣዋጣዋለህ? በእውነቱ በጣም ያሳፍራል። የሚለጠፍ ነገር ጠፋ፤ አለቀብህ እንዴ? በትችል አንባቢወችህ ዋጋ ሰጥተው ሊያነቡትና ሊማሩበት የሚችሉበትን የተሳለ ነገር ብትለጥፍ የሚሳል ይመስለኛል። ብሎግህ ዋጋ ቢስ እንዳይሆንብህ እሰጋለሁ፤ በዚህ ከቀጠልክ(በጔዳው የተወራውን ሁሉ የምትለጥፍ ከሆነ) አይቀርልህም። ለእኔ ግን ጥሩ ትምህርት ሆነኝ ከማን ጋር ምን አይነት ወሬ ማውራት እንዳለብኝ። መቸም ለራስህ ብቻ አንብበህ እንደማታስቀረው ተስፋ አለኝ፤ ዳሩ ለጠፍከው አለጠፍከው ሁሉም አንድ ነው ለእኔ። እህህህም አሁንም ደግሜ እለዋለሁ በእውነቱ በጣም ነው የታዘብኩህ ለካስ ያለ ነገር አልነበረም እንደዛ ስታስለፈልፈኝ የነበረው! ስለእውነት ግን አንተ እንዳልከው አቋምህን ለማስቀየር አልነበረም ንግግራችን የተጀመረው፤ የጽሁፍህ ማጣፈጫ መሆኑ ነው እንዴ ይገርማል ወይ ጉድ እኛው እርስ በራሳችን ???? ከማን ጋር ይሆን ያለ አንዳች ስጋት የልብን ገልጦ ማውራት የሚቻለው???? አንደበታችንን ልንጠባበቅ?? በጣም ያሳዝናል። ወንድሜ ሆይ በነገር ሁሉ ጌታ ማስተዋሉን እንዲሰጥህ እመኝልሀለሁ። ሌላማ ምን እልሀለሁ???

Anonymous said...

ena min maletish new EHITACHIN? If u are from our BET, u should face this critic!!! Lemin tiferiyalesh? What secrets have you in ur mind? If you have a reasonable stand, lets reason it together and follow it. But if you are following the WIDEST road, we, your brothers are concerned and want to rescue you. MIN Mistir neger ale? Poletica asimeselishiw eko.....
BTW I am from East Europe

Anonymous said...

......I said the WIDEST, bcoz TEWAHIDO is the NARROWEST ROAD, which leads to Christos.

Anonymous said...

እዚህ ያሉት አባቶች ስደታቸው ለቤተ ክርስቲያን ስላልሆነ ጉዳዩን የሚያዩት ለነሱ የሚጠቅም ነገር እንዳለው በአንክሮ ነው:: እነሱ በብልሃት ያልያዙትን ቤተ ክርስቲያንን ማጥፋት አባ ፓውሊ ሲያደርጉላቸው ሲያዩ፣ አሁን የሚመረምሩት እሳቸውም የታዘዙት ልክ እንደስደተኞቹ ( ተሃድሶዎቹ) ከአንድ ቦታ ነው ወይስ አይደለም ነው:: ከአንድ ቦታ ከሆነ እነሱ ሳያውቁት በላያቸው ላይ ሌላ አፍራሽ መቀጠሩ ለምንድን ነው እያሉ ነው የሚጨነቁት:: ለነሱ ዋናው ነገር ቤተ ክርስቲያናችንን ጠፍታ ማየት ነው:: ግን አትሞኙ እዚህ ኢሠታ ና ኢህአፓ የነበሩ ከሃዲዎችን ከነክህደታቸው አሳምነው፣ መናፍቃኑን ጳጳሳት ብለው ስለዘለቁ ሃሳባቸው የተሳካ እየመሰላቸው አንዳንድ ደካማዎችን ቢያወናብዱም ሊያውቁት የሚገባው "ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተችው በክርስቶስ ደም በመሆኑ የሲኦል ደጆችም አይችሏትም ተብሎ ቃል ኪዳን የተሰጣት ስለሆነ አትፈርስም" እርግጥ ለነሱ ቆብ እና ቀሚስ አውልቀው በሱፍ እና በከረባት ካላስተማሩባት ትጠፋለች ለሚመስላቸው " ሱፍ እና ከረባት ሌባ ነው ትልልቆቹን ባንኮች እነ Bear Sterns , Leman Brothers and Maril Lynch የመሳሰሉትን ያጠፉ ናቸው:: ተስፋ ቁረጡ እናንተው ተላግታችሁ ትጠፋላችሁ እንጂ እርሷስ አትጠፋም:: ያከመሬት ሲዎድቅ አይዞህ መሬቱን ሰበርከው የተባለውን ህጻን ይመስላሉ እነሱ ስለከዱ ኃይማኖት ይጠፋል ብለው ያስባሉ:: የሚያሳዝኑት ተከታዮቻቸው ናቸው በፈቃዳቸው ማሰቢያ ህሊናቸውን እንዲጫወቱበት የፈቀዱት:: የሚያሳዝነው እንዳው ዝም ብለው ሬሳቸውን ያርቃሉ " ከአገር"

Anonymous said...

እስኪ እኔም አንዳንድ ነጥቦች ላነሳሳ ::

በመሠረቱ , የሃይማኖት አባቶች በተለይ , በፓትርያርክነት ደረጃ ያሉት ; በተሳሳተ መንገድ ላይ ቆመው እየታዩ :

ተራ ካህናትንና : ብዙ ጠለቅ ካለ የሃይማኖት ትምሕርት ዕውቀት የሌላቸውን ምእመናን :

""እነሱን አትዩ : ከመስመር አትውጡ ........."" እያሉ መጨቅጨቁ ተገቢ አይመስለኝም ::

ሃይማኖቱ የተመሰረተውና እየቀጠለ የመጣው እኮ : በቃል ከሚነገረው ይልቅ :
የሃይማኖቱ አባቶች በሚኖሩት መንፈሳዊ ሕይወት ነበር ::

----------------------------------

ከአቡነ ጳውሎስ በተጨማሪ : ለችግሮች መንስኤነትና መባባስ ምክንያት ናቸው ያልኋቸውን አንዳንድ አባቶችን : እስኪ ለአብነት ያህል ልጥቀስ

1. አቡነ ገብርኤል
በዕድሜም ሆነ በዕውቀት ከታላላቆች የሚመደቡ አባት ነበሩ ::

በሚሰሯቸው ተግባራት ግን እንዲህ ሆነው አናይም ::
የቆየውን አቆይቼ , ከማውቀው ብቻ ልነሳና ::

. በ 1991 (ኢት -አቆጣ ) አካባቢ ; ከኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስነቴ ቀይሩኝ ካሉ በኋላ : ዕቃዬን ላምጣ ብለው ተመልሰው : በግሪክ አድርገው አሜሪካ በመግባት አቡነ ጳውሎስን በ VOA እና በሌሎችም ሚዲያዎች ሲያወግዙ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ::

. ምርጫ 97,ትን ተከትሎ በተከሰተው ቀውስ ወቅትም :: ከሰልፈኛው ጋር ወጥተው ሕዝቡን ሲያስተባብሩና ሲያበረታቱ በመላው አማኞችና በብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ዘንድም እውነተኛ አባት ናቸው ተብለውም ነበር ::

. አቡነ ገብርኤል ግን ከዘመመበት የሚዘሙ እንጅ እውነተኛ አልነበሩምና : የአየሩን ሁኔታ አጢነው ሲያበቁ
ተስፋ ሲሰጡት የነበረውን ህዝብ በትነው : ከአባ ጳውሎስ ዕግር ወድቀው ይቅርታ ተደረገላቸውና ወደ አንጋችነታቸው ተመለሱ ::

. ባለፈው ዓመት (2001) በተደረገው "ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ይከበር የሚል " ትክክለኛ የአባቶች እንቅስቃሴ ወቅት :
አባ ገብርኤል : ከአባ ጳውሎስ ጎራ በመሰለፍ : እውነተኛ አባቶችን በማሳጣት :
በአደባባይ ወጥተውም "'አባ ጳውሎስ እውነተኛ ሐዋርያ ናቸው "" እያሉ ሲያቀነቅኑላቸው ታዘብን ::

ለነገሩማ አባ ጳውሎስ እንዲመረጡ ታላቁን ሚና የተጫወቱትና ""እንደሳቸው ያለ ፓትርያርክ ተመርጦ አያውቅም "" እያሉ ሲያወድሷቸው የነበሩትስ እሳቸው አልነበሩ ?

. ከዚያም በላይ ደግሞ : አሜሪካን አገር እያሉ :
በገለልተኛ ስም ያቋቋሟትን ልደታ ቤተ ክርስቲያን : ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን እንድትገባ ማድረግ ሲገባቸው : አዲስ አበባ ሆነው በሪሞት ኮንትሮል የሚቆጣጠሯት የግል ንበረታቸው በማድረግ : ሲፈልጉም እየመጡ ቫኬሽናቸውን ያሳልፉባታል ::

የሌሎችንም በቀጣይ
እመለስበታለሁ :

ታዲያ እንደነዚህ ያሉ : በቤተ ክርስቲያኗ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ያሉ ጳጳሳት ባሉበት እና እንደ ናቡከደነጾር ዓይነት የአሕዛብ ጠባይ ባለው ፓትርያርክ የሚመራ ሲኖዶስ እንዴት ሆኖ ነው እውነተኛ ብለን የምንከራከርለት ??

እውነት ነው :
አንዳንድ ደጋግ እና እውነተኛ አባቶች መኖራቸው የታወቀ ነው :

ነገር ግን : ምንነቱ በውል ባልታወቀ ምክንያት በሞት (አቡነ ዮሴፍ , አቡነ ኤልያስ , አቡነ ሰላማ , አቡነ ማቴዎስ ,...አቡነ መልከ ጼዴቅ ) , በበሽታ (አቡነ ቄርሎስ , አቡነ ቶማስ , አቡነ ኤልያስ ....) እየተቀጩ ሰማዕትነት ከሚቀበሉ በቀር : ምንም ለውጥ ማምጣት አይችሉም ::

ስለዚህ
በቤተ ክህነት አስተዳደርም ሆነ በገለልተኛነት ያለነው : እርስ በርስ መነታረኩን አቁመን :

ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ህልውና እና ቀጣይነት በትጋት ልንጸልይና ልንመካከር ይገባናል ::

እርስ በርሳችን እየተጨቃጨቅን : እግዚአብሔርስ እንዴት አድርጎ ጸሎታችንን ይስማን ?

ሕዝበ ክርስቲያኑስ እንዴት ብለን እንረጋጋ : በጣም እየታወከን እኮ ነው ያለነው ::

There is NO geleltegna church except not mentioning Aba Paulos's name.So called under Synod are also registered assets of 'Tigray Development Association.'Except NEW YORK SILASSIE, there is no church registered under EOTC.As to the services it is the so called 'Geleltegna'that follow and conduct absolutely Tewahedo's cannon in mass service,matrimony,christening,hymn service,etc.So Abel DO NOT DIVIDE US as if these churches are different.Believe it or not,these churches, where 90% of Tewahedo's faithfuls go,will not mention Aba Paulos's name ever.But they are all Tewahedo's churches!Mentioning his name does not make the churches undr Synod and vice versa.
What do you want these churches do to become under the Synod that those who claim to be so are doing?
I am sur you do not have answer.you just try to look pro one church,so are we.