Friday, July 16, 2010

በስደት የትውልድ ሓላፊነት

 ይህ በአካባቢያችን ስለምትገኘው ቤተ ክርስቲያን በተመለከተ በማኅበረ ቅዱሳን ድኅረ ገጽ ላይ የተገኘ ጽሑፍ ነው።
የማህበረ ቅዱሳን ድህረ ገጽ ፦የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሐዋርያት የፈጸሙትን ተግባር ቀዳሚ ሥራዋ አድርጋ የዘመናትን ድንበር እየተሻገረች አገልግሎቷን ስታከናውን ቆይታለች፡፡ የወንጌልን ብርሃን ላልደረሳቸው ሁሉ ታደርሳለች፡፡ ተምረው ያመኑትን፤ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቀች፤ የመንፈስ ቅዱስን ልጅነት እንዲያገኙ፣ በክርስቶስ ክርስቲያን እንዲሆኑ ታደርጋለች፡፡ በሀገር ውስጥም ይሁን ከሀገር ውጪ በመላው ዓለም በዝርወት /በስደት/ ያሉ ልጆቿን እስከመጨረሻው ትጠብቃለች፡፡ የዘላለማዊው ሕይወት የሰማያዊው መንግሥት ወራሾች እንዲሆኑም ታበቃለች፡፡

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን በውጪው ዓለም የምታከና ውነው ዘርፈ ብዙ መንፈሳዊ አገልግሎትም የሐዋርያዊ ተልእኮዋ አካል ነው፡፡ በተለይም በሰሜን አሜሪካ የቅድስት ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ ጉዞ ዘመናትን አስቆጥሮ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ቢደርስም፤ በአስቸጋሪ ፈተናዎችና ውጣ ውረዶች ውስጥ ማለፍን እና ጽናትን ጠይቋል፡፡
 ዛሬ በሰሜን አሜሪካ ያለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገልግሎት፤ በሦስት አህጉረ ስብከት ተዋቅሮ፣ በመንበረ ጵጵስና፣ በጽ/ቤት፣ ባለው መጠን በሚቻለው ሁሉ በሰው ኃይል እና በጀት ተደራጅቶ፤ ለአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትና ለምእመናን በተሻለ ሁኔታ የቅርብ አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል ሆኖ መገኘቱ፤ የቅድስት ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ ጉዞ ዕድገት ተጠቃሽ ደረጃ ነው፡፡

ከዚህ ቀደም በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የተጠናከረ አደረጃጀትና ለምእመናኗ የቀረበ አልገሎት አለመኖሩ፤ የቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ የሚጠበቅበትን ያህል ተጠናክሮ እንዳይስፋፋ አንድ ምክንያት መሆኑ ሁሉም የሚገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡ በቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ የአንዲት ቤተክርስቲያንን ማእከላዊና ጠንካራ መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት በማድረግ፤ የብፁዓን አባቶች ቡራኬ፣ የካህናቱና መምህራነ ወንጌል ትምህርትና ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እንዲሁም የቅርብ ክትትል የሚፈለገውን ያህል አለመዳረሱ፤ በዚያ የነበረውን የቅድስት ቤተክርስቲያንን እንቅስቃሴና የምእመናኗን ሕይወት ለፈተና እንደዳረገው እንረዳለን፡፡

የቅድስት ቤተክርስቲያን ሃይማኖታዊ ቀኖናዋ ሥርዓቷ እንዳይጠበቅ፣ ማእከላዊ አንድነቷና መዋቅራዊ አሠራሯ እንዳይከበር፣ ቃለ አዋዲዋ መመሪያዋ እንዲጣስ በር ከፍቷል፡፡ በዚህም ከቅድስት ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ ይልቅ የራሳቸውን ዓላማና ጥቅም የሚያስቀድሙ ሁሉ በፈለጉት ጊዜና ቦታ «ቤተክርስቲያን» እንደ ግል የንግድ ሱቅ እስከመክፈት ምእመናንም በዚህ የተሳሳተ ተግባር ግራ እስከመጋባት ደርሰዋል፡፡ የጎጠኝነት አመለካከት እያቆጠቆጠ «ቤተክርስቲያን የዚህ ጎጥ ነች» በሚል የምእመናንን አንድነት እየተፈታተነ በእናት ቤተክርስቲያን ላይ ያላቸውን እምነትና ተስፋ ሲሸረሸር ቆይቷል፡፡ የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ቤተክርስቲያንን ከተቀደሰ አገልግሎቷ ውጪ የዓላማቸው ማስፈጸሚያ እንድትሆን ጥረት አድርገዋል፡፡ የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ማስፋፊያና የአስፈጻሚዎቹ መሸሸጊያ የሆኑም ጥቂቶች አይደሉም፡፡

ይህ ሁሉ ፈተና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተለይም በሰሜን አሜሪካ እንዲሁም በመላው ዓለም በዝርወት /በስደት/ ላሉ ልጆቿና በወንጌል ብርሃን እንድትደርስላቸው ለሚጠብቁ ሁሉ፤ ሐዋርያዊ ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ፣ ስብከተ ወንጌሉ በሚፈለገው   መጠን እንዳይስፋፋ አድርጓል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች በስደት የሚኖሩ ምእመናን እና ሕፃናት ልጆቿ፤ ሃይማኖታቸውን ተምረው፣ የቤተክርስቲያናቸውን ሥርዓት፣ ትውፊት፣ ታሪክ አውቀው፣ መልካም ባሕላቸውን፣ ቋንቋቸውን ተረድተው፣ ማንነታቸውን በሚገባ ተገንዝበው፣ በመልካም ሥነምግባር ተኮትኩተው እንዳያድጉ፤ ይህንንም በጥናት በስትራቴጂ ዕቅድ ይዛ እንዳትሠራ አድርጓል፡፡

ለዚህም ነው በሰሜን አሜሪካ ያለው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዘርፈ ብዙ መንፈሳዊ አገልግሎት እንደየአስፈላጊነቱ በየአህጉረ ስብከቱ ተደራጅቶ መጠናከሩ በበጎ መልኩ የሚጠቀስ አንድ መፍትሔ ነው የምንለው፡፡ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ አንድነት እንዲስፋፋና የበለጠ እንዲጠናከር አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትና አባቶች፣ በጉባኤ እየተገናኙ በመወያየትና ተግባራዊ ተሳትፎ በማድረግ አርአያነት ያለው ተግባር እየፈጸሙ ነው፡፡ ከገቢያቸው ፈሰስ እያደረጉ አህጉረ ስብከቱን እየደገፉ ነው፡፡ ምእመናን ለቤተክርስቲያን አንድነት የሚያሳዩት ቀናኢነት በተለይም ወጣቱ ትውልድ ለመንፈሳዊው አገልግሎት መነሣሣቱና በትጋት መንቀሳቀሱ የወደፊቱን ብሩሕ ተስፋና ውጤታማነት ያመለክታል፡፡ አብያተክርስቲያናት ሲተከሉ የአንዲት ቤተክርስቲያንን ሥርዓትና መመሪያ እንዲከበር ቃለ ዓዋዲውን መሠረት ማድረጋቸው ተጠቃሽ ተግባር ነው፡፡

እነዚህን መልካም ተግባራት አጠናክሮ በመቀጠልና በየዘርፉ በማሻሻል ለበለጠ ውጤታማነትና የተሳካ ሐዋርያዊ አገልግሎት ማብቃት ሁሉም እንደየድርሻው መጠን ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ በተግባር የሚገለጽ ጉዳይ ነው፡፡

ስለዚህ በሰሜን አሜሪካ ያሉትን አህጉረ ስብከት በአገልጋዮች፣ በጽ/ቤት፣ በበጀትና ሥራ መሣሪያ በማጠናከርና እንደየአካባቢው እና ምእመናን ተጨባጭ ሁኔታ በማደራጀት በጥናትና በዕቅድ ላይ የተመሠረተ ውጤታማ ሥራ እንዲያከናውኑ ማስቻል ቀዳሚው ጉዳይ መሆን አለበት፡፡

በሰሜን አሜሪካም ሆነ በመላው ዓለም በዝርወት /በስደት/ ያለውን ሕዝብ እንዲያገለግሉ የሚላኩ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች፣ ካህናት፣ መምህራነ ወንጌል፤ የሚሔዱበትን ተልእኮ፣ የተልእኮአቸውን ዘርፈ ብዙ ዓላማ፣ የሚላኩበትን ቦታ ሁኔታ፣ የምእመናንን አኗኗር ወዘተ በሚገባ ተገንዝበው እንዲዘጋጁ የሚያስችል ሥልጠና መስጠትና በአግባቡ ማሠማራት አስፈላጊ ነው፡፡

የቤተክርስቲያን ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያዎች ከአካባቢው አጠቃላይ ተጨባጭ ሁኔታ፣ የማኅበረሰቡ የሥራ ጠባይ፣ ልማድና አኗኗር፣ ከዚያ ሀገር የመንግሥት ሕግና አስተዳደራዊ አሠራር ወዘተ ጋር እየታዩና እየተገናዘቡ ተዘጋጅተው የሚላኩበትን ሁኔታ ማጥናትና ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ምእመናን የቅድስት ቤተክርቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓት፣ ቀኖና በሚገባ እንዲያውቁት ማድረግ፤ ስለቤተክርስቲያን ማእከላዊ አንድነት፣ መዋቅራዊ አደረጃጀትና አሠራር፣ ስለቤተክርስቲያን አተካከል ወዘተ ግንዛቤያቸው እንዲያድግ ትምህርት ሥልጠና መስጠት፤ አውቀውም ለቤተ ክርስቲያን አንድነትና ሥርዓት መጠበቅ እንዲቆሙ ማስቻል ይገባል፡፡

የቅድስት ቤተክርስቲያንን ሐዋርያዊ ተልእኮ ማሳካት፣ አንድነቷና ሥርዓቷ ተጠብቆ እንዲዘልቅ ማድረግ የቤተ ክርስቲያን አባቶችና አገልጋዮች ሁሉ ቀዳሚ ተግባርና ሓላፊነት በመሆኑ ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ መቆም አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡

የትም ቦታ ብንሆን፤ የመንፈሳዊው ሕይወታችን ምንጭ፣ የመልካም ባሕል ዕሴቶቻችን፣ የመከባበርና መተሳሰባችን ማኅደር፣ የፍቅር የሰላም እና የማንነታችን መሠረት፣ የሃይማኖታዊና ሀገራዊ አንድነታችንም መገለጫ ነች ቅድስት ቤተክርስቲያን፡፡ ስለዚህ የቀደሙት ቅዱሳን አባቶቻችን በብዙ መሥዋዕትነት ያቆዩልንን ቤተክርስቲያን፤ እምነቷን፣ ሥርዓቷን፣ ትውፊቷን፣ አንድነቷን ጠብቀን ለሚቀጥለው ትውልድ ማቆየት የትውልድ ሓላፊነታችን ነው፡፡

3 comments:

Anonymous said...

Ay Mahbere kidusan!

Leboch minew tadia tinfish atlu abatachu
taot siteklu mahberachu andaizega new woys degfachu new?yenante zimta algeba alen sew hulu sinchacha.

Anonymous said...

I think the MK guys had started to discuss the problems with the Begashaw Mafia group three years before. I remember the issue was hot specially on Mezmur and Sireate Betekeristian on Hamer Metshet. I dont think its time to comment on the Hawult, because Aba Paulos may shut them down at this critical time. Everybody knows the idea and every Meemen is responsible to act on behalf of the Church, at this time like Organizing A Committee and asking for the Patriarch for His stand, orthodox or catholic?
At this time, the Follower is leading the Church, so I, myself, am very eager to stand for EOTC until death, if there is somebody with organizing ability can accompany me........Lets stand for our Church. Why dont we stand, for Her?

Anonymous said...

Yesinodos abalat none yemitilu likane papasat hulachu aba paulos bikebelutm baykebelutm enante tesebsibachu bmewsen ksiltanachew awrduachewna enantem meswatnetn tekeblu lkirstianum edel situn eneketelachu yetewahdo meri aydelum yewust bada enji kesiltan ketesenabtu bohala begulbetachew biketlu
memnanu yeminadergwn enadergalen enante gin kuretuna kesiltan aswegduachew.
lesemaetnet teshkedadmu