Wednesday, July 21, 2010

ማንን እንምረጥ?

“የምን ምርጫ? የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ መሮታል” እንደምትሉኝ አልጠራጠርም። ይሄኛው ምርጫ ለየት ይላል። የምርጫው ተፎካካሪዎች የሚወዳደሩት መራጮችን መንግስተ ሰማያት ለማስገባት ነው። ምርጫው የሚካሄደው በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ነው። ይህ ምርጫ በሚገርም ሁኔታ ዘወትር ከሚደረገው የምርጫ ጫወታ ይለያል፤ ምክንያቱም የምርጫ ቦርድ የለውም። እንዲሁም የምርጫ ታዛቢም የለውም፤ ታዛቢው ግን የመራጮቹ ህሊና ብቻ ነው። መራጮቹም ማንን መምረጥ እንዳለባቸው የሚወስኑት በሚቀርብላቸው አገልግሎት ነው። አካባቢውን ለማያውቁ መራጮች(እንግዶች) ግን የመምረጥ እድል አያገኙም። እነዚህ እንግዶች የሚጓዙት ለመጀመሪያ ጊዜ በሚያገኙት ሰው በመረጠላቸው ምርጫ ነው። እናም መራጮቹ ግራ የተጋቡ ይመስላሉ፤ምክንያቱም የምርጫው ተፎክካሪዎች(ተወዳዳሪዎች) ሁሉም “እኔ ትክክል ነኝ” እያሉ መራጮቻቸውን ለመሳብ ይሯሯጣሉ፤ ፉክክሩም መራጮችን መንግስተ ሰማያት ለማስገባት ነው።


የምርጫ ተወዳዳሪዎቹ(ተፎካካሪዎቹ) በጣም በርካታ ሲሆኑ፤እያንዳንዳቸው የራሳቸው የሆነ ልዩ ጠባይ፤ምልክት እንዲሁም ችግሮችም አሉባቸው። በዚህ ምርጫ ላይ የግል ተወዳዳሪዎችም ይገኙበታል። እስኪ የምርጫው ተፎካካሪዎች(ተወዳዳሪዎች) ስለራሳቸው ለመራጮቻቸው በአንደበታቸው የሚናገሩትን የምረጡኝ ዘመቻቸው አንድ ባንድ እንየው።

የመጀመርያው የዚህ ምርጫ ተፎካካሪ ራሱን “እናት ቤተ ክርስቲያን” ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው። የዚህ ቡድን ልዩ የምርጫ ምልክቱ አባ ጳውሎስ እና አባ ማትያስ ናቸው። ይህ ቡድን መራጮቹን “በእኛ በር ካልገባችሁ በስተቀር ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት አይቻልም” በማለት ራሱን ብቸኛ እና ትክክለኛ ብሎ መራጮቹን መንግስተ ሰማያት ለማስገባት ለፉክክር ቀርቧል። “ተጠሪነቴ በቀጥታ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ነው” ይላል። መራጮች ግን “ይህ ቡድን ችግሮች ስላሉበት እኛን መንግስተ ስማያት ሊያስገባን አይችልም” ይላሉ። መራጮች የዚህ ቡድን ችግሮች ሲዘረዝሩ “ስብስቡ የአንድ ቋንቋ(ትግርኛ) ተናጋሪዎች ናቸው፤ እንዲሁም ደግሞ ቡድኑ በሁለት የተከፈለ ነው የአባ ጳውሎስ እና የአባ ማትያስ” በማለት ይተቻሉ። ስለዚህ “ከእውነት መንገድ እርቀው እንዴት በእነሱ መንገድ ሄደን መንግስተ ሰማያት ልንወርስ እንችላለን”? እያሉ መራጮች ጥርጣሬያቸውን ይናገራሉ።

ሁለተኛው የምርጫው ተወዳዳሪ ደግሞ ራሱን “ገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን” ብሎ የሚጠራ ቡድን ነው። ይሄኛው ቡድን የምርጫው ልዩ ምልክቱ ለጳጳሳት አለመታዘዝ እንዲሁም ደግሞ ጳጳሳትን አለመቀበል ነው። ቡድኑም በምረጡኝ ዘመቻው የሚያስቀምጣቸው ነጥቦች “ታላላቅ ሰባኬ ወንጌል አለን፤ ኢትዮጵያ ውስጥ እንኳ የማይሰጥ የተሟላ አገልግሎት እንሰጣለን” የሚሉት ናቸው። ሌላው መከራከሪያ ነጥባቸው ደግሞ “የአባ ጳውሎስ አስተዳደር መቀበል ማለት ለወያኔ ቀጥተኛ ድጋፍ መስጠት ነው፤ ይህ ደግሞ ዲያቢሎስን መምረጥ ስለሚሆን መንግስተ ሰማያትን ሊያስገባ አይችልም” በማለት ለመራጮቻቸው ያቀርባሉ። በድጋሚም “እውነተኞች እኛ ብቻ ነን በእኛ መንገድ ያልሄደ የዘለለም መንግስት አይውርስም” እያሉ ራሳቸው ለምርጫው ፉክክር ያቀርባሉ። እነዚህኞች ወገኖች መራጮች እይታ ሲገመገሙ “ከሰባቱ ሚስጥራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱን ያፋለሱ፣ ጳጳሳትን አለመቀበላቸው ከኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖት አስተምሮ ውጪ ስለሚያደርጋቸው፣ በተጨማሪም ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን የወጡ ናቸው” የሚል ትችት ይቀርባቸዋል። የዚህኛው ቡድን ችግር ይህ ብቻ አይደለም ይላሉ መራጮች እንዲሁም “የቤተ ክርስቲያን የመጨረሻው ውሳኔ ሰጪ አካል ቦርድ እንዴት ይሆናል? አቢያተ ክርስቲያናቱ በባለቤትነንት የያዙት እነ ማን ናቸው? ተረካቢውስ ማን ሊሆን ይችላል?” የሚሉ ጥያቄዎችን ያነሳሉ። በዚህም የተነሳ መራጮቹ “ታድያ ይሄ ሁሉ ችግሮች እያሉባቸው በእነሱ መንገድ ሄደን መንግስተ ሰማያት እንዴት እንወርሳለን”? በማለት ከላይኛቹ ጋር ተመሳሳይ ጥርጣሬ እዳላቸው ያሰማሉ።

ሶስተኛው የምርጫ ተወዳዳሪ ራሱን “በሀገረ ስብከት የሚተዳደር ቤተክርስቲያን” ብሎ የሚጠራ ነው። የዚህኛው ቡድን ልዩ የምርጫ ምልክቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር ይጠበቅ የሚል ነው። ቡድኑም በእድሜ እላይ ከተጠቀሱት በጣም የሚያንስ ሲሆን በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሶስት ሊቃነ ጳጳሳትን አስተናግዶዋል። በምረጡኝ ዘመቻ “እኔ ትክክለኛው የኢዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አስተዳደር መዋቅር የጠበኩ፣ እንዲሁም ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሙሉ ቀኖና ሳይፋለስ ለትውልድ የሚተላለፍበት ቦታ ነው” እያለ ራሱን ለፉክክሩ ያቀርባል። ስለዚህ “መራጮች በዚህ በእውነተኛ መንገድ ካልገባችሁ በስተቀር የእግዚአብሔርን መንግስት አትወርሱም” በማለት ስለ ራሱ ይናገራል። በመራጮች እይታ “ይህ ቡድን በአካሄድ ትክክል ቢሆንም አባ ጳውሎስ እስካሉ ድረስ ግን ችግሮች አሉበት” እየተባለ ይተቻል። በዚህም ምክንያት “የአባ ጳውሎስ አስተዳደር ተቀብለን እንዴት ዘላለማዊ መንግስት እንወርሳለን”? በማለት መራጮች ያላቸውን ጥርጣሬ ይናገራሉ።

አራተኛው የምርጫ ተወዳዳሪ ደግሞ ራሱን  “ስደተኛ ቤተ ክርስቲያን” ብሎ የሚጠራ ነው።  የቡድኑ ልዩ የምርጫ ምልክቱ “እውነኛና ህጋዊ ሲኖዶስ” የሚል ነው።  ይህ ቡድን በምረጡኝ ዘመቻው “በግፍ ከሀገር የተሰደደን እውነተኞች እኛ ብቻ ነን፣ በምእመኑ ፍላጎት ያሻችሁን እናደጋለን፣ በኦርጋን መዘመር ትችላላችሁ” የሚሉትን ነጥቦች ያስቀምጣል። ስለዚህ “ይህ እውነተኛውና ህጋዊው ሲኖዶስ ካልተቀበላችሁ በስተቀር የመንግስቱ ወራሾች ልትሆኑ አትችሉም” እያሉ ለውድድሩ ቀርበዋል። መራጮች ግን “ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደተረዳነው በተለያየ መንገድ ጳጳሳት እንዲሁም ፓትርያርክ ከሀገራቸው ሊሰደዱ ይችላሉ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን አትሰደድም መንበሩም እዛው ሀገሩ ላይ መሆን አለበት፣ ከተዋህዶ እምነት አስተምሮ ውጪ በኦርጋን እንዲዘመር ይፈቅዳሉ” እያሉ ቅሬታቸውን ያሰማሉ። በዚህም የተነሳ “ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እየጣሱ እኛን እንዴት ወደ መንግስተ ሰማያት ሊመሩን ይችላሉ”? የሚል ጥያቄ መራጮች ያነሳሉ።

አምስተኛውና የመጨረሻው ተፎካካሪ  ደግሞ የግል ተወዳዳሪዎች ናቸው። የእነዚህኞቹ ልዩ የምርጫ ምልክት “አቶ እገሌ፣ቄስ እገሌ፣ አባ እገሌ፣ጳጳስ እገሌ” የሚል የግለቦች ስም ነው። ቡድኑም በግልጽ የሚያስቀምጠው የመወዳደሪያ ነጥቦች የሉዋቸውም። በግላቸው በራሳቸው መንገድ ሄደው የራሳቸው የሆነ ቤተ ክርስቲያን አሉዋቸው። እነዚህ የግል የምርጫው ተፎካካሪዎች መራጮችን ለመሳብ በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ የተለያዩ ነገሮች ሲናገሩ ይሰማሉ። በእነዚህ ላይ የመራጮች ቅሬታ “በቤተ ክርስቲያን ስም የግል ሀብትን ማካበት፣የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጥሰት፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጪ መሆን” እየተባሉ ይተቻሉ። በዚህም ምክንያት “የቤተ ክርስቲያንን ሀብት በግል ስማቸው አስመዝግበው እየታዩ፤እንዲሁም ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ መሆናቸው እይታወቅው እኛን የዘላለማዊው መንግስ ጉዞ መሪ ሆነው እንዴት ሊያደሱን ይችላሉ? በማለት መራጮች ጥያቄያቸውን ያቀርባሉ።

ታዲያ እኛ መራጮች ምዕመናን የትኞቹን የመንግስተ ሰማያት አስገቢ ተፎካካሪ ቡድኖችን እንምረጥ? የትኛውን ወገን ነው የኦርቶዶሳዊት ተዋሕዶ እምነት አስተምሮ ሳያፋልስ የያዘው? መልሱን ለተመልካቹ ልተወው።

እግዚአብሔር ተዋሕዶ  ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን

6 comments:

Gebre said...

thank u for this clear and meaningful article ....i think it will show us who is doing what in bird eye view , if we want to be neutral non-sided until we realy know the truth side of those party
can any body be neutra , non-sided and tell me who he/she think the right party for our church ...who is realy From God ?????

i am waiting the the responce!!!

Anonymous said...

I belong to Jesus Christ under the true Orthodox Church .The rest division is full of crap and out of biblical truth!!!.(GELATIYA 5:15)

Anonymous said...

Yemengestesemaya megebiyaw ber dergetoch sayhonu. Megebiyaw Alfana Omegea Megemeriyana mechershaw, Sebatun mahtem yefetaw, yemengiste semayat kulfe beeju yalew, yegziyabeher leeg yehonew ke kidst dengel mariam yeteweledew, Yenazeretu Geta Eyesu Kirstos becha new. Selezih ewnetegnawn megebeya meretu. Yegziyabeher menfes kegna gara yehun amen.

Anonymous said...

ይቅርታ አርግልኝና ለራስህ ግራ የገባ ነህ!!

zetewahdo said...

Dear brother,
I have gone through ur posts,and to be frank, I dont feel there is that much of a spiritual value in some of ur posts.Please at least post what is fnd relevant for our spiritual welfare,when it is significant.And review ur posts as Ive seen some unexpected misquotes (as 'yemezgiyawn biret bitkawem' for 'yemewgiyawn ...).May God help us to keep and promote our unity.

Unknown said...

ለዘተዋሕዶ አስታየየት ሰጪ፤
በመጀመሪያ ስለምክርህ እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
በአካባቢያችን መስማት ለፈለገ የስብከተ ወንጌል እጥረት ያለ አይመስለኝም። በሪድዮ፣በኢንተርኔት እንዲሁም በየደብሩ በጉባኤ ይሰበካል። ችግሩ የሰማነውን ተግባር ላይ አለማዋል ነው እንጂ። የዚህ ብሎግ ዓላማ የቀድሙት አባቶቻችን ጠብቀው ያስቀመጡልንን የቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት፣ ቀኖና፣ ትውፊት እና አስተዳደራዊ መዋቅር ለትውልድ ሳይሸረፍ እንዲተላለፍ የመወያያ ሀሳቦችን ማቅረብ ነው። ይህንን የሚቃውሙ ወገኖችም በተቃራኒው እኛም እንቃወማቸዋለን። አስተያየት ሰጪውም ከነዚህ ወገኖች ትመስለለህ። ለሁሉም ልብ ይስጠን!!!