Thursday, July 29, 2010

የዲሲ ርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማሪያም ቤተ ክርስቲያን የማን ናት?

የዳንኤል እይታዎች ድህረ ገጽ ላይ “የብርጭቆው ወይስ የምንጩ ውኃ” ሳነብ ብዙ ትዝታዎች ቀሰቀሰብኝ። እኔ ያለሁበት አካባቢ ዘመነ መሳፍታዊ የቤተ ክርስቲያን ክፍፍልም ተምልሼ እንዳየው አደረገኝ። ገጠመኜም አውጥቼ እንድናገር ተገደድኩኝ። ዲ/ን ዳንኤል የእኛ አካባቢ እንዲህ በማለት ገልጾታል “በውጭ ሀገር እየኖረ ይህንን እቃወማለሁ የሚለው ወገኔም ቢሆን ቤተ ክርስቲያኑን በታቦቱ ስም ከመጥራት ይልቅ በወንዙ እና በጎጡ መጥራት የሚቀናው ነው፡፡ «የነ እገሌ ቤተ ክርስቲያን» የሚባል ኑፋቄም፣ ዕብደትም የሆነ አመለካከት እንደልቡ እጁን ከትቶ የሚጓዘው እዚያው ባሕር ማዶ ነው”፡፡ ድንቅ ገለጻ! ።


እስኪ ከገጠመኞቼ አንዱን ላካፍላችሁ ቀኑን በርግጠኝነት ባላስታውሰውም በ1999 ዓ.ም ሰኔ ወር አካባቢ ይመስለኛል፤  የዲሲ ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት አጠቃላይ ስብሰባ ተጠርተን ነበረ። የጥሪው ምክንያት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ በወቅቱ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ወደ ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ይግቡ ወይስ አይግቡ? በሚል አጠቃላይ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባልቱ ውሳኔ እንዲያሳልፉ ነበር። በዚህ ውይይት ላይ አንድ ትልቅ አባት ተነስተው አስተያየት ሲሰጡ “አቡነ ጳውሎስ በደካማ ጎናችን ገብተው የእኛ የራሳችን ሰው አቡነ ቀውስጦስ ላኩብን፤ ስለዚህ እስከ አሁን የነበሩትን አባቶች ሳንቀበል ቀርተን አሁን ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ የእኛ ወገን ስለሆኑ መቀበል የለብንም” በማለት ሀሳባቸው ሰነዘሩ። የእኚህ አባት ሀሳብ ከተሰብሳቢዎች ዘንድ ተቃውሞም ድጋፍም ነበረው። እኔ በወቅቱ ለአካባቢው ገና አንድ ዓመት ያላስቆጠርኩ እንግዳ ስለነበርኩ እኚህ አባት ባነሱት ሀሳብ ተደናግጬ ነበረ።  “እናተ ማን ናችሁ”? “የትኛውስ ወገን ናችሁ”? ብሎ ለመጠይቅ ጌዜ የሚሰጠው ጉዳይ አልነብረም፤ ነገር ግን በዕለቱ ጥያቄውን አላነሰሁትም ነበር። ከቆይታ በኋላ ግን ለተናጋሪው አባት ጥያቄዬ ማንሳቴ አልቀረም እሳቸውም መልሱን ለመናገር አላፈሩበትም በሚገባ አጥንት እና እነሱ አንኳ ባይሆን አያቶቻቸው አብረው ይጠጡት የነበረ ወንዝ እየቆጠሩም አስረዱኝ።

በእርግጥ በዲሲ ርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ድህረ ገጽ ላይ የተቀመጠው መተዳደሪያ ደንብ ሲታይ ምንም ባለቤትነት በተመለከተ የተጻፈ ነገር የለም፤ነገር ግን በመጀመርያ አንቀጹ “ቤተ ክርስቲያኑ በዋሽንግተን ዲ.ሲ. የተቋቋመ ሕጋዊ አካል ነው” ይላል። ዶክተር አክሊሉ ሀብቴ በሰኔ 21/2002 ዓ.ም በዓለ ንግስ ላይ “እቺ ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ንብረት ናት” በማለት ተናግረዋል። ሕዝብ የተባሉት አሁን በአባልነት መዝገብ የተቀመጡት ነውን? ከሆኑስ በመተዳደሪያ ደንቡ እነዚህ ሕዝቦች የንብረቱ ባለቤት መሆናቸው ለምን አልተገለጸም?  ጥያቄዬ ቤተ ክርስቲያኒቱ አሁን ለአቡነ ጳውሎስ አስረክቡ አይደለም፤ ነገር ግን ለቀጣዩ ትውልድ ግልጽ አቋም አስቀምጦ ማለፍ ያስፈልጋል። ቢያንስ “አቡነ ጳውሎስ ሲያልፉ የቤተ ክርስቲያኒቷ ባለቤተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት” ብሎ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ ማስቀመጥ ግድ ይላል።  እንዲያ ካልሆነ ተረካቢው ማን ይሆን? የዘወትር ጥያቂዬ ነው። በሀገራችን በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናተ በግለሰዎች፣ በቡድኖች፣ በሀገር ገዢዎች፣ በነገስታቱና በመኳንቱ ቢታነጹም ባለቤቷ ግን ዘመን የማይቀይራት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ናት። በእኛ አካባቢስ? መልሱን ለተመልካቹ  ልተወው።

10 comments:

Anonymous said...

በእውነቱ ከሆነና እውነተኛ የቤ/ክ ልጅ ከሆንክ፤ በትክክል የማንነቷን የማወቅ ፍላጒት ካለህ ይሄንን "የማይረባና የማያንጽ፤ከፋፋይ" የሆነ ተራ ጥያቄህን እዚህ ላይ በመለጠፍ ሳይሆን እውነትን ፈላጊ ከሆንክ ለጥያቁህ በቂ የሆነ መልስ ሊሰጥህ የሚችል አካል ስላለ ወደዛ ብትሄድ የሚሳልህ ይመስለኛል። እነሱ እንደ አንተ በጓዳ ሳይሆን በግልጽ በአውደ ምህረት ላይ የማን እንደሆነች ብቻ ሳይሆን ወራሷም ማን እንደሆነ ግልጽ በሆነ ቌንቌ ተናግረውት ነበር። የዶ/ር አክሊሉ ንግግር ብቻ ነበር እንዴ የተሰማህ? ይመስለኛል አንተ ግን ለመልካም ነገር ሳይሆን አእምሮህ ፤ እግርህና አንደበትህ ለክፉ ነገር የሚፋጠንብህ ሰው ነህ። እንዲያው በእነዚህ አባቶች ላይ ያለህን ጥላቻ ከራስህ ጋር ብቻ ይዘህ መቀመጥ ሲገባህ ለምን በሌሎቻችን ላይ ለመዝራት እንደምትሞክር አይገባኝም፤ በእኑ መንፈሳዊነት እንዲህ ነው? ማን ይሆን የሰበከልህ? ታላቁ መጽሀፋችንስ ወዳጆቻችንን ብቻ ሳይሆን "ተላቶቻችንን እንድንወ ፤ የሚያሳድዱንን እንድንመርቅ" ነበር የሚያዘን የአንተ ግን ተለየ ። እንዲያው የዲሲዋን ቅ/ማ ቤ/ክ ካላነሳህ ሀሳብ አይመጣልህም ፤ ጽሁፍህ ውበት አይኖረውም ፤ አንባቢም አታገኝም ያሉህ ትመስላለህ። እንደዛ ነው እንዴ? አንድ ነገር ግን ልንገርህ? አንተ የምትፈልጋት የትኛዋን ሰላም እንደሆነ ባላውቅ ጌ/መ/ኢ/ክ የሰጠን ሰላም ግን በአመጽና በተንኰል ሳይሆን በፍቅር እንደምትገኝ አቃለሁ አምናለሁም እናት ቤ/ክኔም ይህንን ነው የሰበከችልኝ። እናም ወንድሜ ሆይ ሀሳብህ እንዲሰምርልህና ስራህም የተቃና እንዲሆን "ፍቅርህ" በዙሪያህ ላሉት ሀሳብህን ለሚደግፉት ብቻ ሳይሆን "እንደ አንተ አስተሳሰብ" የለየሀቸውንና መጥፎ አመለካከት ላለህ ለደ/ሰ/ቅ/ማ ቤ/ክ አባቶች ጭምር ቢሆን መልካም ይመስለኛል። ግን ለምንድን ነው ጽሁፎችህ ከማስተማርና ከማነጽ ይልቅ "ነገረኛነት" ጐልቶ የሚታይባቸው? ዳሩ አንተ ምን ታደርግ !

Anonymous said...

I agree with the commentator, Dr. aklilo, why not others. ? the answer for " your question" Yene dr. aklilo and dr. amare nat

Unknown said...

የመጀመሪያው ስም የለሹ አስተያየት ሰጪ፤
ለተሰጠኝ ምክር እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
አንተ የምትላቸው አባቶች ጥላቻ የለኝም ጥላቻዬ ግን ጎጠኝነት እና በአንድም በሌላም ለራስ ጥቅም መቆምን ነው። ዓላማዬም ለአንዲቷ ለሐዋርያዊቷ ቤተ ክርስቲያን እንቁም ነው። ሽፍንፍኑን ይውጣና ችግሮቻችን እንነጋገር። ምን አልባት አስተያየት ሰጪው የማታውቃቸው አውቀሀቸውም ደግሞ በጥቅም ምክንያት ጆሮ የተዘጋብህ ለቁጥር የሚያዳግቱ ብዙ ችግሮች አሉ። መሸከም የማትችላቸው ብዙ በሚስጥር የተያዙ መረጃዎች ልነግርህ እችል ነበር ግን ወቅቱ ሲደርስ ይወጣሉ። አሁን የተጻፈው ግን በአደባባይ በግልጽ የተነገሩ ናቸው። በዚህ ብሎግ ላይ እቺ አጥቢያ ቤተ ክስቲያን በስም የተነሳቸው ለመጀመሪያ ግዜ ነው። ጎጠኞች አይደለንም የሚባል ከሆነ ኢ-ሜል አድርግልን ማንነታቸው በተመለከተ ዝርዝሩን ምላሽ ታገኛለህ።
ለሁሉም ልብ ይስጠን!!

Anonymous said...

"የምለውን ተመልከት ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ"
በጣም የምትገርም ሰው ነህ! ማንነቴን እንኳን ሳታውቅ ጥቅመኛና ከዚህም የተነሳ እውነት የተጋረደብኝ ሰው አድርገህ አስቀመጥከኝ! ታሳዝናለህ እንዲያው መሰረት የሌለውንና በጥላቻ ተሞልተህ የምታወራልኝን ለመስማት የምቋምጥ ስራ ፈት እንኳን አይደለሁም። ወይስ አንተ የተመረዝክበትን ክፉ መንፈስ በእኜም ላይ ለመዝራት? አንተም ታሳዝነኛለህ። ብቻ ይቅርታ አድርግልኝና የማይገባ ሀይለ ቃል እንድናገር ታደርገኛል ወንድሞቻችንስ አስተማሪ፤ ውስጥን የሚነካና የሚጠይቅ ጽሁፍ ይጽፋሉ የአንተ ግን የሚያስቆጣ፤ ሀይለ ቃልን እንዲናገሩ ፤ እንዲቃረኑህ የሚያደርጉ ናቸው ምን ይሆን የጐደለህ? ወደ ታላላቆችህ ሄደህ ምክር ቢጤ ብትጠይቅ፤ ከእውቀታቸውም ከፍለው እንዲሰጡህ ብታማክራቸው የሚሳልህ ይመስለኛል እህህ አባቶች ሲተርቱ "ከመጠምጠም መማር ይቅደም" አይደል የሚሉት? ምንአልባት ከተጠቀምበት! ዳሩ ካንተና ከመሰሎችህ በቀር ስለቤ/ክ አዋቂና ተቆርቋሪ ስለሌለ " ከእኛ ወዲያ ላሳር" ካላችሁ ቆያችሁ፤ እህህ ግን ደግሞ የትም አትደርሱም እንዲያው የታሪክ ጥቁር ተባሳ ጣዬች እንዳትሆኑ እፈራለሁ። በታምም ደግሞ ብዙ እንደምታውቅ አድርገህ ራስህን አትቁጠረው። ኅረ ለመሆኑ ማን የሚሉህ የስለላ ድርጅት ነህ? መረጃ ምናምን እያልክ የምትቀባትረው? እስከ አሁን ካልከው ስለማይብስ "ግልጽ ይውጣ" አይደል እያልክ ያለኅው ? እውነተኛና ተቆርቋሪ ከሆንክ ማስፈራሪያህ ይብቃን አለኝ የምትለውን በግልጽ ተናገር። አባቶች ያሉበት ወቅታዊ ችግር ሁሉም የሚያውቀውና ጸሀይ የሞቀው ነው። ይሄ ችግር ደግሞ አንተ እንዳስቀመጥከው ለግል ጥቅማቸው ማስከበሪያ እንዳልሆነ አንደበትህ "ከሌላ የተነሳ" ሌላ ቢያወራም ልብህ ግን ጠንቅቆ ያውቀዋል። በእውኑ እነሱስ ይሄንን እለት እለት የሚናፍቁት መሆኑን አንደበቴን ሞልቸ እናገራለሁ። ለፈጣሪ ፈንታ በስጠት የሚገባቸውን በማድረግ ያችን ቀን ይጠባበቃሉ እንጅ ፤ ከምእመኑ አይንና ጀሮ የተሰወረ ተንኰለስ የለባቸውም። እባክህ ወንድሜ! እንዲያው የተኲረኰርክ እየመሰለህ የድፍረት ሀጢያት እንዳይገዛህ ብትጸልይ የሚሳልህ ይመስለኛል። አንድ ነገር! እንዲህ እራስን እየደበቁ መወንጀልና ስም ማጥፋት እንደማይቻልና ቢቻልም ግን መጋለጥና ህግ ፊት መቅረብም እንዳለ ላስታውስህ እወዳለሁ። ዳሩ ስለምትላቸው ነገሮች ማንም ጀሮም ሆነ ለተራ ወሬ ጊዜ ስለሌለው ብለህ ብለህ ሲደክምህ በራስህ ጊዜ ታቆመዋለህ። ልብ ይስጥህ። ሌላማ ምን ልትባል ትችላለህ?። አስተዋይ ልቡናን ለሁላችን ያድለን።

Anonymous said...

dear bloger , still you are doing under assignment for Tageye Pauls or Your holiy father. we have to agree something , still you don't undersand your fathers problem and still you are far from the truth. you live in the free world , but still you are in dark and you live in the abba Meles's friend house . there is no synode or there no church leader in ethiopia. don't spend your time following those evil church leaders.
I hope you know the truth one day

Unknown said...

ከላይ ስም የለሹ አስተያየት ሰጪ
እኔ የማንም ወገን አይደለሁም የተሰቀለው ክርስቶስ አምነው ከተቀበሉ ወገን ነኝ። እስቲ የሚያመዛዝን ህሊና ካለዎት ከዝህ በፊት በደጀ ሰላም ላይ በአቤል ቀዳማዊ ወይም በአቤል ወለቴ የተጻፉትን በመመልከት ፍርድ ይስጡ።
http://www.dejeselam.org/2010/07/blog-post_13.html
http://www.dejeselam.org/2009/11/blog-post.htm

Anonymous said...

አስያየት ሰጭ ሆይ
መጀመሪያ ራስክን አታጽድቅ !!!
ከዚያ ለልጁ ያለህን ጥላቻ አስወግድ ፡ ቀዳማዊ ድፍን የአቡነ ጳዉሎስ ደጋፊ አይመስለኝም። ግን ይሄ ማለት የአሜሪካ አባቶችን አካሄድ ትክክል አያደርገዉም፤ አቡነ መልከ ጼዴቅም እኮ የደርግ ታማኝ አገልጋይ ነበሩ፡ ካህናትን ለዉትድርና መፍቀዳቸዉ ተረሳ እንዴ ?! አኔ ግን አልረሳዉም ፤ ካህን ዘመዴን ስላጣሁበት !! እንዴዉም አቡነ ጳዉሎስ ሳይሻሉ ይቀራሉ ከዚህ አንጻርማ!!
እኔ ምለዉ ግን ሁለቱም ጥፋት እየሰሩብን ነዉ፤ ስለዚህ መካከለኛ ገንቢ ሐሳብ እንፈልጋለን !!!

Anonymous said...

http://kidanemhret.ning.com/

Anonymous said...

Dear bloger and all audiance,
I personaly appricate the bloger to tell the truth about what is going on in R.A.D.S DC. The anonymous writer seem to me some one insider in that particular church, the way he interprate things what has been said originally does not match with the idea. There is one thing we all know about Debre Selam. The fathers plus the corrapt board members there are all, they are ethier friends and family of the two clery in that church. We all know in order to be the board member or the so called (inner circle) you have to be someone from (Behata Lemariam) church in Addis or the surrounding area. There is a big corruption in that church.
I can tell you a story what happen a while ago, one of my friend passed away here in the United States, as we all know people ask other fewllow Ethiopians for some fund to send the body to the deciesed parent home to our beloved country. and we approched church adminstrator about the situation. Immagine by then there was no the so called (Eder) I was a member who the adminstrator Knows me from scratch of that church washing the parking lot when it was bought at frist. The admistrator ask me who is your fiend? I told him that he used to live in Addis, then the second questions was where are his families from? by then my blood getting hotter, I told him "Kisis this is not about his family birth place or their where about, it's about scotring his body in full owner to his country" if we can ask people who will be willing to help us as we always do to other people. Then I was told the person is not our member and we can ask anyone to help you nor you can not ask anyone in this primesis of the church.
I almost cry for his crulness, for God seck the person already died and its not the church who will give the fund, it's the people of our community. Since then I almost stop going over there and I do not hate him for that I simpetize for him.
I have seen a lot there as the bloger specifically said at the biggning of the article. However, the anonymous writer twice, he either one of the share holder or close family of this people. We have to be away from nepotisem, you said God was crucified for all of us not specifically for those who are in that church alone. He is our saviour also. Forget the division, lets all work on our unity. Our mother church was undivided when we were given, it's not about Abune Paulos, it's the church. you may have got lots of benefite from this church more than others. However, you are the one throwing the spere towards our mother church. So please stop for a moment and think your action, your action may hurt so many generation to come. Unless we stop this division today I do not know where we all endup. WE are now figting today, think about our childeren where they would say they are belong to, they can't say they are from our home land EOTC because we show them to have an independant church like the protestants do.
Where are we right now???please for the sack of our church, those who burn alive for this church, who are sacrifies for this church. What would their soul would say to us today????
God help us united! amen.

Anonymous said...

So wonderful!I like this blog!