Monday, August 2, 2010

የማንም ደጋፊ አይደለሁም

አንተ የማን ወገን ነህ? የማንስ ደጋፊ ነህ? የሚሉ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ደርሰውኛል። እኔ የማንም ደጋፊ ወይም የማንም ወገን አይደለሁም፤ ነገር ግን የተሰቀለውን ክርስቶስ አምነው ከተቀበሉ የተዋሕዶ ልጆች መሀከል አንዱ ነኝ። የቤተ ክርስቲያን ህጓ፣ ሥራዓቷ እና ቀኖናዋ ተጠብቆ ለትውልድ ይተላላፍ ብለው ከሚጮሁት ብዙ ተዋሕዶአውያንም መካከል አንዱ ነኝ። እስኪ ከዚህ በፊት በደጀ ሰላም ላይ ያቀረብኳቸው አንደንድ ጽሑፎች፦

አንዳንድ ነጥቦች ስለ ሕገ ቤተ ክርስቲያን

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 18/2009)
(አቤል ዘቀዳማዊ እንደጻፈው)
እስቲ ቅዱስ ፓትርያርኩም ሆነ ብዙዎቹ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የማይቀበሉት ሕገ ቤተ ክርስቲያን  ስለ ፓትርያርክ ስልጣንና ተግባር ምን ይላል? ለዚሁ ጥያቄ መልስ ለማግኘት በራሳቸው በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተቀባይነት ያገኘውን ሕገ ቤተ ክርስቲያን ካነበብኩት ላካፍላችሁ።
1. ፓትርያርክ ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው (ሕገ ቤተ ክርስቲያን  1991)፣
2. ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስና የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባዎችን ይመራል፣
3. በቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ለብፁዓን ጳጳሳት የሊቀ ጵጵስና መዓረግ ይሰጣል፣
4. ለታላላቅ ገዳማት አበ ምኔቶችና በሀገረ ስብከቱ ለተመረጡ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች የመዓረግ ስም ይሰጣል፣
5. ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጡና የተላለፉ ሕጎች፤ ደንቦች፤መመሪያዎችና ልዩ ልዩ ውሳኔዎች በተግባር መዋላቸውን ይከታተላል፣
ስለ ቅዱስ ፓትርያርክ ከስልጣን መውረድስ ሕገ ቤተ ክርስቲያን  ምን ይላል?

ፓትርያርኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ላይ ከተሾመ በኋላ የተቀበለውን ኃላፊነት በመዘንጋት፦
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ን ትምህርተ ሃይማኖት የሚያፋልስ፤ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ ተግባር ፈጽሞ ከተገኘ፣
• በፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ አምስት ከቁጥር 172 እስከ 208 በተደነገገው መሰረት በደለኛ ሆኖ ከተገኘ፣
• በኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ በ1991 በወጣው ሕገ ቤተክርቲያን አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ ሰባት መሰረት በተሾመበት ቀን የገባውን ቃለ መሐላ ያልጠበቀ እንደሆነ፣

በአጠቃላይ ታማኝነቱ፤ መንፈሳዊነቱና አባትነቱ በካህናትና በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት ያጣ ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ መሆኑ በትክክል ከተረጋገጠ ከስልጣኑ ይወርዳል። በሱ ምትክም ሌላ ተመርጦ ይሾማል። ፓትርያርክ እስኪሾም ግን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ይመረጣል። (የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን  1996 አንቀጽ 16)

ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይህ ሆኖ ሳለ የአሁኑ ቅዱስ ፓትርያርክ ከላይ የተጠቀሱትን ሕጎች ሁሉ እያፈረሱ፤ እኛም እያየናቸው የቅዱስ ሲኖዶሱም አባላት እያዩዋቸው እስካሁን ድረስ በዝምታ ታልፈዋል። ከዚህ በኋላስ መፍትሔው ምንድር ነው? ተስፋ ቆርጦ መተው ወይስ ከጥቂቶቹ ለሕገ ቤተ ክርስቲያን  ተቆርቋሪ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ አይዞዋችሁ እኛም ከጎናችሁ ነን በማለት መስራት? መልሱን ለውድ ደጀ ሰላማውያን/ት በመተው አንድ ነገር ግን ላሰምርበት እወዳለሁ የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን  “በፓትርያርክ ላይ ፓትርያርክ” የሚል ሕግም ደንብም የላትም።
እግዚአብሔር ተዋሕዶ  ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን

(ደጀ ሰላም፤November 1, 2009)
 አዲስ አበባ ሀ/ስብከት ያለምንም መፍትሔ ወደ ሌላ የተስፋ ወር 
(አቤል ወለቴ)
በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ሥር የሰደደውን የአስተዳደር ችግር ለማስወገድ ተጀምሮ የነበረው እንቅስቃሴ “ለመጨረሻ ጊዜ መፍትሄ ያገኝ ይሆን?” በማለት የተዋሕዶ ልጆች በያሉበ በተስፋ ሲጠባበቁት የቆየው የወርኃ ጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ብዙዎቹም የተጠቀሱት ችግሮች መፍትሄ ሳይገኝላቸው በድጋሚ ለግንቦቱ ምልዓተ ጉባኤ አስተላልፎታል።

በሐምሌ ወር በአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ እና በሌሎችም የሕዝብ ግንኙነት ጣቢያዎች እንደሰማነው ብፁዓን አባቶች ቅዱስ ፓትርያርኩ ላይ አንስተውት የነበረው መሠረታዊ ጥያቄ ተድበስብሶ ታልፏል። ይህንንም ጥያቄ ባነሱት ብፁዓን አባቶች ላይ ጥቃት ያደረሱት የቤተ ክህነቱ ተናካሾች ለፍርድ አልቀረቡም።

የቤተ ክርስቲያኒቱን ዘመንን ያልዋጀ ብልሹ እና ኋላ ቀር የአስተዳደር ችግር መፍትሄ ከማበጀት ይልቅ፤ የግለሰቦች ፀብ በማስመሰል አለባብሰው በይቅርታ አልፈውታል። ይቅር መባባሉ መልካም ቢሆንም መሠረታዊ እና መልስ ይሹ ለነበሩት የአስተዳደር በደል ጥያቂዎች ግን ምላሽ ማግኘት ነበረባቸው። ሚሊየነር ከሆነው ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጋር ተያያዥነት ያለው የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጉዳይ ሶስት ሙሉ ቀን ፈጅቶ፣ ብፁዕነታቸውም ጊዜያዊ የሥራ መደብ አግኝተው፣ ችግሩም በዘላቂነት ሳይፈታ አሁንም ለግንቦቱ ምልዓተ ጉባኤ መተላለፉን ሰምተናል።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከሌሎች ሀገረ ስብከቶች በተለየ ሁኒታ በሕገ ቤተክርስቲያን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሕግ ቢቀመጥለትም ሕጉም በትክክል እየተተረጐመ አይመስልም። ሕገ ቤተክርስቲያን “የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በ1991 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው ሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 35/ ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት የሚመራ የአስተዳደር ዐቢይ ኮሚቴ አለው። ዐቢይ ኮሚቴው በቅዱስ ሲኖዶስ ይሰየማል” ይላል።
የዐቢይ ኮሚቴው አባላት፦
• ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሚመረጡ ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት ወይም ጳጳስት፣
• ከጠቅላይ ቢተክህነት ሶስት አባላት፣
• ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚመረጡ ሦስት አባላት፣
• በድምሩ ዘጠኝ አባላት ይኖሩታል።
የዐቢይ ኮሚቴው ሰብሳቢ በቅዱስ ሲኖዶሱ ከተመረጡት ሊቃነ ጳጳሳት ወይም ጳጳስ ወይም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ይሆናል። የዐቢይ ኮሚቴው የአገልግሎት ዘመን ሶስት ዓመት ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ የኮሚቴው አባላት በሙሉ ወይም በከፊል ለተጨማሪ ሦስት ዓመት ብቻ ሊመረጡ ይችላሉ። ዐቢይ ኮሚቴው ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ይሆናል።
የተቀመጠው ሕግ ይህ ሆኖ ሳለ ቅዱስ ፓትርያርኩ ግን ሀብታሙን (ሚሊየነሩን) የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት “የራሴ ሀገረ ስብከት ነው” በማለት ፈላጭ ቆራጭ የአገዛዝ ክንዳቸው ሲሰነዝሩበት ይታያሉ።


(ደጀ ሰላም ኦገስት 3/2009)

 የምእመናን ቀን በዓል
ስለ ዲሲው የምእመናን ቀን በዓል አቤል ዘቀዳማዊ እንደዘገበው
ጅምር ሆኖ እንዳይቀር እንጂ በዋሽንግተን ዲሲ ሀምሌ 22 እና 26 2001 ዓ.ም የተካሄደው የምእመናን ቀን በዓል ይበል በርቱ የሚያሰኝ ነበረ። ጅምር ሆኖ እንዳይቀር ያልኩበት ምክንያት እዚሁ አካባቢ ያሉት አብያተክርስቲያናት በተለያዩ ጊዜያት ስለ አንድነት እንዲሁም አንድ ሆነናል በማለት ይናገራሉ፤ ነገር ግን ፍፃሜያቸው ወደ ቀደመው ግብራቸው ነው። ከዚሁ በዓል አዘጋጆች እንደተረዳሁት ዋናው ዓላማቸው የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ምእመናንን አንድ ማድረግ የሚል ነው። የዝግጅቱም መልዕክት “ምንም እንኳ አባቶች ቢለያዩም እኛ ምእመናን ግን ከአንዲት ተዋሕዶ እምነት የተወለድን ስለሆንን አንለያይም አንድ ነን” የሚል ነበር። ታድያ አንድነትን ማን ይጠላል? ይህ የታለመው አንድነት እንዲመጣ ግን የአንድነት መሠረት ምን መሆን አለበት የሚለው መታወቅ አለበት። በእርግጥም ከአንዲት ተዋሕዶ ሃይማኖት መወለዳችን አንድ ያደርገናል። በአባቶች መከፋፈል ምክንያት እኛም ምእመናኑም ተከፋፍለናል።

ስለዚህ የዚሁ የተቀደሰ ዓላም አዘጋጆች አንድ ነገር እንድታስቡበት እወዳለሁ፤ ይኸውም ወደ ፍጹም አንድነት እንድንመጣ ከዝግጅቱ አንድ ክፍል ውስጥ ለእይታ ያቀረባችሁት የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ የአስተዳደር መዋቅር የሚለው እዚሁ እኛ ያለንበት አካባቢ በተግባር እንዲውል ከሚመለከተው ክፍል ሁሉ ብትነጋገሩበት ሥራችሁ የበለጠ ዋጋ ያገኛል። የአድነቱም መሰረት መሆን ያለበት እሱ ነው፤ ዝም ብለን አንድ እንሁን የምንል ከሆነ ግን ሁል ጊዜም ከተለያዩ አንደበተ ርዕቱ ሰባኪን ወንጌል የምንሰማው ቃል ነው። በዘላቂነት አንድነታችን የሚጸናው ቤተክርስቲያናችን አንድ ስትሆን ብቻ ነው። አንድነቷም የአስተዳደር መዋቅሯ ከላይ ከቅዱስ ሲኖዶስ እስከ ታች አጥቢያ ቤተክርስቲያን ድረስ ያለው ሁሉም ሲጠብቀው ብቻ ነው።

ከዚህ በፊትም በዚሁ በደጀ ሰላም አንድ አስታያት መስጫ ቦታ ላይ እንደገለጽኩት በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ማለትም ዲሲ፤ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ውስጥ በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ስም የሚጠሩ በብዛታቸው 18 (አስራ ስምንት) በአስተዳደር አይነታቸው ደግሞ 7 (ሰባት) የተለያዩ አብያተክርስቲያናት ይገኛሉ። የአብያተክርስቲያናቱ አይነት እኔ የማውቃቸውን ልንገራችሁ፦
1. ራሱ ስደተኛ ሲኖዶስ ብሎ የሚጠራው ቡድን ውስጥ የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት
2. ራሳቸው ገለልተኛ ነን በማለት የሚጠሩ በገለልተኝነት የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት
3. በግለሰብ ስም የአባ ኤገሌ ወይም የአቶ ኤገሌ ተብለው የሚጠሩና በግለሰቦቹ የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት
4. ፓትርያርኩን እንቀበላለን ነገር ግን ሀገረ ስብከት አንቀበልም የሚሉ አብያተክርስቲያናት
5. የኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ እንቀበላለን ነገር ግን ፓትሪያርክ አባ ጳውሎስ አንቀበልም የሚሉ አብያተክርስቲያናት
6. ከአሜሪካ ውጪ በሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት ወይም ቆሞሳት በበላይ ጠባቂነት ወይም በባለቤትነት የሚመሩና የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት
7. የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር በመጠበቅ በሀገረ ስብከት የሚተዳደሩ አብያተክርስቲያናት
እስቲ ስለቤተክርስቲያናችን አንድነት እንወያይ ጎበዝ!!! የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ቃለ ዓዋዲ ወይም የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ደንብ ስለ የቤተክርስትያን አስተዳደር ምን ይላል?
እግዚአብሔር የቤተክርስቲያናችን አንድነት ይጠብቅልን። አሜን!!

8 comments:

Anonymous said...

Good job, God bless you!!!

Anonymous said...

አየ!አቶ አቤል ቀዳማዊ! በጣም የሚገርሙ ሰው ነዎት፤ በእውነቱ ከሆነ የትኛውም አስተያየት ሰጭ የእርስወን የየትኛው የመሆነዎት ነገረ አስጨንቆት የጠየቀዎት የለም "ብዙዎች" በማለት ብዙ አንባቢ እንዳለወት ለማስመሰል እንኳን አይሞክሩ፤ ጽሁፎችዎት ለውይይና ለምክክር የማይጋብዙ ወገንተኝነትዎትን አጉልተው የሚያሳዩ መሆናቸው ያው በግልጽ የሚታይ ነው። በእያንዳንዱ ጽሁፍዎት ያሉት አስተያየቶችም እህህ! በቁጥር ናቸው መቸም ልብ ያሉት ይመስለኛል። እስኪ ልጠይቅዎት! ለመሆኑ አስተያየቶችን የሚለጥፏቸው ለእርስዎ ያስደሰቱዎትንና ሀሳብዎትን የሚደግፉትን እየመረጡ ነው አይደል? ምክንያቱም ነጻ የመወያያ መድረክ ብለው በከፈቱት ለዚህ ብሎግ የላኩትን አስተያየቴን አፍነው አስቀርተውብኛል፤ ለምን ይሆን? እርስዎ የናቋቸውን አባቶችና ሰባኪዎችን አቃሎና ንቆ የሚጽፍልዎትን በግልጽ ሲለጥፉት፤ የሚፈሯቸው ሰባኪያን ስም ሲጠቀስ ደግሞ ከለጠፉት በኌላ እንደገና አንስተው ሲደብቁት፤ ለምን እንደዚህ ይሆናል እያደረጉት ያለው ነገር ልክ አይደለም የሚልዎትን ደግሞ ጭራስ አፍነው ሲያስቀሩት፤ ታዲያ እርስዎ ነዎት እውነተኛ?፤ እውነተኛ ቀጥተኛ እያሉ የሚቀባጥሩት? ድንቈም እቴ! በማውራትማ ቢሆን ኖሮ!!! ደግሞ ስለማንነትዎት ለማስረዳት ብዙ የተቸገሩ አልመሰለዎትም? እህህ ይልቅስ የቆዪትን በመጠቃቀስዎት ጥሩ ጸሀፊ አለመሆንዎትን አስረግጠውልናል፤ የዘነጋነውን በጊዜው ግን የታዘብነዎትንና በጥያቄ ያለፍነውን ነገር አሁን መልሰውልናል። ደግሞስ ስለእርስዎ ማንነትና ከየትነት ማን ይደንቀዋል? በነጻ ሀገር ለህሊናዎት ከተመቸዎት አለኝ የሚሉትን መዘዙን ከቻሉት የፈለጉትን ማለት ይችላሉ። ደግሞ የሚገርመኝ ለዚህ መሰሪና ኢመነፈሳዊ ለሆነው ተግባርዎት ለራስዎት የሰጡት ስያሜ? "ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ" እንደሚባለው መሆኑ ነው? እንደኔ እንደኔ ግን ስያሜዎት ቢሆን የሚሳል ብየ የማስበው ""ቃየል ዳግማዊ"" የሚለው ስያሜ የሚስማማዎት ይመስለኛል። መቸም የወንድሙ የአቤል ገዳይ የሆነው የቃየል ታሪክ የሚጠፋብዎት አይመስለኝም፤ ያው መ/ቅዱሱን ጠንቅቀው ያውቁት የለ?! አዎ የእርስዎ ብእርም ከፍቅር ይልቅ ጥላቻን በመስበክ የብዙ አባቶችንና ወንድሞችን ህሊና ጎድቷልና በምን ይለያል? አዎ ይህንንም አስተያየቴን አፍነው ሊያስቀሩት ይችላሉ ለራስዎት የሚያደሉ የራስዎትን ገመና መሰፈን የሚያቁ ሰው ነዎትና። ለነገሩ ለጠፉት አለጠፉት ግድ የለኝም። ብቻ ልብ ይስጠዎት።

Anonymous said...

ymaneme hune egna mine agebane?

Anonymous said...

So? Who cares!!! Yemaneme mehone techilaleh....mani gede alwena about u???

Anonymous said...

you have the right to choice where ever you want to belong, but you have to know one thing , the holiy synode in ethiopia is fake. it is already taken its power by the government and it is not the assembly of holiy spirit.( not yemenefese kidus gobae). please understand. that is your mine problem. it is good to write and express your opinion, but don't mislead people. we the people who are living in usa and europe or canada, we know who is the true leader.Talk to your MK or EPDRF people or cadres.I am true christine like you practice your religion. enough is enough from now on abba paouls is responisble to Melese not ethiopian orthodox tewehedo church followers. A. Pauls , he doesn't care about you , Jesus cares for you. A. Pauls as long as EPDRF or Meles in power, you can't do anything about abba pauls.you think the problem is Abba Merkorewes or A. Paul, if you say one of them , you are wrong, the problem is Melese and leftover takers of ethiopian orthodox church bishops who are surrender themselves for the world.
Thanks

Anonymous said...

Eere ebakihe? Ymaneme wegeni ayedelehime endi? weyi! alekerebehem...mognehin felege...diro newe yemane wegene mehonehen tenekekne yemenawekewe...geni lemeni mewashite asfeleghe?

Anonymous said...

I wonder why these guys want to write their highly negative comments. I dont think they are reading the content of the post.
Hi guys, you just hate him because you are retricted to one 'Atibiya'. why dont you think of the Church in general. Please dont hurt your self, while trying to fight the truth. If you really are true Christians work for the benefit of the Church, for unity and commen understanding! If you find any false information on his post point that out let's know the truth. otherwise, whether you love it or not, you should understand that 'Independent church' is the practice of prosistant. There is only one church and one administration. (Even if we have issues with the current administration)

Learn, open your heart.

Sorry, I wrote it in English. I will setup amharic software for my for my next comment.

Anonymous said...

Abel Quedamawi you are telling the truth about the "Geleltegna" Churches. though the supporters of these "churches" obviously want yu to get discouraged and stop what you are doing. Believe me i've been surving in "Geleltegna" church for more than 8 years everything you said is true but the commentators in this blog mostly are so naive they just believe what they hear. keep what you are doing we need more people like you.