Sunday, October 10, 2010

“ሐውልቱ” በመዲናችን በዋሽንግተን ዲሲም እየተሰራ ነው

በዋሽንግተን ዲሲ የምትገኘው ርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ዛሬ መስከረም 30፣ 2003 ዓ/ ም ከሥርዓተ ቅዳሴ በኋላ የሽልማት ስነስርዓት በዓል ተከብሮ ውሎዋል:: ተሸላሚዎቹም ከካህናት በኩል ሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ኅይሌ ሲሆኑ ከምእመን ወገን ደግሞ ዶ/ር አክሊሉ ኀብቴ ናቸው:: ሽልማቱም የረዥም ግዜ አገልጋዮች በሚል ነው:: ሸላሚው በግንቦት ወር መጨረሻ አካባቢ ሊቀ ሊቃውንት በቨርጂኒያ ዉድ ብሪጅ ቤተ ክርስቲያን ባርከው የከፈቱለት ዲ/ን ጌታሁን ነው:: እንግዲህ የቅዱስ ፓትርያርኩ ሸላሚዎች እነ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ፤ ሊ/ካህናት ጌታቸው ዶኔ ፤ዲ/ን በጋሻው ደሳለኝ እና ሌሎች የጥቅም አጋሮቻቸው ሲሆኑ፤ እዚህ ሀገር የግብር ጓዳቸው ሸላሚው ዲ/ን ጌታሁን እና ምን አልባትም ሌሎች የጥቅም አጋሮቹ ተባብረውታል::

ይህቺ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ውጪ የራስ ገዝ ወይም  “የገለልተኛ አስተዳደር” አስተምህሮ የምታራምድና የምታስፋፋ አጥቢያ ናት:: እንዲሁም ደግሞ ዛሬ ሽልማት የተበረከተላቸው ምእመን “ገለልተኛ” የሚለው የአስተዳደር አስተምህሮ የፈጠርኩት “እኔ ነኝ” በማለት በድፍረት በስብሰባ መድረኮች ይናገራሉ:: የቀደሙት አባቶቻችን ለ1660 ዓመታት ለኢአማንያን የማምሉክ እና ለከሊፋ ነገስታት እየገበሩ የቤተ ክርስቲያን መዓከላዊነት ጠብቀው መንበረ ማርቆስ ባይመቻቸውም አብረው ኖሩ:: እነዚህ አርቆ አስተዋዮቹ አባቶቻችን መንበረ ማርቆስ ፖለቲካ እያራመደች የአስተዳደር አድሎ ይታይባታልና ተገንጥለን ራሳችን እንቻል ማለት ይችሉ ነበረ፤ ነገር ግን ግዜው እስኪደርስ በጥበብና በአስተዋይነት በሐዋርያት ትውፊት መሠረት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ጠብቀው ኖሩ:: አሁን በእኛ ዘመን ግን ይህ የሐዋርያት ትውፊት አፍርሰው በቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ አዲስ አስተምህሮ “የራስ ገዝ” ወይም ገለልተኛ አስተዳደር የፈጠሩ ሰዎች ለሽልማት በቁ:: ነገ ደግሞ እንደ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መንደርተኞች “ለታሪክ ሰሪዎቻችን ሐውልት እናቁምላቸው” እንበሚሉን ጥርጥር የለውም፤ ምክንያቱም ቅዱስ ፓትርያርኩ ከሽልማት በኋላ ነው ወደ ሐውልቱ የሄዱት::

በሌላ ዜና በርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የስልጣን ሽኩቻ መነጋገሪያ እየሆነ ነው:: የቤተ ክርስቲያኒቱ የረዥም ግዜ አስተዳዳሪ ሊቀ መምራን ዶ/ር አማረ ካሴ እና የቦርድ ሰብሳቢው ርዕሰ ደብር ቀሲስ አብረሃም ኅ/ሥላሴ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት የሁለቱ ደጋፊዎች ምእመናን ለሁለት እየተከፈሉ ናቸው:: የቤተ ክርስቲያኑ መተዳደሪያ ደንብ “የአስተዳደር ቦርድ አባላት በነጻ የሚያገለግሉ” ናቸው ይላል፤ የአሁኑ የቦርድ ሰብሳቢ ርዕሰ ደብር ቀሲስ አብረሃም ኅ/ሥላሴ ግን “እየተከፈላቸው ለምን የቦርድ ሰብሳቢ ሆኑ”? የሚል ጥያቄ ተነስቶባቸዋል:: እኚሁ የአስተዳደር ቦርድ ሰብሳቢ ካህን “የቤተ ክርስቲያኑ አሥተዳዳሪ ቀሲስ ዶ/ር አማረ ካሴይ ሥራ መስራት ሥላልቻሉ አጠቃላይ ሥራ የምሰራው እኔ ስለሆንኩ ቤተ ክርስቲያኑ በሙሉ ግዜ ማስተዳደር አለብኝ” በማለት ጥያቄ አንስተዋል:: ጥያቂውም ለአስተዳደር ቦርድ አባላት እንዲሁም ለአጥቢያው ማህበረ ካህናት አቅርበዋል:: በዚህም ምክንያት የአጥቢያው ምእመናን እና ካህናት የዶ/ር ደጋፊ እና የአብረሃም ደጋፊ እየተባባሉ በሁለት እየተቧደኑ ናቸው::

2 comments:

Anonymous said...

Stop Gossiping Mr. blogger!!!!!!!!!!!!1

ፍቅረማርቆስ ስጦታው said...

ከነሱ ምን ይጠበል እታድያ ከዚህ በላይ ምን ይስሩ ነው የምትለው አቤል ወንድሜ ጥቅም ፍለጋ ቤተክርስቲያንን ተጠጉ በጥቅማቸው የሚመጣውን እየገፍ ጥቅማቸውን ካላሰቡ ምን ማሰብ አለባቸው? ለዘመናት ሳትከፋፈል የቆየች ቤተክርስቲያን በነሱ ምክንያት ስትገነጣጠል እነሱ ለምን ብለው የማቢያ ሞራል አልፈጠረባቸውም እነዚህን አይደል ሆዳቸው አምላካቸው ሀሳባቸው ምድራዊ ያላቸው ስለዚህ የምድር ሀሳባቸው ተሳክቷል ሀውልት አሰርተዋል ገንዘብ ሰብስበዋል ቤተሰቦቻቸውን ጠቅመዋል ከዚህ በላይ ምድራዊነት ምን አለ አቤል?