Thursday, November 18, 2010

የዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውዝግብ ቀጥሎዋል

ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በአካባቢያችን በቁጥር 20 ከሚሆኑት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መካከል “ገለልተኛ” አስተዳደር ሥር ነን ከሚባሉት መካከል አንዱ መሆኑ ይታወቃል::  አጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑን አሁን በሚያስተዳድረው ቦርድ እና “የምእመናን ተቆርቋሪዎች ነን” በማለት ራሱን የሚጠራ ቡድን  መካከል የተፈጠረው ውዝግብ ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን አሁንም ቀጥሎዋል::


ይህ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ከሌሎች “ገለልተኛ አስተዳደር ሥር ነን” ከሚሉት አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት መካከል የራሱ የሆነ ለየት ያለ አቋም በመተዳደሪያ ደንቡ አስቀምጧዋል:: ለየት ከሚያደርጉት ጠባያት መካከል በመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ ሁለት ተራ ቁጥር አራት ላይ የተገለጸው አጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ “ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርሰቲያን ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት” በሚለው ንዑስ አንቀጽ ላይ “ዋና መቀመጫው አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የሆነውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የሚቀበልና በአንቀጽ ሁለት ንዑስ አንቀጽ አምስት በፊደል ተራ “ሐ” የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የመንፈሳዊ አስተዳደር ግንኙነት ያለው” ይላል:: እንዲሁም በዚሁ አንቀጽ በተራ ቁጥር አምስት ከፊደል ተራ “ሀ” እስከ “ሐ” ላይ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ የተገለጸው “የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በመሆናቸው የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቡራኬያቸውን ይቀበላል።  የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ቦርድ ለደብሩ አስተዳዳሪነት ለመረጠው ካህን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መንፈሳዊ መመሪያ ይሰጣሉ። ሀገረ ስብከቱም ሆነ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር ቦርድ በሚያከናውነው የዕለት ተዕለት ተግባርም ሆነ አስተዳደር ማለትም በሰው፤ በንብረትና በገንዘብ አስተዳደር ጣልቃ አይገቡም” ይላል http://kidusmichaeldc.org/wp-content/uploads/2008/09/dmqm-bylaw.pdf:: ሌሎች “ገለልተኛ አስተዳደር ሥር ነን” የሚሉ አቢያተ ክርስቲያናት ሀገረ ስብከትን በተመለከተ በመተዳደሪያ ደንባቸው ላይ አላስቀመጡም::

እንግዲህ የቀጠለው ውዝግብ “የምእመናን ተቆርቋሪዎች ነን” በማለት ራሱን የሚጠራው አካል አሁን ቤተ ክርስቲያኑን በሚያስተዳድረው ቦርድ ላይ በርካታ ጥያቄዎችን አንስቷዋል:: ከጥያቄዎቹም መካከል “መተዳደሪያ ደንብ ይቀየር፤ የቦርድ ምርጫ ይካሄድ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሂሳብ ይታሰብ” የሚሉት ዋናዎቹ ናቸው:: በተለምዶ እነዚህ አካላት በአጥቢያው ዘንድ “ተቃዋሚዎች” በሚል መጠርያ ይታወቃሉ::

ለዓመታተት የዘለቀው ይህ ውዝግብ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የተፋለሰው ለማስተካከል አይደለም:: ምክንያቱም አሁን ያለው ቦርድ ሆነ የምእመናን ተቆርቋሪዎቹ ወይም ተቃዋሚዎች የቀኖና ቤተ ክርስቲያን መፋለስ በተመለከተ የተነሳ ጥያቄ የለም::

ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ምእመናን “ይህ ሁሉ ጣጣ ያመጡብን ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ናቸው” በማለት በምሬት ይናገራሉ:: ብፁዕነታቸው የዛሬ አምስት ዓመት አካባቢ ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ “ቤተ ክርስቲያኑ ሙሉ በሙሉ በእናት ቤተ ውስጥ ማስገባት ይችሉ ነበረ፤ ይህ ቢያደርጉ ኖሮ ይህ ውዝግብ አይፈጠርም ነበር” የሚሉ ወገኖችም አሉ:: ይህም ሆኖ አሁን ያለው ቦርድ የብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ደጋፊ ስለሆነ በዓመት ሁለት ግዜ ብፁዕነታቸውን ከኢትዮጵያ ድረስ ያስመጣል የምእመናን ተቆርቋሪ የሚለው ቡድን ግን የብፁዕ አቡነ ፋኑኤል መምጣትም ጭምር ይቃወማል::

2 comments:

Anonymous said...

minew Abezachihut min adrigu new yemtilachew ?yasazinal sebakiwin papasun pristun zemariwin techiten nekfen mann linamesegein new Abune Fanueil deg abat nachew ye lmat sew nachew D C mikaeil yaserut church new yedekemubet

Anonymous said...

ከላይ የተናገረው (የተናገረችው) ሰው በእውነት አይናችንን አሳውረን ካልሆነ በስተቀር እኝህ አባት እውነተኛ አባት እንዳልሆኑ በጣም ብዙ መረጃዎች በተለያየ መልኩ እየወጡ ነው "ጉድ እና ጅራት እያደር ይወጣል" እንዲሉ አባ መላኩ እና አባ ሠረቀ በመተባበር በዚህ በከተማችን ላይ ትልቅ ሥራ እየሰሩ ነው፣ ይህ ሥራ በእውነት ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪነታቸው ወይም ለህዝበ ክርስቲያኑ አሳቢ በመሆናቸው ሳይሆን ለራሣቸው ግላዊ ጥቅም ወይም ጉርስ አስበው እንጂ። እንደ እውነቱ ከሆነ እኚህ አባት ከጥቅም አጋራቸው አባ ሠረቀ ጋር በመሆን ቤተክርስቲያናችንን ለማፍረስ ከሚያገሉ ወገኖች ጋር በመሆን እነሱ ከውስጥ ጠላቶቻችን ከውጪ ይኧው ድብደባውን ጀምረዋል።

ሕዝቤ ሆይ ንቃ እንዳለ እዚህ ዋሺንግተን አካባቢ የምንገኝ ህዝበ ክርስቲያን ሁሉ ነቅተን ይህች ርትይት የሆነች ቤተክርስቲያናችንን ልንታደግ ይገባባል፣ ነገ ልጆቻችንን የምንነግረው እስኪጠፋን ድረስ ታሪኳን ሊቀይሩ፣ ስሟን ሊያጠፉ ደፋ ቀና በማለት ላይ የሚገኙት እነዚህ እኛን መስለው ጠቦቶቻችንን ሊነጥቁ የመጡ ተኩሎች ናቸው፣ ዛሬ ላይ ሆነን ሃላፊነታችንን አለመውጣታችን ነገ በታሪክ ሊያስወቅሰን በትውልድ ሊያስጠይቀን እንደሚችል መዘንጋት ያለብን አይመስለኝም።

ውድ ወገኖቻችን የተዋህዶ ልጆች በ፵ እና በ፹ ቀናችን ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ፣ በቅድስት ቤተክርስቲያን የተወለድን ልጆች ዛሬ በእነዚ የታሪክ ጉድፎች ታሪካችንን፣ ስመ ክርስትናችንን ለማጥፋት እላይ ታች በሚሉበት ጊዜ ሁላችን የአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች በመሆናችን በአንድነት ልንሰራ፣ ልንተባበር እና የነዚህን የናት ጡት ነካሾች አፍራሽ አቆርቋዥ ስራቸውን ልናጋልጥ እንዲሁም በቅንነት ለሚመላለሰው የተዋህዶ ልጆች ልናሳውቅ ጊዜውና ወቅቱ ያስገድደናል።

እንደሚታወቀው እነዚህ አባት መሳዮች ወደከተማችን ባለፈው ሣምንት ሲመጡ በጉያቸው ይዘው የገቡት ትልቅ አጀንዳ እንዳላቸው የተለያዩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፣ ነገር ግን በየግላቸው በሳምንት ልዩነት ወደዚህ ሲመጡ (ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሉ በኃላ) የራሳቸው የሆነ ሽፋን ይዘው ነው የመጡት ለምሳሌ አባ መላኩ ሲመጡ በደብረ ምሕረት ቤተክርስቲያን አካባቢ ለሚያውቋቸው የሰጡት ማስተባበያ (በጭንቅላታቸው ላይ ውሃ ነገር እንደታየ) ዶክተራቸው ኢትዮጵያ እንደገለፀላቸው ገልፀው እዚህ በገቡ በሁለተኛው ቀን ግን ተመርምሬ ነፃ መሆኔን በምርመራ ተረጋገጠልኝ በማለት የሃሰት ምክንያት አቅርበው በደብረ ምሕረት ቤተክርስቲያን ያሉ ምዕመናን አባታችን ጤነኛ ናቸው በማለት ባለፈው ማክሰኞ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ትልቅ ፈንጠዝያ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። ግን ለመሆኑ እንዲህ አይነት ምርመራ ውጤቱ በተመረመሩ ቀን ይደርሳል እንዴ?? ለምንስ እንዲህ አይነት ሽፋን አስፈለገ? ሊሰሩት የተሰጣቸው የቤት ሥራ በእጅጉ የደብረ ምሕረትን ምዕመናን ሊያሳዝን እንደሚችል ጠንቅቀው ስላወቁ አይመስላችሁም? ለምንስ እንደሌላው ጊዜ አቶ አባተ ቤት አልተቀመጡም? ምናልባት የመጡበትን ዓላማ ለማሳካት የተለየ ቦታ ቁጭብለው በስልክ የሚዶልቱበት፣ በጨለማ በዓላማ አንድነት ካላቸው ጋር በግልጽ በጽህፈት ቤቱ ቁጭ ብለው እኛኑ ለማጥፋት ለመነጋገር እንዲመቻቸው አይመስላችሁም? ደግሞ የነገሩ መገጣጠም ( አይ ሱባኤውን እዚሁ በቅርብ ሆኜ ልከታለል) ማለታቸውስ ለነገሩ በቅርቡ ሥራቸውም ዕቅዳቸውም ይፋ ስለሚወጣ አብረን የምናየው ነገር ይመስለኛል፡ ልብ ያለው ልብ ይበል ከማለት ሌላ በአሁን ሰዓት ምንም የምለው የለም።
ይቆየን