Friday, December 3, 2010

“ነጭ እንቁ በአዳም ገላ” የተሰኘው መጽሐፍ የዲሲ ማኅበረ ካህናትን አጋለጠ

የዋሽንግተን ዲሲ ማኅበረ ካህናት ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምን በተመለከተ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት አስተምህሮ ጋር ያላቸው ልዩነት የገለጹበት መረጃ የያዘ መጽሐፍ በገበያ ላይ ዋለ:: “ነጭ እንቁ በአዳም ገላ” በሚል ርእስ በመምህር ሀብተ ማርያም ተድላ የተዘጋጀው መጽሐፍ የዛሬ ስድስ ዓመት በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ “በገለልተኛ አስተዳደር ሥር” ያሉት በወቅቱ ማኅበረ ካህናት ተብሎ ይጠራ የነበረው በእመቤታችን አስተምህሮ ከኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ጋር ያላቸውን ልዩነት የሚገልጽ የተፈራረሙበት ሙሉ መረጃ አካቶ ኢትዮጵያ ውስጥ በገበያ ላይ ውሎዋል::


በወቅቱ ተነስቶ የነበረው “ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ከአዳም የወረሰችው ሀጥያት አለባት” የሚሉት በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ እና በአባ መዓዛ በየነ የሚመራው በአንድ ወገን፤ “ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ከአዳም የወረሰችው ሀጥያት የለባትም” የሚሉት በሊቀ መዘምራን ሞገስ እና በቀሲስ አብረሃም ኅ/ሥላሴ የሚመራው በሌላ ወገን ተሰልፈው ነበረ:: ይህ መጽሐፉ በገበያ ላይ የዋለው ጉዳዩ በአካባቢያችን አሁንም በድጋሚ በተነሳበት ወቅት ላይ ነው::

ኅዳር 16/1997 ዓ/ም ለቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩን እዲያይላቸው የጻፉት ደብዳቤ እንደሚያሳየው ከሆነ፤ የማኅበረ ካህናቱ ሰብሳቢ ሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ኃይሌ ጨምሮ የርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ማእምራን ዶ/ር አማረ ካሣዬ፤ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ፤ መጋቤ አእላፍ መክብብ አጥናው፤ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል፤አባ መዓዛ በየነ እና ሊቀ ህሩያን ቀሲስ ከፈለኝ ወልደ ጊዮርጊስ  “እመቤታችን ከአዳም የወረሰችው ሀጥያት አለባት” በማለት የሚያስተምረው ቀሲስ አስተርአየ ጽጌን በመደገፍ ፈርመው ነበረ:: ይህ አሁን በገበያ የዋለው “ነጭ እንቁ በአዳም ገላ” የሚለው መጽሐፍ የእነዚህ ካህናት ዝርዝር እና በጉዳዩ ላይ እስከነ ሙሉ መረጃው ጭምር ጸሐፊው ትንተና ሰጥተውበታል::

በወቅቱ የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ማትያስ እነዚህ “በገለልተኛ አስተዳደር ሥር እንመራለን” የሚሉት ማኅበረ ካህናት የቀሲስ አስተርአየ ጽጌ አስተምህሮ በመደገፍ ያነሱት ሃይማኖታዊ ጥያቄ በጽሑፍ 12 ገጽ የያዘ ጥር 18/1997 ዓ/ም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እመቤታችን በተመለከተ ያላት አስተምህሮ ምላሽ ሰጥተውበት ነበረ::

ይህ አሁን ከስድስት ዓመታት በኋላ ተመልሶ የተነሳው የጥንተ አብሶ ትምህርት ሁለት ምክንያቶች አሉት:: አንደኛው ምክንያት በርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ያሉት ካህናት አሁን እርስ በርስ በስልጣን ሽኩቻ የገጠሙት አምባጓሮ ሲሆን፤ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ “ማርያማዊ  ሕገ ሃይማኖትና ተማሕጽኖ” በሚል ርእስ በርዕሰ ደብር ቀሲስ አብረሃም ኅ/ሥላሴ የተጻፈው መጽሐፍ ናቸው:: ይህ መጽሐፍ ጉዳዩ ካለፈ ከስድስት ዓመታት በኋላ መጻፉ “ጸሐፊው እስከ አሁን የት ነበሩ”? የሚል ጥያቄ ያስነሳባቸው ሲሆን፤ እንዲሁም ደግሞ የስልጣን ተቀናቃኛቸው ሊቀ ማእምራን ዶ/ር አማረ ካሣዬ ለማጥቃት የተጻፈ ነው በማለት እየተተቹ ነው:: በዚህም ምክንያን ሳንሱር ያልተደረገ መጽሐፍ ስለሆነ በደብሩ እናዳይተዋወቅ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ሊቀ መምራን አማረ ካሳዬ አግደውታል::

በሌላ በኩል ደግሞ በወቅቱ ድንግል ማርያም ከአዳም የወረሰችው ሀጥያት የለባትም በሚል ወገን ተሰልፎ የነበረው ርዕሰ ደብር አብረሃም ኅ/ሥላሴ  አሁን  የርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የቦርድ ሰብሳቢ ይህን ጉዳይ በተመለከተ የጻፉት መጽሐፍ በአጥቢያው ተነስቶ የነበረው የካህናቱ አለመግባባት የበለጠ እዲሻክር አድጎታል::

ይህ በአጥቢያው ካህናት የተነሳው አለመግባባት የአጥቢያው ምእመናንም ለሁለት የከፈለ ሲሆን፤ ካህናቱ ደግሞ ለሶስ ተከፋፍለዋል:: የርዕሰ ደብር አብረሃም ኅ/ሥላሴ ደጋፊ በአንድ ወገን የሊቀ ማእምራን ዶ/ር አማረ ካሣዬ ደጋፊ በሌላ ወገን እንዲሁ ደግሞ ከሁለቱም አይደለሁም የሚለው ገለልተኛ በሌላኛው ወገን ሆነው ተከፋፍለዋል::  ይንን አስመልክቶ ሀሙስ ምሽት በ16/04/2003 ዓ/ም የአቢያው የአስተዳደር ቦርድ እና የማህበረ ካህናቱ ስብሰባ ላይም ለሁለት ተከፍለው፤ እልህ አስጨራሽ ስብሰባ ያካሄዱ ሲሆን፤ ጉዳዩም ከስልጣን ሽኩቻ ወደ ሃይማኖታዊ ጥያቄ እያመራ መሄዱን የውጥ ምንጮች ገልጸዋል::

3 comments:

Anonymous said...

እግዝዮ አምላክ ሆይ አድነን !!!
እኛ እውነተኛ ፈጣሪያችንን ለማግኘት ወደ ቤተ
እግዚአብሔር ቤት እንሀዳለን
ምነው የስደቱ ሳይበቃን
ኣባቶች ያዋቂ አጥፊ ሆናችሁ
አሜሪካ ገለልተኛ ኢትዮጵያ ስትሄዱ ቤተ ክህነት
ጉልበት እየሳማችሁ ምስኪኑን ስደተኛ ታማካኛላችሁ
አይበቃም ዎይ? ግፉ!!!!!!!!!!!
ንስሃ ግቡ መ ቸም ከናንተ ሰው የሚማረወው ድፍረት ነው ይብቃችሁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
በቃ በቃ !!!!!!!!!!!

Ethiopia said...

እግዝዮ አምላክ ሆይ አድነን !!!
እኛ እውነተኛ ፈጣሪያችንን ለማግኘት ወደ ቤተ
እግዚአብሔር ቤት እንሀዳለን
ምነው የስደቱ ሳይበቃን
ኣባቶች ያዋቂ አጥፊ ሆናችሁ
አሜሪካ ገለልተኛ ኢትዮጵያ ስትሄዱ ቤተ ክህነት
ጉልበት እየሳማችሁ ምስኪኑን ስደተኛ ታማካኛላችሁ
አይበቃም ዎይ? ግፉ!!!!!!!!!!!
ንስሃ ግቡ መ ቸም ከናንተ ሰው የሚማረወው ድፍረት ነው ይብቃችሁ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
በቃ በቃ !!!!!!!!!!!

Betelehem said...

እኔ በኢትዮጵያ አስተያየት ላይ የምለው ቢኖር
እነዚህ ያለ መአከላዊ አስተዳደር ቤተክርስቲያን
እንደ ሱቅ በደረቴ እልፍ እልፍ እያሉ ከፍተው
ያሉ አባቶች ልበላቸው (ግማሾች ግራ የገባቸው ሌሎች
ደግሞ የተኩላ ለምድ ለብሰው ምስኪኑን ስደተኛ
ደሙን የሚመጡ መናፍቃን ናቸው ብል ማጋነን
አይደለም:: እስቲ ልብ በሉ በየአሜሪካ ከተሞች
በ ኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ ያለውን ንትርክ:: ታዝባችኋል?
እውነት ለሃይማኖቸው እውነት ለኢትዮጵያኖች
ያዘኑ ቢሆኑ ለአንድነት በቆሙ ነበረ::
ያለው መንግስት ከፋፈለ ይባላል? በኦ.ተ.ካህን ስም
መተው በጵጵስና ስም በ መነኩሴ ስም ህዝቡን ከፋፍለው ለራሳቸው ሃብት ማደለቢያ አደረጉት
እግዝዮ!! ለኢትዮጵያ ቤ/ክ ጌታ ሰው ይፍጠርላት::
አሜን!!!!!!!!!!!!!ይደረግልን!!!!!!!!!!!!!!!!!!!