Tuesday, January 11, 2011

ያለ ኤጲስ ቆጶስ ፈቃድ ቀሳውስት የባረኩት አዲስ ቤተ ክርስቲያን እውቅና ተሰጠው

ያለ ሊቀ ጳጳስ ፈቃድ ካህናት ተሰባስበው የባረኩት የቨርጂኒያው ውድ ብሪጅ "ደብረ መድኅኒት ኢየሱስና ብስራተ ገብርኤል"  ቤተ ክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲ ርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እውቅና ተሰጥቶት ምእመናን ሄደው እንዲገለገሉበት ሰሞኑን በመድረክ እና በቤተ ክርስቲያኒቱ ሬድዮ ማስታወቂያ ተነገረ። ደብረ መድኅኒት ኢየሱስና ብስራተ ገብርኤል በማለት በካህናቱ የተሰየመው ይህ “ቤተ ክርስቲያን” የተባረከው ወይም በአካባቢው አጠራር “የተከፈተው” በሰኔ ወር 2002 ዓ.ም የበዓለ ጰራቅሊጦስ ዋዜማ ቅዳሜ ዕለት ነበረ። በውቅቱ ተገኝተው የነበሩ ካህናት ዝርዝር፦

 • ሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ኃይሌ (ከዲሲ ር/አ/ቅ/ማ/ቤተ ክርስቲያን)

 •  ቀሲስ ዘላለም (ከዲሲ ር/አ/ቅ/ማ/ቤተ ክርስቲያን)

 • ዲያቆን ጌታሁን (ከዲሲ ር/አ/ቅ/ማ/ቤተ ክርስቲያን)

 • ቀሲስ ምስጢረ(ከዲሲ ር/አ/ቅ/ማ/ቤተ ክርስቲያን)

 • ዲያቆን እሸቱ(ር/አ/ቅ/ማ/ቤተ ክርስቲያን)

 • አባ እስጢፋኖስ በዋዜማ የተገኙ (ከዲሲ ደ/ም/ቅ/ሚ/ ቤተ ክርስቲያን)

 • አባ ምህረት(ከዲሲ ደ/ም/ቅ/ሚ/ ቤተ ክርስቲያን) አሁን ዳላስ ቲክሳስ ናቸው

 • ዲያቆን ብሩክ (ከደ/ም/ቅ/ሚ/ ቤተ ክርስቲያን)

 • አባ ፊልጶስ በዋዜማ የተገኙ(ከቨርጂኒያ ልደታ ለማርያም ቤ/ክ)

 • ቀሲስ ብሥራት(ከቨርጂኒያ ልደታ ለማርያም ቤ/ክ)

 • ዲያቆን ዮሐንስ(ኩኩሻ) (ከሜሪላንድ ደ/ገ/ቅ/አማኑኤል ቤ/ክ)

ይህንን ድርጊት ያበሳጫቸው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብረሃም የተከፈተው ቤተ ክርስቲያን ክርሲያኖች እንዳይደለገሉበት ቃል ምዕዳን አስተላልፈው ነበረ። እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኑም ቤተ ክርስቲያን ተብሎ እንዳይጠራ በተሰጣቸው ሥልጣን መሠረት አግደውት ነበር ፤ እግዱ ግን ይፈታ አይፈታ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። ይህንን ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ ቤተ ክርስቲያን ባርከን ከፈትን ላሉት ካህናት እስከ አሁን ድረስ የተወሰደ ቅጣት መኖሩ የታወቀ ነገር የለም። የቤተ ክርስያናችን የሕግና የሥርዓት መጽሐፍ የሆነው ፍትሐ ነገስት ቄስ ወይም ዲያቆን በሀገሩ የተሾመውን ኤጲስ ቆጶስ ንቆ አቃሎ ለብቻው ቤተ ክርስቲያን ከሠራ ኤጲስ ቆጶሱ እስከ ሦስት ጊዜ ጠርቶት ካልመጣ እሱና እሱን የመሰሉት ከሹመታቸው ይሻራሉ ይላል(ፍትሐ ነገስት አንቀጽ ፷ ረስጠብ 19)። ቄሱ እንኳን ያለ ሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ፈቃድ ቤተ ክርስቲያን መክፈት ቀርቶ ያለበትን ቤተ ክርስቲያን ትቶ ወደ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ከሄደ እንዲመለስ ተነግሮት ካልተመለሰ ከሹመቱ ይሻራል ይላል (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 6 ረስጣ 14 ኒቂያ 14)። ሕገ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ደግሞ ፍትሐ ነገስት እንደሚያዘው ድርጊቱን ለፈፀሙ ካህናት ሥልጣነ ክህነታቸው ስለመሻሩ ከሀገረ ስብከቱም ሆነ ከሊቀ ጳጳሱ ግን ለምእመናን የተላለፈ መልዕክ የለም።

ይህ ሆኖ ሳለ በሀገረ አሜሪካ ከተመሰረቱት አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት መካከል በእድሜ አንጋፋ የሆነው እና “በገለልተኛ አስተዳደር” ውስጥ የሚተዳደረው የዋሽንግተን ዲሲ ርዕሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ያለ ኢጲስ ቆጶስ ፈቃድ “የተከፈተ” ቤተ ክርስቲያን እውቅና መስጠቱን ብዙዎች የአጥቢያው ምእመናን እና ሰንበት ተማሪዎችን አበሳጭቶዋል።

ድርጊቱም በተፈጸመበት ወቅት (ለማንበብ የሚከተለውን ይጫኑ) በደጀ ሰላም ይህንን ዘገባ አቅርቤ ነበር። ይህንን ጽሑፍ ያበሳጨው የየዛኔው ዲ/ን የአሁኑ ቀሲስ (ለማንበብ የሚከተለውን ይጫኑ) ተስፋዬ መቆያ የቤተ ክርስቲያኑ መመስረት ደግፎ ትምህርት ማስተማሩ የሚታወስ ነው።

4 comments:

Anonymous said...

አይ የአንተ ነገር,,,የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ,,,ሆነ እኰ ነገርህ፤ ካህናት አባቶችና ዲያቆናት ወንድሞች በአንድነት ስንት ነገር ብለውና ተባብለው የአድነት ለውጥ ለማምጣት ስንት እየጣሩ ባለበት ሰአት አንተ አሁንም ከየትም በምትለቃቅመው፤ በማያንጸው፤ ተራ በሆነው ጽሁፍህ የግለሰቦችን ስም እየጠቀስክ ልዩነትን ትሰብካለህ?,,,አሁንም እዛው ነህ?,,,ምንአለ ቢበቃህና ልብህን ለጽድቅ ስራ ብታነቃው?,,,አንተው ጨልሞብህ ምን አለ ሌላውም በአንተ የጽድቅ ብርሀን በደበዘዘበት የጥፋት መንገድ እንዲሄድ ባታደርግ?,,,ልብ ይስጥህ ሌላማ ምን ትባላለህ?,,,እኛስ በአንተ ጥፋት እናዝንልሀለን እንጂ አናዝንብህም!!!,,,ግን ሰው እንዴት ሁልግዜ ጠማማን ነገር ያስባል?,,,ልዩነትንስ ይሰብካል?,,,ይህንን በማድረግ ርስት መንግስተ ሰማይን መውረስ የሚቻል ከሆነ (ክፉ ወሬን በማውራት፤በልዩነት) አስረግጠህ ጻፍልንና እኛም እንደ አንተው ክፉ፤ የማያንጽ ተራ ወሬን እያወራን ራሳችንን ለጽድቅ እናዘጋጅ!!! አገሩ እንደሆን ለዚህ የተመቸ ነው።,,,አንተ ግን መንፈሳዊ ነህ መንፈሳይ?,,,እህህህ,,,ድንቄም መንፈሳዊ!!!

Anonymous said...

" ይህንን ድርጊት ያበሳጫቸው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብረሃም የተከፈተው ቤተ ክርስቲያን ክርሲያኖች እንዳይደለገሉበት ቃል ምዕዳን አስተላልፈው ነበረ። እንዲሁም ቤተ ክርስቲያኑም ቤተ ክርስቲያን ተብሎ እንዳይጠራ በተሰጣቸው ሥልጣን መሠረት አግደውት ነበር "

ይገርማል
እነዚህ ሰዎች የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መሰበክ የክርስትና ሕይወት መስፋት
የነሱን የባዶ ሥልጣን የሚያጋልጥባቸው ስለሆነ ይፈራሉ ከዛም ይበሳጫሉ ቢችሉ ያስፈራራሉ
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አትፍሩ መላእክትም ሐዋርያትም አትፍሩ ብለው ማስተማራቸውን አያውቁም

ለ1500 ዐመታት በላይ ክርስቲያኖች ኢትዮጵያውያን ቤተ ክርስቲያን ሰርተው ሲገለግሉ ጳጳስ ሊቀ ጳጳስ አልነበረም

ጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የሰበከው በሜዳ በተራራ በሰዎች ቤት ነው

ሐዋርያት ጴጥሮስ ጳውሎስ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በመስበክ ደከሙ እንጂ ሕንፃ ለመባረክ በመኪና በአውሮፕላን ወርቅ በአንገታቸው አርገው ተከናንበው አልተንሸራሸሩም

አንተም አሐቲ ተወሕዶ ብለህ በጠራሀት BLOG የምትጽፈው የሚያሳስብ ጉዳይ አይደለም

Hailemariam said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ
አሜን!!!!!!!!!!
ከዚህ ከፍ ብሎ በዚህ ጉዳይ ላይ ሃሳባችሁን የገለጣችሁ
ወገኖች ለመሆኑ ሁለት ጊዜ እራሳችሁን ጠይቃችሗል?
ወይስ የቁጭት የንዴት ይመስላል መልሳችሁ:: እውነት
የኢትዮጵያ ቤ/ክ ጳጳስ 1500 ዘመን አልነበራትም
ማለት ስድብ አይሆንም ወይ? ዲ ሲ ባልኖር የእያንዳንዱን ቤ/ክ አሳዛኝ ውዥንብር ባላውቅ በቆጨኝ
አንድ እውነት ልንገርህ ወገኔ የፓትሪያርክ ፓውሎስ
በኢትዮጵያ ላይ መቀመጥ የኔን ተዋህዶ እምነት ማቆም አይችልም::ይህን ስልህ በኢ.ኦ.ቤ/ክ..
ችግር የለም ሳይሆን እንደ ጉሊት መደብ እዛም አዛም
ከፈትን ማለቱ ሳይሆን የሚበጀን :: አንድ ሃሳብ
አንድ ልብ ሆነን ወደ እግዚአብሔር ማልቀስ ነው
እኛ ኢትዮጵያውያን ነን እምነታችን ንጽሂት ተዋህዶ
ናት:: ከዚህ ወደ ኢትዮጵያ ስንሔድ ስደተኛ ሲኖዶስ
ደጋፊነታችን ገለልተኛነታችን ፓስፊክ ኦሽን ላይ
ፍሪዝ እናረገዋለን :: ያቺ የሰው ልጅ ተወልዶ
ያለ ወቅታዊ ልብስ: ምስኪን ወገኔ ደሃ አደጉ ያለ
ተመጣጣኝ ምግብ የሚኖርባት ሃገራችን ምድራዊ
ገነት ገና ከተሳፈርንበት አይሮፕላን ስንወርድ ማቀዝቀዣ ወይም ማአሞቅያ ሳይከፈትልን በተፈጥሮ
ለጤና ተስማሚ በሆነ አየር የቤተሰብ የዘመድን
ናፍቆት ተወተን ልንዳር የሄድን ተድረን ስለት
ያለን የተሳልንበት ቤ/ክ ስለት አስገብተን::በ አሜሪካ
ዲሞክራሲ የስደተኛ እና ውስጡ 4 አይነት መልክ
ያለው ግራ የገባውም ኢትዮጵያ ቤ/ክ በተክሊል ሲዳር ዲያቆኑም መዘምራኑም ገለልተኛ ነኝ አይልም የኢትዮጵያ ኦ/ተዋህዶ ልጅ ነኝ ነው የሚለው
የእርግማን ነገር ሆኖ ወደ አሜሪካ ሲመለስ ያ ፓስፊክ ላይ ፍሪዝ ያደረገው የመለያየት መንፈስ እጥፍ ድርብ ሆኖ እላያችን ላይ ይከማራል::
እኛ አሁን እየተከተልን ያለነው እያስደሰትን ያለነው
ስጋችንን ነው እንጂ ፈጣሪያችንን አይደለም:: እውነትማ ከተጋረደች ቆየች:: እኔ እውነቱን ልንገራችሁ ሃዘኔን ለመግለጽ ቃላት አይደለም እንባም
አይበቃኝም:: በነጮች ሴራ መላው አፍሪካ በቅኝ
ግዛት ስትማቅቅ እንግሊዝ አሜሪካንን ያህል አገር
ካናዳን ያህል አገር ገዝታ ኢትዮጵያንም ጭምር ስትወር የጠበቀን ፈጣሪ ነበር:: የቅዱሳንን ጸሎት
እንባቸውን ትህትናቸውን እያየ ለምን ልባቸው ለእግዚአብሔር የተመቸ ስለነበር:: እነሱ የኖሩት
ለገንዘብ ሳይሆን ለጥቅማጥቅም ሳይሆን ለሚወዷት
ሃገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያና ንጽሂት ለሆነችው
ተዋሕዶ ሃይማኖታቸው ነው:: ታድያ ወገኖቼ
አንተ ከየትኛው ነህ ብትሉኝ? መልሴ እግዚአብሔር
ለኢትዮጵያ ቤ/ክ ሰው ይፍጠርላት!!!! ከሚሉት::
ምነው ብትሉኝ በዚሁ አሜሪካ በ ዺ ሲ ያነበኩት
መጽሃፍት አብዛኛው እንደየ ፓርቲው ይለያያል
ቛሚ ምስክር ከ 10 አመት በፊት :: ከዚህ አለም
በሞት የተለዪት አቡነ ይስሃቅ የጻፉት እንዲሁም
በምገለገልበት ደብር በ ማርያም ቤ/ክ ማህበረ ካህናት ሰኔ 15 1994 ማኅተም የተባለው እና
ሌሎችም የብዙ ብዙ ናቸው? ታድያ እኔም እንደ
ተዋህዶ ልጅነቴ ያቅሜን እየረዳሁ እየታዘዝኩ
አገልግያለሁም ተገልግያለሁም የተለያዩ ጥያቄዎችንም
ጠይቄማለሁ:: ጅምሩ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ማህበረ ካህናት በመጽሔቱ ጀርባ በአሁንዋ ደቂቃ እነዛ
ሊቃውንት አባታቸውን የኒታ ይሉ የነበሩ ቆሞሳት
ቀሳውስት ሲበጣበጥ- ይቅር ተባባሉ ብለው የሚያስተምሩን እንሱ ፈጽመው ለይቅርታ ልባቸው
ያለዘበ መሆኑን ሳይ አዝኛለሁ:: የኢትዮጵያ ፓትሪያርክም ዘረኛ እና ጉድፋቸውን አስተካክሉ
ሲባሉ ቂም በቀለኛ ከሆኑ: ስደተኛ ሲኖዶስ ያሉት
ወገኖች ቅዳሴ ቖነጻጽለው ፒያኖ አስገብተው
መናፍቁን ፓስተር ክህነት ሰተው:: ኢትዮጵያ የሞዝቦልድ ሰራተኛው ጡረታ ከወጣ በኁላ ጎጡ
ተቆጥሮ መላከ.... ተብሎ የስደተኛው ገንዘብ ጠብደል ያለ ደሞዝ እየተከፈለው ፓትርያርክ በህይወት እያለ ፓትርያርክ አይሾምም መንግስት
እንመሰርታለን ሲል:: የገለልተኛ አባቶቼ ደግሞ
የስደተኛ ሲኖዶስ ጳጳሳት ሹመት አውግዘናል ሲሉ
የኢትዮጵያው ሲኖዶስ የውጭውን ሲያውግዙ::
አቡነ....አባ ጳውሎስ ትክክለኛ ፓትሪያርክ ናቸው
በለው ሲገቡ እን ቆሞስ ......ከነበሩበት ማህበር
ተነጥለው ጳጳስ ሆኑ ሲባል እን እገሌ ባለ -- ፎቅ
ቤ/ት አሰሩ ሲባል:: ሌላው ማሕበረ ቅዱሳንን ሲኮንን: ሁሉም እራሱን ንጹህ አድርጎ እኔ ትክክልነኝ
ሲል አንዳንዱ ደግሞ እኔ እያለሁ ሌላ ካህን ድርሽ
እንዳይል ሲል እንደ ስልክ እንጨት ግትር ብሎ ህዝቡን ውስጥ ውስጡን ሲከፋፍል ታድያ ወገኔ
ጥፋቱ የአንድ የ ፓትሪያርክ ፓውሎስ ብቻ ሳይሆን
የሁላችንም ነው:: አባቶች በግልጽ ልውቀሳችሁ
1) ለስጋችሁ አድልታችሁ ለመንበሩ ይበቃል
ብላችሁ ይደልዎ ብላችሁ ተባርካችኋል ::መቃወም
የጀመራችሁት አሜሪካ ስትገቡ ነው:: ለምን?
ቢባል እንደ እን ሐዋርያ ጳውሎስ ለ ክርስቶስ
ቤ/ክ የሚሰዋ ጠፍቶ በ አሁኑ ሰአት ሁሉም እራሱን
የህንጻ ባለቤት አድርጎ መነክሴ አባቶች ሳይቀሩ
የሚያወሩት ስለ ዸሞዝ አነሰብን እንጂ:: ስለ ቤ/ክ
አንድነት አይደለም:: እንደውም በስደት አለም የምንገኝ: ምእምናን የቤ/ክ ስራትዋን ስለማናውቅ
ጥሩ መጠቀሚያ ሆነናል: አብረን በመርመስምስ ዛሬ ሀይማኖታችን የደረሰችበት ችግር ተጠያቂ ነን
እስቲ ንገሩኝ ወገኖቼ የ ኢትዮጵያ ስህተት ነው
እያልን እዚህም እየባስን ነው እንደውም እኮ ኢትዮጵያ ከላይ ውጥንቅቱ ይውጣ እንጂ ህዝበ ክርስትያኑ አንድ ልብ ነው:: አሜሪካ ካንዱ ቤ/ክ
ወደ ሌላው ብንሄድ እኮ ካህኑ እንድ ህጻን አኩርፈው
መስቀል ለማሳለምም ይቀፋቸዋል::
ታድያ ሁላችንም ቁጭ ብለን እጃችንን ንጹህ አድርገን
ፓትሪያርኩን ስናማ እድሜ ጨመርንላቸው::
ሁላችንም ተዋሕዶ አማኞች :: ለአፍታ ሃሜቱን
ትትን ወደ ፈጣሪያችን በእንባ በጸሎት ብንጮህ
አምላክ በሰማን ነበር::
ይሀው ሁከቱ ገሃድ እየታየ ነው::
ክፍል ሁለት ይቀጥላል
እግዚአብሔር የ ቤ/ክ ትንሳኤዋን ያሳየን!!!
ኃይለማርያም ከ ዋሽንግተን

Tekelemariam said...

ኃ/ማርያም ልቤ ውስጥ ያለውን ተንትነህ ነው የጻፍከው:: አንድ ወንድማችን ስሙን ካልተሳሳትኩ
ዲ/ን ሕዝቅያስ ማሞ የተባለ የሕዝቡን ጥያቄ ማን
ይመልሰው እና ኦ/ተዋሕዶ መጻሕፍ ቅዱሳዊ ናት
አይደለችም ብሎ ያስተማረው ትምህርት ልብ የሚነካ
ነው:: ሐይማኖቱ ለሚገደው ኢትዮጵያዊ በሙሉ::አባቶች ታረቁ ብሎ እንደጥንታችሁ በአንድነት
ሆናችሁ ባርኩን ብሎ ሕዝቡንም ወገኖች እናንተም
አባቶችን በምታገኙበት ቦታ በቃ በሏቸው አንድ እንሁን
ብሎ አስተማረ በ ሲ ዲ ም ጭምር :: ሐይማኖታችን እንዴት ልዩ በሰባቱ ሰማያት ሚስጥራት በየደረጃ ሐዋርያት የሰሩትን ስርኣት
ብዙ ተማርን :: እኔ ያዘንኩት ምነው አባቶቼ ያን
የመሰለ እውቀት ይዘው ስለ ሰማያዊው ጸጋ እያስተማሩን: ወገኖቼ ይሕን አለም አትውደዱት ሀላፊ ነው እና እያሉ ብዙዎች ግን የሚኖሩት የሚሰብኩንን ሳይሆን እኛን የሚያሰናክል ነው ያ ነው
እኔን የሚያሳዝነኝ:: ታድያ ዲ/ን ዝቅያስ ምን እንዳለ
ታውቃለህ አባቶች ብቻቸውን ምንም ማድረግ አይችሉም ነበር እኛም ከስር ባንርመሰመስ ::
ካለንበት ሃገር እንኳን ዩናይትድ ማለት ምን ማለት
መማር ያቃታቸው ክርስትያኑ ሕዝብ ሳይሆን እራሳቸው አባቶቻችን ናቸው::
ተክለማርያም ከ ሜሪላንድ