Sunday, February 27, 2011

"የመጽሐፍ ሂስ ወይስ የዶሮ ኩስ" ይድረስ ለቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

እዚህ ሀገረ አሜሪካ ውስጥ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ እና አባ መዓዛ በየነ “እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአዳም ኃጥያት ወርሳለች” የሚል አስተምህሮ እያስፋፉ ናቸው:: ሁለቱንም በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ስም የየራሳቸው የሆነ በግል የሚያስተዳድሩት ቤተ ክርስቲያን አላቸው:: ይህንን አስተምህሮ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እንደማትቀበለው ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ታምሩ የዛሬ ስድስት አካባቢ ምላሽ ሰጥተውበት ነበር:: የእነዚህን ሰዎች አስተምህሮ በመቃወም በ2002ዓ/ም መምህር ሀብተ ማርያም ተድላ የተባሉ አንጋፋ አባት “ነጭ እንቁ በአዳም ገላ” በሚል ርእስ የመልስ መጽሐፍ ጽፈውበታል:: እንዲሁም ደግሞ ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው በበኩላቸው የእነዚህ ግለሰዎች አስተምህሮ የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ እንዳልሆነ በጽሑፍ ምላሽ ሰጥተውበት ነበረ:: በቅርቡ ደግሞ በቀሲስ አብረሃም ኅ/ሥላሴ “ማርያማዊ ሕገ ሃይማኖትና ተማኅጽኖ” በሚል ርእስ የአስተራየ አስተምህሮ በመቃወም መጽሐፍ ጽፈዋል:: ቀሲስ አስተራየ ጽጌ የቀሲስ አብረሃም ኅ/ሥላሴ መጽሐፍ በመቃወም 32 ገጽ ያለው ጽሑፍ “ኢትዮ ሚድያ” ድህረ ገጽ ላይ ጽፈው ነበረ:: የሚከተለው ጽሑፍ ለአስተርአየ ጽጌ ምላሽ የሚል ደርሶኛል:: መልካም ንባብ::

የመጽሐፍ ሂስ ወይስ የዶሮ ኩስ
ይድረስ ለ “ጠልሰም በዲሲ ደብተራ” ጨንቋሪ
ከደብተራ እሳቱ ቦጋለ

Thursday, February 24, 2011

መንፈሳዊ አስተዳደር መቼ ተጀመረ? ማንስ ጀመረው? ክፍል ሁለት

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ሐዋርያዊት በመሆኗ የቀደሙትሙት አባቶቻችን ሐዋርያት ያስቀመጡት ትውፊት ሳታፋልስ መንበሯን መንበረ ማርቆስ በማድረግ ለ1600 ዘመናት ኖራለች:: ቤተ ክርስቲያናችን ምንም እንኳ ጥንታዊት ብትሆንም በራሷ ልጆች መመራት የጀመረችው ግን ገና አንድ ምዕተ ዓመት እንኳ አልሆናትም:: ቤተ ክርስቲያናችን የምትመራበት የሥርዓት መጽሐፍት አሏት:: የመንፈሳዊም የዓለማዊውም እውቀት የነበራቸው የሃርቫርድ ዪኒቨርስቲ ተመራቂው ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ እና በሌሎችም ምሁራን የተረቀቀው ቃለ ዓዋዲ በ1965ዓ/ም በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በአገልግሎት ላይ ውሎዋል:: ይህ ቤተ ክርስቲያናችን የምትመራበት ቃለ ዓዋዲ በዚህ በሰሜን አሜሪካ የምንኖር ምእመናን፤ ካህናት እንዲሁም ሰንበት ተማሪዎች በአብዛኛው ማለት ይቻላል ተግባራዊ ማድረግ አልቻልንም::  የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር በተመለከተ ቃለ ዓዋዲ መሠረት በማድረግ አንዳንድ ነጥቦች እንደሚከተለ ቀርቦዋል::

Friday, February 18, 2011

መንፈሳዊ አስተዳደር መቼ ተጀመረ? ማንስ ጀመረው? ክፍል አንድ

“መንፈሳዊ አስተዳደር ከእግዚአብሔር የተግኘ፤ነገደ መላእክት የተመሩበት፤የቀደሙ አባቶች በሕገ ልቦና የተገለገሉበት፤በሕገ ኦሪትና በሕገ ወንጌል በተግባርና በፅሑፍ የተገለጠ ነው”። (የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር ገጽ ፩)
፩    መንፈሳዊ አስተዳደር በዓለመ መላእክት
 •   ሰማያዊውን የእግዚአብሔር ዙፋን የሚሸከሙ ኪሩቤል/ዐርባዕቱ እንስሳ/፤ መንበሩ የሚያጥኑ ሱራፌል/ሃያ ዐራቱ ካህናተ ሰማይ/ መንፈሳዊ አስተዳደር ተለይቶ ተሰጥቶአቸዋል።
 •  ኃይላት በመንፈሳዊ ሕይወት የደከሙ ክርስቲያኖችን እንዲያበረታቱ በአመላካዊ ጥበብ ታዘዋል::
 •   አርባብ(የሚጋርዱ) የእግዚአብሔርን መንበር በክንፋቸው ይሽፍናሉ::
 •   ሥልጣናት ፍጥረተ ዓለምን እንዲጠብቱ የምጽአት አዋጅ እንዲያበስሩ ተወስኖላቸዋል::
 •   የሥልጣን ተዋረድን በሚያመለክት ሁኔታ ለዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት አለቃ ተሹሞላቸዋል::  “ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጣሁ” ኢያሱ 5፤14 

Saturday, February 12, 2011

አንድ የአስተዳደር መዋቅር ለምን?

 •  በሀገረ አሜሪካን በየ ዘርፉ የተበታተኑት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በአንድ የአስተዳደር መዋቅር ቢሰባሰቡ ጠቀሜታው ምንድ ነው? ጉዳቱስ? በአንድ መዋቅር ማስተሳሰር አንድነትን ያመጣዋልን?አንድነት ማለትስ ምን ማለት ነው?  
 •     ቤተ ክርስቲያን አንድ ብቻ የአስተዳደር መዋቅር ለምን አስፈለጋት? የቤተ ክርስቲያን የአስታዳደር መዋቅር ሃይማኖታዊ ይዘቱስ ምንድ ነው?
 •  የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰሜን አሜሪካን ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ዕድሜ ብታስቆጥርም እንደ ሌሎች አሐት አብያተ ክርስቲያናት ማለትም(ኮፕት፤ ህንድ፤አርመኒያ፤ሶርያ) በአሜሪካን ሀገር በፌደራል ደረጃ ህጋዊ እውቅና የላትም:: ህጋዊ እውቅናውስ ያላገኘችበት ምክንያት ምንድ ነው? ህጋዊ እውቅና ብታገኝ ጠቀሜታው ምንድ ነው? ጉዳቱስ?
 •  አሁን በተለያዩ እስቴቶች በግለሰዎች ሥም እየተገዙ(እየተሰሩ) ያሉት አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት ቀጣይ ለሚረከበው ትውልድ የሚኖረው ተጽዕኖ ምንድ ነው? በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ስም(ባለቤትነት) ያልተገዙበት ምክንያትስ ምንድ ነው?
 •   አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን ከመከላከል አንጻር በአንድ መዋቅር መሆን ጠቀሜታ ይኖረው ይሆን?
 •  የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰሜን አሜሪካ ሌላ የተለየ ቀኖና ያስፈልጋታልን?
 • የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር በአሜሪካ ማጠናከር ከኢህአዴግ(ወያኔ) ጋር ያለው ተዛምዶስ ምንድ ነው?
በእነዚህና በመሳሰሉት በቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር መዋቅር ዙርያ የሚነሱ ጥያቄዎች አስተያየታችሁን እንድለግሱ በትህትና እጠይቃለሁ:: qedamawi@gmail.com, qedamawi@live.com
እግዚአብሔር ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!!