Saturday, February 12, 2011

አንድ የአስተዳደር መዋቅር ለምን?

  •  በሀገረ አሜሪካን በየ ዘርፉ የተበታተኑት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በአንድ የአስተዳደር መዋቅር ቢሰባሰቡ ጠቀሜታው ምንድ ነው? ጉዳቱስ? በአንድ መዋቅር ማስተሳሰር አንድነትን ያመጣዋልን?አንድነት ማለትስ ምን ማለት ነው?  
  •     ቤተ ክርስቲያን አንድ ብቻ የአስተዳደር መዋቅር ለምን አስፈለጋት? የቤተ ክርስቲያን የአስታዳደር መዋቅር ሃይማኖታዊ ይዘቱስ ምንድ ነው?
  •  የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰሜን አሜሪካን ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ዕድሜ ብታስቆጥርም እንደ ሌሎች አሐት አብያተ ክርስቲያናት ማለትም(ኮፕት፤ ህንድ፤አርመኒያ፤ሶርያ) በአሜሪካን ሀገር በፌደራል ደረጃ ህጋዊ እውቅና የላትም:: ህጋዊ እውቅናውስ ያላገኘችበት ምክንያት ምንድ ነው? ህጋዊ እውቅና ብታገኝ ጠቀሜታው ምንድ ነው? ጉዳቱስ?
  •  አሁን በተለያዩ እስቴቶች በግለሰዎች ሥም እየተገዙ(እየተሰሩ) ያሉት አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት ቀጣይ ለሚረከበው ትውልድ የሚኖረው ተጽዕኖ ምንድ ነው? በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ስም(ባለቤትነት) ያልተገዙበት ምክንያትስ ምንድ ነው?
  •   አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን ከመከላከል አንጻር በአንድ መዋቅር መሆን ጠቀሜታ ይኖረው ይሆን?
  •  የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በሰሜን አሜሪካ ሌላ የተለየ ቀኖና ያስፈልጋታልን?
  • የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር በአሜሪካ ማጠናከር ከኢህአዴግ(ወያኔ) ጋር ያለው ተዛምዶስ ምንድ ነው?
በእነዚህና በመሳሰሉት በቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር መዋቅር ዙርያ የሚነሱ ጥያቄዎች አስተያየታችሁን እንድለግሱ በትህትና እጠይቃለሁ:: qedamawi@gmail.com, qedamawi@live.com
እግዚአብሔር ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!!

1 comment:

Anonymous said...

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

መቸም የቤተክርስቲያናችን ነገር ሲነሳ ሁላችንንም የሚያንገበግበን ብዙ ችግር አለ ይህም ልጆቿ ሁሉም እራስ ወዳዶች በመሆናቸው የራሳቸው ስም ከፍ እንዲል እንጅ ስለ ቤተክርስቲያን ምንም የማይጨነቁ በመሆናቸው ስለ ቤተክርስቲያን ሰላም ብዙ መፍትሔ እያለ እያወቁ መፍትሔውን አፍነው ይዘው ቁጭ ብለዋል እስከ መቼ ይሆን ? አንድ አስተዳድራዊ መዋቅር ለቤተክርስቲያናችን በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም ቤተክርስቲያን አንዲት ስለሆነች ,,,አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት ኤፌ 4፥5 ,, አሁንም ቢሆን ቤተክርስቲያን አንዲት ነች የተከፋፈልነው ያልታደልነው ጡት ነካሽ የሆነው ልጆቿ ነን እንጅ ቤተክርስቲያን ምንጊዜም አንዲት ነች በተለይ በዚህ ባለንበት አሜሪካን ሃገር ያለው መከፋፈል የሃይማኖት መሪዎች ችግር ነው እንጅ ህዝቡ በተለያየ መንገድ ይገናኛል ለቅሶ ቤት ሰርግ ቤት መዝናኛ ቦታ አንድ ነው የሚጣላው ቤተክርስቲያን ሲመጣ ነው ምክንያቱ ደግሞ የሃይማኖት አስተማሪዎቹ ከአንድነት ይልቅ መለያየትን ስለሚሰብኩ ህዝቡ ግራ ተጋባ ከ 3 ዓመት በፊት የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሊቀጳጳስ ሆነው ተሹመው የነበሩት የአሁኑ የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ጥሩ መንገድ ለማስያዝ ሞክረው ነበር ህዝቡን ወደ አንድነት መልሰውት ነበር ያው አልቆዩም ተነስተው ሄዱ ለምን እንደሆነ አይገባኝም ጥሩ እንቅስቃሴ የሚያሳዩ አባቶች በቦታቸው ላይ እንዲቆዩ አይደረግም ታዲያ በሳቸው ተተክተው የመጡት አቡነ አብርሃምም የበኩላቸውን እየሞከሩ ነው ያሉት ነገር ግን ወጣቶችን ብቻ ይዘው ለመጓዝ መወሰናቸው መንገዳቸው የትም እንደማይደርስ ያሳያል ምክንያቱም ወጣቱ ምንም ችግር የለበትም ወጣቱ ሊያዝ የሚችለው ምሁራኑ እና አዋቂዎች አብረው ሲያዙ ነው እንጅ ልጆችን ብቻ ይዞ እጓዛhl።ሁ ማለት በኔ አስተያየት በደንብ ሊጤን የሚገባው ነገር ነው እላለሁ ደግሞም በአሜሪካን ሃገር ውስጥ ባሉት አብያተክርስቲያናት ውስጥ ያሉት ምሁራን ብዙ ስለሆኑ ከነሱም ጋራ ተመካክሮ ለመስራት ቢሞከር ይሻላል እንጅ በየቦታው ጥቂት ወጣቶችን እየገነጠሉ ቤtt,ክርስቲያን ማቋቋም ከበፊቱ ስህተት የተለየ መልክ የለውም ምክንያቱም ቤተክርስቲያን መቋቋሙ ሳይሆን ህዝቡ ወደ አንድነት መጥቷል ወይ ? ነው ጥያቄው ቤተክርስቲያን ለመክፈትማ እዚህ ሃገር ችግር የለም እንኳን ጳጳስ ዲያቆንም ምዕመኑም ከፍቻለሁ እያለ ነው ቁምነገሩ እሱn አይደለም ጳጳሱ ሲከፍቱ ቆሞሱም እየከፈቱ ነው እዚህ ላይ የምናየው የባሰ ልዩነቱን እያሰፋነው ነው መቸም እኔ የሚመስለኝ ተቀራርቦ ለመወያየት እራስን ዝቅ አድርጎ በትህትና ተጉዞ አንድነት የሚመጣበትን መንገድ መፈለግ ነው እንጅ የሚሻለው አሁን እየተጓዝንበት ያለው መንገድ ሙሉ በሙሉ ስለቤተክርስቲያን ሲባል የታለመመንገድ ነው ለማለት ያዳyt,ኛል ምክንያቱም በውስጡ ብዙ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮች ስላሉበት ነው በተረፈ ሃሳቤን ከተቀበላችሁት አስተላልፉት ካልተመቻችሁ ግን እንደአስተያየት ተመልክታችሁ trash ማድረግ ትችላላችሁ የሰላም አምላክ መድኃኔ ዓለም ለቤተክርስቲያናችን ሰላሙንና አንድነቱን ይስጥልን አሜን

ፍቅረ ማርያም ነኝ ከዋሽንግተን ዲሲ