Thursday, February 24, 2011

መንፈሳዊ አስተዳደር መቼ ተጀመረ? ማንስ ጀመረው? ክፍል ሁለት

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ሐዋርያዊት በመሆኗ የቀደሙትሙት አባቶቻችን ሐዋርያት ያስቀመጡት ትውፊት ሳታፋልስ መንበሯን መንበረ ማርቆስ በማድረግ ለ1600 ዘመናት ኖራለች:: ቤተ ክርስቲያናችን ምንም እንኳ ጥንታዊት ብትሆንም በራሷ ልጆች መመራት የጀመረችው ግን ገና አንድ ምዕተ ዓመት እንኳ አልሆናትም:: ቤተ ክርስቲያናችን የምትመራበት የሥርዓት መጽሐፍት አሏት:: የመንፈሳዊም የዓለማዊውም እውቀት የነበራቸው የሃርቫርድ ዪኒቨርስቲ ተመራቂው ሊቀ ጉባኤ አባ አበራ በቀለ እና በሌሎችም ምሁራን የተረቀቀው ቃለ ዓዋዲ በ1965ዓ/ም በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በአገልግሎት ላይ ውሎዋል:: ይህ ቤተ ክርስቲያናችን የምትመራበት ቃለ ዓዋዲ በዚህ በሰሜን አሜሪካ የምንኖር ምእመናን፤ ካህናት እንዲሁም ሰንበት ተማሪዎች በአብዛኛው ማለት ይቻላል ተግባራዊ ማድረግ አልቻልንም::  የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር በተመለከተ ቃለ ዓዋዲ መሠረት በማድረግ አንዳንድ ነጥቦች እንደሚከተለ ቀርቦዋል::

  የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ
 •  የቤተርስቲያን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎትን የተሟላ ለማድረግ ከአጥቢያ ቤተክርስቲያን እስከ መንበረ ፓትርያርክ የሚደራጅ የካህናትና የምእመናን ማኅበራዊ መዋቅር ነው::
 •  የራሱ መዋቅርና የአሰራር ደንብ አለው::
 • ይህም የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ደንብ ቃለ ዓዋዲ ይባላል::
 •  ቅዱስ ሲኖዶስ ባለው ሥልጣን በ1965 ዓ.ም የወጣውን ቃለ ዓዋዲ በ1970 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜና በ1991 ዓ.ም ለሦስተኛ ጊዜ አሻሽሎ አውጥቶታል::
 • በቃለ ዓዋዲ ላይ፤ ስብከተ ወንጌልን ስለማስፋፋት መንፈሳዊና ዘመናዊ ት/ቤትን ስለማቋቋም የልማት ተቋማትን ስለመገንባት ስለመረጃና ቅርስ አያያዝ ስለ ሰንበት ት/ቤት አደረጃጀት በሰፊው ተዘርዝሯል::
 •  ካህናትንና ምእምናንን በሚያሳትፍ መልኩ ተደንግጓል::
 •  ይህም የቤተክርስቲያን ስንዱ እመቤትነትን ይመሰክራል::
 •  እኛንም ድርሻችን እንድንወጣ ያስገነዝበናል::
 •  በቃለ ዓዋዲ አንቀጽ 3 ቁጥር 1 ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ባለችበት ቦታ ሁሉ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እንዲቋቋም ያዛል
በየደረጃው የተቋቋመና የሚቋቋም የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤያት .   ፩.    የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ
 •    በአንድ አጥቢያ ወይም ሰበካ ውስጥ የሚገኙ ካህናት፤ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በአንድነት ተደራጅተው የሚመሰርቱት ነው::
 • የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ካህናትን፤ ምእመናንንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ያካተተ ጠቅላላ ስብሰባ የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ጠቅላላ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ይባላል::
 •   ቃለ ዓዋዲ አንቀጽ 8 የሚያክናውነውን ሥራ ይገልፃል::
 •  ጠቅላላ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ከአምስት ያላነሱ ከዘጠኝ ያልበለጡ አባላትን ያካተተ የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ /ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴን/ ያቋቁማል::
 •  የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ የአጥቢያው ቤተክርስቲያን ጠቅላላ  መንፈሳዊ ጉባኤና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ሊቀ መንበር ይሆናል::
 •  ለሰበካው መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባአኤ /ሥራ አስፈጻሚ/ አባልነት የሚመረጡ ካህናት፤ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች በቃለ ዓዋዲ አንቀጽ 10 በቁጥር 2 ከሀ-ሐ የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል::
 •   የመንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ/ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ/ ምርጫ በወረዳው ቤተክህነት አቅራቢነት በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ይጸድቃል::
 •  ተጠሪነቱም ለአጥቢያ ቤተክርስቲያን ጠቅላላ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ነው::
 •  በሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ/ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ/ በአባልነት የተመረጠ ካህን ወይም ምእመን በተመረጠበት አገልግሎት የሚቆየው ለሦስት ዓመት ነው::
 •  ከሁለት ጊዜ በላይ በተከታታይ መመረጥ አይችልም::
 •   የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ/ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ/ ሥልጣንና ተግባር በቃለ ዓዋዲ አንቀጽ 12 ተመልክቷል::
፪.    የወረዳ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ
 • በወረዳው ቤተክህነት ሥር ብዛታቸው ከአንድ በላይ የሆኑ አብያተክርስቲያናት በተወካዮቻቸው አማካኝነት በወረዳው ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ሰብሳቢነት የወረዳ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ያቋቁማሉ::
 • ተወካዮቻቸውም ከእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን በአስተዳዳሪው የሚመሩ አንድ ካህን፤ አንድ ምእመንና አንድ ወጣት ሲሆኑ የወረዳው ቤተክህነት ፀሐፊና የልዩ ልዩ ክፍሎች ሃላፊዎች አባላት ይሆናሉ::
 •  ይህም በዓመት አንድ ጊዜ የሚሰበሰብ የወረዳው ሰበካ ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ ይሆናል::
 • የወረዳው ሰበካ ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ በወር አንድ ጊዜ የሚሰበሰብ የወረዳ ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ/ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ/ ይመርጣል::
 •  የሁለቱም ሥልጣንና ተግባር በቃለ ዓዋዲ አንቀጽ 33 እና 35 ላይ ተመልክቷል::
 •  የወረዳው የቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ለወረዳው ሰበካ ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤና ለአስተዳደር ጉባኤው/ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው/ ሊቀመንበር ነው::
፫.    የመንበረ ጵጵስና ሀገር ስብከት ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ
 •  በአንድ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የወረዳ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤያት ተወካዮቻቸውን በመላክ የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት መንፈሳዊ ጉባኤን ይመሰርታሉ::
 • እያንዳንዱ የወረዳ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባአኤ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በማስመረጥ አንድ ካህን፤አንድ ምእመንና አንድ የሰንበት ት/ቤት አባል ከወረዳው ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ጋር ዐራት አባልትን ወክሎ ወደ ሀገረ ስብከቱ ይልካል::
 •  የሀገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊና የክፍል ሓላፊዎች የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት ይሆናሉ::
 •   የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የጉባኤው ርእሰ መንበር ነው::
 •  የመንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ሰበካ መንፈሳዊ የአስተዳደር ጉባኤ/ሥራ አስፈጻሚ/ ከአራት የማያንሱ ከስምንት የማይበልጡ ሆነው ከካህናት፤ከምእመናንና ከሰንበት ት/ቤት አባላት በጠቅላላ ጉባኤ ይመረጣሉ::
 •   የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴውና የመንበረ ጵጵስና የሰበካ ጠቅላላ መንፈሳዊ ጉባኤ ተግባርና ኃላፊነት በቃለ ዓዋዲ አንቀጽ 42 እና አንቀጽ 41 ላይ ተደንግጓል::
፬.    የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ
 •  ከየሀገረ ስብከቱ የተወከሉ ካህናት፤ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤት አባላት ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላታና የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያና የድርጅት ኃላፊዎች ጋር በአንድነት የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤን ይመሰርታሉ::
 •   የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን አጠቃላይ ስብሰባ ነው::
 •    ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው::
 • ፓትርያርኩ የጉባኤው ርእሰ መንበር ሲሆኑ የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጅ ም/ሊቀመንበር ይሆናሉ::
 •   ከመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ አባላት የተመረጡ፤የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ የአስተዳደር ጉባኤ/የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ/ ይቋቋማል::
 •  የመንበረ ፓትርያርክ ሰበካ አጠቅላይ መንፈሳዊ ጉባኤና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት በቃለ ዓዋዲ አንቀጽ 48 እና አንቀጽ 50 በዝርዝር ተገልፃል::

1 comment:

Anonymous said...

ante ignorant , do you think , there is true leadership in ethiopian orthodox church. you know it. you have dictator patriaric who doesnt obey the synode. he built his own god.he is elected by the weyane goverment.shame on you brother. if you are a preacher please say the true word. stop your poision. there is a fake leadership in ethiopian orthodox church. you heard about " abba zekarias ". he stole the church's money.ask adisu abebe , the voa journalist. you know you are living in america. YOu know this word" lead by example" do be spy. preach God's word not Gms propeganda,
think about it, you are living in freedom not slavery .