Monday, April 25, 2011

ማስታወቂያ ከ "ዝክረ አቡነ መልከ ጼዴቅ" ማኅበር

            አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን።
ወዳጅ ሊቀ ጳጳስና ብዙ ይሠራሉ ተብለው ተስፋ የተጣለባቸው ትጉህ ሐዋርያ፣ አንደበተ ርቱ ሰባኪ፣ መላ ዘመናቸውን ከስብከተ ወንጌል ሳይለዩ ከገጠር እስከ ከተማ ከሀገር ውስጥ እስከ ባህር ማዶ ወንጌልን ተጫምተው ወንጌልን ተሸክመውና ወንጌልን ተመርኩዘው በቅድስት ቤተክርስቲያን የኖሩ በእውነት ስለ እውነት እግዚአብሔርን ያገለገሉ ታላቅ አባት ነበሩ

 ኢት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የከምባታ ሃድያ ጉራጌና ስልጢ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የነበሩት ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን አንድነት አብዝተው የታገሉ የሊቃነ ጳጳሳት የመንፈስ ኩራት የጀርባ አጥንትና የቤተክርስቲያን መስካሪ ኮኮብ አባት በይበልጥም ቤተክርስቲያን በልማት ራሷን እንድትችል እና ከልመና እንድትላቀቅ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ይተጉ ነበር ብዙ ሥራዎቻቸው መካከል አንዱና ዋነኛው የነበረው ለነገይቷ ቤተክርስቲያናችንና አገራችን መልካም ዜጋን ለማፍራት በማሰብ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ሕፃናትን በማሰባሰብ ዘመናዊውንና መንፈሳዊውንም ትምህርት ማስተማር ነበር። የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆነና ብፁዕነታቸው ሕፃናቱ ያሰቡት ቦታ ሳይደርሱ በድንገት ዐረፍተ ዘመን ገታቸው።  
 
እነዚህ የነገ የአገርና ቤተክርስቲያን ተስፋ የሆኑ ሕፃናትም እንደ አባትና እናት እየተንከባከቡ የሚያሳድጓቸውን መንፈሳዊ አባት ማጣታቸው ለእነርሱ ጥልቅ ዘን እና የመንፈስ ስብራት ነበር። ስለዚህም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕፃናት አረጋውያንና መነኮሳት ለከፍተኛ ችግር ሊጋለጡ እንደሚቸሉ በመንገዘብ በሀገር ቤትና በውጭ ሀገር ባሉ የዕነታቸው የመንፈስ ልጆችና ምዕመናን አሳሳቢነት "ዝክረ አቡነ መልከ ጼዴቅ" የሚባል መንፈሳዊ የአገልግሎት ማኅበር በስማቸው ተመስርቶ የገቢ ማሰባሰብ ሥራ እየራ ይገኛል።

በብፁነታቸዕረፍት መላው ሕዝበ ክርስቲያን አዝኗል፤ ሆኖም በሕይወተ ሥጋ  ቢለየኑም  በአኅጉረ ስብከታቸውና በምሑር ገዳመ ኢየሱስ ጀምረውት የነበሩትንና ያቀዱትን ሥራዎቻቸውን ለማገ አሳዳጊ የሌላቸውን ሕፃናት በማሳደ ፣ትምህርት ቤቶቻቸውን በማጠናከርና፣ ገዳሙን በመንከባከብ የቤተክርስቲያን ልጅነታችንን ለመወጣት በአንድነት እንድንነሣ በትህትና እንሳስባለን።   

በመሆኑም የተከበራችሁ የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች፣ ካህናትና ዲያቆናት፣ ሰባክያነ ወንጌል እና መምራን፣ የሰበካ ጉባዔ ወይም የቦርድ አስተዳደር አባላት፣ መንፈሳዊ የአገልግሎትና የጽዋ ማኅበራት፣ ዘማርያንና ዘማርያት፣ የሰንበት ት/ቤት አባላት ምእመናን ና ምእመናት እና የተለያዩ የንግድ ተቋማት ባለቤቶችና ባለሃብቶች እንዲሁም በጎ አድራጊ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጉዳዩን አንገብጋቢነትና አሳሳቢነት በመረዳት አቅማችሁ የፈቀደውን የገንዘብ፣ የዕውቀትና የቁሳቁስ አስተዋጽ በማድረግ እንድትተባበሩ በትህትና እንጠይቃለን። ለምታደርጉልንም አስተዋጽ ከወዲሁ ምጋናችንን በልዑል እግዚአብሔር ስም እናቀርባለን።

በመሆኑም በዋሽንግተን ዲ.ሲ. ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የፊታችን ዳግም ትንሣኤ ማለትም እሁድ ሚያዚያ ፳፬ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም (May 1st, 2011 )ከቀኑ ፲፪ ሰዓት(6 PM) ጀምሮ የእራት ምሽት የተዘጋጀ መሆኑን እየገለጽን ህን የእራት ምሽት እና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ዝግጅት ሊረዳ የሚችል ማንኛውንም እርዳታ እንዲደርጉልን ትብብርዎን በሕፃናቱ ስም እየጠየቅን     ይህንንም ዝግጅት በኢንተርኔት (Live Broadcast U-stream ) ና በፌስ ቡክ  በቀጥታ የምናስተላልፍ መሆኑን እየገልጽን እርዳታችሁንም  በዚሁ አጋጣሚ online መለገሥ እንደምቻልም እያሳወቅን እግአብሔር ራዎን ይባርክልዎ ዘንድ  የዘወትር ሎታችን መሆኑን እንገልፃለን።  
ለበለጠ መረጃ በድረ ገጻችንን www.zamt.org እንዲሁም በስልክ ቁጥር 202-656-ZAMT (9268) ያገኙናል፡፡


                                              ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

              አቶ ግርማ ማሞ
                  Signed
የዝክረ አቡነ መልከ ጼዴቅ ማኀበር ሰብሳቢ


 


 
ቆሞስ አባ ፈቃደ ኢየሱስ ክንፈ ሚካኤል

                     Signed

የዝክረ አቡነ መልከ ጼዴቅ ኮሚቴ የበላይ ጠባቂ

ቆሞስ አባ ፈቃደ ኢየሱስ ክንፈ ሚካኤል


ቆሞስ አባ ፈቃደ ኢየሱስ ክንፈ ሚካኤል

                     Signed

የዝክረ አቡነ መልከ ጼዴቅ ኮሚቴ የበላይ ጠባቂ

 


No comments: