Tuesday, June 28, 2011

ጥያቄ አለኝ?

ይህንን ጥያቄ መታሰቢያ ኃይለ ሚካኤል ከተባሉ ግለሰ ፌስ ቡክ(face book) ላይ የተገኘ ነው::  ሁል ጊዜ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ ስናስባት ብዙኀኑ ምእመናን የሚያነሱት ምላሽ ያላገኘ ጥያቄ ነው:: ጥያቄው ወደ እውነተኞቹ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ቢደርስ ተገቢውን ምላሽ ያገኛል የሚል እምነት አለኝ::  እኔም አንዳንድ ነጥቦች ለማንሳት ተገድጃለሁ:: 
እንግዲህ  እኛ ባለንበት ዘመን በሰሜን አሜሪካ የምንኖር የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች በአባ ጳውሎስ አስተዳደር ፍትሕ ጎደለ የሚሉ ወገኖች ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር በመነጠል “ራስችን ችለናል ወይም ገለልተኞች ነን (indenedent church)” በማለት ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር መዋቅር ከተገለሉ  ሁለት አስርት ዓመታትን አስቆጥረዋል። እንዲሁም በቅርቡ “የገለልተኞች ጳጳስ ይሾምልን” በማለት እጀ መንንሻ ይዘው መንበረ ፓትርያኩ ድረስ በመሄድ ደጅ በመጥናት ላይ ናቸው::

Monday, June 20, 2011

“እኔም እነደ ባሕራን ሆኜ ነበረ” ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል

በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት 12/09/2003 ዓ/ም የሰኔ ሚካኤል ዓመታዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል ለማክበር ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ተገኝተው ነበረ::  ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በዲሲና አካባቢው ከሚገኙት በቁጥር 20 ከሚሆኑት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መካከል “ገለልተኛ” አስተዳደር ሥር ነን ከሚባሉት መካከል አንዱ ነው። ደብሩ የዛሬ አምስት ዓመት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ጵጵስና ሲሾሙ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ “የዋሽንግተን ዲሲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን ሰርቼ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሰጥቻለሁ” በማለት በመናገራቸው በደማቅ ሁኔታ የተጨበጨበለትና መንበረ ጵጵስና እንደሚሆን ቃል ተገብቶለት የነበረ ቤተ ክርስቲያን ነው። አጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ በባለቤትነት ወይም “article of incorporation” ከተመዘገቡት ሦስት ግለሰዎች መካከል አንዱ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ናቸው::

Tuesday, June 14, 2011

አልአዛርን ከሞት ያስነሳው ማን ነው? ለበጋሻው ደሳለኝ እና ለደጋፊዎቹ ለእነ ለተስፋዬ መቆያ የተሰጠ መልስ

(ታምራት ፍስሃ)፦  የዓለም መምህር የተዋሕዶ ምስክር የተወደደ ቅዱስ ቄርሎስ የሃይማኖትን ነገር እንዳስተማረን እንናገራለን:: ሃይማኖት አበው ዘቄርሎስ ምዕራፍ (70 -72) 
“ሥላሴ አትበሉ፣ እግዚአብሔር አትበሉ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሉ” (በጋሻው) ለማድመጥ ይህንን ይጫኑ
ምስጢረ ሥላሴ በከፊል ፦
እግዚአብሔር በአካል ሦስት በባህርይ አንድ ብለን እናምናለን፡፡ይኸውም  አንድ መለኮት ፣ አንድ ባሕርይ ፣ አንድ ልዕልና ፣ አንድ ጌትነት ፣ አንድ ክብር ፣ ከጥንት አስቀድሞ  የነበረ አንድ ቀዳማዊነት ነው:: ደግሞም በሦስት አካላት ፣ በሦስት ገፅት ፍፁማን ናቸው ፤ ግዙፋን አይደሉም ፣ ያልተፈጠሩ ናቸው ፣ ድካም የማይስማማቸው  የማይለወጡ ናቸው ፣ ለመገኘት ጥንት ለዘመን ፍፃሜ የላቸውም፡፡
 
ስለ ወልደ እግዚአብሔር በከፊል፦
ዳግመኛም ከአብ ባሕርይ የተገኘ አምላክ ፣ ቃል ፣ ወልድ ፣ ያልተፈጠረ ፣በመለኮት አንድ ከሚሆኑ ከሦስቱ አካላት አንድ አካል ፣ ከአብ ጋር ትክክል የሚሆን ፣ ዓለም ሳይፈጠር በመለኮታዊ  ልደቱ ከአብ የተወለደ ፣ ፍፁም  እግዚአብሔር አብን በመልክ የሚመስለው ፣ በባሕርይ የሚተካከለው የማይመረመረ የጌትነቱ መታወቂያ እንደሆነ እናምናለን፡፡ በገፁ በአካሉ ልዩ የሚሆን የአብ ልጅ ፣  አምላክ ፣ ቃል በአባቱ ፈቃድ ፣  በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ለእኛ ቤዛ ሆኖ ተሰጠ፡፡ ያልተፈጠረ ፣ ሥጋ ያልነበረው ፣ የማይለወጥ እርሱ እግዚአብሔር ቃል በማይመረመር ግብር በመልኩ ፣ በአምሳሉ  የፈጠረንን እኛን ሰዎችን ለማዳን ከአብ አንድነት ሳይለይ ከሰማይ ወረደ፡፡

Monday, June 13, 2011

እውን ተሐድሶ የለምን?

በቀደሙት ዘመናት የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በድብቅ ነበረ::  በዚህ ወቅት ግን አይናቸው አፍጥጠው ጥርሳቸውም አግጠው የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እየተዋጓት ነው:: ይህንን   ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ዓለም ድረስ በስውር በዘረጉት መዋቅር ዓላማቸውን በማስፈጸም ላይ ናችው::  ቅዱሳንን የመዝለፍ አስተምህሮዋቸው በአደባባይ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ::  [ለመስማት ይህንን ይጫኑ} እግዚአብሔር አትበሉ፤ ሥላሴ አትበሉ፤ የናዝሬቱ ኢየሱስ ብቻ በሉ የሚለው የእነ በጋሻው ደሳለኝ ስብከት ህያው ምስክር ነው:: “ተሐድሶ የለም ወንድሞቻችን በፈጠራ እየከሰሳችሁ ነው፤ እነ በጋሻው እና ጓደኞቹ ተሐድሶ አይደሉም” በማለት የሚናገሩት እነ ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ ለምን ይሆን?

በጣም የሚያሳፍረው በቅዱሳኑ ስም ድህረ ገጽ ከፍተው ቅዱሳንን መሳደባቸው ነው:: ከእነዚህም ውስጥ {ለማንበብ ይህንን ይጫኑ} አባ ሰላማ በማለት የተከፈተው ብሎግ ጻድቁ አባታችን ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፤ ቅዱስ አባታችን አባ ሕርያቆስ ፤ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በይፋ እየሰደቧቸው ነው:: ይህ ብሎግ በአባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የፈጠራ መረጃ አቀባይነት እና ተባባሪነት ይመራል:: 

የሚከተለውን ጽሑፍ ተሐድሶውያን  ቅዱሳንን የዘለፉበት ነው::

Friday, June 3, 2011

“ተሐድሶ የለም” ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ

መቀመጫውን በሰሜን  አሜሪካን ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ በዕለተ ረቡዕ 06/02/2011 በሰርክ ጉባኤ በደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ "ተሐድሶ የሚባል ነገር በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የለም" በማለት አስተማረ:: እንዲሁም ደግሞ ጸረ ተሐድሶ እንቅስቃሴ እያካሄዱ የሚገኙት ማኅበራት እና ግለሰዎች ላይ ተስፋዬ መቆያ የወቀሳ እና የተቃውሞ ድምጹን አሰምቶዋል:: ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ “ተሐድሶ የለም” ብሎ መናገር መብቱ ቢሆንም፤ ነገር ግን የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ የሚታገሉ ወገኖችን መወንጀል አይገባውም ነበር::