Friday, June 3, 2011

“ተሐድሶ የለም” ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ

መቀመጫውን በሰሜን  አሜሪካን ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ በዕለተ ረቡዕ 06/02/2011 በሰርክ ጉባኤ በደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ "ተሐድሶ የሚባል ነገር በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የለም" በማለት አስተማረ:: እንዲሁም ደግሞ ጸረ ተሐድሶ እንቅስቃሴ እያካሄዱ የሚገኙት ማኅበራት እና ግለሰዎች ላይ ተስፋዬ መቆያ የወቀሳ እና የተቃውሞ ድምጹን አሰምቶዋል:: ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ “ተሐድሶ የለም” ብሎ መናገር መብቱ ቢሆንም፤ ነገር ግን የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ የሚታገሉ ወገኖችን መወንጀል አይገባውም ነበር::


ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ መኖሩን ለምን እንደተቃወመው ለጊዜው የሚታወቅ ነገር የለም:: እንዲሁም ደግሞ በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ እውን ‹‹ተሐድሶ›› የለምን? በሚል ርዕስ ተሐድሶን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሑፍ ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ ተቃውሞታል::

የተዋሕዶ ልጆች የቤተ ክርስቲያናችን የውስጥ መናፍቃንን ለማጋለጥ በአንድነት በተረባረቡበት በዚህ ወቅት “ተሐድሶ የለም” ብሎ መቃወም የሰባኪው ማንነት ጥያቄ  ውስጥ ያስገባዋል:: 

ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ እንደዚህ አይነት ተቃውሞ ሲያቀርብ ይህ የመጀመሪያ አይደለም፤ የዛሬ ዓመት አካባቢ ቨርጂኒያ ውድ ብሪጅ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጪ በግለሰዎች ስም እና በቀሳውስቱ ስያሜ ተሰጥቶት ኢየሱስ ወብስራተ ገብሬል በሚል ቤተ ክርስቲያን “ተከፍቶ”  ነበር:: ይህንን ድርጊት ያበሳጫቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ አመሠራረት በተመለከተ ፍትሐ ነገሥትን መሰረት ያደረገ ጽሑፍ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ለምዕመናን አሰራጭተው ነበር:: በዚህም ጊዜ የዛኔው ዲ/ን የአሁኑ ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ “ወንጌል ይሰበክ እንጂ ቤተ ክርስቲያን ያለ ጳጳስ መባረክ ይቻላል” በማለት አስተምሮ ነበረ:: እንዲሁም ደግሞ ቀኖና ይጠበቅ በማለት ጽሑፉን ያሰራጩ ወገኖች ተስፋዬ መቆያ “የወንጌል ጠላቶች” በማለት ተቃውሟቸውም ነበረ:: ለማንበብ ይህንን ይጫኑ ዲ/ን ተስፋዬ መቆያ ለምን ተቆጣ?    

እግዚአብሔር ተዋሕዶ  ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን

18 comments:

Anonymous said...

በእርግጥ ለእናንተ ስጽፍ ይህንን ታወጡታለችሁ ብዪ አይደለም ግን እነደው ህሊና ካላችሁ በጥሞና እንድተከታተሉት ነው። ተሐድሶ አለ ብላችው እንደምታምኑት ሁሉ፡ ይህንን በመቃውም በመዝሙር፡ በስርዓተ ቤተክርስቲያን በሃይማኖት በመጠበቅና በማስጠበቅ የሚታገሉትን ምነው አትረዱ።፡ለምሳሌ በማርያም ያሉ ካህናት ስለ እመቤታችን የመሰከሩትን ምነው ለምዕመናን በመስነበብ ከጎን መሰለፋችሁን አታሳዮ----

Anonymous said...

Look what he shared here:
http://www.kesistesfayemekoya.com/2011/06/normal-0-false-false-false-en-us-x-none.html#more

Anonymous said...

ወያኔው ጠፍተህ ነበር፤ ወያኔ ኢትዮጵያ ወጣቱን ማሰር ሲፈልግ አደገኛ ቦዘኔ ይላል፡፡ አንተ ላባ ጳውሎስ ያልተመቸውን ሰው በተሐድሶ ስም ትመታለህ፡፡ የማያረጅ ነገር አይታደስም የቤተክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና እና ስርአቷ አያረጅም ስለዚ አይታደስም፡፡ የቤተክርስቲያንን አንዱንም ስርአት ይለወጥ ይቅር ይታደስ የሚል ሁሉ መናፍቅ ከሐዲ ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችን የመጀመሪያው መናፍቅ አ...ቡነ ጳውሎስ ሲሆኑ እሳቸውንም ተከትለው ብዙ መናፍቅ ጳጳሳትም ካህናትም ውስጥ ውስጥ አሉ፡፡ እነዚህ አሁን የቤተክርስቲያን ስርአት እንዲህ መሆን አለበት፣ መቀይር አለበት ብለው በግልጽ ካስተማሩ፤ ለምድን ነው እንደ ቀድሞ ስርአት ጉባዩ ተጠርቶ በግልጽ ፍላጎታቸውን አሳውቀው ክርክር ተደርጎ ከተረቱ ንሰሀ ገብተው ወደተዋህዶ እምነታቸው እዲመለሱ እምቢ ካሉ ተወግዘው እዲለዩ ማድረግ የሲኖዶሱ ሀላፊነት ነው፤ ታዲያ አቡነ ጳውሎስም ጨምሮ ነው፡፡ ሲኖዶሱ ይህንን ሳያደርግ አውግዞ ከቤተክርስቲያን ሳይለያቸው ዝም ብለን የተጣላነውን ሰው ሁሉ ተሀድሶ ተሀድሶ ብንል መዘዙ ብዙ ነው፡፡ ከዛ ይልቅ ሲኖዶስ መፍትሔ እስኪሰጥበት ድረስ፤ እነሱ መቀየር አለበት የሚሉትን ስርአት ለህዝቡ ማስተማር ተገቤ ነው፡፡

Anonymous said...

i try to see his website and one of his recommended website is the website which is against orthodox tewahdo and mahbere kidusan ,what the hell is going on in his mind?
actually i believe there is no "tehadoso" they want "change" of orthodox tewahdo to protestantism

Anonymous said...

እዩት ኢሄ ደሞ ከላይ ያለው አንድ ነገር ሲባል አባ ጳውሎስ ......አርፈህ በተነሳው ርእስ ላይ ያለህን አስተያየት አትሰጥም

Anonymous said...

degmo kesis tesfayey min aderege new yemtilut hulun bedelga bilchihu tzelkutalachihu sebakiw -zemariw -kahinu papasu hulu menafik tebale tawaki zemari psebak tesedebe tedebedebe semonun degmo man yiketsil yihon /

Anonymous said...

መምሬ መቆያ ፣ “ክርስቶስ ፍጡር ወይስ ፈጣሪ” በሚል አርስት ርእሰ ደብር ቀሲስ አብርሃም የጻፉትን መጽሐፍ መደምደሚያ ብታነበው እንዲህ አትሳሳትም ነበር። የቤተ ክርስቲያንንም የዓለሙንም ትምሕርት የጠነቀቁ ሊቅ ናቸውና ከሳቸው ተማር። ምስክርነታቸውም እውነት ነው።ርእሰ ደብር በመጽሐፋቸው ካነሱት ቁም ነገር በተጨማሪ መጽሐፋቸው ውስጥ የሚገኝ ታላቅ ነገር አለ። እውነተኛ የቤተክርስቲያን ፍቅር! መምሬ ፣ርእሰ ደብር እንዳንተ ተሐድሶ ወይም መናፍቅ የለም አይሉም። እንዲህ ይላሉ “ሊለውጥ የሚችለው ክፍልም ቢሆን መለወጥ ያለበት በሲኖዶሱ ውሳኔ መሆን ይገባዋል። ሁሉም በየፊናው እየተነሳ ለዘመናት የቆየን ይትበሃል ያለጥናትና ያለምክክር ለመለወጥ መሞከር ሕገ-ውጥና ኢትውፊታዊ ነው።...................ለሃይማኖት የመቆሙና መናፍቃንን የመዋጋቱ ኃላፊነት በጥቂት አስተዋዮች ካሕናትና ምእመናን ላይ የሚወድቅ ይሆናል።”
መምሬ መቆያ - አየህ ያንተና የርእሰ ደብር ልዩነት ምን እንደሆነ።እሳቸው ስለሚወድዋት ቤ|ክ እውነት ተናገሩ-ጻፉ። አንተ ግን ስለ $ ብለህ ተናገርክ-ጥቅምህ እንዳይቀርብህ-ትዝ ይልሃል ውድብርጅ አለቃህ ቤ|ክ ሲከፍቱ የተናገርከው፤ አሁን ደግሞ የምትጠላቸውን ሰዎች ለመስበር ተናገርክ።ወንጌልን ሸቀጥከው። አየህ ፓትርያሪኩ ቢያመሳቅልዋትም ቤ|ክ ቤታችን ናት።ወንጌል በማስፋፋት ስም አትዋሹ! አትነግዱ! ወይ መድረኩን ቤ|ክን ለሚያውቁዋት ለነ ርእሰ ደብር ልቀቁ።

Aklilu

Anonymous said...

ferste of fore thank you asteyayeten alaskerachihum ahun alun keminlachew tawaki sebakiyan andu kesis tesfaye mekoya new sew yemwedachewin memihiran hulu tehadiso -menafik malet ayigebam bizu memihiran -zemaryan- kesawsit menafik yemil sim tesetsachew yekere yelem sewn mawgez- meleyet-masaded -medebdeb beza yetenagere hulu menafik kehone min malet yichalal ene tehadiso yelem alalkum menorun amnalehu neger gin kesis tesfaye mekoya yebet kirisitiyan lij new menkebakeb yigebalk hod masbas yelebnim Begashaw -Dagim - Zerfe -Mirtnesh - Ashenafi -Estifanos-Tewodros ezira - Habtamu -Yetmwork-Tadewos wezete ... tehadiso ketebalu manew yekerew ? wedefit Azinew wede lela neger kegebu yasazinal sewn memeles yikedmal santsara mewenjel ayigebam yesewin sim matsifatim hatsiat new asbubet Kidane mihiret tihunen

Anonymous said...

Selam ezih bet,
I was reading most of the comments after the article. Most of us made the same mistake again and again, I don't know why Tesfaye Mekoya is an issue, remember he is a human bing, leave alone him those who reach to the highes of church hirarchy made misake about our church patriarch plus bishops. We don't bother by his comment, one thing he reviel himself that he is standing with those who are trying to distroy our canon of our church. We all know him that he is fall for "$" if he get paid, he will say anything. Cheep and dirty like him. He would have stand with the people instead of those dogs who try to polish the best our church with their dirty wrong teaching.
Tesfaye Mekoya already told us he stand with Aba Sereke, Begashaw and Yared Ademe. We already saw his picture on the video
http://www.youtube.com/watch?v=ThSJdTpH9V4&feature=related

Anonymous said...

When i read this article i wanted to make sure he really said that. Unfortunately, he did really say it...just in case you don't want to hear the whole sibket listen to where is said "There NO Tehadeso" starting from 36min and 10 sec (36.10)
Here is the link http://www.ustream.tv/recorded/15104332

Anonymous said...

Here is the link http://www.ustream.tv/recorded/15104332
He deleted the video and his writing from the site. Though he edited and re post it on his video site. Do you have the video or audio? i hope you do.
Ben

Anonymous said...

ውድ ወንድሞች "ቀሲስ" ተስፋዬ መቆያ ክብረ መንግስት እያለ መናፍቅ ተብሎ መባረሩን ታወቃላችሁ? ማንም ሰው ይህንን ሊያረጋግጥ ይችላል::ይህንንም እንዲያብራራ ብሎጉ ላይ ጥያቄ ልኬያለሁ

Anonymous said...

ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ ክብረ መንግስት መናፍቅ ተብሎ ከሰንበት ትምህርት ቤት መባረሩን ታውቃላች ከ 10 አሰከ 15 አመት በፊት የሆነ ነው:: ይህንኑ እንዲመልስ በብሎጉ ላያ ጥያቄ ልኬያለሁ

Anonymous said...

ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ ከብረ መንግስት ገና ወጣት እያለ (ከ 10 እሰከ 15 አመት በፈት) ከሰንበት ትምህርት ቤት መናፍቅ ተብሎ ተባሮ አዲ አበባ አንደመጣ ታውቃላችሁ?ይህንንም እንዲመልስ ብሎጉ ላይ ልኬለታለሁ::

Anonymous said...

ተሃድሶ የሚባለው ህቡዕ ድርጅት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተመሳስሎ እንደሚሰራ መሪጌታ ሙሴ የተባለው ዘርዝሮ አስረድቷል ፡፡ አሠራራቸውን ሁሉ አጋልጧል ፡፡ ያጋለጠው ለተዋህዶ እምነት ወግኖ ሳይሆን በማውገዝ ነው ፡፡ ይህን የማያምን ካለ በአባ ሰላማ ድረ ገጽ ላይ ማዳመጥ ይችላል ፡፡ የለም ማለት ክህደት ነው ፡፡ የተሃድሶ አባላት ግዕዝ ተናጋሪ ሊቃውንትና እስከ ዛሬ ድረስ ሁሉንም ለመሰብሰብ የሚታገሉት ወንጌላውያን ነን የሚሉት በሙሉ ተደራጅተው ነው ፡፡

Anonymous said...

why this tehadso people not go to pente chuerch . long live tewhdo

alex said...

who is he? wedajoche bete kiristiyan yemanim lehacham lehch metregiya honech eiko pleas say somthing? abatochchin eiko tekebrew askebrewat neber.

Anonymous said...

ተሀድሶ ማስፈራሪያ ሆነ እኮ አኛ በዬት በኩል እማር መድረኩን ከማስተማር አባእከሌ የህን አሉ እሱን አንብቡ ምንየሚሉት ነው ማስተማር ነው እውቀትን መስተላለፍ ነው ላሉባልታ ፍጆታ ዜናውን ማውጣት ምን ይጠቅማል ማን ምንፍቅና እንዳለብት የታወቃል መሰሪ ሁሉ፡፡