Monday, June 13, 2011

እውን ተሐድሶ የለምን?

በቀደሙት ዘመናት የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ በድብቅ ነበረ::  በዚህ ወቅት ግን አይናቸው አፍጥጠው ጥርሳቸውም አግጠው የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እየተዋጓት ነው:: ይህንን   ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ዓለም ድረስ በስውር በዘረጉት መዋቅር ዓላማቸውን በማስፈጸም ላይ ናችው::  ቅዱሳንን የመዝለፍ አስተምህሮዋቸው በአደባባይ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ::  [ለመስማት ይህንን ይጫኑ} እግዚአብሔር አትበሉ፤ ሥላሴ አትበሉ፤ የናዝሬቱ ኢየሱስ ብቻ በሉ የሚለው የእነ በጋሻው ደሳለኝ ስብከት ህያው ምስክር ነው:: “ተሐድሶ የለም ወንድሞቻችን በፈጠራ እየከሰሳችሁ ነው፤ እነ በጋሻው እና ጓደኞቹ ተሐድሶ አይደሉም” በማለት የሚናገሩት እነ ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ ለምን ይሆን?

በጣም የሚያሳፍረው በቅዱሳኑ ስም ድህረ ገጽ ከፍተው ቅዱሳንን መሳደባቸው ነው:: ከእነዚህም ውስጥ {ለማንበብ ይህንን ይጫኑ} አባ ሰላማ በማለት የተከፈተው ብሎግ ጻድቁ አባታችን ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፤ ቅዱስ አባታችን አባ ሕርያቆስ ፤ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በይፋ እየሰደቧቸው ነው:: ይህ ብሎግ በአባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የፈጠራ መረጃ አቀባይነት እና ተባባሪነት ይመራል:: 

የሚከተለውን ጽሑፍ ተሐድሶውያን  ቅዱሳንን የዘለፉበት ነው::

+++
 ባለፈው ጽሑፋችን ሰይጣን የኢትዮጵያውያንን ደም ለማፍሰስ ገና እያሰበ መሆኑን እና ባማህበረ ቅዱሳን አማካኝነት ቅሥቀሳ እያደረገ እንደሚገኝ፣  አስታውቀን ነበር። ይኸው ከተናገርን ገና ሁለት ሳምንት ሳይሞላን በተክለ ሃይማኖት ምክንያት በተክለ ሃይማኖት ደጀ ስላም [መርካቶ] ድብደባ ተጀምሯል። 

ዲያቆን ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል "ማህበረ ቅዱሳን ወይስ ማህበረ ሰይጣን‚ በሚል እርስ ያሳተመው መጽሐፍ በጣም ተጋነነ ተብሎ ሲተች ሰምቼ ነበር መጽሐፉ ግን ዛሬ በተግባር የተረጋገጠ እውነተኛ ምስክርነት መሆኑን ከማህበረ ቅዱሳን ተግባር መረዳት እንችላለን። በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ ያለው መንፈስ ደም የማፍሰስ ጥማት ያለው መሆኑን በማጋለጥ ደጋግመን ብንጮህም የተገነዘበን ግን እጅግ ጥቂት ሰው ነው የሚል ስጋት አለን። እኛ ስም ለማጥፋት የተንሳን ሰዎች አይደለንም፣ በማህበረ ቅዱሳን ምክንያት የሚመጣው የርስ በርስ ጦርነትና የቤተ ክርስቲያን ለሁለት መከፈል ከወዲሁ የታየን አገር ወዳድና የቤተ ክርስቲያናችን ቅናት የሚበላን ኢትዮጵያውያን ነን እንጂ።

ማህበረ ቅዱሳን መንፈሳዊ ድርጅት ቢሆን አብረነው ለመስራት ዝግጁ ነበርን መንፈሳዊ አይደለም የምትሉበት ምክንያት ምንድን ነው? ለሚል ጠያቂ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ያለውን ጥላቻ በማየት የማህበሩን መንፈስ መገምገም ይቻላል እንላለን። ኢየሱስን ለድርጅታቸው ክርስቲያናዊ ሽፋን ለመስጠት ይጠሩታል እንጂ እጅግ የሚደነግጡበት ስም ነው።"ጌታ ኢየሱስ‚ ብለው ለመጥራት እጅግ ይከብዳቸዋል አንዳዴ ለመስበክ ስሙን ይጠራሉ ግን የርሱን ሐሳብ ሳይሆን ራሳቸው የተቋቋሙበትን አላማ በመስበክ ያጭበረብራሉ። ሰው ምን ይለናል በሚልም ይሉኝታ ስሙን የሚጠሩትም አሉ።

ይህን ጽሑፍ የምታነቡ ሁሉ እኛንም ለመታዘብ ከፈለጋችሁ በአካባቢያችሁ የሚገኝን የማህበረ ቅዱሳን አባል "ጌታ ኢየሱስ‚ "የናዝሬቱ ኢየሱስ‚ "ኢየሱስ አዳኝ ነው‚ የሚሉትን የከበረና ምሥጢራዊ ስም በማንሳት መንፈሱ ምን ያህል እንደሚረበሽና እንደሚቆጣ መመልከት ትችላላችሁ የማህበረ ቅዱሳን አባል መሆኑንና አለመሆኑን እንኳ በዚህ ስም አጠራር ለይቶ ማወቅ ይችላል። ሆኖም ግን መንፈሱ ጌታችን መድኃኒታችን የሚለውን አጠራር በመዘርዘር ለማጭበርበር ይሞክራል። መንፈሱ ጋታችን መድሃኒታችን ማለት ከቻለ የናዝሬቱ ኢየሱስ ሲባል ለምን ይደነግጣል? ይህ ነው እንቆቅልሹ!

ታዲያ ማህብረ ቅዱሳን የናዝሬቱ ኢየሱስ ሲባል የሚደነግጥ ከሆነ የተቋቋመበት ዋና አላማ ምንድን ነው?
የመጀመሪያው የማህብረ ቅዱሳን አላማ የሥጋ ዘመዶቹ የሆኑትን የተክለሃይማኖት ተከታዮችና የዘራ ያዕቆብን የተበላሸ ታሪክ ለመሸፋፈን ነው። ወንጌል እንዲሰበክና እውነቱ እንዲወጣ አይፈልጉም፤ ተክለሃይማኖት ተከታዮችና ዘራያዕቆብ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እና ሕዝብ ላይ የፈጸሙት ተንኮል እንዲገለጥባቸው አይፈልጉም። ለዚህም አላማቸው ወንጌል እንሰብካለን እያሉ በወንጌል ስም የተክለሃይማኖትን ገድልና ተረት በመስበክ ሕዝቡ የተሳሳተ ወንጌል እየሰማ እንዲደነዝዝ ያደርጋሉ።

ሁለተኛው ደግሞ በተክለ ሃይማኖት ስም የተሰወረውን አላማቸውን ማሥፈጸምና መንበሩን መውረስ ነው። ለዚህም የተለያዩ መነኮሳትን በመመልመል ለጵጵስና እያቀረቡ የሲኖዶሱን አባላት በማብዛት መንበረ ፓትርያርኩን መቆጣጠር ነው። ይህን የማህበረ ቅዱሳን ፍላጎት ያወቁ መነኮሳትም የተክለ ሃይማኖትን ሥእል ከትራሳቸው በማድረግ፣ ደብረ ሊባኖስ ሄዶ በመመንኮስ፣ ስለ ተክለ ሃይማኖት በማስተማር፣ የተክለዬ ታማኝ ወዳጅ መሆናቸውን በማሳየት ጵጵስናን ለመሾም ደጅ እየጠኑ ነው።
ለምሳሌ፦ በተክለ ሃይማኖት ስም የሥጋ ሥራ እየሠሩ ያሉትን ወገኖች ለማስደስትና የማህበረ ቅዱሳን ታማኝ ወዳጅ ለመሆን ጥረት ከሚያደርጉት አባት መካከል አንዱ ተክለ ሃይማኖትን እና ገብረ መንፈስ ቅዱስን ወደ አሜሬካ በመውሰድ የዲሲ እና የአትላንታ ታቦቶች አድርገው ወዳጅነትን አትርፈዋል።

የትግሬዎችንና የቡልጋዎችን ወዳጅነት ለማትረፍ ያሰቡት የዳላሱ ቄስ---- ደግሞ አቡነ አረጋዊንና ተክለ ሃይማኖትን ደራርበው ታቦት አድርገዋል። ሁሉም የሰውን ወዳጅ ለማብዛት እንጂ የሃይማኖት ሥራ ለመሥራት የሚፈልግ የለም። በአዲስ አበባ ከተመሠረቱት ወደ መቶ ሃምሳ ከሚጠጉት አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በኢየሱስ ስም የተሰሩት ሁለት ብቻ ሲሆኑ በአሜሪካ ግን አንድ ብቻ የኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን አለ [በውጩ ሲኖዶስ ሥር]። ኢየሱስ የሚለውን የተጸውዖ [ዋና መጠሪያ] ስም የፈሩ አንዳድ ምእመናን ግን መድኃኔ ዓለም የሚለውን የግብር ስም [የሥራ ስም] በማንሳት ቤተ ክርስቲያን መሥርተዋል። ይህም ተመስገን ነው።

የማህበረ ቅዱሳን መንፈስ ያለባቸው አቡነ ... ወደ አሜሪካ ከሄዱ ጀምሮ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን የከፈቱ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ ተክለ ሃይማኖት [ዲሲ]፣ ገ/መንፈስ ቅዱስ [አትላንታ]፣ ራጉኤል [ዲሲ]፣ ገብርኤል [ኬንታኪ] ወዘተ ናቸው። ኢየሱስን ግን ረስተውታል ከዘላለሙ ፍርድ በመስቀል ሞቶ ያዳናቸው እውነተኛ ወዳጅ ግን እርሱ ነበር። እነሱ ግን አንድ ቤተ ክርስቲያን እንኳ በስሙ ለመትከል ፈቃደኛ አይደሉም "ለወፎች መጠለያ ለቀበሮዎች ጉድጓድ አላቸው የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት እንኳ የለውም‚ በማለት ጌታ አስቀድሞ ባይናገር እጅግ ይገርመን ነበር።  ዛሬ ኢየሱስ የሚለውን ስም ደፍሮ ለማንሳት ትልቅ እምነትን ይጠይቃል፤ ኢየሱስ የሚለውን ስም ከቤተ ክርስቲያን እያስወጡ ወደ አሜሪካ እንኳ የዘው የሚሮጡት አቡዬን እና ተክልዬን ነው ድሮስ ወደ አሜሪካ እየተሄደ ያለው በዘመድ አይደል! ኢየሱስማ ምን ዘመድ አለው? እንኳንስ ወደ አሜሪካ የሚወስደው በኢትዮጵያም እነ ዳንኤል ክብረትና ዘመድኩን እያሳደዱት ነው።

ወደ ተነሳንበት ርእስ እንመለስና የተክለ ሃይማኖት ጠበቃ ነን ያሉ በማህበረ ቅዱሳን አሰልጣኝነት በሥውር የተደራጁ ወንበዴዎች አገልጋዮችን መደብደብ ጀምረዋል። ቀሲስ አሸናፊ ገብረ ማርያምን፣ ዘማሪ ዳግማዊን፣ ዘማሪ ምርትነሽን የድንጋይ ናዳ በማውረድ በመርካቶ ተክለ ሃይማኖት ደብድበዋቸዋል። ይህ ቡድን የማህበረ ቅዱሳን "አማራጭ ኃይል ተብሎ በሥውር የተደራጀው ጉዳት ለማድረስ የተዘጋጀው ቡድን አካል ነው።

ባሁኑ የኢትዮጵያ ትውልድ ከሃያ አምስተኛ ኪሩብነት እየወረዱ የመጡትን አባት ተክለሃይማኖትን በዚያው በኪሩብነታቸው ለማቆየት ሲባል በቡድን ተደራጅቶ መደባደብ ዋና የማህበረ ቅዱሳን አማራጭ ሆኗል። ታዋቂው ደራሲ በውቀቱ ስዩም "እግር የሌለው ባለ ክንፍ  በሚል ያቀረበው ጽሑፍ ተክለ ሃይማኖትን ጥያቄ ላይ የጣላቸው ሲሆን ትንሽ ዱላ መቅመሱ ተሰምቷል። "አለባብሰው ቢያርሱ በአረም ይመለሱ‚ እንደተባለው ሃያ አምስተኛ ኪሩብ ብናደርጋችውም፤ ስድስት ክንፍ ብናወጣላቸውም፣ ቃል ኪዳናቸውን ብናበዛውም፣ ቤተ ክርስቲያን እየሰራን ብንሰብክላቸውም፣ ብንዘምርላቸውም፣ ከትውልዱ እንደማዕበል እየፈሰሱ ያሉ ጥያቄዎችን ማቆም ግን አልተቻለም። ምክንያቱም ጻድቁን "ሰይጣንን ገርዘው የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ አድርገውታል‚ የሚለው ትምህርት ጥያቄ ላይ ጥሏቸዋል። ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ 5፥ 6 ላይ "መገረዝም ሆነ አለመገረዝ አይጠቅምም‚ ብሎ አስተምሮ እያለ ሰይጣንን መግረዝ ለምን አስፈለገ? በውነቱ ይህ የሐዋርያትን እምነት ከሚከተል ሰው ይጠበቃልን? እንዲህ ዓይነቱን ማፈሪያ ታሪክ በማረም ፈንታ በርሳቸው ምክንያት ባልተገረዙ የቤተ ክርስቲያን ወንበዴዎች ተጠግቶ፣ ደም ለማፍሰስ መጣደፉ ግን አግባብ አይደለም።

እኛን የሚያስፈራን ግን ማህበረ ቅዱሳን እነምርትነሽን መደብደብ እንዳማራጭ የሚወስደው ከሆነ ዱላው ነገ ወደ ማህበረ ቅዱሳን አባላት ፊቱን ማዞሩ የማይቀር መሆኑ ነው። እናም የቤተ ክርስቲያን የርስ በርስ ጦርነት ከመነሳቱ በፊት የመጨረሻ እልባት ይደረግለት ስንል እንማጸናለን። መንግሥትም ቢሆን እንዲህ ዓይነቱ መከፋፈል ለፖለቲካ ይጥቅመኛል ብሎ እንዳያስብ፤ ይህ ከሁሉም የከፋ ኋላ ቀርነት ነው ድህነትን እየተዋጋን እንዳለን ሁሉ ኋላ ቀርነትንም መዋጋት አለብን እምነት በሕሊና እንጂ በጉልበት አይሆንም፤ በጉልበት እንዲያምን የተደረገ ሰው እስላም እንጂ ክርስቲያን ሊሆን አይችልምና ማህበረ ቅዱሳን ወንበዴዎችን በማደራጀት የከፈተውን ጦርነት እንደገና ቁጭ ብሎ ያስብበት።

ዘማርያኑም ማስተዋልና ትግሥት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል በደም ፍላት መንፈሳዊ ሥራ አይሰራም በእግዚአብሔር ፊት በጾምና በጸሎት በመውደቅ እንጂ።አንዳዶቻችሁ ግን ወዘሮ እጅጋየሁን መጠጋታችሁን አልወደድነውም። እርሷን ተዋትና እግአዚአብሔርን ተጠጉ፤ በፖሊስና በዘመድ ኃይል ፍርድን ለማግኘት አትሞክሩ። ይህ የወንጌል ሕይወት ነው ብለን አናምንም። በናንተ ላይም ጥያቄ አለን ወንጌል ሰላማዊ ስለሆነ እየወደቅን ብዙዎችን ከወደቁበት እናነሳለን እንጂ ደካማዎችን በጉልበት እየጣልን ለመቆም አንሞክር። ይህን ከናንተ ያርቀው አሜን!  
ይቆየን ተስፋ ነኝ

5 comments:

Anonymous said...

What in the world is this??? do they really think that any body who reads their article will believe they are true Orthodox christians? No way!!!

Anonymous said...

አሐቲ ተዋሕዶ ጸሐፊዎች በጣም የምትገርሙ ናችሁ። ብቻ ሁሌ እጸልይላችኃለው። ክርስቲያን ከሆናችሁ ምናለበት ዲያቆን በጋሻው ወይም ቀሲስ ተስፋዬ ብትሉ? አርዮስን የለየ መንፈስ ሳይለይ እናንተ የምትሽቀዳደሙት። ወየውላችሁ አረ እናንተ እየጠቀማችሁ መስሏችሁ እንዳትጠፉ። ይህች በሎግ ወይም ሌሎቻችሁ ቤተክርስቲያንን ወይንም ሰውን አያስታርቅም ታርቃለችሁ እንጂ። አረ ጸሎት የታለ ምናለ ድረ ገጻችሁ የምታስተምሩበት ቢሆን? በናንተ ወሬ ሀይማኖታችን አትድንም። ጠብቁ ግን ዝም ያለው አምላክ ይመጣል እናም ሁሉን እናያለን። በመጣ ጊዜ ግን ምህረቱን ያውርድላችሁ።

Anonymous said...

በተስፋ መቆያ እንኮን አትፍረዱ ምክንያቱም ምንም የሚያውቀው የለም ከቤተክህነት ወይም ከቤተመንግስት ወይም እንደ ቢጠዋቹ ጥሩ ጀሮ ጠቢም አይደለ መቃብር ቤት እመቤታችን ተገለጠችልኝ ብሎ አገልጋይ ካህናቱን ከሕዝብ ጋር ሲያበጣብጥ ወንድሙ አዲስ አ በባ አመጣው ከዛም በመምህር ዘላለም ወደ አሜሪካ እዛ ማንም በሌለበት ተሐድሶ የለም ቢል የሚስገርም አይደለም

Anonymous said...

Abetu Egziabher amelachachin kekehadian na menafikan betecheristianachinen tebklen

Ke Adola mariam said...

In fact Tesfaye was not ousted from the Sunday school some 15 years ago. During that time he has no record of following the teaching of "Tehadiso". At that time he proceeded to Addis to pursue his theology education at St. Ba'ata Le Mariam church at 4 kilo. As far as my knowledge he dropped the study and engaged in preaching service in Addis Ababa and outside Addis. It is during this time that convinced himself such preaching is a good business of living and joined the group of preachers for business such as Diakon Begashaw and the like.