Tuesday, June 14, 2011

አልአዛርን ከሞት ያስነሳው ማን ነው? ለበጋሻው ደሳለኝ እና ለደጋፊዎቹ ለእነ ለተስፋዬ መቆያ የተሰጠ መልስ

(ታምራት ፍስሃ)፦  የዓለም መምህር የተዋሕዶ ምስክር የተወደደ ቅዱስ ቄርሎስ የሃይማኖትን ነገር እንዳስተማረን እንናገራለን:: ሃይማኖት አበው ዘቄርሎስ ምዕራፍ (70 -72) 
“ሥላሴ አትበሉ፣ እግዚአብሔር አትበሉ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሉ” (በጋሻው) ለማድመጥ ይህንን ይጫኑ
ምስጢረ ሥላሴ በከፊል ፦
እግዚአብሔር በአካል ሦስት በባህርይ አንድ ብለን እናምናለን፡፡ይኸውም  አንድ መለኮት ፣ አንድ ባሕርይ ፣ አንድ ልዕልና ፣ አንድ ጌትነት ፣ አንድ ክብር ፣ ከጥንት አስቀድሞ  የነበረ አንድ ቀዳማዊነት ነው:: ደግሞም በሦስት አካላት ፣ በሦስት ገፅት ፍፁማን ናቸው ፤ ግዙፋን አይደሉም ፣ ያልተፈጠሩ ናቸው ፣ ድካም የማይስማማቸው  የማይለወጡ ናቸው ፣ ለመገኘት ጥንት ለዘመን ፍፃሜ የላቸውም፡፡
 
ስለ ወልደ እግዚአብሔር በከፊል፦
ዳግመኛም ከአብ ባሕርይ የተገኘ አምላክ ፣ ቃል ፣ ወልድ ፣ ያልተፈጠረ ፣በመለኮት አንድ ከሚሆኑ ከሦስቱ አካላት አንድ አካል ፣ ከአብ ጋር ትክክል የሚሆን ፣ ዓለም ሳይፈጠር በመለኮታዊ  ልደቱ ከአብ የተወለደ ፣ ፍፁም  እግዚአብሔር አብን በመልክ የሚመስለው ፣ በባሕርይ የሚተካከለው የማይመረመረ የጌትነቱ መታወቂያ እንደሆነ እናምናለን፡፡ በገፁ በአካሉ ልዩ የሚሆን የአብ ልጅ ፣  አምላክ ፣ ቃል በአባቱ ፈቃድ ፣  በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ለእኛ ቤዛ ሆኖ ተሰጠ፡፡ ያልተፈጠረ ፣ ሥጋ ያልነበረው ፣ የማይለወጥ እርሱ እግዚአብሔር ቃል በማይመረመር ግብር በመልኩ ፣ በአምሳሉ  የፈጠረንን እኛን ሰዎችን ለማዳን ከአብ አንድነት ሳይለይ ከሰማይ ወረደ፡፡

 
ስለ ቃል ሥጋ መሆን በከፊል፦
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ሲሆን ሰው ሆነ ፤ ከጌትነቱ ክብር ፈፅሞ አልተለየም ፤ ምንም ሰው ቢሆን እርሱ ከፍጡራን ሁሉ በላይ ነው ፤ በመለኮቱ  ህግን የሰራ ሲሆን እነሆ ህግን በመፈፅም ተገኘ:: ህግን ሲሰጥ በነበረበት ባሕርይውም ፀንቶ ኖረ፡፡ በመለኮቱ ገዢ ሲሆን የተገዢ ባሕርይን ገንዘብ አደረገ ፣ ግን የጌትነት ክብር ከእርሱ አልተለየም :: አንድ ሲሆን ለብዙወቹ  ምእመናን በኩር ሆነ ፤ በአንድነቱም  ፀንቶ ኖረ፤ በማይመረመር ምስጢር እንደ እኛ በመሃፀን መፀነስን ወደደ ፤ እርሱ ሰው እንደመሆኑ በመሃፀን ሳለ በባሕርይ መለኮቱ በሰማይ በምድር ፣ ከምድርም በታች ምልኡ ነው:: በማይመረመር በማይነገር ጌትነቱም በአብ እሪና ይኖር ነበረ ፤ የሕይወት እስትንፋስ ያላቸው ሁሉ በላይ በታች ያሉ ፍጡራንም ሁሉ በመሃል እጁ ናቸው ፤ አሽናፊ ፈጣሪ እርሱ እንደ ከሃሊነቱ ሁሉን ያዝዛቸዋል፡፡
 
ስለ መለኮትና ትስብእት በከፊል ፦
እግዚአብሔር ወልድ በድንግል መሃፀን ሳለ በሰማይም በምድርም ከአባቱ ጋር አንድ ባሕርይ መለኮት ህልው ነውና ከሃጢአት በቀር በመሃፀን ሆኖ ከተፈጠረ ከፍፁም ትስብእት ጋርም በማይመረመር ባንድ ባሕርይ መለኮት መቸም መች አንድ ነውና፡፡ እግዚአብሔር አብን በመልክ የሚመስለው ፣ በባሕርይ የሚስተካከለው እርሱ ቀምቶ እግዚአብሔር የሆነ አይደለም፤ ራሱን አዋርዶ የተገዥን ባሕርይን ገንዘብ አደረገ እንጂ ፤ መለኮትስ እንደሰው  በድንግል መሃፀን ያለ የእለት ፅንስ በመሆን በድንግል ማህፀን ሳለ በሰማይ በምድር ምልኡ ነው፡፡ ደግሞ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በጥቂት በጥቂት ማደጉን ወንጌላውያን ፃፉልን :: በየጥቂቱ ያደገ ግን መለኮት አይደለም ፡:  በሰማይም በምድርም የመላ ነውና ፤ በሁሉ በሰማይ በምድር የመላው እንዴት ያድጋል? ከተዋሐደው ሥጋ ጋር አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነውና በየጥቂቱ ማደግን ገንዘብ አደረገ፡፡ ከኃጥት ብቻ በቀር እንደ እኛ በስራው ሁሉ ተፈተነ ፣ ተራበ ፣ ተጠማ ፣ ደከመ ፣ አንቀላፋ ፣ በላ ፣ ጠጣ ፣ አለቀሰ ፣ ተከዘ ፣ አዘነ ፣ ታመመ ፣ ሞተ ፣ ተገነዘ ፣ በመቃብርም ተቀበረ ፤ ይህስ እንዴት ለመለኮት ይነገራል? ነገር ግን እግዚአብሔር ቃል በተዋሐደው ሥጋ ስለእኛ ይህን ሁሉ ገንዘብ አደረገ፡፡ መለኮት ግን ከመከራ ሁሉ የራቀ ነው፡፡ (ወይንስ) በባህር ላይ ተራመደ ፣ ሙታንን አስነሳ ፣ ድውያንን ፈወሰ ፣ ከሞት ተነሳ ፣ በዝግ ቤት ገባ ፣ ወደ ሰማይ አረገ እንደምን ይባላል? ይህ የትስብእት ገንዘቧ አይደለምና ፣ ነገር ግን ሰውን ሰለመውደዱ የቃል ገንዘብ ለትስብእት ሆነ እንጂ ፤ እኛም ሰው አምላክ ሆነ ስለዚህ እንላለን፡፡ እንግዲህስ እግዚአብሔር ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋው ሞተ እንላለን እንጂ በባሕርይው (በመለኮቱ) ከሞተስ እነሆ አብም ሞተ ደግሞ እንላለን ፣ እነሆ መንፈስ ቅዱስ ሞተ ደግሞ እንላለን ፤ ነገር ግን መለኮት ህማም ሞት ስለሌለበት እግዚአብሔር ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋው ሞተ እንላለን፡፡
 
እንግዲህ የቅዱስ ቄርሎስን ትምህርት እንደተማርን እንዲህ እንላለ:-

ታዲያ አልዛርን ከሞት ያስነሳው ማን ነው? ወይንስ እግዚአብሔር የሚለው ስም ከሦስቱ አካላት የማን ነው? እናንተ አልዛርን ከሞት ያስነሳው ኢየሱስ ነው፤ እግዚአብሔር አይደለም የምትሉ እስኪ መልሱልኝ::  ይህ ስም የአብ ብቻ ነውን? አባቶች እንዳስተማሩን ይህስ የሦስቱም የአንድነት ስማቸው ነው፡፡ እኛም እግዚአብሔር ስንል ፤ እግዚአብሔር አብ ፣ እግዚአብሔር ወልድ ፣እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ማለታችን እንደሆነ እናውቃለን፡፡ እስኪ መልሱልኝ ? አልአዛርን ከሞት ያስነሳው ኢየሱስ ብቻ ነው የምትሉ መለኮትን ትከፍሉት ዘንድስ ማን አስተማራችሁ? ወይንስ ለሥላሴ ስንት መለኮት አለው? ሥላሴ ግን በባሕርይው አንድ መለኮት እንደሆነ  እናውቃለን፡፡ ወይንስ ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት ያስነሳው በቃል ገንዘብ ነውን? ወይንስ በትስብእት ገንዘብ? ይህንስ የኢየሱስ ክርስቶስን ባሕርይ ትከፍሉ እንደሆነ ጠየቅኳችሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ በተዋሕዶ አንድ እንደሆነ እኛ የኦርቶዶክስ  ክርስቲያኖች እናምናለን፡፡ እንግዲህ የቃል ገንዘብ ለትስብእት እንደሆነ በመለኮቱ ሰማይና ምድርን የመላ ፣ በስልጣኑ ሁሉን የፈጠረ እርሱ በመለኮቱ  ስልጣን አልአዛርን ከሞት አስነሳው እንላለን :: የሥላሴ መለኮትም አንድ ነውና ሥላሴ ደግሞ አልአዛርን ከሞት አስነሳው እንላለን ፣ ይህም መለኮት የእግዚአብሔር አብ ነውና  እግዚአብሔር አብ አልአዛርን ከሞት አስነሳው ደግሞ እንላለን፤ ለመንፈስ ቅዱስም ይህ ይነገር ዘንድ ይሆናል፡፡ መለኮት ከትስብእት ለአይን ጥቅሻ እንኳን እንዳልተለየው  አንድ በሆነው መለኮት አብም መንፈስ ቅዱስም ወልድን በስራው ሁሉ አልተለዩትም ፤ እግዚአብሔር ወልድም ምንም ሥጋን በመልበሱ በምድር ቢሆን በመለኮቱ ግን ከዙፋኑ አልተለየም:፡

እንዲህ ስንል ግን እግዚአብሔር አብ ሞተ እንላለንን? ወይንስ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተሰቀለ እንላለን? እስኪ መልሱልኝ መለኮት ይሞታልን? ይሰቀላልን? አይሞትም አይሰቀልምም::  ስለዚህም እግዚአብሔር አብ ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፣ ወይንም ሥላሴ ሞቱ አንልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ወልድ በተዋሐደው ሥጋ ስለእኛ ይህን ሁሉ ገንዘብ አደረገ ብለን እናምናለን ፡፡ እንግዲህስ ይህን አባቶች አስተማሩን ፤ እናንተ(በጋሻው እና ደጋፊዎቹ) ግን አዲስን ትምህርት ከየት አመጣችሁት?
እኛ ግን አልአዛርን ባስነሳው በእግዚአብሔር እናምናለን፡፡
        ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፣ ወለ ወላዲቱ  ድንግል ፣ ወለ መስቀሉ ክብር፡፡

7 comments:

Berhanu said...

Is this web site created to condemen Kesis Tesfaye and DSK Mariam?

Mahdere said...

well said. Thank you.

Anonymous said...

My question is to the blogger. You really need help. It is clear you have a problem! BIG BIG problem!!
What does kessis Tesfaye Mekoya has to do with this????

You don't know what you are doing at all. By the way what do you do for a living? It looks you have nothing to do except to reflect some kind of jeleousy on our church and preachers.

Just Shut Up!!

Anonymous said...

Its funny my orthodox friends mentioned about how bloggers are the new way of separating the orthodox people. I never knew about all this website and now i know. I work for the Government Office in DC. Its funny how you guys use the system, because i know who you guys are and how you guys run the database. You guys don't know how to use the internet because you do not know how hide yourself. I am looking at your files in front of my screen. anyways i will keep all this info because one day i might reveal it.

Anonymous said...

Ejig girum Betam yetewedede orthodoxiawi leza yetewahido bereket tmihirtnew, Yegetachin Fikiru Ye Dingl Miljawa, Yemelahikt Tibeka ayleyewo, Kale Hiwotin Yasemalin!

Ameha said...

ወይ ጉድ!!! እንደ አገር ቤት "የመንግሥት ሠራተኛ ነኝ፤ አውቄሃለሁ፤ ቆይ ጠብቅ አገኝሃለሁ" እያሉ በኢንተርኔት ማስፈራራት ተጀመረ እንዴ? አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች የምትወረውሯቸውን ቃላት እያስተዋላችሁ አድረጉ! ሃሳብን በነፃ ማንሸራሸር የሚቻልበት አገር ላይ እየኖርን ጭንቅላታችን ግን የሚያስበው እንደ አገር ቤት እየሆነብኝ ነው። እዚህ መጣጥፍ ላይ የተነሳው የቀሲስ ተስፋዬ ስም ብቻ እንጂ የማርያም ቤተ ክርስትያን አይደለም። ስለ ቀሲስ ተስፋዬ የኑፋቄ ትምህርት እንጂ ምዕመናን ለመከፋፈል የተጠቀሰ መልዕክት የለም። ዕውን ቀሲስ ተስፋዬ የተሳሳተ መልዕክት እያስተላለፈ አይደለምን? አንድ በቅርብ የታዘብኩትን ምሣሌ ላቅርብላችሁ፡- በሰንበተ እሑድ ሚያዝያ 30/2003 "ቀኑ መሽቷልና አብረኸን ዕደር" በሚል ርዕስ ስለ ጌታ ከመቃብር መነሳት ሲያስተምር "ክርስቶስ መቃብር ክፈቱልኝ፣ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ከመቃብር በተነሳበት ወቅት ጠባቂዎቹ ወደ ካህናት አለቆች ሄደው የአጋጠመውን ነገር እንዳስረዱና ገንዘብ ተከፍሏቸው ወደ ቦታው ላይ በመሄድ የእርሱ ደቀ መዝሙራት እንደ ሰረቁት አስወሩ ብለው ቢመክሯቸው እነዚያ ጠበቂዎች ግን ሳይናገሩ ቀሩ፤ እግዚአብሔር ልሣናቸውን ዘጋው" በማለት ተናግሯል። ትምህርቱ በፊልም ስለሚቀዳ እንደገና መመልከት ይቻላል። እውነት ግን እንደዚህ ነበር የተፈጸመው? ማቴ. 28፡15 "እነርሱም ገንዘቡን ተቀብለው እንደ አስተማሩአቸው አደረጉ። ይህም ነገር በአይሁድ ዘንድ እስከ ዛሬ ድረስ ሲወራ ይኖራል።" ይላል። ስሕተቱ የተፈጸመው ካለማወቅ ወይስ ሆን ተብሎ ይሆን? እኔ ተቃውሞዬን የምገልጸው የቀሲስ ተስፋዬ አስተምህሮ ላይ ብቻ ነው። አንዳንድ ምዕመናን እሱ የተሳሳተ ነገር በሚያስተምርበት ወቅት ቤተ ክርስትያኗን እየጣሉ እንደሚወጡ ነግረውኛል። ከዚያ በተረፈ ግን ማንም የርዕሰ አድባራት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያንን ቢቃወም በዝምታ አላልፈውም። የቤተ ክርስትያኗ አስተዳደር የሚቀበለው የኢትዮጵያውን ቅዱስ ሲኖዶስ ነው። ምንም እንኳ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን ሥርዓት በቅዳሴ ወቅት የፓትርያርክ ስም የሚጠቀስ ቢሆንም፣ ያለንበት ዘመን ፓትርያርኩ በግብራቸው "የኛ ናቸው" ለማለት የማያስደፍር በመሆኑ ስማቸው አለመጠቀሱን እኔም እደግፈዋለሁ። "የጳጳሳቱ አለቃ" እየተባለ መታለፉ ራሱ በቂ ነው። የዘወትር ጸሎቴ እግዚአብሔር በደላችንን ይቅር ብሎ እሳቸውን ከቤተ ክርስትያናችን እንዲነቅልልን ነው። አንድ ኃይማኖት ኖሮን አባቶች ለግል ጥቅማቸው ሲሉ በከፋፈሏት ቤተ ክርስትያን ምክንያት እኛ ምዕመናን እርስ በርሳችን መነቋቆሩን ትተን እግዚአብሔር አንዲቷን ቤተ ክርስትያን እንዲመልስልን ተግተን መጸለይ፣ መጾም፣ መስገድ፣ ንስሐ መግባት ይጠበቅብናል። በተረፈ ልብን እና ኩላሊትን የሚመረምር እግዚአብሔር ብቻ ስለሆነ "ይኼ ገለልተኛ ነው፤ ይኼ ደጋፊ ነው፤ ይኼ ተቃዋሚ ነው" የሚባለውን ነገር ትተን ሕሊናችን ወደ ፈቀደው ቤተ ክርስትያን እየሄድን ወደ እግዚአብሔር እንጩህ። ቤተ ክርስትያናችንን ለውርደት የዳረጓት አባቶች በእርጅና ምክንያት ወደ ማታልፈው ዓለም ከመጠራታቸው በፊት እርቅ ፈጽመው ወደ አንድነት እንዲመልሱን የምትቀርቧቸው ሰዎች ካላችሁ አሳስቧቸው። የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስትያን ግን መቼም አትሞትም።።።

Anonymous said...

This is a wonderful text. It teaches us one of the deep theological details of our church. Thank you very much. Kalehiwot yasemalin.