Monday, August 15, 2011

"ይቅርታ" ከዲያቆን ዳንኤል ክብረት

በማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በገባው ቃል መሠረት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት “ዕንቁ” ለተሰኘው መጽሔት በጻፈው መልዕክት “እንግዲህ በአብራከ ሕሊናዬ ተንበርክኬ ይቅርታ እጠይቃለሁ” በማለት ይቅርታ ጠይቋዋል:: ዕንቁ መጽሔት ላይ የቀረበው የይቅርታ መልዕክት የሚከተለውን ፒዲፍ በመጫን ያንብቡ:: READ IN PDF

ይኅንን ይቅርታ አስመልክቶ ቀሲስ ወንድምስሻ አየለ በፌስ ቡክ ላይ ያስቀመጡትን የግል አስተያየታቸው እንደሚከተለው ቀርቦዋል::
+++
መንግሥተ ሰማያት ገብቼ ተመለስኩ!
ዕለቱ እሑድ ነሐሴ ፰ ከጠዋቱ ፭ ሰዓት ነው። የቤተክርስቲያን የፍልሰታው የመጨረሻ ሰንበት የአምልኮ ሥርዓት ተፈጽሞ ብዙው ወደ ቤቱ ገብቷል፤ በቤተክርስቲያን ግቢ መዘግየት ደስ የሚላቸው ወዳጆቿ ደግሞ የፍልሰታን በረከት እያጣጣሙ ገና እየተመለሱ ነው፤ ይህ በራሱ ደስ ያሰኛል። ቋንቋው አይገባንም የማይሉት ሰዓታትና በየዓመቱ የሚናፈቀው ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ተደምጦ አይጠገብም፤ ከሥጋ ድካም ጋር እየታገሉ ብቻ ለዘመናት የሚበቃውን ስንቅ ማከማቸት ነው። እኔ ደግሞ ቅዳሜ የታተመችውን ዕንቁ መጽሔት በማየቴ ለመግዛትና ይዘቷን ለማየት ጓግቻለሁ፤ ሰሞኑን የኤሌክትሮኒኩና ፕሪንት ሚዲያውን ሳስስ የቆየሁበትን አጀንዳ ይዛ ተገኝታለችና። ምን ላድርግ የራሷ ሚዲያ የሌላት ግን «ታላቅ» የሚያስብሏት ታሪክ፣ ሕዝብ፣ ሀብት፣ ቅርስ፣ ጥበባት፣ ወዘተ ያላትን የቤታችንን ጉዳይ ለራሳቸው ሴኩላር ዓላማ ከተቋቋሙ ምንጮች ነውና የምናገኘው፤ ቢያምርም፣ ቢመርም ለጊዜው ግድ ነው።

Wednesday, August 10, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን “ሥውር አመራር” እንደሌለው ገለጸ

ዲያቆን ሙሉጌታ ኃይለማርያም ለእንቁ መጽሔት የሰጠውን ቃለ ምልልስ መነሻነት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ባነሳቸው ነጥቦች ላይ የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጉባኤ ውሳኔ ማሳለፉን በደጀ ሰላም ብሎግ ተገልጾ ነበር:: ይህንን የማኅበሩ የሥራ አመራር ጉባኤ ውሳኔ ሙሉ ዘገባ በማኅበረ ቅዱሳን መካነ ድር ላይ ተዘግቦዋል:: መግለጫው እንደሚያመለክ ተው ከሆነ ማኅበሩ ሥውር አማራር እንደሌለው እና አመራሩም ሙሉ ለሙ ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል እንዳልሆኑ አረጋግጦዋል:: ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ማኅበሩን አስመልክቶ ያሰራጨውን ጽሑፍ ሥህተት እንደሆነ ጉባኤው በሙሉ ድምጽ የወሰነ ሲሆን ዲያቆን ዳንኤልም ላሰራጨው ጽሑፍ ማስተባበያ እንዲሰጥበት ተወስኖዋል:: ዋና ጸሐፊው ዲያቆን ሙሉጌታ ኃለማርያም ለእንቁ መጽሔት በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ ስለ አባላት የፖለቲካ ተሳትፎ የተናገሩት የማኅበሩ አቋም አለመሆኑንና እሳቸውም ማስተባበያ እንዲሰጡበት ተወስኖዋል::
ሙሉ መግለጫውን እዚህ በመጫን ያንብቡ:: 

 

+++
የ6 ወር የሥራ አመራር ስብሰባ ውሳኔዎችን አስመልክቶ ከማኅበሩ የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ::

 መግለጫውን ለማንበብ የሚከተለውን ይጫኑ::

በማኅበራችን ማኅበረ ቅዱሳን ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ያደረገው የ6ወሩ የሥራ አመራር ስብሰባ ወሳኔዎችን አስመልቶ ከማኅበሩ ሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ።

Tuesday, August 9, 2011

በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተሰራጨ የሐሰት መረጃ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ድህረ ገጽ ላይ የወጣው የሐሰት መረጃ አስመልክቶ ማኅበረ ቅዱሳን መግለጫ ሰጥቶዋል:: ይህ ድህረ ገጽ በማደራጃ መምርያው ስም በአባ ሠረቀ ብርሃን ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚዘጋጅ ይታወቃል:: ሙሉ መግለጫውን እንደሚከተለው ቀርቦዋል::
+++

በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተሠሩ የሐሰት ሰነዶችን አስመልክቶ ከማኅበሩ ሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

Thursday, August 4, 2011

ማኅበረ ቅዱሳን በአባ ሰረቀ ብርሃን የክስ ሂደት ላይ መግለጫ ሰጠ

ማኅበሩ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል በስም ማጥፋት ወንጀል መክሰሱን ይታወሳል:: የክሱ ሂደት በፍርድ ቤት እየታየ ባለበት ሁኔታ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጻፉት ደብዳቤ መነሻነት የፍትሕህ ሚኒስቴር ክሱ እንዲቋረጥ አድርጓል:: ይህንን አስመልክቶ ከማኅበረ ቅዱሳን የተሰጠ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል::

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

በማኅበረ ቅዱሳን ማመልከቻ አቃቤ ሕግ በአባ ሠረቀ ብርሃን ወልደሳሙኤል ላይ አቅርቦ የነበረው የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ የተቋረጠበት ሂደት አስመልክቶ ከማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ፦

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ባለፉት 19 አመታት በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ተዋቅሮ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። በእነዚህ ዘመናትም ቀላል የማይባሉ መልካም አስተዋጽኦዎችን ለቤተ ክርስቲያን አበርክቷል። አሁንም እያበረከተ ይገኛል። ማኅበሩ በየሁለት ዓመቱ ዕቅዱን ለመምሪያው የሚያቀርብ ሲሆን ሪፖርቶችንም በየስድስት ወሩ ያቀርባል። ከመምሪያው ኃላፊዎች ጋርም በመልካም ስምምነት ሲሠራ ቆይቷል።