Sunday, September 18, 2011

“እውነት እንዴት ትነገር”?????

ደመላሽ ታደሰ የተባሉ ጦማሪ የሚከተለውን ጡመራ እንድንወያይበት አድርሰውናል:: እንወያይበት::

እውነት እንዴት ትነገር? የምናገራቸው እውነቶች ጎዱኝ:: በቤተ ክህነትም በቤተ መንግሥትም እውነት አርነት ታወጣኛለች ብዬ ተስፋ ባደርግም ይብሱኑ ተንገዋልዬ ወደ ጫፍ ወጥቻለሁ ::

በዚህም ምክንያት በቤተ መንግሥትም ለሀገሬና ለራሴ በቤተ ክህነትም ለምዕመኑ በትንሽዋ አቅሜ ልጠቅምና ልጠቀም እንዲሁም ላፍስ የምችለውን ሰማያዊ ፋይዳ አጣሁ::

Sunday, September 11, 2011

አድናቂ እንጂ መካሪ ለሌላቸው የወንጌል መምህራን የተላከ መልዕክት

የሚከተለውን ጽሑፍ የዚህ ጡመራ መድረክ ተከታታይ ከሆኑ ግለሰብ የደረሰን ነው::  መልዕክቱም አድናቂ እንጂ መካሪ ለሌላቸው አንዳድ አስበውበትም ይሁን ሳያስቡበት በፖለቲካው ለተዘፈቁት የወንጌን መምህራንን ይመለከታል:: መልካም ንባብ::
+++
ለእኛ የማናውቀውን ንገሩን ለእናንተም የሚያምርባችሁን ልበሱ!
በላፈው ዓመት ከእናንተ ብዙ ተምረናል። በሃይማኖት እና ማሕበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ብዙ ቁም ነገሮችን ቀስመናል። ቃለ ሕይወት ያሰማልን። ታዲያ ውጤቱን ሁላችንም በሕይወታችን የምናየው ቢሆንም፤ ዓመት መጨረሻ ላይ ስለትምህርት አሰጣጡ ሁኔታ ተማሪዎች በተራቸው አስተማሪዎቻቸውን የሚገመግሙበት አሰራር ደግሞ አለ። ይህ አሰራር ሀገራችን ውስጥ በመጠኑ ቢሰራበትም፤ በሰለጠነው ዓለም ግን በስፋት ይጠቀሙበታል። ዓላማውም ስህተቶችን አርሞ መጪውን የትምህርት ዘመን የተሻለ ውጤታማ ለማድረግ ብቻ ነው። በዚሁ መሠረት እኔም ከተማሪዎቹ አንዱ ስለነበርኩ ፤ ለዚህ ተብሎ የተዘጋጀልኝ ፎርም ባይኖርም ራሴ ባመቸኝ መልኩ መስተካከል አለበት የምለውን  እነሆ!

እናንተ አስተማሪ የምትባሉት ተማሪዎቻችሁ የማያውቁትን ስለምትናገሩ እንጂ የሚያውቁትን ስለምትደጋግሙ አይደለም። አስተማሪነታችሁም በሁሉም ዘርፍ ሳይሆን እኛ በምናውቀው እና አስተማሪዎቻችን አድርገን በተቀበልናችሁ ትምህርተ ሃይማኖትን በተመለከተ ብቻ ነው። ይህ ሲሆን እኛም በተማሪነታችን እናንተም በአስተማሪነታችሁ ቦታ ቦታችንን እንደያዝን የመማር ማስተማሩ ሂደት ይቀጥላል። አስተማሪ ሆናችሁ የምትቀጥሉት እኛ አስተማሪዎች ብለን ስለተቀበልናችሁ ብቻ እንጂ ለአስተማሪነት የሚያበቃ ዲፕሎማ ወይም ዲግሪ ስላላችሁ አለመሆኑን አስተውሉ…..በአዲሱ ዓመት!