Tuesday, November 22, 2011

ቤተ ክርስቲያን መልስ አላት

READ IN PDF
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ በተለያዩ ዘመናት አያሌ መናፍቃን ተነስተው ነበረ:: ከአርዮስ ጀምሮ ብዙ መናፍቃን በክህደታቸው ምክንያት ሊቃውንቱ ከቤተ ክርስቲያን አውግዘው ለይተዋቸዋል:: አውግዞ መለየትም ብቻ ሳይሆን መናፍቃን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎችም መልስ ተሰጥቶባቸዋል:: ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ ለመናፍቃን መልስ የሚሰጡ ሊቃውንትን አፍርታለች:: ቤተ ክርስቲያን ምልዑ ናት የሚባለው ለዚህም ነው:: 

አሁን በእኛ ዘመን ተረፈ አርዮሳውያን የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ሳይረዱ፤ ነገር ግን ግዕዝ ስለተናገሩ ብቻ ሁሉንም ነገር እናውቃለን የሚሉ ሰዎች ተነስተዋል:: ለምሳሌ “አባ ሰላማ” የተባለው ብሎግ ማየት በቂ ምስክር ነው:: ይህ ብሎግ ቤተ ክርስቲያናችን የምታስተምረው ነገረ እግዚአብሔርን ይቃወማል:: የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት አይቀበልም፤ ነገር ግን የተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ እንደሆነ እያስመሰለ ሲያጭበረብር ይታያል:: የቅዱሳን ገድል እና የቅዱሳን መላእክት ድርሳን የሚተቸው የዘመናችን ተረፈ አርዮሳዊው ለ“አባ ሰላማ” ብሎግ መልስ የሚሆን የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ተመርጉዘው መልአከ ሰላም ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው እንደ ሊቃውንቱ አባቶቻቸው ጦምረዋል:: ይህንን በመጫን ያንብቡ CLICK HERE TO READ
መልካም ንባብ::

“ለእኔ የሚናገርልኝ ሰው ከሌለ እኔው ራሴ ስለ ማንነቴ ልንገራችሁ” ( ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል)


አቡነ ፋኑኤልና ካህን መስሎ ከቆመው BODY GUARD ጋር
ፁዕ አቡነ ፋኑኤል ምእመናንን በመናቅ “እቺን ደብረ ምሕረ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሰራኋት እኔ ነኝ፤ ሥለዚህ ንብረቴ  ነው:: ማንም ውጣ ሊለኝ አይችልም” በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል:: ሙሉ ዘገባው ይህንን በመጫን ያንብቡ (PDF);; ዘገባው የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ ከሚል ብሎግ የተወሰደ ነው:: 

Tuesday, November 15, 2011

ማኅበረ ቅዱሳንን ለምን ጠሉት??

 READ IN PDF
አባ ሰላማ በማለት በቅዱሳን ስም እየተጠራ ቅዱሳን መላእክትን፣ እመቤታችንን እና ጻድቃንን  የሚዘልፈው “አባ ሰላማ” የተሰኘው የተሐድሶ መናፍቃን ብሎግ፤ በማያፍር አንደበቱ ማኅበረ ቅዱሳንን በመሳደብ ላይ ይገኛል:: ማኅበረ ቅዱስንም “የቅዱሳኑ የስድብ በረከት ለእኔም ይድረሰኝ” በማለት ይመስለናል ለብሎጉ ምን ዓይነት መልስ ሰጥቶ አያውቅም::

“አባ ሰላማ” ብሎግ በ1992 ዓ/ም ከቤተ ክርስቲያ ተወግዘው የተለዩት የተሐድሶ መናፍቃን በድሬዳዋዎቹ ቡድን እንደሚመራ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ::

ይህ የመናፍቃኑ ብሎግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ማኅበረ ቅዱሳን ላይ በሬ ወለደ ዓይነት ወሬዎች ይዘግባል:: ሰሞኑን ከተዘገቡ የሐሰት ውንጀላዎች መካከል “ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤ አባላቱን በግድ ወርሃ ጽጌ እንዲጾሙ ያዛል” የሚል ነው:: በእርግጥ ዲያቢሎስ ጾም መች ይወዳል፤ የግብር ልጆቹ ቢቃወሙም አይደንቅም::  ወርሃ ጽጌን ብዙዎች ምእመናን እና ካህናት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስደቷን በማሰብ በፈቃድ እንደሚጾሙት የሚታወቅ ነው:: እንግዲህ አንዳንድ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችም በፈቃድ ይጾሙታል የሚል እምነት አለን::

Sunday, November 13, 2011

“እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአዳም ኃጥያት አልወረሰችም” ሊቀ ኅሩያን ከፈለኝ ወልደ ጊዮርጊስ

READ IN PDF
“እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም  የአዳም ኃጥያት አልወረሰችም” ሊቀ ኅሩያን ከፈለኝ ወልደ ጊዮርጊስ
የዛሬ ዓመት አካባቢ “ነጭ እንቁ በአዳም ገላ” የተሰኘው መጽሐፍ የዲሲ ማኅበረ ካህናትን አጋለጠ በሚል አንድ ዜና መዘገባችን ይታወሳል:: ዜናውን እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ:: የማህበረ ካህናቱ አባል የነበሩት ሊቀ ኅሩያን ከፈለኝ ወልደ ጊዮርጊስ በመጽሐፉ ከተጠቀሱት መካከል ነበሩበት:: ይኅንን አስመልክቶ እውተኛ አቋማቸው የሚገልጽ ጽሑፍ ከቤተ ደጀኔ ብሎግ ላይ አግኝተናል:: ጽሑፉም  እንደሚከተለው ቀርቧል:: መልካም ንባብ::   
+++
ከሊቀ ኅሩያን ከፈለኝ ወልደ ጊዮርጊስ
ሊቀ ኅሩያን ከፈለኝ
            «ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን፥ ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤»
ማቴ ፭፥፴፰።
ይህ ቃል፦ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦ በምንም ነገር ቢሆን መማል ፈጽሞ እንደማይገባ ከተናገረ በኋላ የተናገረው ቃል ነው። እኔም እውነት የሆነውን እውነት፥ ሐሰት የሆነውን ደግሞ ሐሰት ለማለት ይኽንን ሕያው የሆነውን የጌታዬን የአምላኬን የኢየሱስ ክርስቶስን ቃል መነሻ አድርጌያለሁ።
             
ቅዱሳን አባቶቻችን ጥንተ ጠላታቸው ሰይጣን የተለያየ ክብረ ነክ ስድብ ሲሰድባቸው በትእግሥት ያሳለፉት፥ በአኰቴት ይቀበ ሉት ነበር። ስለ ሃይማኖታችው መዋረድ ለእነርሱ ጸጋ ነውና። ቅዱስ ዳዊት ከዙፋኑ ወርዶ ከተርታው ሕዝብ ጋር ተሰልፎ በመዘመሩ ሜልኰል ወለተ ሳኦል አሽሟጣው ነበር፥ እርሱ ግን ሽሙጡን በጸጋ ተቀብሎ ስለ እግዚአብሔር ክብር ገና ከዚህ የበለጠ ራሱን እንደ ሚያዋርድ ነግሯታል። ፪ኛ ሳሙ ፮፥፳-፳፪። የገዛ ልጁ አቤሴሎም አሳድዶት በስደት በሚንከራተትበትም ጊዜ የሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ፥ ሳሚ የሚባል ሰው በሕዝቡና በመኳንንቱ ፊት ሰድቦታል። ይህ በዳዊት ላይ የወረደ ስድብና ውርደት ያሳዘናቸውና ያበሳጫቸው የሶር ህያ ልጆች ሰይፋቸውን መዝዘው ነበር። በዚህን ጊዜ ቅዱስ ዳዊት፦ «ተዉት ይስደበኝ፤ (ይርገመኝ፥ ያዋርደኝ፤)፤» ብሎአቸዋል። በየዘ መኑ የተነሡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንም ስድቡን ብቻ ሳይሆን ሰይፉን፥ እሳቱን፥ ግርፋቱን ሁሉ ታግሠው እስከ ሞት ድረስ ጸንተዋል። «እስከ ሞት ድረስም የታመንህ ሁን፤ የሕይወት አክሊልንም እሰጥሃለሁ።» የተባለውን በተግባር ፈጽመዋል። ራእ ፪፥፲። በሃይማ ኖታቸው ሲመጡባቸው ግን ትእግሥት የላቸውም፥ «መናፍቅ» ሲሉአቸው ዝም አይሉም።

Saturday, November 12, 2011

“የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አከብራለሁ፣ የተመደብኩበት ቦታ እሄዳለሁ” ብፁዕ አቡነ አብረሃም

ብፁዕ አቡነ አብረሃም
 READ IN PDF
ዛሬ በሲልቨር እስፕሪንግ ሜሪላድ ኆኅተ ምሥራቅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የቅዳሴ ቤት ለማክበር የተገኙት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብረሃም ወደ ኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ ወደ መደባቸ ሀገረ ስብከት እንደሚሄዱ ገለጹ:: ብፁዕነታቸው የተመደቡበት ቦታ የሚገልጽ ደብዳቤ ህዳር 1፣ 2004 ዓ/ም እንደደረሳቸው ገልጸው፤ ነገር ግን ለዚህ ሀገረ ስብከት ስለተመደበ አባት ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል:: ብፁዕነታቸው አንዳንድ ጅምር ሥራዎች ሥላሉዋቸው እስከ ታህሣሥ ወር አጋማሽ ድረስ ለመቆየት ለቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ መጻፋቸውም ጭምር ገልጸዋል:: በዕለቱም ትምህርታቸው “እኔ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እና ቀኖና ይከበር ብዬ እያስተማርኩ፤ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የምጥስበት ምክንያንት ምንም የለኝም” በማለተ ተናግረዋል:: አንዳንድ ሰዎች “ዛሬ ለምን የቅዳሴ ቤቱን አከበርክ”? ብለው ይጠይቁ ይሆናል፤ ነገር ግን ዛሬ የተገኘሁበት ምክንያት አስቀድሞ የተያዘ መርሀ ግብር በመሆኑ እንዲሁም ደግሞ ከሀገረ ስብከቱ መነሳቴ እንደ እናተው ዜና ከማንበብ ውጪ ሌላ ምንም የደረሰኝ መልዕክት ስላልነበረ ነው::  ሥለዚህ በዛሬው እለት የቅዳሴ ቤት ማክበሬ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን የወጣ አይደለም ብለዋል::

Thursday, November 10, 2011

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከፍተኛ ተቃውሞ ይጠብቃቸዋል፣ቅዱስ ሲኖዶስ በሰሜን አሜሪካን የቤተ ክርስቲያን ችግር ንክኪ የሌለባቸው አባቶች እንዲመድብ ፊርማ እየተሰባሰበ ነው

 READ IN PDF
የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 02/2004 ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚገቡነት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከፍተኛ ተቃውሞ እንደሚጠብቃቸ እየተነገረ ነው:: ብፁዕነታቸው ከዚህ በፊት የሰሩዋቸው ኢ-ክርስቲያናዊ ተግባራት በዚህ አካባቢ በሰፊው የሚታወቅ ስለሆነ ተቃውሞው የከፋ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል:: በሰሜን አሜሪካ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ማኅበር፣ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኙት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት፣ በገለልተኛ አስተዳደር ስር የሚገኙ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች እና በሰሜን አሜሪካ የማኅበረ በዓለ ወልድ አባላት ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ ይጠብቃቸዋል ተብሎዋል:: “የግል ቤተ ክርስቲያን ያለው አባት እንዴት ቤተ ክርስቲያን አንድ ሊያደርግ ይችላል”? የሚል ጥያቄ እየተነሳ መሆኑም እየተነገረ ነው::

Wednesday, November 9, 2011

የፓትርያርክ ጳውሎስ ቁማርና የቤተክርስቲያን ተስፋ

 ከቀሲስ ወንድምስሻ አየለ ፌስ ቡክ የተወሰደ:: READ IN PDF
ቁማር ከመዝናናት ሌላ ጥቅም ለማግኘት ሲባል የሚጫወቱት ሕጋዊና ሕገወጥ ጫወታ መሆኑና ማንኛውንም ጫወታ በቁማርነትም ሆነ በመዝናኛነት ለይቶ የመጫወቱ ድርሻ የተጫዋቹ መሆኑ ግልጥ ነው፤ ካርታን ለመዝናኛነትም፣ ሲያስፈልግ ደግሞ በሕገወጡ ቁማርነትም መጫወት እንደሚቻል። ይህም መንፈሳዊውን ሥልጣን በያዘው ሰው ዘንድ መነገሩ እጅግ የሚያሳስብና የሚያሳዝን ነው። «አባት»ን ቁማርተኛ ብሎ ለሚናገረውም ሁለት ጊዜ ብቻ ሳይሆን አሥር ጊዜ አስቦ ዓላማንም ለይቶ የሚጸናውን ከያዙ ላያሳፍር ብሎም ሊጠቅም ይችላል። ተሳድቦና ዘልፎ ለመርካት ወይም ብስጭትን ለመወጣት ሊረዳ ቢችልም ከኅሊና ዕዳ ነፃ ለመሆን ግን እውነተኛ መረጃ ይፈልጋል፤ እንደነ በጋሻውም በአደባባይ ለመገላበጥ አይገደድም። እኛምይህን ታሳቢ አድርገን እንቀጥል።

ከረጅሙ ታሪካቸው ባጭሩ

Tuesday, November 8, 2011

የብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካ መመደብ ተቃውሞ ለምን አስፈለገ???

READ IN PDF
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደዘገብነው በሰሜን አሜሪካ ለቤተ ክርስቲያን ክፍፍል ዋናኛው ተዋናኝ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ነበሩ:: ብፁዕነታቸ የጵጵስና ማዕረግ ከማግኘታቸው በፊት “አባ መላኩ” በመባል ይጠሩ ነበረ:: በወቅቱም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ነበሩ:: የዛኔው አባ መላኩ ብፁዕ አቡነ ማትያስን አልቀበልም በማለት “ገለልተኛ” ቤተ ክርስቲያን አቋቋመው ነበረ:: ከሌሎች ከግባበሮቻቸው ጋር በመሆን አሁን የሚሰግዱላቸ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ለመቃወም “የገለልተኞች” የካህናት ማኅበር አቋቁመው ነበረ:: አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የዚሁ “የገለልተኞቹ” ማኅበረ ካህናት ከአባልነት በተጨማሪም በኃላፊነት ሰርተዋል::

Friday, November 4, 2011

አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል እና "አባ ሰላማ " ብሎግ

 TO READ PDF CLIK ON HERE
“አባ ሰላማ” የተሰኘው  ብሎግ የተዋሕዶ ድምጽ እዳልሆነ የአደባባይ ላይ ምስጢር ነው:: የሚያወጣቸው ጽሑፎች እዚህ ላይ እንዳናወጣቸው ዳግም ቅዱሳን መላእክትን፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እንዲሁ ጻድቃንን መሳደብ ስለሚሆንብን አናወጣውም:: ይህ አባ ሰላማ የሰኘው ብሎግ አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የቤተ ክህነቱ መረጃ እያቀበሉት ለወራት ቤተ ክርስቲያናችንን ሲያንቋሽሽ እና ሲሳደብ ሰንብቶዋል:: አሁንም ቢሆን የተዋሕዶ ሃይማኖት የምታስተምራቸው እና የምትቀበላቸው መሠረታዊ ትምህርቶችን በመንቀፍ ላይ ይገኛል:: እነ ዲ/ን በጋሻው ደሳለኝ እና አባ ሰረቀ ወልደ ሳሙኤልን እየደገፈ በተለያዩ ግዜያት ብዙ ጽሑፎችን አቅርቧል:: ነገር ግን ማኅበረ ቅዱሳንን በማውገዝ እና በመንቀፍ በተደጋጋሚ ያለመሰላቸት በመጣር ላይ ነው::

Thursday, November 3, 2011

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ቅዱስ ሲኖዶስን እንዴ ለሁለተኛ ግዜ አታለሉት?

TO READ IN PDF CLICK ON HERE
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የጵጵስና ማዕረግ በተሾሙበት ዕለት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ፊት ቆመው “በአሜሪካን ሀገር ቤተ ክርስቲያን ሰርቼ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስረክቤያለሁ” በማለት ተናግረው ነበረ:: በዚህም ምክንያት ምልዓተ ጉባኤው በደስታ ተቀብሎት ለብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ተጨብጭቦላቸው ነበር::  ይህ “ሰርቼ አስረክቤያለሁ” ያሉት የዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ግን እርሳቸው ከሄዱበት ጊዜ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያኑ አባላት እርስ በርሳቸው በመካሰስ ላይ እየኑሩ ነው:: በወቅቱ ብፁዕነታቸ እውነትም የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለቤትነት(ይዞታነት) ቢያደርጉት ኖሮ ይሄ ሁሉ ችግር አይመጣም ነበረ:: የዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንደ ብፁዕነታቸው አወዛጋቢ ሆኖ እየኖረ ነው:: ለደብሩ ውዝግብ መንስኤውም እርሳቸው ናቸው:: ብፁዕነታቸው “ሰርቼ አስረክቤያለሁ” የሚሉት ቤተ ክርስቲያን ግን፤ በባለቤትነት የተመዘገቡት ከሶስቱ ግለሰዎች አንደኛው ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ናቸው::  ነገር ግን ብፁዕነታቸው ያላደረጉትን አድርጌያለሁ በማለት ቅዱስ ሲኖዶስን ዋሽተዋል:: የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ግን እስከ ዛሬ ድረስ እንደተበጣበጡ ይኖራሉ::