Thursday, November 3, 2011

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ቅዱስ ሲኖዶስን እንዴ ለሁለተኛ ግዜ አታለሉት?

TO READ IN PDF CLICK ON HERE
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የጵጵስና ማዕረግ በተሾሙበት ዕለት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ፊት ቆመው “በአሜሪካን ሀገር ቤተ ክርስቲያን ሰርቼ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስረክቤያለሁ” በማለት ተናግረው ነበረ:: በዚህም ምክንያት ምልዓተ ጉባኤው በደስታ ተቀብሎት ለብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ተጨብጭቦላቸው ነበር::  ይህ “ሰርቼ አስረክቤያለሁ” ያሉት የዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ግን እርሳቸው ከሄዱበት ጊዜ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያኑ አባላት እርስ በርሳቸው በመካሰስ ላይ እየኑሩ ነው:: በወቅቱ ብፁዕነታቸ እውነትም የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለቤትነት(ይዞታነት) ቢያደርጉት ኖሮ ይሄ ሁሉ ችግር አይመጣም ነበረ:: የዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንደ ብፁዕነታቸው አወዛጋቢ ሆኖ እየኖረ ነው:: ለደብሩ ውዝግብ መንስኤውም እርሳቸው ናቸው:: ብፁዕነታቸው “ሰርቼ አስረክቤያለሁ” የሚሉት ቤተ ክርስቲያን ግን፤ በባለቤትነት የተመዘገቡት ከሶስቱ ግለሰዎች አንደኛው ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ናቸው::  ነገር ግን ብፁዕነታቸው ያላደረጉትን አድርጌያለሁ በማለት ቅዱስ ሲኖዶስን ዋሽተዋል:: የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ግን እስከ ዛሬ ድረስ እንደተበጣበጡ ይኖራሉ::


የዛሬ አምስት ዓመት አካባቢ ተሹመው ወደ አሜሪካ ሲመጡ እዚህ የሚኖሩ ምዕመናን ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን አንቀበልም ብሎ አባረዋቸው ነበረ:: ዘንድሮስ እንዴት ሊቀበላቸው ይችላል? ተስተካክለዋል እንዳንል አልተስተካከሉም፤ ምክንያቱም ሐዋሳ ላይ ከአሜሪካ በላይ ጥፋት እንዳጠፉ ሰምተናል:: በጥፋታቸውም ምክንያት ከሀገረ ስብከታቸው እንደተባረሩም እናውቃለን:: ይህም ብቻ አይደለም ከሀገረ ስብከታቸው ውጪ እዚህ ሀገረ አሜሪካ እየመጡ ከአንድም ሁለት ጊዜ ስልጣነ ክህነት ሲሰጡ፣ “የገለልተኞች” ቤተ ክርስቲያን ሲባርኩ በአይናችን አይተናቸዋል::

ታድያ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ቅዱስ ሲኖዶስን በዚህኛው ምልዓተ ጉባኤ ምን ብለው ቢያታልሉት ነው? መጀመርያ ያባረራቸው ምዕመን ጋር በድጋሚ የሚላኩት? እንዴትስ ልንቀበላቸው እንችላለን? መታሰብ አለበት::

“በገለልተኛ” አስተዳደር ውስጥ ነን የሚሉ አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት ቢሆኑ እንኳ የቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ አስተዳደር ጠልተው ከሆነ የተገለሉት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን መቀበል ያለባቸው አይመስለንም:: ከተቀበሉ ግን እውነቱን አሁን ይወጣል:: ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እንደተመኙትም “የገለልተኞች” ጳጳስ ሆነው ይኖያሉ:: “ገለልተኞቹ” ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ከተቀበሉ ጥላቻው የአቡነ ጳውሎስ አስተዳደር አይደለም ማለት ነው:: ምክንያቱም የተበላሸው አስተዳደር ገና በማቆጥቆጥ ላይ ያለውን የአሜሪካውን አስተዳደር የበለጠ እንዲበላሹት ልኳቸዋልና::

እኛ አባ “እገሌን” ከመደገፍ ወይም አባ “እገሌን” ደግሞ ከመጥላት አይደለም:: ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ግን በሀገረ አሜሪካ በፍጹም አንድነትን ማምጣት እንደማይችሉ ተፈትነው ታይተዋል:: ሥለዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ አንድነትን ሊያመጣ የሚችል አባት ለሀገረ አሜሪካ አስፈላጊ መሆኑን ሊያጤነው ይገባል::

5 comments:

Anonymous said...

Yihema Fitsum Tilacha Neaw Eyantsebareqachu Yalachehut. Libona Binorachu ena Mizanawi Zegeba Maqreb Bitechelu Melkam Neaw!

Anonymous said...

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ግን በሀገረ አሜሪካ በፍጹም አንድነትን ማምጣት እንደማይችሉ ተፈትነው ታይተዋል::

Anonymous said...

እንደውነቱ ከሆነ አቡነ ፋኑኤል ቀደም ብለው እዚህ በመጡበት ጊዜ በሄዱበት ቦታ ሁሉ "እዚህ የምታዩን ሀገረ ስብከት የምትሉትን እንቆጣጠረዋለን" "አሁንም ባለሙሉ ሥልጣን እኔ ነኝ" በማለት ሕዝበ ክርስቲያኑን ሲያደናግሩ ነበር። ይበልጥ የሚያሳዝነው ግን በኣንድ ወቅት የተናገሩት ነው፥ ከአንድ አፈ ቀላጤ ጋር ቁጭ ብለው ሲወያዩ፣ ይህ ሰው "አባታችን ለምንድን ነው እንደዚህ ሰው አፍ ውስጥ የሚገቡት፥ ሥራዎትን ድሮ እኛ በደንብ እናውቃለን ነገር ግን ከነዚህ ሰዎች ጋር ያሎት ማለትም ከነበጋሻው በጣም ሰው ሁሉ አይወደውም ለምን መልካሙን ስሞትን ያበላሻሉ?" ብሎ ጠይቋቸው ነበር፣ እርሳቸው ያሉት ግን "እኛ እንኳን እዚህ ማዕረግ ላይ ደረስን እንጂ፣ ከዚህ በኃላ ማንም ምንም ሊያመጣብን አይችልም፥ እስከ ዛሬ ስንገፋ ኖረናል አህን ግን ሲገፉን የነበሩትን በኃይል ገፍተን እናስወጣቸዋለን" ብለው ሰውየውን አስደንግጠውታል። ታዲያ እኚህ አባት በእውነት እዚህ መጥተው ቤተ ክርስቲያንን አንድ የማድረግ ሥራ ሊሰሩ ቀርቶ በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን ጥላ ስር የተሰባሰቡትንም ከመበተን ወደ ኃላ እንደማይሉ በግልጽ አሳይተውናል።

ከዚህ በተጨማሪ የዛሬ 15 ወይም 16 ዓመት አካባቢ አባ መላኩ ሆነው ሲሰሩ የነበረው ሁሉ ሕዝብ የማወቅ መብቱ ተጠብቆ ሊታወቅ ይገባል ባይ ነን በተለይ ከብፁዕ አቡነ ማቲያስ ጋር 5 ዓመት የፈጀ ክስ ተካሰው የቤተክርያኗን መልካም ሥም ለማጥፋት እነ ቀሲስ ታደሰን እያስፈራሩ ኑና መስክሩልኝ አለበለዚያ ሰው እኔን በጣም ያምነኛል ስለዚህ መጥፎ ነገር አስወራባችኃለው ሰው መጥቶ እናንተ ጋር አያስቀድስም እኔን ደግፋችሁ ፍርድ ቤት ካልመሰከራችሁልኝ በማለት፣ ከዚያ በተጨማሪ ፍርድ ቤቱ ለምን አትስማሙም እንደማያችሁ ሁለታችሁም የአንድ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች (servant) ናችሁ ብሎ ዳኛው ሲጠይቅ ያኔ አባ መላኩ "እኔ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አገልጋይ አይደለሁም" ብለው በመመለሳቸው ሰውን ሁሉ አስደንግጠው አንዳንድ በወቅቱ የነበሩ ፍርድ ቤት የነበሩ ሰዎች ምነው የለበሱት ቀሚስ፣ ያደረጉት መስቀል፣ በእጆ የያዙት መስቀል ሁሉ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አይደለም ወይ ሲባሉ የክህደታቸው ብዛት "ማነው ለኢትዮጵያ ቤተክርቲያን የሰጠው፥ ቀሚሱም መስቀሉም ቤተክርስቲያኑም የግልሌ የራሴ ነው" ነበር ያሉት በቅርብ ጊዜ እነዛን ዶክሜንቶች ሁሉ በእጃችን ስላሉ ለዚህ ዝግጅት ክፍል እንልከዋለን።
የያኔው አባ መላኩ (አባ ፋኑኤል) በዚህ አካባቢ መጥተው ሥራ ሊሰሩ ቀርቶ ልክ ያኔ ሲያደርጉ እንደነበረው የግል ጥቅማቸን ሲያሳድዱ ብዙ ነገሮች እንደሚበላሹ እሙን ነው ስለዚህ በተለይ በካሊፎርኒያ እና ዲሲ አካባቢ የምትኖሩ ምዕመናን በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ወደ አሜሪካ ለመምጣት በዝግጅት ላይ ያሉትን ሀሰተኛ ምልዕክተኛ በሰላዊ ሰልፍ ከፍተኛ ተቃውሞ አድርጎ ልክ የአዋሳ ክርስቲያኖች እንዳደረጉት የማድረግ ክርስቲያናዊ ግዴታ ያለብን ይመስለኛል።

አፄ ሱሲንዮስ ከእንግዲህ ተዋህዶ ይፍረስ፣ ካቶሊክ ይንገስ ብለው ባወጁት አስደንጋጭ አዋጅ የተዋሕዶ ልጆች ከሊቅ እስከ ደቂቅ በበቂስ በመውጣት ንሴብሖ ብለው ወደ ጎንደር በሚሄዱበት ጊዜ ንጉሱ በየዋሕነት 12,000 የተዋሕዶ ልጆች ሰማዕትነት ተቀብለዋል፤ የሃይማኖት ነገር ስለሆነ መስዋዕትነት ግድ ስለነበረ እነዚህ ክርስቲያኖች ባይኖሩ ኖሮ እኛ እያንዳንዳችን ዛሬ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሚለው ስም ባልኖረ ነበር ነገር ግን እግዚአብሔር በጥበብ ከዘሩ አንድ ባያስቀርልን ኖሮ እንጠፋ ነበር ወይም ተስፋ አይኖረንም ነበር እንዳለው ነብየ እግዚአብሔር ኢሳያስ አሁንም እኛ ሀይማኖት ለዋጭ፣ ትውፊት አውዳሚ፣ ሥርዓት ደምሳሽ መጥቷል ብለን ለሚቀጥለው ትውልድ አስበን አንድ ነገር ማድረግ ግድ ይለናል ሀገሩ አሜሪካ ነው እንኳን ባንድ ሰው ላይ በኦባማም ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ይቻላል ስለዚህ የዚህ ጡመራ አዘጋጆች አንድ ነገር ብታዘጋጁ መልካም ነው እላለሁ ያማለት የሃይማኖት ግዴታችንን መወጣት እንደሆነ እንዲቆጠር ከወዲሁ ለመግለጽ እወዳለሁ።
ቸር ይግጠመን

Anonymous said...

Yesinodosu wusane yemenfeskidus wusane new bilen kamenen endih aynet Ames mansat lemenfes kidus wusane alemegezat yihonibnal lebego endiadergew meseley yishalal

Anonymous said...

yemechereshaw asteyayet sechi ante endemitlew ye awassa hizb tikikl alneberem malet new mikniyatum awassa yetmedebut be kidus sinodos new filagotachin ewnetegna abat yilakilin menafik anifeligm new wendime endesew hulachinm enwedachewalen be hymanot kin keld yelem selamawi self enwetalen