
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንደዘገብነው በሰሜን አሜሪካ ለቤተ ክርስቲያን ክፍፍል ዋናኛው ተዋናኝ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ነበሩ:: ብፁዕነታቸ የጵጵስና ማዕረግ ከማግኘታቸው በፊት “አባ መላኩ” በመባል ይጠሩ ነበረ:: በወቅቱም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ነበሩ:: የዛኔው አባ መላኩ ብፁዕ አቡነ ማትያስን አልቀበልም በማለት “ገለልተኛ” ቤተ ክርስቲያን አቋቋመው ነበረ:: ከሌሎች ከግባበሮቻቸው ጋር በመሆን አሁን የሚሰግዱላቸ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ለመቃወም “የገለልተኞች” የካህናት ማኅበር አቋቁመው ነበረ:: አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የዚሁ “የገለልተኞቹ” ማኅበረ ካህናት ከአባልነት በተጨማሪም በኃላፊነት ሰርተዋል::
እንግዲህ ሁለቱንም ማለትም የዛኔው “አባ መላኩ” የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እና አባ ሰረቀ ብርሃን የጵጵስና ማዕረግ እንደሚያስፈልጋቸው ወሰኑ፤ በዚህም ምክንያት የዋሽንገተን ዲሲው “የገለልተኞቹ” የካህናት ማኅበርን በተመሳሳይ ግዜ ከዱ:: ለምን እንደከዱ ግን በወቅቱ ግልጽ አልነበረም:: ማህበረ ካህናትን መክዳታቸው ብቻ ሳይሆን ምዕመናንን ዋሽተዋል:: “ምንድ ነው የዋሹት”? ትሉ ይሆናል:: ውሸቱ እንዲህ ነው:: ሁለቱም የየራሳቸው በስማቸው ያቋቋሙት ቤተ ክርስቲያን አላቸው:: የጵጵስና ማዕረግ ፈልገው ወደ ኢትዮጵያ ሲሄዱ ግን ቤተ ክርስቲያናቸውን “ወደ ኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስረከብን፣ የምንተዳደረውም በኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው” በማለት ተናገሩ:: በግዜው ምእመናኑ ተደናገሩ:: መደናገርም ብቻ ሳይሆን ለሁለት ተከፈሉ:: ውሳኔያቸውን የተቀበሉ አብረው ቆዩ፤ በውሳኔያቸው ያልተስማሙት ግን ተለይተው ወጡ::
ታዲያ የግል ንብረታቸው ነገር ግን ምዕመናን የሰሩትን ቤተ ክርስቲያን ወደ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መለስን ይበሉ እንጂ፤ እስከ አሁን ድረስ ግን የሁለቱም ስም በባለቤነት (articles of incorporation) ላይ እንደተመዘገበ አለ:: አጥቢያቸውም ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አላስቀየሩትም:: የሚገርመው ነገር እዚህ አሜሪካን ምዕመናንን ብቻ ሳይሆን የዋሹት ኢትዮጵያ ሄደውም ቅዱስ ሲኖዶስ ጭምር ዋሹት:: በአሜሪካን ሀገር ቤተ ክርስቲያን ሰርተን አስረከብን በማለት::
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እንደ ግብር አባታቸው እንደ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በትልቁ ፎቶዋቸውን አሰርተው ከሥዕለ እግዚእ በላይ አሰቅለዋል:: ሌሎችንም ዝርዝር ጉዳዮች በሰፊው እንመለስበታለን::
እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያናችን አንድነት ይጠብቅልን!!!
2 comments:
this idea very annoying for ethiopian orthodox church
All accurately and honestly put. Thank you
Post a Comment