Saturday, November 12, 2011

“የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አከብራለሁ፣ የተመደብኩበት ቦታ እሄዳለሁ” ብፁዕ አቡነ አብረሃም

ብፁዕ አቡነ አብረሃም
 READ IN PDF
ዛሬ በሲልቨር እስፕሪንግ ሜሪላድ ኆኅተ ምሥራቅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን የቅዳሴ ቤት ለማክበር የተገኙት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብረሃም ወደ ኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ ወደ መደባቸ ሀገረ ስብከት እንደሚሄዱ ገለጹ:: ብፁዕነታቸው የተመደቡበት ቦታ የሚገልጽ ደብዳቤ ህዳር 1፣ 2004 ዓ/ም እንደደረሳቸው ገልጸው፤ ነገር ግን ለዚህ ሀገረ ስብከት ስለተመደበ አባት ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል:: ብፁዕነታቸው አንዳንድ ጅምር ሥራዎች ሥላሉዋቸው እስከ ታህሣሥ ወር አጋማሽ ድረስ ለመቆየት ለቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ መጻፋቸውም ጭምር ገልጸዋል:: በዕለቱም ትምህርታቸው “እኔ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት እና ቀኖና ይከበር ብዬ እያስተማርኩ፤ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የምጥስበት ምክንያንት ምንም የለኝም” በማለተ ተናግረዋል:: አንዳንድ ሰዎች “ዛሬ ለምን የቅዳሴ ቤቱን አከበርክ”? ብለው ይጠይቁ ይሆናል፤ ነገር ግን ዛሬ የተገኘሁበት ምክንያት አስቀድሞ የተያዘ መርሀ ግብር በመሆኑ እንዲሁም ደግሞ ከሀገረ ስብከቱ መነሳቴ እንደ እናተው ዜና ከማንበብ ውጪ ሌላ ምንም የደረሰኝ መልዕክት ስላልነበረ ነው::  ሥለዚህ በዛሬው እለት የቅዳሴ ቤት ማክበሬ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን የወጣ አይደለም ብለዋል::


ብፁዕነታቸው “ቤተ ክርስቲያን ልካኝ አሜሪካን መጥቼ ነበረ፤ አሁንም ቤተ ክርስቲያን ወደ ላከችኝ ቦታ እሄዳለሁ” በማለት ሲናገሩ በበዓሉ የተገኙት ምእመናን እና ካህናት በእንባ እንደተራጩ በቦታው የተገኙ የአይን ምስክሮች ገልጸውልናል::  

በሰሜን አሜሪካን የኢ/ኦ/ተ/ቤ ታሪክ ሀገረ ስብከት የሚለውን ስም እንኳ በምእመናን ዘንድ አይታወቅም ነበረ:: ብፁዕ አቡነ አብረሃም እዚህ አካባቢ ተመድበው ከመጡ በኋላ ግን ሀገረ ስብከት በስም ከመታወቁም በላይ፤ ለሀገረ ስብከቱ ጽፈት ቤት የአካባቢው ምእመናን አሰባስበው አስተምረው እንዲገዛ አድርገዋል:: ብፁዕነታችው የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤ መግዛት ብቻ ሳይሆን፤ መንበረ ጵጵስና አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እንዲመሰረት አድርገዋል:: እንዲሁም ደግሞ የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና እንዲከበረ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ እስቴቶች በመዘዋወዛር ምእመናንን እያስተማሩ በርካታ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በቤተ ክርስቲያናችን መዋቅር ውስጥ እንዲመሰረቱ አድርገዋል:: ለቤተ ክርስቲያን ቀኖና እና ሥርዓት መከበር የማይበገረው ብርቱ አቋማቸው በተለይም በወጣቶች ዘንድ እጅግ በጣም ተወዳጅ አባት ናቸው::

“የእኔ እና የእናንተ አባቶች ንጽሕት ሃይማኖት ከሙሉ ሥርዓቱ ጋር፤ እንዲሁም ቀኖና ቤተ ክርስቲያን እና ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን  ሳያፋልሱ ከቀደሙት አባቶቻቸው የተረከቡትን ለእኛ አስረክበውናል። ለእኔ  እና ለመሰሎቼ በመንፈስ ቅዱስ  ለምንወልዳቸው ልጆቻችን፣ ለእናተ ደግሞ በሥጋ ለምትወልዱዋቸው ልጆቻችሁ በዚህ በዲያስጶራው ዓለም ምን  ዓይነት ቤተ ክርስቲያን አስረክበናቸው ልናልፍ ይሆን?” በማለት በተገኙበት ቦታ ሁሉ የቤተ ክርሲያናችን ቀኖና እንዲጠበቅ የሚያስተምሩት ብፁዕነታቸው በዛሬው እለትም ይህን ትምህርታቸው እንደደገሙት ተገልጾልናል::

በተለያየ መልኩ በዘር፣ በፖለቲካ፣ በገንዘብ እንዲሁም ደግሞ በሃይማኖት የተከፋፈለችው የሰሜን አሜሪካን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለማስታረቅ የበኩላቸውን ጥረት አድርገዋል::  ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጪ ያሉት “ገለልተኛ” አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር እንዲገቡ ጥረት ያደርጉ እንደነበረም ይታወቃል::  ብፁዕነታቸው “አሳምነኝ እና እኔም ላሳምንህ” የሚለው የቀኖና ቤተ ክርስቲያን መከበረ በየዙት አቋማቸው ምክንያት በተለያየ ነገር የተያዙት አጥቢያዎች ወደ ቤተ ክርስቲቷ መዋቅር ስር ሊገቡ አልቻሉም::

ብፁዕነታቸው በሰሜን አሜሪካን  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሀገሪቱ ሕግ መሰረት የአሜሪካን መንግስት እንዲያውቃት እና መብቷም እንዲከበረ (patent right) እንዲኖራት ብዙ ጥረዋል::

በዛሬ ዕለት በቤተ ክርስቲያናችን ሕግ እና ሥርዓት መሰረት በሲልቨር እስፕሪንግ ሜሪላንድ የተቋቋመው አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ከጊዜያዊ ኮሚቴው ስለ ቤተ ክርስቲያኑ መመስረት አስመልክቶ መልዕክት ተላልፎ ነበረ::

+++

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::
የተከበሩ ብፁዕ አባታችን አቡነ አብርሃም፣
በኢ/ኦ/ተ/ ቤተ ክርስቲያን የዲሲ እና አካባቢው ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
አባቶች ካህናት፣ ወንድሞች ዲያቆናት፣
ወንድሞች እህቶች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት፣ ታሪካዊት፣ ሐዋርያዊት እና ሲኖዶሳዊት ናት። ይህች ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እኛ በምንኖርበት አካባቢ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ቀኖናዋ ተጥሶ በተለያየ መልኩ ውጥን ቅጡ በማይታወቅ ሁኔታ አንድነቷ ተንዶ ፈተና ላይ ትገኛለች:: ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ችግር ተመልክቶ ለዘለቄታው መፍትሔ እንዲገኝለት ሊቀ ጳጳስ በመመደብ ሀገረ ስብከት ተመስርቷል። ሀገር ስብከቱም ከተመረተ ወዲህ በዓይን የሚታዩ፣ በእጅ የሚጨበጡ ለውጦች አሉ፤ ለምሳሌ የሀገረ ስብከቱ መንበረ ጵጵስና አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መመስረት፣ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መኖሪያ እና ጽ/ቤት ግዢ መፈጸም የሚጠቀሱ ናቸው።

ቤተ ክርስቲያናችን ከገጠማት ፈተና መፍትሔ ከሚሆኑ ሥራዎች መካከል አንዱ ከእናት ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር ሰንሰለት ያተቋረጠ እንዲሁም ደግሞ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ያላፋለ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን መመረት ነው። ከግንዱ ያልተለዩና ትክክለኛውን የቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር መዋቅር የጠበቁ አጥቢያ አያተ ክርስቲያናት በየቦታው ከተመረቱ፤ የሚቀጥለው ትውልድም ግራ ሳይጋባ እና ከማንም ጋር ሳይካሰስ ቤተ ክርስቲያኒን ይረከባል። ይህ ካልሆነ ግን ችግሩ የበለጠ ሥር ሰዶ ትውልዱም እያወቀ ሲመጣ ግራ በመጋባት ከቤተ ክርስቲያን ይሸሻል። ስለዚህ ሐዋያዊት ለሆነችው የኢ/ኦ/ተ/ቤ እውነተኛ ድም የሚሰማባቸው፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ያላፋለሱ፣ ሐዋያዊ ትውፊቷ የጠበቁ አጥያ አያተ ክርስቲያናት እንደሚያስፈልግ በማመን ይህን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ለመመስረት ተገደናል::

የዚህ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ለመመረት ውይይት የተጀመረው የካቲት 12፣ 2002 ዓ/ም አንዲት እህታችን “እንኳን ማርያም ማረችሽ” ለማለት ተሰባሰቡ ወንድሞች አማካኝነት ነው:: ውይይቱ እየሰፋ መጥቶ ጉዳዩን ወደ ብፁዕ አባታችን አቡነ አብሃም ዘንድ በግንቦት ወር 2002 ዓ/ም  መነሻ ሳቦቻችን ይዘን ሄድን:: ብፁዕነታቸውም በደስታ ሳቡን ተቀብለው፤ በሚያስፈልገን ነገር ሁሉ ለመርዳት ከጎናችን እንደሆኑ ቃል ገብተውልን ተለያየን::

የብፁዕ አባታችን ቡራኬ እና መመያ ከተቀበልን በኋላ ሳቡን ለአካባቢው ምእመናን የሚዳረስበት ሁኔታ እያጠናን ቆየን:: ይሁን እንጂ በተለያዩ የቤተ ክርስቲናችን ፈተናዎች ምክንያት የጀመርነው ሥራችን በጣም ወደ ኋላ አዘገየን:: ምንም እንኳ ቢዘገይም የእግዚብሔር ፈቃድ እስካለበት ድረስ አጥቢያው መመረቱ እንደማይቀር እናምን ነበረ::

የዚህ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን መመረት ምክንያት የሆኑን ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው:-
1.        በሲልቨር እስፕሪንግ እና አካባቢው ለምንኖር የቤተ ክርስቲያኒ ልጆች ትክክለኛውን የቤተ ክርስቲያን ድምፅ የምንሰማበት ምቹ እና በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓት መረት የተመረተ አማራጭ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አለመኖ
2.     በኢ/ኦ/ተ/ቤ ሥርዓት እና ቀኖና መረት በሀገ ስብከቱ የተቋቋመው መንበረ ጵጵስና ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ለዚህ አካባቢ ነዋሪዎች ሩቅ በመሆኑ
3.     አጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ ከተቋቋመ  ቤተ ክርስቲያን ሥርዓቷን፣ ቀኖናዋን፣ እውነተኛ ድምን ለአካባቢው ነዋሪዎች የምታስተምርበት አመቺ ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋል ሚል
ሐሳብ እና እምነት ነው።

በሐሳባችንን እና በፍላጎታችን መሠረት እግዚአብሔር አምላካችን ፈቃዱ ሆኖ እነሆ ዛሬ ይህ አገልግሎት ሊጀመር አስችሎታል። ለዚህ ያደረሰንን አምላካችንን እያመሰገንን ለዚህ እንድንበቃ በአባታዊ ምክራቸው፣ በቡራኬያቸው እና በትምህርታቸው የመሩንንና ያጽናኑንን ብፁዕ አባታችንን ከልብ እናመሰግናለን። ረዥም ዕድሜ እና የአገልግሎት ዘመን እንዲሰጣቸው አምላካችንን ዘወትር እንለምናለን። ከዚህም በተጨማሪ ለዚህ አገልግሎት መሳካት የተባበሩ አካላትን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!            .

.

3 comments:

Anonymous said...

Let it be the will of God and let the mercy of God be onto you

Haile Zemariam said...

Words can’t explain our deep sorrow and sadness. What can we say? …… We do respect your farsighted decision and we will follow what you thought us about respecting the decision of the Holy Synod. You worked and always work for the unity of THE ETHIOPIAN ORTHODOX TEWHIDO CHURCH. We will miss you very much; you are one of the brave and exemplary fathers of our age. May God bless the rest of your life and spiritual service.

Haile Zemariam

Anonymous said...

you truly believe Abune Abraham united The Ethiopian orthodox Church?

God will pay him back for what he has done to our community. It took so long but God answered our prayer.

God is good.