Sunday, November 13, 2011

“እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአዳም ኃጥያት አልወረሰችም” ሊቀ ኅሩያን ከፈለኝ ወልደ ጊዮርጊስ

READ IN PDF
“እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም  የአዳም ኃጥያት አልወረሰችም” ሊቀ ኅሩያን ከፈለኝ ወልደ ጊዮርጊስ
የዛሬ ዓመት አካባቢ “ነጭ እንቁ በአዳም ገላ” የተሰኘው መጽሐፍ የዲሲ ማኅበረ ካህናትን አጋለጠ በሚል አንድ ዜና መዘገባችን ይታወሳል:: ዜናውን እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ:: የማህበረ ካህናቱ አባል የነበሩት ሊቀ ኅሩያን ከፈለኝ ወልደ ጊዮርጊስ በመጽሐፉ ከተጠቀሱት መካከል ነበሩበት:: ይኅንን አስመልክቶ እውተኛ አቋማቸው የሚገልጽ ጽሑፍ ከቤተ ደጀኔ ብሎግ ላይ አግኝተናል:: ጽሑፉም  እንደሚከተለው ቀርቧል:: መልካም ንባብ::   
+++
ከሊቀ ኅሩያን ከፈለኝ ወልደ ጊዮርጊስ
ሊቀ ኅሩያን ከፈለኝ
            «ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን፥ ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤»
ማቴ ፭፥፴፰።
ይህ ቃል፦ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦ በምንም ነገር ቢሆን መማል ፈጽሞ እንደማይገባ ከተናገረ በኋላ የተናገረው ቃል ነው። እኔም እውነት የሆነውን እውነት፥ ሐሰት የሆነውን ደግሞ ሐሰት ለማለት ይኽንን ሕያው የሆነውን የጌታዬን የአምላኬን የኢየሱስ ክርስቶስን ቃል መነሻ አድርጌያለሁ።
             
ቅዱሳን አባቶቻችን ጥንተ ጠላታቸው ሰይጣን የተለያየ ክብረ ነክ ስድብ ሲሰድባቸው በትእግሥት ያሳለፉት፥ በአኰቴት ይቀበ ሉት ነበር። ስለ ሃይማኖታችው መዋረድ ለእነርሱ ጸጋ ነውና። ቅዱስ ዳዊት ከዙፋኑ ወርዶ ከተርታው ሕዝብ ጋር ተሰልፎ በመዘመሩ ሜልኰል ወለተ ሳኦል አሽሟጣው ነበር፥ እርሱ ግን ሽሙጡን በጸጋ ተቀብሎ ስለ እግዚአብሔር ክብር ገና ከዚህ የበለጠ ራሱን እንደ ሚያዋርድ ነግሯታል። ፪ኛ ሳሙ ፮፥፳-፳፪። የገዛ ልጁ አቤሴሎም አሳድዶት በስደት በሚንከራተትበትም ጊዜ የሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ፥ ሳሚ የሚባል ሰው በሕዝቡና በመኳንንቱ ፊት ሰድቦታል። ይህ በዳዊት ላይ የወረደ ስድብና ውርደት ያሳዘናቸውና ያበሳጫቸው የሶር ህያ ልጆች ሰይፋቸውን መዝዘው ነበር። በዚህን ጊዜ ቅዱስ ዳዊት፦ «ተዉት ይስደበኝ፤ (ይርገመኝ፥ ያዋርደኝ፤)፤» ብሎአቸዋል። በየዘ መኑ የተነሡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንም ስድቡን ብቻ ሳይሆን ሰይፉን፥ እሳቱን፥ ግርፋቱን ሁሉ ታግሠው እስከ ሞት ድረስ ጸንተዋል። «እስከ ሞት ድረስም የታመንህ ሁን፤ የሕይወት አክሊልንም እሰጥሃለሁ።» የተባለውን በተግባር ፈጽመዋል። ራእ ፪፥፲። በሃይማ ኖታቸው ሲመጡባቸው ግን ትእግሥት የላቸውም፥ «መናፍቅ» ሲሉአቸው ዝም አይሉም።

       
እኔ ይኽንን መግለጫ ከአምስት ዓመታት በኋላ እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ለማውጣት የተገደድኩት፥ በ2002 ዓ.ም. በተከበሩ በመምህር ሀብተ ማርያም ተድላ በተጻፈ መጽሐፍ ላይ እና በሰሞኑ ለቅድስት ተዋህዶ ሃይማኖት ለመሠዋት በተዘጋጁ የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ወጣቶች ለቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ተሃድሶ መናፍቃን ባቀረቡት አቤቱታ ላይ «ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ፤» ሆኜ በመገኘቴ ነው።
       
አባታችን መምህር ሀብተ ማርያም ተድላ፥ በዲሲ እና አካባቢዋ አብያተ ክርስቲያናት ትብብር ተቋቁሞ በነበረው የካህናት ማኅበር፥ በ«ቄስ» አስተርአየ ጽጌ፤ አቅራቢነት ተነሥቶ የነበረውን የሃይማኖት ክርክር 219 ገጽ በሆነው መጽሐፋቸው የማያዳግም ኦርቶ ዶክሳዊ መልስ ሰጥተዋል። ይህም በዘመናቸው ለተነሡ መናፍቃን በአፍም በመጽሐፍም መልስ ከሰጡ ጥንታውያን ሊቃውንት ጋር የሚያሰልፋቸው ነው። በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ዙሪያ፦ «ጥንተ አብሶ ነበረባት፤» በሚሉ ወገኖችና «ጥንተ አብሶ አልነ በረባትም፤» በሚሉ ወገኖች መካከል ዱላ ቀረሽ ክርክር በሚደረግበት ጊዜ እኔም በቦታው ተገኝቼ ነበር። ምክንያቱም በወቅቱ የማገለ ግለው ዲሲ ማርያም ስለነበረ ነው። የጉባኤውም ቃለ ጉባኤ ጸሐፊ ነበርኩኝ። የጉባኤው ሰብሳቢም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ነበሩ።
       
ይህ የሃይማኖት ክርክር በሚደረግበት ወቅት፦ የ«ቄስ» አስተርአየን ሃሳብ የደገፉ ሰዎች ዝርዝራቸው በመጽሐፉ ላይ ተጠቅሷል። ይኽንን ፍጹም የሆነ ክህደት ከተቃወሙት መካከል ደግሞ እኔ እና ርዕሰ ደብር አብርሃም እንገኝበታለን። ይኽንንም በወቅቱ በስደት እዚህ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፥ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ የነበሩት አቡነ ማትያስ፥ ያውቁታል። በኋላም ለሀገረ   ስብከቱ ተሹመው መጥተው ለነበሩት ለብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ሁሉንም ነገር አስረድቼ ማስረጃዎችን ሰጥቻቸዋለሁ። ጸሐፊው መምህር ሀብተማርያም ተድላ በመጽሐፋቸው ገጽ 34 ላይ፦ «ለቅዱስ ሲኖዶስ በተላከው በማኅበረ ካህናቱ ጽሑፍ አለመግባባት የተፈጠረበት ምክንያት ከሚለው አርእስት ቀጥሎ የሰፈረው ይነበባል። አንደኛው ወገን፦ < አንጺሖ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ> የሚለውን  ቃል ተቀብሎ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የነቢብ፥ የገቢር፥ የኀልዮ ኃጢአት ያልነበረባት የሌለባት ናት። ነገር ግን በአዳማዊ ዘር በኲል ከሚተላለፈው ውርስ መንፈስ ቅዱስ አንጽቷታል ሲል፤ ሁለተኛው ወገን ደግሞ ገና ሳትወለድ በዘር ይተላለፍ ከነበረው አዳማዊ ውርስ ነጻ ናት የሚል ነው፤» ብለዋል። ይህ ትክክል ነው። ትክክል ያልሆነው ይኽንን የተረጐሙበት መንገድ ነው። «ይህ ከዚህ በላይ የሚነበበው የማኅበረ ካህናት ጽሑፍ የተጣመመና የተዛባ (Distorted) በሆነ አጻጻፍ የተቀመጠ ወይም ለማደናገር ሆን ተብሎ የተደረገ አሻሚ ሁኔታ ይታይበታልና መስተካከል ይኖርበታል፤» ብለዋል። ይህም በወቅቱ «እመቤታችን ጥንተ አብሶ አልነበረባትም፤» ብለን የተከራከርነውን ሰዎች እምነት የነካ ነው። ምክንያቱም «ጥንተ አብሶ አልነበረባትም፤» የሚለው የገባው የእኛን እምነት ለማንጸባረቅ እንጂ ለማደናገር አይደለምና ነው። አባታችን መምህር ሀብተ ማርያም ይኽንን ያደረጉት ሆን ብለው እንዳልሆነ ስለሚገባኝ ለወደፊቱ እንዲስተካከልልኝ በትኅትና እጠይቃለሁ።
       
ምንአልባት በወቅቱ ምን እርምጃ ወሰድክ የሚል ጥያቄ ይነሣ ይሆናል፥ ተገቢም ነው። ኅዳር 1 ቀን 1998 ዓ.ም. ስድስት ገጽ የቅሬታና የአቋም መግለጫ በማውጣት በጽሑፍ አሰራጭቻለሁ፥ በሬድዮም አስነግሬአለሁ። በዚህም ምክንያት ከዲሲ ማርያም ከሥራዬ ተባርሬ እስከነ ቤተሰቤ በረሀብ አለንጋ ተገርፌአለሁ። በኋላም ቅዳሜ ቅዳሜ አገለግል ወደነበረበት በሪችመንድ ደብረ መንክራት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ብቻ ተወስኜ በምኖርበት ጊዜ፥ ቤተክርስቲያኗን ወደ እናት ቤተክርስቲያን በማስገባቴ ብዙ ፈተና ደርሶብኛል። ከፈተናውም አንዱ፥ የዲሲ ማርያም አስተዳደር ሪችመንድ ከሚገኘው ቦርድ ጋር በመመሳጠር ፍርድ ቤት ገትረውኛል። ይኽንንም ብፅዕ አቡነ ገብርኤል ያውቁታል። ምክንያቱም ቦርዱ በምስክርነት ጠርቷቸው ፍርድ ቤት ተገኝተው ስለነበረ ነው። መገኘታቸውም በእኔ ላይ ለመመሥከር ሳይሆን የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ለማክበር ሲሉ ብቻ ነበር። ነገር ግን ከሳሾቼ ምንም ማስረጃ ማቅረብ ስላልቻሉ ክሳቸውን ለማቆም ተገደዋል። ዳኛውም ለእኔ ፈርዶልኝ ፋይሉን ዘግቶታል። የእኔ አቋም በግልፅ የታወቀ በመሆኑ ከአሁን ቀደም ከብፁዕ አቡነ ማትያስና ከብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ጋር አሁንም ከብፁዕ አቡነ አብርሃም ጋር እናት ቤተክርስቲያኔን እያገለገልኩ ነው። ሃይማኖቴም የጠራ ነው። በመሆኑም «መናፍቅ» መባልን እምቢ ብያለሁ፥ ነፍሴ ትጸየፈዋለች። በመሆኑም ከአምስት ዓመታት በፊት ያወጣሁትን አቋሜን ዛሬም እነሆ እላችኋለሁ። እስከ ሞት ድረስም ያው ነው፥ አይለወጥም።
                                                                                    ኅዳር 1 ቀን 1998 ዓም
አቋሜ፣
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም «ጥንተ አብሶ» የሚባል ነገር ፈጽሞ የሌለባት፣ ከአባታችን ከአዳም በሰው ልጆች ሁሉ ላይ የወረደው የውርስ ኃጢአት እርሷን ግን በጭራሽ ያልነካት ያልደረሰባት፣ ይህም የሆነው የሰው ዘር ሳትሆን ቀርታ ወይም ልዩ ሰማያዊ ፍጡር ሆና ሳይሆን ከአባቷ ከቅዱስ ኤያቄምና ከእናቷ ከቅድስት ድንግል ሃና የተወለደች ሰማይና ምድርን ለፈጠረ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እናትነት አስቀድማ የተመረጠችና የታጨች በመሆኗ ለዚህ የመረጣት መንፈስ ቅዱስ ገና በእናቷ ማኅፀን ሳለች በዘር ይተላለፍ ወይም ይቆራኝ ከነበረው የውርስ ኃጢአት ጠብቋታል። እንዳይደርስባትም አንጽቷታል /ንፁህ አድርጓታል/። ምክንያቱም ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። ስለዚህም ከሴቶች ሁሉ የተለየች መሆኗን በቅዱስ ገብርኤል አብሳሪነት በቤተ መቅደስ እያለች ከሦስቱ አካላት አንዱን ወልድን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንስ ተነግሯታል። ተበስሮላታል። በዚያን ሰዓትም የመልአኩን ቃል በመቀበል «እንደ ቃልህ ይደረግልኝ» ስትል ብስራቱን ተቀብላለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።

እንግዲህ የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርቱ ከጥንት የመጣው የአባቶቻችንም ምስክርነቱ ዛሬ ደግሞ የእኔም እምነት ይሄ ነው። የማስተምረውም የምመሰክረውም ይህንኑ ነው። ይሁንና ዛሬ ዛሬ እንደሚሰማው «እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መንፈስ ቅዱስ አንጽቷተል ቀድሷታል» የሚለውን አባባል የግድ ከነጻች ኃጢአቱ ነበረባት ማለት ነው አለበለዚያ ከምን አነፃት? በሚል በማይገባ ስህተት ውስጥ ገብተው ይህንኑም በድፍረት የሚናገሩ ሰዎች አልታጡም። ምንም እንኳ መለኮታዊ ጥበብን በሰው ቋንቋ ለመግለጽ አስቸጋሪ ቢሆንም ለማነጻጸርም ቢያዳግትም ለእኛ በሚገባን መንገድ በቀላል ምሳሌ ለማስረዳት ያህል፦ አንድ ሰው ከመኪና ግጭት አደጋ ለጥቂት ድኗል። ታዲያ ይህን ሰው እግዚአብሔር አዳነው እግዚአብሔር ጠበቀው እንላለን። ሆኖም አድኖታል ጠብቆታል ስላልን የግድ ተገጭቶ ነበር የሚለውን ሃሳብ አያስከትልም። ሳይገጭ እግዚአብሔር ጠብቆታልና። ለመዳን ለመትረፍ መገጨት ወይም ለአደጋው መጋለጥ የግድ የለበትም ፈጦ ከመጣው አደጋ ሊሰወር ይችላልና። ጠበቀው አዳነው ማለት እንችላለን። ነገር ግን አዳነው ስለተባለ ጠበቀው ስለተባለ አለበለዚያ ከምን አዳነው ከምን ጠበቀው ስለደረሰበት ስለተገጨ አይደለም ወይ? ብሎ ማሰብ አለማስተዋል ካልሆነ በቀር ሌላ ሊሆን አይችልም። እንደዚሁም ሁሉ እመቤታችንን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከአዳም የውርስ ኃጢአት ጠበቃት፣ እንዳይደርስባት አነጻት ስለተባለ ብቻ ያነጸት ስለነበረባት ነው ብሎ ማመን መከራከር ለእኔ ኅሊናዬ የማይቀበለው ነገር ነው። ስለዚህ በትክክለኛው መልክ መሄድ ሲገባ አዲስ ሃሳብና አዲስ ፍልስፍና ማምጣት ትርፉ ውድቀት ነው። ከቶውንስ የፍልስፍና እናቱ መቸገር ነው ተብሎ የለ። ስለዚህ ለሁሉም የሚበጀው በእመቤታችን ላይ ምርምር ማካሄዱ ሳይሆን ይልቁንስ ለአሥራት ሀገሯ ለኢትዮጵያችን ሰላሙን በአማላጅነቷ እንድታወርድልን በረከቷ እንዲበዛልን ፍቅሯ እንዲጨምርልን መማፀን መለማመን እንጂ እግዚአብሔር ያከበራትን ለእናትነት የመረጣትን በማንና በምንም ምሳሌ የማይገኝላትን ንጽሕተ ንጹሐን፣ ቅድስተ ቅዱሳን በሆነች እናታችን ላይ ቃል መናገሩ አስተያየት መሰንዘሩ በራስ ላይ መልሶ ለመጣል ድንጋይ ማንሳት ነውና ከዚህ መቆጠብ ያስፈልጋል።

እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን።

10 comments:

Anonymous said...

የዲሲ ማርያም ካህናትንም መግለጫ ይህንን በመጫን ያንብቡ
http://www.dskmariam.org/upcom_Eve/DSKMARIAM%20Akuam%20Meglecha.pdf

Anonymous said...

ለሊቀ ኅሩየን ከፈለኝ ወልደ ጊዮርጊስ፡- ሰላመ እግዚአብሔር ከእርስዎ ጋር ይሁን፡ ከደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዳይሰጡ የተደረጉት ከጥንተ አብሶ ጋር በተገኛኘ ጉዳይ አልነበረም። በሌሎች ችግሮች እንጅ። ለምሳሌ ከሚከፈልዎ ደመወዝ ላይ ለመንግሥት ታክስ አልከፍልም በማልትዎ ችግር ተፈጥሮ እንደነበር ያስታዉሳሉ። ዛሬ በጥንተ አብሶ ጉዳይ ላይ ያልዎትን አቋም ማሳውቅዎ የሚያስመሰግን ነው። የሰው ልጅ የሚዳኘው በዛሬው ሕይወቱ እንጅ በነበር ሕይወቱ አይደለምና። የማርያም ካህናትም በጥንተ አብሶ ጉዳይ ያላቸውን ያላቸውን አቋም በድረ ገጻቸው ላይ አውጥተዋል። ዛሬ በጽሑፍዎ የማርያም ካህናት በጥንተ አብሶ ጉዳይ ችግር እንዳለባቸው አድርገው ማቅረብዎ እና እራስዎን ነጻ ለማድረግ መሞከርዎ ያሳዝናል። ጽድቅ የሚገኘው በራስ እምነትና ምግባር እንጅ በሌሎች እምነትና ምግባር አይደለም። በመሆኑም ሌሎች ምንም ይሁኑ ምን የራስዎን አቋም በወቅቱ ሁላችሁም ያመናችሁበትን ጽፋች ኋል፣ አሁን ደግሞ ያላችሁን አቋም አሳውቃችኋል። ስለዚህ እውነቱን ይናገሩ። እርስዎን ለማጽደቅ ሌሎችን አይኮንኑ። አክባሪዎ ንስሐ ልጅዎ

Anonymous said...

ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በርጥቡ . . .

ቀሲስ በረከትዎ ይድረስብኝና
አዳም ቅጠሏን ስለበላ የስጋ ሞት እስረኛ ሆነ እንላለን፤ ማርያም ከዚያ እዳ ነጻ ከሆነች ለምን በስጋዋ ሞተች? ልብ በሉ ቤተ ክርስቲያናችን አዳም ቅጠሏን ባይበላ ኖሮ አይሞትም ነበር ብላ ታስተምራለች። ማርያም የአዳም አበሳ ካልደረሰባት ለምን በስጋ ሞተች?
አሁን ግን በልቶም ልጁ(ማርያም) ከበደሉ ነጻ ሆነች ተባለ(አንድ ተፋልሶ)፤ ከዚያ ደግሞ ነጻ ብትሆንም በስጋ ግን ሞተች ተባለ(ሌላ ተፋልሶ)።
ማርያም ጌታችንን "ታዐብዮ ነፍስ ለእግዚአብሔር ወትትሐሰይ መንፈስየ በአምላኪየ ወመድሐኒየ . . ." (መድሐኒየ)ያለችው የአዳም አበሳ ከሌለባት መድሐኒት ለምን አስፈለጋት? ያልታመመ መድሐኒት ያስፈልገዋልን?
ማርያም ጥንተ-አብሶ አለባት ማለት እኮ ከሐጢአት መስራት ጋር አይያያዝም። ጥንተ-አብሶ ማለት እኮ ሞተ-ስጋ ነው፤ ይህ ደግሞ አዳም በሰራው ሐጢአት የመጣ ነው። በስጋዋ በሕሊናዋ በነፍሷ ሐጢአት የለባትም፤ ነገር ግን አዳም ስለመበደሉ ምክንያት እጣዋ በስጋ ከሚሞቱት ከሁሉም ሰው ወገን ነው፤ ልጇ ቢያስነሳትም። ቤተ ክርስቲያናችን ወደ እንደዚህ አይነት ተፋልሶ ውስጥ ከመግባት ከአሐት አብያተ ክርስቲያናት ነገሩን መርምራ መጓዝ ነበረባት። ይልቁን አወቁ የምንላቸው ሊቃውንቶቻችን ነገሩን ከምንፍቅና ጋር ከማያያዝ ተቆጥበው ባስተዋይነት ቢያደርጉት መልካም ነበር። ሌላው በጣም የምናከብራቸው መምህራን እየደጋገሙ "ካቶሊኮች ማርያምን ሐይለ-አርያማዊት ይሏታል" የሚሉት ከየት አግኝተውት ነው? ሐይለ-አርያማዊት ማለት(Immaculate Conception)ከሆነ እኛ ራሳችን አሁን እየተጓዝንበት ያለው መንገድ ራሱን ነው። በመሰረታዊው የክርስትና ትምህርት ላይ ተፋልሶ የማያስከትለው ትምህርት ግን ከላይ እንዳብራራሁት በግብጻውያን ኮፕቶች የተያዘው አቋም ነው ፤ እመቤታችን ራሷ ሐጢአት ያልሰራች ብትሆንም አዳም በሰራው ሐጢአት ግን ተሸንፋ ለሞተ-ስጋ ተሰጥታለች፤ በልጇ ሐይል ብትነሳም። ማርያም ከኛ ጉልላት ላይ የሸሸችው በዚህ እውቀት የሌለበትና ጭፍን ጥላቻ የተሞላበት(ሌላውን መናፍቅ ለማለት በሚቸኩል አንደበታችን)ጉዟችን ይሆንን? ወይ ግብጾች ትክክል ናቸው፤ አለበለዚያ እኛ ትክክል ነን። ማርያም ግን ከነሱ ጉልላት ተለይታ አታውቅም። እናንተ ታላላቅ መምህራኖቻችን ነገሩን በቶሎ መርምራችሁ ሰውን ከእንደዚህ አይነት ተፋልሶ ብታድኑት ጥሩ አይመስላችሁም?

ወደመልካሙ እሷው ትምራን።

Anonymous said...

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ እመቤታችን ማርያም ከአዳም በደል(አበሳ) ነጻ ከሆነች ጌታ መወለድ ለምን አስፈለገው? ምክንያቱም ማርያም ያለበደሏ በመሞቷ በበደሉ የሞተውን አዳምን መካስ ትችላለችና። ጌታ እኰ ስጋ ለብሶ የተወለደው ከአዳም ወገን እዳ(ከእጸ በለስ ፍሬ የተነሳ)የሌለበት ሰው ስለታጣ አይደለምን? አባቶች ሆይ እኔ ይህን ሁሉ የምጽፈው ማርያምን ስለማልወዳት ይሆንን? ማርያምንስ መውደድ በስጋ የሞተችበትን ምክንያት ባለመተንተን ይገለጻልን? እመቤታችን ግን በ3 አመቷ ቤተ መቅደስ ገባች በ15 አመቷ(የሴቶች ልማድ ሳይደርስባት) ጌታን ጸነሰች - መንፈስ ቅዱስ ጸለለባት። ከዚያ በሁዋላም ፍጽምናዋ እስከ እለተ-ሞቷ ዘለቀ - ጌታን ከጸነሰች በሁዋላ የሴቶች ልማድ አይደለም ሐልዮ ሐጢአት እንኳን አላገኛትም። ርቱዕና ትርጉም ያለው አረዳድ ይህ ይመስለኛል። በዚህም የምነቀፍ ከሆነ ይሁን - ግብጻዊ ኮፕት ኦርቶዶክስ እሆናለሁ።

የሚያሳዝነው በዘመነ ንስጥሮስ ጊዜ ጌታ/ሎቱ ስብሐትና/ "ሁለት ባሕርይ" መባሉን እቃወማለሁ የሚል አንድ አውጣኪ የሚባል መነኩሴ ነበር። ነገር ሳይመረምር በድፍን ለመቃወም "እንዲያውም ጌታ ከተወለደ በሁዋላ አምላክነቱ ሰውነቱን ውጦታል" ብሎ ሌላ ስሕተት ሰርቶ አረፈው። እኛም "ማርያም አታማልድም" ሲሉን በድፍን ተቃውሞ "እንዲያውም ማርያም የአዳም አበሳ አልደረሰባትም" ብለን ሌላ ተፋልሶ ውስጥ ክትት አልን። ለዚያ ይሆን ዛሬ ዛሬ "ኢየሱስ" ብሎ የሚናገር ሰው በሆነ ባልሆነው "ማርያም" ካላለ በጥርጣሬ አይን የሚታየው? ለመሆኑ ግን "ኢየሱስ" የሚለውን የጌታን ስም ለመጥራት ስንቶቻችንስ እንፈራዋለን? ግን እኮ "መድሐኒት" ማለት ነው። ግን ከአባ ጊዮርጊስ ለዛ እየራቅን አይደለምን? አብዛኛው ምዕመንስ(ራሴን ጨምሮ) "በምልጃ አመካኝቶ" ሐጢአቱን እየደራረበ ከስጋና ደሙ አልራቀምን? ስለቅዱሳን ምልጃ አይሰበክ ማለቴ ሳይሆን፣ ለምን በመጠን አይሆንም?

ኑፋቄን በጥበብ ያስወግዱታል እንጅ በድፍን ተቃውሞ ማስቀረት አይቻልም። የሚያሳዝነው ግን እኛ ጋር ነገር ሳይለዝብ በመክረሩ ምክንያት(ሰው በፍርሐት ምክንያት እንደልቡ ሐሳቦችን ባለማንሸራሸሩ) እኛም ደከምን፣ የእግዚአብሔር ቀኝም ከኛ ተለየች፣ ብዙዎችም በመመረር ወደመናፍቃን ጎራ ተቀላቀሉ።

ወንድሞች ሆይ ይህን የምለው ወድጄ አይደለም። ባለፈው ከአንድ ወዳጄ(የተከበረ ዲያቆን ነው) ጋር ስንወያይ ምክንያቱን ሳያስረዳኝ ነገሮችን ጠምዝዞ 'አንተ እንደነእንትና . . .' አለኝ። ቤተ ክርስቲያን የሚናደዱና 'እኔ እንከን የለብኝም' የሚሉ እንጅ ሐሳብ በማንሸራሸር የሚያምኑ ሰዎች ስለራቋት አዘንኩላት። ትውልዱ ደግሞ በጥበብ ካልሆነ በቅናት የሚመራ አይደለም። 'ቢቀርብኝስ . . .' አይነት ትውልድ ነውና!!!

For the Blogger,
Do you believe in the Power of Prayers? Do you think you will bring any difference by talking?
Why don't you organize a prayer day for our Church?
Everybody talks the sins of others, and nobody listens. What an awful chatter?

አቤቱ አስተዋይ አባት አድለን።

Anonymous said...

አቤት ትገርማላችሁ!! ፀሎቱና ፆሙ ቀርቶ እምብርታችሁ እስኪገለበጥ እየበላችሁ ስትጠግቡ ያለኃቅማችሁ የእመቤታችን ነገር መመርመር ጀመራቸሁ፣ አሁን የእናንተ ክርክር የሚያፀድቅ ይመስላችኋል? ምን አለ ይህን ክርክር ትታችሁ የፅድቅ ስራ ብትሰሩ? መልሱ ለጠፋችሁ አባ ጊወርጊስ ዘጋስጫን ጠይቁ ከመጽሐፈ ሚስጢር ላይ ጠቅሶ ይነግራችኋል፡፡
አይ ቤተ ክህነት ቤተ ትክነት ማለት ይሻላል!!!

Anonymous said...

[url=http://buyaccutaneorderpillsonline.com/#9641]accutane without prescription[/url] - buy accutane , http://buyaccutaneorderpillsonline.com/#2654 order accutane

Anonymous said...

[url=http://buyaccutaneorderpillsonline.com/#13754]order accutane[/url] - order accutane , http://buyaccutaneorderpillsonline.com/#4600 generic accutane

Anonymous said...

[url=http://buyaccutaneorderpillsonline.com/#5586]buy cheap accutane[/url] - buy accutane , http://buyaccutaneorderpillsonline.com/#2072 order accutane

Anonymous said...

[url=http://buyonlinelasixone.com/#3904]lasix no prescription[/url] - lasix online , http://buyonlinelasixone.com/#5659 lasix online without prescription

Anonymous said...

እንዲህ ላልከው ወንድም/እህት
"አዳም ቅጠሏን ስለበላ የስጋ ሞት እስረኛ ሆነ እንላለን፤ ማርያም ከዚያ እዳ ነጻ ከሆነች ለምን በስጋዋ ሞተች? ልብ በሉ ቤተ ክርስቲያናችን አዳም ቅጠሏን ባይበላ ኖሮ አይሞትም ነበር ብላ ታስተምራለች። ማርያም የአዳም አበሳ ካልደረሰባት ለምን በስጋ ሞተች?"

እንዴት እንደምታስብ ግራ ገባኝ ... እስኪ ይህን መልስልኝ

ክብር ይግባውና ጌታችን የሞተው ጥንተ አብሶ ስለነበረው ነው? !!!

ሰይጣን እውነትን እያስመሰለ ገደል እንዳከትህ !