Tuesday, November 15, 2011

ማኅበረ ቅዱሳንን ለምን ጠሉት??

 READ IN PDF
አባ ሰላማ በማለት በቅዱሳን ስም እየተጠራ ቅዱሳን መላእክትን፣ እመቤታችንን እና ጻድቃንን  የሚዘልፈው “አባ ሰላማ” የተሰኘው የተሐድሶ መናፍቃን ብሎግ፤ በማያፍር አንደበቱ ማኅበረ ቅዱሳንን በመሳደብ ላይ ይገኛል:: ማኅበረ ቅዱስንም “የቅዱሳኑ የስድብ በረከት ለእኔም ይድረሰኝ” በማለት ይመስለናል ለብሎጉ ምን ዓይነት መልስ ሰጥቶ አያውቅም::

“አባ ሰላማ” ብሎግ በ1992 ዓ/ም ከቤተ ክርስቲያ ተወግዘው የተለዩት የተሐድሶ መናፍቃን በድሬዳዋዎቹ ቡድን እንደሚመራ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ::

ይህ የመናፍቃኑ ብሎግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ማኅበረ ቅዱሳን ላይ በሬ ወለደ ዓይነት ወሬዎች ይዘግባል:: ሰሞኑን ከተዘገቡ የሐሰት ውንጀላዎች መካከል “ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤ አባላቱን በግድ ወርሃ ጽጌ እንዲጾሙ ያዛል” የሚል ነው:: በእርግጥ ዲያቢሎስ ጾም መች ይወዳል፤ የግብር ልጆቹ ቢቃወሙም አይደንቅም::  ወርሃ ጽጌን ብዙዎች ምእመናን እና ካህናት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስደቷን በማሰብ በፈቃድ እንደሚጾሙት የሚታወቅ ነው:: እንግዲህ አንዳንድ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችም በፈቃድ ይጾሙታል የሚል እምነት አለን::


በአጽዋማት ወቅት በሚሰበሰበው የቁርስ ዳቦ አማካኝነት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሌለባቸው አካባቢዎች ቤተ ክርስቲያን እንደተሰሩ ሰምተናል አይተናልም:: የሰንበት ትምህርት ቤተ አዳራሽ በሌለባቸው አጥቢያዎች ደግሞ የመማርያ አዳራሾች እንደተሰሩ የአይን ምስክሮች ሲናገሩ እንሰማለን:: ታድያ ተሐድሶዎቹ ከቁርስ ዳቦ በመሸጥ የተሰበሰበው ገንዘብ “በእኛ ኪስ ለምን አልገባም” ለማለት ይመስላል “አባ ሰላማ” ብሎግ አምርሮ ተቃውሞታል::

ለመሆኑ “አባ ሰላም” ብሎግ እና ሌሎች መሰሎቻቸው ማኅበረ ቅዱሳን ሚጠሉ ሰዎች እነ ማን ናቸው? ለምንስ ይጠሉታል? ብለን እንጠይቅ ይሆናል:: በአጠቃላይ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚጠሉ ሰዎች በሦስት ከፍለን እንያቸው::

፩. ማኅበረ ቅዱሳን በዓላማ እንዲጠፋ የሚፈልጉ:: እነዚህም:-
  •  ተሐድሶ መናፍቃን ( ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ)
  •    መናፍቃን የውጭ (“ጴንጤ”)
  •   አክራሪ እስላሞች 
እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ቡድኖች የማኅበሩን አገግሎት በደንብ ጠንቅቀው ያውቁታል:: እንዲሁም ዓላማውም በሚገባ ተረድተውታል። አክራሪው እስላም በቤተ ክርስቲያን ላይ በተለያዩ ጊዜያት የሚያደርሱት ጥፋት እየተከታተለ መረጃ እየሰበሰበ እኩይ ተግባራቸውን እያጋለጣቸው ስለሆነ፤ የማኅበሩን መኖር የእግር ላይ እሳታቸው ነው። ወደፊትም ላቀዱት ጥፋት ይከታተለናል ብለው ስለደመደሙ ማኅበሩ እንዲጠፋ ደፋ ቀና ሲሉ ይታያሉ:: ማኅበረ ቅዱሳን “ኢትዮጵያን የማስለም ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅፋት ሆኖብናል” ብለው በግልፅ በተለያዩ የእስልምና ፓል ቶክ ውይይት እየሰማናቸው ነው።

ሌሎቹ ሁለቱን የውስጥ(ተሐድሶ) እንዲሁም የውጭ መናፍቃን ግብራቸው እና ዓላማቸው ማኅበሩ በሚገባ አውቆት አጥብቆ እንደሚቃወማቸው ያውቃሉ:: ስለዚህ የተለያዩ አጋጣሚዎች በመጠቀም የማኅበረ ቅዱሳን ስም ሲያነሱት እናያቸዋለን:: ለዚሁም “አባ ሰላማ” ብሎግ ማየት በቂ ማስረጃ ነው:: ሁለቱንም የመናፍቃን ቡድን የተዋሕዶ እምነትን የማጥፋት ዘመቻቸው ማኅበረ ቅዱሳን እስካለ ድረስ ማስፈጸም አንችልም ብለው ስለወሰኑ፤ በማንኛውም መንገድ እንዲሁም ከአክራሪው እስላም ጋር በመተባበርም ቢሆን ማኅበሩን ሊያጠፉት ይፈልጋሉ።

፪.  በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለያዩ ጥቅማ ጥቅም የተሳሰሩ ሰዎች

ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ድረስ በጥቅማ ጥቅም የተሳሰሩ ቡድኖች ማኅበረ ቅዱሳንን ይጠሉታል የሚል እምነት አለን:: እነዚህኞቹ በጊዜአዊ ጥቅምና ሥልጣን የሰከሩ ናችው።እነ ወይዘሮ እጅጋየሁ እና ቡድኖቻቸውም እዚህ ቡድን ላይ መድበናቸዋል:: ማኅበሩን የሚጠሉበት ዓላማቸው ደግሞ ተግባራቸውን ሥለሚቃወም ነው:: እንዲሁም ደግሞ ያጋልጠናል ብለውም ይሰጋሉ:: የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ይከበር የሚለው ጥብቅ አቋሙ በተቃራኒው ይህን በማይፈልጉት ጥቅመኞ ማኅበሩን እንዲጠሉ አድርጓቸዋል:: ይኸው እነዚህ “ሆዳቸው አምላክ” የሆነባቸው ወገኖች ማኅበሩን ቢችሉ ለማፍረስ ነበረ፤ ነገር ግን ስላልቻሉ ስም የማጥፋት ዘመቻ ቀጥለውበታል::

፫.  የማኅበሩን አገልግሎትና ዓላማ ያልተረዱ ወገኖች

እነዚህ ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳንን በስም ብቻ ያውቁታል። የማኅበሩን ስም እንኳ የሰሙት ከተሐድሶ መናፍቃን፣ ከተለያዩ ሚድያዎች እንዲሁም ደግሞ ከአክራሪ እስላም ነው። እናም አንድ ጊዜ ብቻ የሰሙትን ወሬ ይዘው ማኅበረ ቅዱስንን ይጠሉታል። እንደው ማኅበረ ቅዱዳን ማን ነው?፤ ዓላማው ምንድ ነው? በቤተ ክርስቲያኒቱስ የትኛው መዋቅር ሥር ነው? ብሎ ለመጠየቅ ጆሮዋቸው የዘጉ አይጠፉም:: ነገር ግን ለመጠየቅ ተዘጋጅተው ምላሽ ለማግኘት አጋጣሚው ያላገኙ ወገኖች እንዳሉም እንገምታለን።

ማኅበረ ቅዱሳን አንዳንድ ለሚነሱ የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ምላሽ ቢሰጥ መልካም ነው እንላለን:: ሐሰት ተደጋግሞ ሲነገር እውነት ይሆናል እንደሚባለው ማኅበሩ በተመለከተ የሚወጡ የሐሰት ውንጀላዎች በተቃራኒ ማሰተባበያ ቢሰጥባቸው የሚል እምነት አለን::
እግዚአብሔር ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን።

23 comments:

Anonymous said...

betam tikikil neh !!!!!!

Anonymous said...

betam tikikil neh !!!!!!

Anonymous said...

betam tikikil neh !!!!!!

Haile Zemariam said...

I am a proud member of Mahebere Kedusan, but I will not say MK is a perfect association. I do believe people may make mistakes while doing something, which is natural! Why we always see the bad side of MK? What about other associations? Why only MK? “Mahebere Kedusan min aderege???” This article in Ahati Tewahido definitely answered my questions perfectly. But why do you believe MK should waste its precious time and human power to respond to these foolish insults? Leave alone a true Christian, anybody who believes in truth can see and judge the bad mentality of those brothers wasting time insulting others without their fault. Kedus Metsafes “awrew be Kedusan lay yesedeb neger yenager zend andebet tesetew” aydel yemilew? Ke MK belay Kedusan bemisedebubet blog MK min belo selerasu mels yest? Yediabilos andebet kemehon yetebeken! Amen.

Haile Zemariam

Dawit bekele said...

Wow, you are write, and MK keep the church under the God, we always promote mahibere kidusan.
Members of mahibere kidusan sometimes make amista so you have to accept as one associaton.
God bless Ethiopia

Anonymous said...

ማሀበረ ቅዱሳን ያባቶቸን ርስት አላስነጥቅም አለ እነርሱ ደግሞ በሁለት ቢላዋ መብላት ፈለጉ ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን በጉልበቱ በገንዘቡ በእውቀቱ ይረዳል እነርሱ ደግሞ ከቤተክርስቲያን ገንዘብን ይወስዳሉ የየዋሁን ምእመን ገንዘብ ይሰበስባሉ .....ታዲያ እነርሱ ያልጠሉት ማን ይጥላው

Anonymous said...

ሁሌም መልካም ነገር የሚሠራ ጠላቱ በቅርቡ ነው። እነዚህ ሰዎች ማኅበሩን ቢጠሉት እውነት አላቸው። ምክንያቱም ቤተክርስቲያኒቷን
አሳልፈው ለጠላት ቢሰጧት የሚያገኙትን ቱባ ዶላር፤ ሌት ተቀን ስለ ሃይማኖታቸው በሚያስቡ የቤተክርስቲያን ልጆች ቢመክንባቸው እንዴት አይጥሉት። ታዲያ ለሥጋዊ ድሎታቸው ሲሉ ዲያቢሎስ እንደሻቸው የሚጋልባቸው የግብር ልጆቹ ያልጠሉት ማን ይጥላው?

Anonymous said...

ሁሌም መልካም ነገር የሚሠራ ጠላቱ በቅርቡ ነው። እነዚህ ሰዎች ማኅበሩን ቢጠሉት እውነት አላቸው። ምክንያቱም ቤተክርስቲያኒቷን
አሳልፈው ለጠላት ቢሰጧት የሚያገኙትን ቱባ ዶላር፤ ሌት ተቀን ስለ ሃይማኖታቸው በሚያስቡ የቤተክርስቲያን ልጆች ቢመክንባቸው እንዴት አይጥሉት። ታዲያ ለሥጋዊ ድሎታቸው ሲሉ ዲያቢሎስ እንደሻቸው የሚጋልባቸው የግብር ልጆቹ ያልጠሉት ማን ይጥላው?

Anonymous said...

እግዚአብሄር ያበርታቸው፡፡ሁሌም ቢሆን ማህበረ ቅዱሳን ለቅድስት ቤ/ከ እውቀታቸውን፤ ጊዜያቸውን፤ጉልበታቸውን ሳይቆጥቡ ሲያገለግሉ ነው የማየው፡፡እግዚአብሄር ጽናቱን ይስጣቸው!

ezrabiruk said...

why do you believe MK should waste its precious time and human power to respond to these foolish insults? Leave alone a true Christian, anybody who believes in truth can see and judge the bad mentality of those brothers wasting time insulting others without their fault

hailemariam said...

betam assgerami new mahibere kidusan ahunm bekena afatagn mels endisetlin efeligalehu ene yegbi gubae temari negn tsom endntsom yemiyasgedid hig eskahun dires alayehum beki yehone timhirt eyeseten rasen awke betechrstiann lemagelgel korche endnesa eyaderegelgn ena eyaderegelin new yemigegnew

Anonymous said...

እግዚአብሄር ያበርታቸው፡፡ሁሌም ቢሆን ማህበረ ቅዱሳን ለቅድስት ቤ/ከ እውቀታቸውን፤ ጊዜያቸውን፤ጉልበታቸውን ሳይቆጥቡ ሲያገለግሉ ነው የማየው፡፡እግዚአብሄር ጽናቱን ይስጣቸው

Anonymous said...

tiru new bertu deje selam gin bearfln
I am proud member of MK

Anonymous said...

ማሀበረ ቅዱሳን ያባቶቸን ርስት አላስነጥቅም አለ እነርሱ ደግሞ በሁለት ቢላዋ መብላት ፈለጉ ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን በጉልበቱ በገንዘቡ በእውቀቱ ይረዳል እነርሱ ደግሞ ከቤተክርስቲያን ገንዘብን ይወስዳሉ የየዋሁን ምእመን ገንዘብ ይሰበስባሉ .....ታዲያ እነርሱ ያልጠሉት ማን ይጥላው

Anonymous said...

ማሀበረ ቅዱሳን ያባቶቸን ርስት አላስነጥቅም አለ እነርሱ ደግሞ በሁለት ቢላዋ መብላት ፈለጉ ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን በጉልበቱ በገንዘቡ በእውቀቱ ይረዳል እነርሱ ደግሞ ከቤተክርስቲያን ገንዘብን ይወስዳሉ የየዋሁን ምእመን ገንዘብ ይሰበስባሉ .....ታዲያ እነርሱ ያልጠሉት ማን ይጥላው

Anonymous said...

ማሀበረ ቅዱሳን ያባቶቸን ርስት አላስነጥቅም አለ እነርሱ ደግሞ በሁለት ቢላዋ መብላት ፈለጉ ማህበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን በጉልበቱ በገንዘቡ በእውቀቱ ይረዳል እነርሱ ደግሞ ከቤተክርስቲያን ገንዘብን ይወስዳሉ የየዋሁን ምእመን ገንዘብ ይሰበስባሉ .....ታዲያ እነርሱ ያልጠሉት ማን ይጥላው

Anonymous said...

እግዚአብሔር ልብ ይስጣቸው

Unknown said...

I wish we had more Mahiberat like MK.

Unknown said...

I wish we had more Mahiberat like MK.

Unknown said...

I wish we had more Mahiberat like MK.

offef said...

How about teaching us what the true picture of KD. The more people know the less they listen to the insult and false accusations and they will lead others to the truth

Ewnet ke menchu said...

ከዝርዝር ውስጥ ለሆዳቸው ያደሩ ተረስተዋል።እመብርሃን ትይላቸው።

Anonymous said...

እባካችሁ በእዉነት ቤተ ክርስቲያንን የምትወዱ ሁሉ MK ንም መዉደድ አለብን ለምን ብንል በሙሉ ጊዜዉና ገንዘቡ ከቤተ ክርስቲያን አልተለየም። tnbitu yifetsem zend gid newuna mengist be mengst hizb be hizb lay ... getachin tenagroal . le hulum egziabher wede melkam menged yimran amen.