Sunday, December 30, 2012

የኢትዮጵያ መንግሥት ዓላማውን ግልጽ አድርጓል፤ እኛም አውቀናል

 • የመንግሥት ደጋፊ የጡመራ መድረኮች “አስታራቂ ኮሚቴው” ላይ ዘምተዋል፤
 • ከጳጳሰቱ መካከል የዕርቁ እንቅፋት የሆኑት አባቶች በግልጽ ታውቀዋል፤ ስማቸውን ከማውጣታችን በፊት አሁንም ሐሳባቸውን ይቀይሩ እንደሆነ እንጠብቃቸዋለን፤
 • ጉዳዩን ያቀነባበሩት የአዲስ አበባው ልዑክ አባል የሆኑት ን/ዕድ ኤልያስ አብርሃ ናቸው ተብሏል፤
 • የአዲስ አበባው ልዑክ አባቶች ዲሲ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ከተጠሩ በኋላ ተገደው እንዲፈርሙ ተደርገዋል፤
PDF  ሙሉ ዘገባው የደጀ ሰላም ብሎግ ነው::
 በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ አልገባኹም በሚል ሰሞኑን መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ለዕርቁ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ የሄዱትን የሰላምና አንድነት ጉባኤውን አባል ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን አስሮ ወደ አሜሪካ ከላካቸው ወዲህ ለዕርቁ ያለው የተስፋ ደጅ መዘጋቱ እሙን ሆኗል። መንግሥት የዕርቁ ድርድር ለይስሙላ እንጂ “ከምር” እንዲሆን አልፈለገም ነበር።
ነገሩ ከምር ሲሆን ግን “የጭቃ ጅራፉን” መምዘዝ ይዟል። ለዲፕሎማሲ ይጠቅመኛል ብሎ የፈቀደው ዕርቅ መሰካት ሲጀምር ከዲፕሎማሲው ከማገኘው ትርፍ በሩን መዝጋት ይሻለኛል ያለ መስሏል። የራሱን ፓርቲ አባል በፓትርያርክነት ለማስቀመጥ በጠራራ ፀሐይ ወረራውን ቀጥሏል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ሊ/ካ ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁን በግድ ወደ አሜሪካ መለሳቸው

 •   Listen VOA Interview
 •     የኢትዮጵያ መንግስት ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን ከሀገር አባረራቸው
 •     ጉዳዩን ያቀነባበሩት የአዲስ አበባው ልዑክ አባል የሆኑት ን/ዕድ ኤልያስ አብርሃ ናቸው ተብሏል፤
   ዘገባውን የወሰድነው ከደጀ ሰላም ብሎግ ነው::
 በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ አልገባኹም በሚል ሰሞኑን መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ለዕርቁ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ የሄዱትን የሰላምና አንድነት ጉባኤውን አባል ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን አስሮ ወደ አሜሪካ መለሳቸው። እዚያው አስሮ ያላስቀራቸው አሜሪካዊ ዜግነት ስላላቸው ነው ተብሏል። ከእርሳቸው ጋር ለዚሁ ጉዳይ ወደ ኢትዮጵያ የሄደው የሰላምና አንድነት ጉባኤው ሌላ አባል ዲ/ን አንዱዓለም ዳግማዊ ስላለበት ሁኔታ አልታወቀም። ዝርዝሩን እንደደረሰልን እናቀርባለን። 
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።

Saturday, December 29, 2012

ዲ/ን አባይነህ ካሴ በ፲ኛ ዓመት የማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሥራ አመራር ጉባኤ አባል ሆነው አልተመረጡም::

ሐራ ዘተዋሕዶ የጡመራ መድረክ የቤተ ክርስቲያን ትልቁ አጀንዳ በመተው ግለሰብን በማግዘፍ/በማግነን ማኅበረ ቅዱሳንን በማኮምሸሽ  በተከታታይ ጡመራዎቹ  ላይ  አይተናል::  ይህ ሐራ ዘተዋሕዶ የጡመራ መድረክ  ከተሃድሶዎቹ ብሎጎች በተለየ ሁኔታ እና አቀራረብ ማኅበረ ቅዱሳንን በመተቸት “አገልግሎት” ጀምሮዋል::  በእርግጥ ለጡመራ መድረኩ መልስ የመስጠት ስልጣኑ የለንም::  ነገር ግን እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን ማኅበረ ቅዱሳን ለሚሰራቸው ሥራዎች በአይናችን አይተናል:: በጆሮዋችንም ሰምተናል:: ስለዚህ ለማኅበሩ በጎ ሥራ ምስክሮች ነን:: የማኅበሩ ክፍፍል በአይናችን ማየትም ሆነ  በጆሮዋችን መስማት አንፈልግም:: 

ሐራ ዘተዋሕዶ የተሰኘው የጡመራ መድረክ “በ፲ኛ ዓመት የማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ዲ/ን አባይነህ ካሴ የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጉባኤ አባል ሆኖ ተመርጦ ነበረ”  የሚል የፈጠራ/የሐሰት ዘገባ ስላየን  ዝም ብለን ማለፍ አልቻልንም:: በማኅበረ ቅዱሳን ፲ዓመት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ 17 አባላት ያሉት የሥራ አመራ ጉባኤ እንደተመረጡ በማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያዎች ላይ ተዘግቦ ነበረ::  ሙሉ ዘገባውን እኛም እዚሁ ብሎግ ላይ አቅርበነው  ነበረ::  ለማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጉባኤ አባላት ከተመረጡት  17ቱ አባላት ዝርዝር ውስጥ ዲ/ን አባይነህ ካሴ በጠቅላላ ጉባኤ አልተመረጡም ነበረ:: ነግር ግን የኢዲቶሪያል ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተመድበው ነበረ:: መረጃው እንደሚያሳየው የኢዲቶርያል ቦርድ ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር አሸናፊ በየነ ናቸው::

Tuesday, December 25, 2012

የ6ኛ ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴው “የተመረጠ” ሳይሆን “የተሰየመ” ነው

  ሙሉ ዘገባው የደጀ ሰላም ነው::
6ኛውን ፓትርያርክ ለማስመረጥ ተቋቁሟል የተባለው አስመራጭ ኮሚቴ በጥቆማ ስም ዝርዝራቸው የተበተነ እንጂ ብዙዎቹ ይስማሙበት ወይም አይስማሙበት እንዳልተጠየቁ ምንጮቻችን ገልጸዋልይህንን ተከትሎ ማኅበረ ቅዱሳን ምርጫው እንዲካሄድ በሾርኔ እንደተስማማ ተደርጎ በድረ ገጾች መዘገቡ አጀንዳው ከምርጫው ወደ ማኅበሩ እንዲዞር ለሚሹ ጥሩ አጋጣሚ ከመፍጠሩም በላይ ማኅበሩ ከቅ/ሲኖዶሱ ጋር ያለውን መልካም የሥራ ግንኙነት ለማጠልሸት ለሚፈልጉ ሰዎች አስደሳች አጋጣሚ እንደፈጠረ እየተነገረ ነው።

ዝርዝሩ እንደሚያመለክተው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስና ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ እንዲሁም ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መምሪያ ኃላፊዎች መካከል ደግሞ የሰበካ ጉባኤ መምሪያ ዋና ሓላፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ እና የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ዋና ሓላፊው መጋቤ ምስጢር ዓምደ ብርሃን ስማቸው ተጠቅሷል። ታላላቅ ገዳማት እና አድባራትን እንዲወክሉ የተደረጉት ፀባቴ አባ ኀይለ መስቀል ውቤ (የደብረ ሊባኖስ ገዳም አበምኔት) እና ንቡረ እድ አባ ዕዝራ (የአኵስም ጽዮን ንቡረ እድ) ሲሆኑ ዲያቆን ኄኖክ አሥራት - ከአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፤ አቶ ባያብል ሙላቴ ደግሞ ከማኅበረ ቅዱሳን የተሰየሙ ናቸው። አቶ ዓለማየሁ ተስፋዬ  (ከኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት)፣ ቀኝ አዝማች ኀይሉ ቃለ ወልድ እና አቶ ታቦር ገረሱ ደግሞ ምእመናንን ወክለው የተቀመጡ ናቸው፡፡

Monday, December 24, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ ፮ኛውን ፓትርያርያክ ለመምረጥ የወሰነውን ውሳኔ በድጋሜ እንዲያጤነው ጠየቀ

 •   ቤተክርስቲያን ስድስት ቦታ ብትከፈል አያገባኝም።” አቡነ ቀሌምንጦስ
 •  “ወነአምን በአሐቲ ቤተክርስቲያን” ማኅበረ ቅዱሳን
 •  ቅዱስ ሲኖዶስ ለእርቀ ሰላሙ ቅድሚያ የማይሰጥ ከሆነ ራሳችንን እናገላለን” በአሜሪካ የኢትዮጵያ አብያተክርስቲያናት ምእመናን
 •  ሐራ ተዋህዶ የተሰኘው የጡመራ መድረክ “ማኅበረቅዱሳን አቋሙን ለወጠ።” የሚለው መሰረተ ቢስ ዜና ግቡ ምን እንደሆነ እያነጋገረ ነው።
 •  “መንግሥት በካርድ ነው የሚመርጠው ፣ ስለዚህ መንግሥት ኃጥያተኛ ነው? እኛ ማን ሆነን ነው በዕጣ ካልሆነ የምንለው? ከመንግሥት እኛ እንበልጣለን?” አቡነ ጎርጎርዮስ 
ሙሉ ዘገባውን የወሰድነው ከአንድ አድርገን ብሎግ ነው:: TO READ IN PDF CLICK HERE
ባለፉት ሃያ ዓመታት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት በማበርከት በቅዱስ ሲኖዶስ እና በምእመናን ዘንድ ታማኚነት ያተረፈው ማኅበረ ቅዱሳን ከአቡነ ጳውሎስ እረፍት በኋላ የቤተክርስቲያን አንድነት ቅድሚያ በመስጠት ቅዱስ ሲኖዶስ ለእርቀ ሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲወያይ ለጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በደብዳቤ ማሳወቁ፣ በህትመትና ኤሌክትሮኒክስ ልሳኖቹ ማሳወቁ እንዲሁም የማኅበሩ አመራሮች አባቶችንና ምእመናን መደበኛ በሆኑና ባልሆኑ መንገዶች በማወያየት የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት መጣራቸው ይታወቃል።

Wednesday, October 10, 2012

ሰባት ጥንታዊ የዋሻ ቤተ መቅደሶች በቆጠር ገድራ ተገኙ

Kotere 03(ማኅበረ ቅዱሳን):- በጉራጌ ሀገረ ስብከት ቆጠር ገድራ በተሰኘ ስፍራ ጥንታዊ የዋሻ ቤተ መቅደስ እንደተገኘና የኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን እንደተተከለ ሰማን፡፡ ቦታው ድረስ ለመሄድ ወስነን የሚመለከታቸው የሀገረ ስብከቱ ሓላፊዎችን ለማግኘት ጥረት አደረግን፡፡ ተሳካልን፡፡ ከአዲስ አበባ ወልቂጤ ያደረግነው ጉዞ የተሳካ ነበር፡፡

ጉዞ ወደ ቆጠር ገድራ መካነ ቅዱሳን ኪዳነ ምሕረት ገዳም

ወደ ቆጠር ገድራ የተጓዝነው መስከረም 14 ቀን 2004 ዓ.ም. ነው፡፡ ወቅቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በተለይም በጉራጌ ብሔረሰብ ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት አንዱ የሆነው የመስቀል በዓል ሲሆን ዋዜማ በመሆኑ ተወላጁ ከተለያየ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም ከአዲስ አበባ እና በሚያስገርም ሁኔታ እየጎረፈ ነው፡፡ “መንገዶች ሁሉ ወደ ጉራጌ አገር ያደርሳሉ” የሚል አስኝቶታል፡፡ የግልና የሕዝብ ማመላላሻ አውቶቡሶች መንገዱ ጠቧቸዋል፡፡ በተለይም ወልቂጤን ይዞ ሌሎችም የገጠር ከተሞች ለየት ባለ የትራፊክ መጨናነቅ ላይ ናቸው፡፡

Friday, September 28, 2012

መጪውን ጊዜ በሃይማኖት “ብሔርተኝነት” መዋጀት

(ማኅበረ ቅዱሳን):-ጊዜ ይመጣል ጊዜ ይሄዳል፡፡ ጊዜ መጥቶ ሲሄድ ግን እንደው ዝም ብሎ አይደለም፡፡ የጊዜውን አሻራ አሳርፎ ነው፡፡ አሻራው ግን አዎንታዊም አሉታዊም ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ምርጫው በጊዜ መጠነ ክበብ ውስጥ ያለው የሰው ልጅ ነው፡፡

የሰው ልጅ ደግሞ በጊዜያት ውስጥ የረቀቀና የገዘፈ ዓለም ባለቤት ሆኖ የተፈጠረና ጊዜ የማይቆጠሩላቸው የሥሉስ ቅዱስ ፍጡር ነው፡፡ በሕያውነቱ ረቂቁን ዓለም- ዓለመ ነፍስን መስሎና ሆኖ ሲኖር፤ በምድራዊነቱ ግዙፉን ዓለም- ዓለመ ሥጋን በተዋሕዶ ነፍስ መስሎና ሆኖ ይኖራል፡፡ በዚህም የሁለት ዓለም ባለቤት ነው፡፡ የሰማያዊና ምድራዊ ወይም የመንፈሳዊና ዓለማዊ፡፡

እንዲህ ሆኖ ሲፈጠር በነጻ ምርጫው እንዲኖር የሚያስችለው ነጻ አእምሮ የተቸረው ብቻ ሳይሆን የምርጫውን ተገቢነትና ትክክለኛነት የሚያረጋግጥበት አእምሮ የተሰጠውም ባለጸጋ ፍጡር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

Thursday, September 13, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ(የማኅበሩ የሥራ አመራር ጉባኤ ሥም ዝርዝር)

ሪፖርታዥ

TAKLL2004 534(ማኅበረ ቅዱሳን):-የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ የመምሪያ ሓላፊዎች፤ ቀሳውስትና ካህናት፤ የፌደራል ጉዳዮች የሃይማኖት ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም.በድምቀት ተጀመረ፡፡


ነሐሴ 29 ቀን 2004 ዓ.ም.

በዋዜማው ነሐሴ 29 ቀን 2004 ዓ.ም. ከቀኑ ስድስት ስዓት ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ የማኅበሩ አባላት ማኅበሩ እያስገነባው በሚገኘው ሕንጻ ውስጥ በመገኘት የሕንጻው ግንባታና በማኅበሩ የአንዳንድ አገልግሎት ክፍሎችን እንቅስቃሴ በመጎብኘት ማብራሪያ እየተሰጣቸው ቆይተዋል፡፡ ከምሽቱ 12፤00 ስዓት ጀምሮ የጠቅላላ ጉባኤው አስተባባሪ ኮሚቴ ባዘጋጀው ትራንስፖርት ከማኅበሩ ዋናው ማእከል አቧሬ ወደሚገኘው አቡነ ጎርጎርዮስ የትምህርትና ሥልጠና ማእከል በመጓዝ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት፤ የመርሐ ግብር ትውውቅ፤ ሕጽበተ እግርና የእራት መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡

Tuesday, September 4, 2012

ቅዱስ ሲኖዶስ ሱባኤ አወጀ

 • ሱባኤው 
  ከጳጉሜን 1/ 2004 - 
  መስከረም 10/ 
  2005 ዓ.ም ድረስ ነው።
 • ቅ/ሲኖዶሱ የአስታራቂ ኮሚቴውን ሪፖርት አዳምጧል::
 • ሦስት የአስታራቂ ኮሚቴው አባላት አዲስ አበባ ናቸው::
 • ቅ/ሲኖዶሱ አካሄዱን ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ቡድኖችን እንደማይታገሥ አስታውቋል::
ሙሉ ዘገባው የደጀሰላም ብሎግ ነው::
 READTHIS NEWS IN PDF
  ቅዱስ ሲኖዶስ መጪው ዘመን ቤተ ክርስቲያናችን ሰላሟንና አንድነቷን የምታረጋግጥበት፣ ዐበይት ተቋማዊ ችግሮቿን በመፍታት ለአገራችንና ለመላው ዓለም ሐዋርያዊ አገልግሎቷን የምታጠናክርበት ይኾን ዘንድ ካህናትና ምእመናን በአንድነት ወደ እግዚአብሔር የሚያመለክቱበትና ከጳጉሜን 1/2004 - መስከረም 10/2005 ዓ.ም የሚቆይ የሱባኤ ጊዜ ማወጁ ታወቀ፡፡ የሱባኤ ጊዜ እንዲታወጅ የተወሰነው ቅዱስ ሲኖዶሱ ትናንት፣ ነሐሴ 28 ቀን 2004 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ሲሆን ዛሬ ማክሰኞ ባደረገው ስብሰባም ቀናቱን ይፋ አድርጓል። (ዝርዝሩን እንደደረሰልን ለማቅረብ እንሞክራለን።) ሱባኤውን የተመለከተ መግለጫ በተከታዮቹ ቀናት በቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊው በኩል እንደሚሰጥም ተመልክቶ ነበር፡፡ በመንፈሳዊው ትውፊታችን እንደቆየን ወደ አዲሱ ዘመን የምንሸጋገርባትና እንደ 13ኛ ወር የምትቆጠረው ጳጉሜን በበርካታ ክርስቲያኖች ዘንድ የፈቃድ ጾም የሚያዝባት ወቅት እንደኾነች ይታወቃል፡፡

Friday, August 31, 2012

ቤተ ክርስቲያንና የፓትርያርክ ምርጫ (ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ)

ቤተ ክርስቲያን አንዲት፣ ቅድስት፣ ኩላዊትና ሐዋርያዊት መሆኗን ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያን ሁሉ ይቀበላሉ፤ በመሠረተ እምነታቸው ውስጥም አካትተው በጸሎትና በአስተምህሮ ይጠቀሙበታል፡፡የዚህ መሠረታዊ ምክንያቱ ደግሞ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ይህ ትምህርት ቢኖርም ነገር ግን መልእክቱን በአግባቡ ካለመረዳት የተነሣ እነ አርዮስና መቅዶንዮስ
በትውፊት ከሐዋርያት ጀምሮ የመጣውን የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ መሠረት መቀበልን ቸል ብለው በራሳቸው መንገድ ሔደው ስለሳቱ በጉባኤ ኒቅያ በማያሻማ መንገድ ቤተ ክርስቲያን አንዲት፣ቅድስት፣ ሐዋርያዊት እና ኩላዊት መሆኗን አስቀመጡ፡፡ በኋላ በጉባኤ ቁስጥንጥንያ ደግሞ ሁላችንም እንድንጸልይበት በተዘጋጀው አንቀጸ ሃይማኖት ላይ (ጸሎተ ሃይማኖት) ‹‹ ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት›› የሚለው የጸሎታችን መፈጸሚያ እንዲሆን ተደነገገ፡፡ በዚህም መሠረት እነዚህን ዓለም አቀፍ ጉባኤያት የሚቀበሉ ሁሉ የሚቀበሉትና የሚመሩበት መሠረታዊ ትምህርተ ሃይማኖት /doctrine/ ሆነ፡፡

‹‹የጎንደር ምንቸት ውጣ … የትግሬ ምንቸት ግባ›› በቤተ ክህነት (ነመራ ዋቀዮ ቶላ )

ይህ የቤተ ክክነታችን ችግር እውነታን የዳሰሰ ጡመራ የዛሬ አራት ዓመት አካባቢ ደጀ ሰላም ብሎግ አስነብባን ነበረ:: አሁንም በተለምዶ ስደተኛ ሲኖዶስ እየተባለ የሚጠራው ቡድን “መንበሩ ለእኔ ይገባኛል” እያለ ነው::ስደተኛው ሲኖዶስ የመሰረቱት በስደት ላይ ያሉት የጎንደር ተወላጅ የሆኑት ብፁዓን  አበው “በትግሬዎቹ/በወያኔ ተገፍተን መንበራችን ተቀማን” እያሉ ለ20 ዓመታት ያህል ምእመናን ሲያምሱ ኖረዋል:: በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያኒቷ በፍቅር መስፋፋት ሲገባት በውጩ ዓለም በጥላቻ እና በጎጠኝነት ለቁጥር በሚያስቸግር ሁኔታ ተከፋፍላለች:: እውነት የጎደሬዎቹ ወደ መንበር መምጣት የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር ይፈታ ይሆን??? አሐቲ ተዋሕዶ በአባቶች መካከል የተፈጠረው መከፋፈል አጥብቃ ትቃወማለች:: ጎጠኝነትን ግን ታወግዛለች::  በስደት ላይ የሚገኙት ብፁዓን አባቶች ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ታርቀው ወደ አገራችው እንዲመለሱም እንፈልጋለን:: የአባቶች መታረቅ የሚመጣው ግን እውነታዎች ሳይደባበቁ በግልጽ አውጥተው ሲነጋገሩ ብቻ ነው ብላ አሐቲ ተዋሕዶ ታምናለች:: የሚከተለውን የነመራ ዋቀዮ ቶላ ጽሑፍ አንብቡት:: መልካም ንባብ::
+++
የቤተ ክርስቲያን ነገር እንዲህ ‹‹አነሰ ሲሉት ተቀነሰ›› እየሆነ፣ እንዲመሯት የተሾሙት አበው እንዲህ ከጎረምሳ ባላነሰ እልኸኝነትና ማን አለብኝ ባይነት ሲመላለሱ ነገሩ ሁሉ ብዙዎችን ግራ እንዳጋባ አለ፡፡ ይህ ዛሬ በቤተ ክርስቲያንና በሃይማኖት ስም የሚፈጸመውን ታሪክ-ይቅር-የማይለው-ድርጊት ለመቃወም ብዕሬን በድጋሚ ለማንሳት ወደድኹ፡፡ አስቀድሜ የቀድሞው 4ኛው ፓትርያርክ ሲመቱን እንዳይፈጽሙ ከሚጠይቋቸው ጋር ለመደመር አንዲት የተማጽኖ ደብዳቤ አቅርቤ ስለነበረ ነው ይህን ‹‹በድጋሚ›› ያልኩት፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ ‹‹በእውነቱ ይህ ሁሉ ቱማታ ለኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በማሰብ ነውን? ወይስ ከጀርባው ሌላ ምክንያት አለው›› የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ መሞከር ነው፡፡

Wednesday, August 29, 2012

"የፓትርያርክ ምርጫ ታሪክና አፈጻጸም በኮፕት ቤተ ክርስቲያን" ከወልደ ማርያም

 ከማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል ድረ ገጽ የወሰድነው  ዘገባ ነው::
የዚህ አጭር ጽሑፍ ዋና ዓላማ በትምህርተ ሃይማኖትና ከሞላ ጎደል በሥርዓተ እምነት ከሚመስሉን አኀት አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ የሆነችው የኮፕት ቤተ ክርስቲያን በ2000 ዘመን ታሪኳ የሚመሯትን ፓትርያርኮች እየመረጠች የሄደችበትን ቀኖና ታሪክና ሥልት ጠቅለል ባለ መልኩ ማቅረብ ነው፡፡ ከሌሎቹ አኀት አብያተ ክርስቲያናት የኮፕት ቤተ ክርስቲያንን የምርጫ ቀኖናና ሂደት ዳስሰን ለማቅረብ የፈለግንበት ምክንያት የቤተ ክርስቲያኗ መንበረ ፕትርክና ለ1600 ዘመናት የቤተ ክርስያናችንም መንበረ ፕትርክና ሆኖ የቆየ ከመሆኑ አንጻር በጽሑፉ የሚወሳው ታሪክ የሚቀርበን በመሆኑ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ መንበረ ፕትርክናዋ በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ወንጌላዊው ማርቆስ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በድምሩ 117 ፓትርያርኮችን እየመረጠች አስቀምጣለች፡፡ ፓትርያርኮቹም የተቀበሉትን ሰማያዊ ሓላፊነት በመያዝ ቤተ ክርስቲያኗ ክፉውንና ደጉን ዘመን አልፋ ዛሬ ካለችበት ደረጃ እንድትደርስ አድርገዋታል፡፡ አሁን ባለችበት ሁኔታ ቤተ ክርስቲያኗ በግብጽና በመላው ዓለም ከ15 እስከ 18 ሚልዮን የሚደርሱ ምእመናን ያሏት ሲሆን እነዚህንም ምእመናን በእረኝነት የሚጠብቁ ከ150 በላይ ሊቃነ ጳጳሳት አሏት፡፡ እነዚህ ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ፕትርክናው ማእከላዊ አስተዳደር በሚመሩ 54 ያኽል አኅጉረ ስብከት በሊቃነ ጳጳስነት ተመድበው ያገለግላሉ፡፡ ከእነዚህ አኅጉረ ስብከት 15 የሚሆኑት ከግብጽ ውጪ በተለያዩ ክፍላተ ዓለም ተቋቁመው በማገልገል ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡

የዋልድባ አብረንታንት መነኰሳት መሰደድ ጀምረዋል

 • ባለፉት ጥቂት ቀናት ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት ተሰደዋል
 • “ታጋይ ገድላችኹ እናንተ አትኖሩም” (የፀለምት - ማይ ፀብሪ ወረዳ ሓላፊዎች)።
  ደጀ ሰላም የወሰድነው ዘገባ ነው::
READ THIS NEWS IN PDF  በዋልድባ አብረንታንት ገዳም መነኰሳት ላይ ባተኰረውና ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ እየተባባሰ በቀጠለው እስርና እንግልት ሳቢያ ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት የፀለምት - ማይ ፀብሪ የፀጥታ ኀይሎች በሚያደርሱባቸው ግፍ ሳቢያ ወደ ሌሎች ገዳማት መሰደዳቸውን፣ በተቀሩትም አባቶች ላይ ድብደባ እየተፈጸመባቸው መኾኑን የሥፍራው ምንጮች እየገለጹ ናቸው፡፡
የዜናው ምንጮች እንደሚያስረዱት÷ የወረዳው ፖሊሶችና ታጣቂዎች በገዳሙ መነኰሳት ላይ የሚፈጽሙት እንግልትና ድብደባ የተባባሰው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ኅልፈተ ሕይወት መሰማቱን ተከትሎ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽኑ ሕመም እና ኅልፈት ገዳማውያኑን ተጠያቂ በማድረግ ነው፡፡ ቀደም ሲል በየጊዜው እየታሰሩ በተለቀቁት አበው መነኰሳት ላይ ያነጣጠረው ይኸው ርምጃ በአሁኑ ወቅት ደግሞ መነኰሳቱ ጨርሶ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ከማዘዝና ከማስገደድ ጋራ የተያያዘ መኾኑም ተመልክቷል፡፡

Monday, August 27, 2012

“ዘይሁብ መርሐ ርቱዐ ለቤተ ክርስቲያን - ለቤተ ክርስቲያን ቅን መሪ የሚሰጥ”(ጸሎተ ኪዳን - ዘሠርክ)

ቤተ ክርስቲያን የምንላት ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስ ከፍጹምና ከማይነገር ፍቅሩ የተነሣ ሰው እስከ መሆን፣ ሰው ሆኖም በዚህ ዓለም ከኃጢአት በስተቀር እንደ ሰው መኖርን፣ ከዚያም በቀራንዮ ቅዱስ ሥጋውን እስኪቆርስላትና ክቡር ደሙን እስኪያፈስላት ድረስ የደረሰላትና የመሠረታት የምእመናን አንድነት (ጉባኤ) ናት፡፡ "ወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላእለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያት" የምንለው ለዚህ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን በወንጌል መሠረትነት በኢየሱስ ክርስቶስ ራስነት በምእመናን አካልነት የተመሠረተች ጉባኤ ናት፡፡

ቤተ ክርስቲያን ስንል የዚህ ዓለም ተጋድሏቸውን በድል አጠናቅቀው ወደ እግዚአብሔር የሄዱ ቅዱሳን (ሐዋርያት፣ ሰማዕታት፣ ሊቃውንት፣ ...) እና ገና በዚህ ዓለም በተጋድሎ ላይ ያሉት የምእመናን አንድነት (ጉባኤ) ናት፡፡ በሰማይ ያለችው ቤተ ክርስቲያን (ጉባኤ) የዚህ ዓለም ጣጣቸውን ጨርሰው የሄዱ፣ ድል አድርገው የድል አክሊላቸውን ለመቀበል እርሱ የወሰነውን ጊዜ የሚጠባበቁ ቅዱሳን ኅብረት ስለሆነች አትናወጽም፤ ስለሆነም ሊቃውንት ይህችን ቤተ ክርስቲያን ድል አድራጊዋ ቤተ ክርስቲያን (Church Triumphant) ይሏታል፡፡ ገና በዚህ ዓለም በጉዞና በፈተና ላይ ያለችውን የአንዲቷ ቤተ ክርስቲያን አካል የሆነችውን ጉባኤ (ቤተ ክርስቲያን) ደግሞ ገና በተጋድሎ ላይ ያለች ቤተ ክርስቲያን (Church Militant) ይሏታል፡፡

Tuesday, August 21, 2012

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ መለስ ዜናዊ በ57 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዪ

ዛሬ ማለዳ ነሐሴ 15፣2004ዓ/ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን  የጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ አድርጓል::

የጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ነፍስ እግዚአብሔር አምላክ ከደጋጎች አባቶቻችን ጎን ያኑር::

Monday, August 20, 2012

ቀጣዩን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ አስመልክቶ ምን ይደረግ?

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ስርዓተ ቀብር በኃላ ምን ይደረግ?  
ድምጽ ከመስጠት በፊት ሊገናዘቡ የሚገባቸው ነጥቦች
1. የፓትሪያሪክ ምርጫን አስመልክቶ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 13፡5 ላይ እንደተጠቀሰው በፓትርያርክ ምርጫ ላይ የሚሳተፉት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ፣ የየመምሪያና ድርጅት ሓላፊዎች፣ የጥንታውያን ገዳማት አበምኔቶች የአድባራት አስተዳዳሪዎች ከየሀገረ ስብከቱ ሰበካ ጉባኤያት በዕድሜ ከሠላሳ ዓመት ያላነሱ የካህናትና የምእመናን ተወካዮች እንዲሁም ዕድሜያቸው 22 አስከ 30 ዓመት የሆኑ የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች ሲሆኑ በጠቅላላው በሰበካ ጉባኤው የሚወከሉት ከአንድ ሀገረ ስብከት አሥራ ሁለት ሆነው በሥጋ ወደሙ የተወሰኑ በሕገ ቤተ ክርስቲያን የጸኑ መሆን አለባቸው ይላል፡፡ ከዚህ በፊቱ እንደተደረገው ፓትሪያሪክ የሚሆነውን ለመወሰን የመጨረሻ ወሳኝ አካላት እነዚህ ከሆኑ ቤተክርስቲያን ላለፉት 20 ዓመታት ካየችው መከራ የከፋ እንደማይገጥማት እርግጠኛ መሆን አይቻልም የሚሉ ወገኖች መኖራቸው፡፡

2. ምንም እንኳን በምርጫ የሚሳተፉ የተዘረዘረ ቢሆንም የአመራረጥ ሥርዓቱን አስመልክቶ ሕገ ቤተ ክርስቲያን የምርጫው አፈጻጸም ቅዱስ ሲኖዶስ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ይሆናል ስለሚል ለእጩነት ከሚቀርቡት ሊቃነ ጳጳሳት 3 ወይም 5 ሊቃነ ጳጳሳት የመምረጥ (ነቀፋ እንደሌለባቸው የማጥራት) ድርሻ ከላይ የተጠቀሱት መሆን ያለበት ሲሆን ከ 3 ወይም 5 ሊቃነ ጳጳሳት የመምረጥ ድርሻ ግን የመንፈስ ቅዱስ ድርሻ መሆን አለበት የሚሉ ወገኖች መኖራቸው፡፡ ፓትሪያሪክን ለመምረጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትውፊትን መሠረት አድርጎ በዕጣ ከመሆን ይልቅ በድምጽ ብልጫ መሆኑ የእግዚአብሔር ፈቃድ የራቀው የሰው ሃሳብ የቀረበው ይሆናል ፤ አጽራረ ቤተክርስቲያንም ሆኑ መንግስትም እጁ እንዲኖርበት መንገድ ይከፍታል የሚል ስጋት አለ፡፡

3. ሐዋርያት የይሁዳን ምትክ ቶማስን የመረጡት በዕጣ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ያረጋግጥልናል፡፡ “ዕጣም ተጣጣሉላቸው፥ ዕጣውም ለማትያስ ወደቀና ከአሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቈጠረ” የሐዋርያት ሥራ 1: 26:: በሐዋርያት መንበር የሚቀመጡ ፓትሪያሪኮችም ከዚህ የተለየ አመራረጥ ሊኖራቸው አይገባም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ ነው የሚመራው እንድንል፣ መንፈስ ቅዱስ የመረጠው ሊቀመጥበት ይገባልና፡፡ ለዚህም የእህት አቢያተ ክርስቲያናትን ተሞክሮ መውሰድ በቅርቡ በግብጽ የሆነውን መመልከት ይገባናል፡፡ በተለይም ጾም እና ጸሎት ታውጆ ሱባኤ ተይዞ ሊሆን ይገባል፡፡ ዕጣውም ከማጭበርበር እንዲርቅ በግልጽ በዐውደ ምሕረት የተጠቀለለ እና ነፍስ በማያውቅ ሕጻን የሚወጣ ሊሆን ይገባዋል የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡

4. ላለፉት ሃያ ዓመታት ቤተ ክርስቲያን ሁለት ፓትሪያሪክ እየተባለ ለሁለት ተከፍላ ፤ በመወጋገዝ እና ሁለት የተለያየ ሹመት በማድረግ ምዕመናን ሲያዝኑ ቆይተዋል፡፡ የተፈጠረውን ችግር ሁለቱም ወገን የየራሳቸው ትክክለኛነትን የሚያጎላ ምክንያት የሚያቀርቡ እንጂ መስዋዕት በመሆን መፍትሔ የሚያመጡ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡ ለዚህ መፍትሔ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ ቀርባላች እና የወደፊቱን አቅጣጫ ማስተካከል የሚገባበት ወቅት አሁን መሆን አለበት የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ ለዚህም ችግሩን ለመፍታት ዋነኛ ችግር የነበረው ከሁለቱ ፓትሪያሪክ ማን ይመራል የሚለው ነበር፡፡ ስለዚህ ይህንን ዘርፈ ብዙ የቤተ ክርስቲያን ችግር መፍትሔ ለመስጠት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስን ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ጥያቄ ማቅረብ አሊያም ወደ እግዚአብሔር ተጠርተው እስኪሔዱ ድረስ ሌላ ፓትሪያሪክ አለመሾም የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡
 ዐውደ ምሕረት የተዋሕዶያውያን የመረጃ መረብን ይጎብኙ::
 ድምጽ ለመስጠት እዚህ ላይ ይጫኑ::

How Do Copitic Orthodox Christians Elect A New Pope? " ግብጻውያን አዲስ ፓትርያርክ እንዴት ነው የሚመርጡት"?

ሰበር ዜና:- ቅዱስ ሲኖዶስ አቃቤ መንበር ሰየመ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚመራ አቃቤ መንበር ሰየመ፡፡ በዚህም መሠረት ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቃቤ መንበር ሆነው የተሾሙ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ፓትርያርክ እስኪመርጥ ድረስ ቤተ ክርስቲያንን በበላይነት ይመራሉ፡፡ 

 ዘገባውን ያገኘነው ከማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል ድረ ገጽ ላይ ነው::

How Do Coptic Orthodox Christians Elect A New Pope? " ግብጻውያን አዲስ ፓትርያርክ እንዴት ነው የሚመርጡት"?

Statute on the Patriarch Election Decree of the President of the Republic for the year 1957 on the endorsement of the statute on the nomination and election of a patriarch of the Coptic Orthodox Christians President of the Republic, Reading Decree 37 of the year 1942 on the endorsement of nomination and election of patriarch for the Coptic Orthodox Christians, amended by Decree 33 of the year 1946, In accordance with the Council of State, Decided:
 Article 1: The statute on the nomination and election of patriarch for the Coptic Orthodox Christians in agreement with the herein decree.
 Article 2: The abovementioned Decrees 37 of the year 1942 and 33 of the year 1946 shall be abrogated.
 Article 3: The minister of the interior shall enforce that decree, to be effective as of the date of publishing in the official gazette. Draft Statute on the Nomination and Election of Patriarch for Coptic Orthodox Christians Chapter I On the Election of Acting Patriarch

 Article 1: If the patriarch’s position became vacant due to the occupant’s death or any other reason, the Holy Synod and the Millī Council shall be convened upon the call of the bishop who is the oldest to have been ordained and under his chairmanship within a span of time that not more than seven days since the date of vacancy in order to select a bishop to be the acting patriarch. A republican decree shall be issued to appoint the acting patriarch to undertake running the affairs of the patriarchate in accordance with the church law and traditions and active rules pending the official appointment of a patriarch. Chapter II On the nomination for the patriarchic chair.

Friday, August 17, 2012

የተቻኮለ የፓትርያርክ ምርጫ፣ ““የገበያ ግርግር …” ይሆናል

“ቤተ ክርስቲያናችን አዲስ ፓትርያርክ ከመምረጧ አስቀድሞ አሁን ከገባችበት ዝብርቅርቅ ሁናቴ ለማገገም፣ ከሐዘኗም ለመጽናናት እና አሠራሯን በሥርዓተ አበው መሠረት ለማከናወን ጊዜ ያስፈልጋታል።”
ዘገባውን የወሰድነው   ከየደጀ ሰላም ብሎግ ነው::
ቅዱስ ፓትርያርኩ እነሆ አረፉ። በብዙ እሰጥ አገባዎች የተሞላው ዘመነ ፕትርክናቸው አሁን ሌላ እሰጥ አገባ ሊፈጥር እነሆ ተፈጠመ። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደቆመች ናት። ይህንን የፕትርክና ምርጫ በሰላማዊና ክርስቲያናዊ መንገድ ማካሔድ ከቻለች ብሩህ ዘመን፣ አልያም ደግሞ በግርግር እና በጥቅመኞች ፍላጎት በሚመራ አሠራር ከተከናወነም ሌላ የመከራ ዘመን ሊጠብቃት ይችላል።

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ አስከሬን ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት መቃብር ጎን ያርፋል

  ሙሉ ዘገባው የደጀ ሰላም ነው:: 

 READ THIS NEWS IN PDF 

 • የቀብር ሥነ ሥርዐቱ ነሐሴ 17 ቀን በ6፡00 በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይከናወናል
 • የቅዱስነታቸው አስከሬን ነሐሴ 16 ቀን ወደ ካቴድራሉ የሚያመራው መንግሥት በሚመድበው ሠረገላ ነው
 • የመንግሥት፣ የአኀት አብያተ ክርስቲያንና የዓለም አብያተ ክርስቲያን ተወካዮች ይገኛሉ    
  


 የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባኤ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የቀብር ሥነ ሥርዐት÷ ኀሙስ፣ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም (August 23/2012) ከቀኑ በ6፡00 በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲከናወን ወሰነ፡፡

Thursday, August 16, 2012

ሕገ ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱስ ፓትርያርክ ምርጫ ምን ይላል???

ምዕራፍ አራት
የኢትዮጵያ ፓትርያርክ
 
አንቀጽ 13
 • ስለ ቅዱስ ፓትርያርክ ምርጫ
1.    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ ቀኖና በሚፈቅደው መሠረት ተመርጦ ይሾማል፡፡
2.    ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ፓትርያርክ ምርጫ በሚወስነው ቁጥር መሠረት አስመራጭ ኮሚቴ ይቋቋማል፣
3.    ለፓትርያርክነት የሚመረጡት ዕጩዎች ከሊቃነ ጳጳሳት ከጳጳሳትና ከኤጲስ ቆጶሳት መካከል ሲሆን ብዛታቸው ከሦስት ያላነሡ ከአምስት ያልበለጡ ይሆናል፡፡
4.    አስመራጭ ኮሚቴው እጩዎችን ጠቁሞ ለቅዱስ ሲኖዶስ ያቀርባል፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዓት መሠረት ምርጫው እንዲካሔድ ይደረጋል፡፡
5.    መራጮች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ፣ የየመምሪያና ድርጅት ሓላፊዎች፣ የጥንታውያን ገዳማት አበምኔቶች የአድባራት አስትዳዳሪዎች ከየሀገረ ስብከቱ ሰበካ ጉባኤያት በዕድሜ ከሠላሳ ዓመት ያላነሱ የካህናትና የምእመናን ተወካዮች እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ22 አስከ 30 ዓመት የሆኑ የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች ሲሆኑ በጠቅላላው በሰበካ ጉባኤው የሚወከሉት ከአንድ ሀገረ ስብከት አሥራ ሁለት ሆነው በሥጋወደሙ የተወሰኑ በሕገ ቤተ ክርስቲያን የጸኑ መሆን አለባቸው፡፡

የአቡነ ጳውሎስ ጳውሎስ ዜና ዕረፍት አጭር ሪፖርታዥ

 • አስከሬናቸው በባልቻ ሆስፒታል ይገኛል፤ ጥቅመኛዋ እጅጋየሁ በየነ “አልሞቱም፤ አስከሬናቸው ይመርመርልኝ” እያለች በማወክ ላይ ትገኛለች::
 • ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአድባራትና ገዳማት አለቆች በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ጥሪ ተደርጓል::
 • የአቡነ ጳውሎስን ቀብር የሚያስፈጽም ኮሚቴ በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት ተቋቁሟል::
 • ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ይሾማል፤ ከቋሚ ሲኖዶሱም ጋራ እየመከረ ይሠራል:: (ሕገ ቤተ ክርስቲያን)
 • “ውሉደ ጳውሎስ” /እነ እጅጋየሁ በየነ/ በፓትርያርኩ ስም “ጳውሎስ ፋውንዴሽን” ለማቋቋም እየተሯሯጡ ነው፤ የሀብት ቅርምቱን ለማመቻቸት ይኾን?
 • በፓትርያርኩ በተለያዩ ዘመዶቻቸው ስም በአንድ የመንግሥታዊው ባንክ ቅርንጫፍ ሦስት አካውንቶች ውስጥ ከ22 ሚልዮን ብር በላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል::
 ሙሉ ዘገባውን የወሰድነው ከደጀ ሰላም ብሎግ ነው::
READ THIS NEWS IN PDF
 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዛሬ፣ ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም፣ ንጋት ላይ በዳጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

Thursday, August 9, 2012

የጅማ ሀገረ ስብከት የ2004 ዓ/ም ጠቅላላ ጉባኤ አካሄደ

 • "ቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ አውጥቶ ያዋቀረውን ማኅበረ ቅዱሳን በአክራሪነት መፈረጅ ቤተ ክርስቲያንን መፈረጅ ነው" ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ
የጅማ ሀገረ ስብከት ጠቅላላ ጉባኤ የ2004 ዓ.ም. ዕቅድና ክንውንን በመገምገም፣ የ2005 ዓ.ም. ዕቅድን በማውጣትና መመሪያ በመቀበል ሰኔ 28-29 ቀን 2004 ዓ.ም. ተካሂዶ ተጠናቀቀ፡፡

ጉባኤውን የመሩት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ጠቅላላ ጉባኤው የ2004 ዓ.ም. የሥራ ግምገማ ማድረጉ ካለፈው ተሞክሮ በመውሰድ ለቀጣይ የተሻለ ለመሥራትና የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማሻሻል የሚረዳ በመሆኑ በቀጣይም የተሳካ ሥራን ለመሥራት ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ስለሺ አስፋው ከ2004 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በተጨማሪ ሀገረ ስብከቱ የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን ለማስከፈት ይረዳ ዘንድ እየተሠራ ያለው ባለ 5 ፎቅ ሕንፃ ግንባታን በተመለከተ የሒሳብ ራፖርት አቅርበዋል፡፡ ለዚህ ሥራም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አድባራትና ግለሰቦችን አመሰግነዋል፡፡

Wednesday, August 1, 2012

በአሜሪካ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን እና ማኅበራትን የሚቃወም ድብቅ የካህናት ስብሰባ እየተካሄደ ነው

  ሙሉ ዘገባው የደጀ ሰላም ብሎግ ነው::
በሰሜን አሜሪካ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ከርስቲያን በምዕራብ ስቴቶች የካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ሥር በሚተዳደሩ አቢያተ ክርስቲያናት ውስጥ የሚያገለግሉ ጥቂት ካህናት፤ ማኅበረ ቅዱሳንን፤ ማኅበረ በዓለ ወልድንና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤንና በጠቅላላው ለቤተ ክርስቲያናቸው የሚቀኑ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችን እና ካህናትን የሚቃወም ድብቅ ስብሰባ እየተካሔደ ነው። ድብቁ ስብሰባ ኦርቶዶክሳውያን የጡመራ መድረኮች የሆኑትን “ደጀ ሰላምን አሐቲ ተዋዶን፣ አንድ አድርገንን፣ ገብር-ሔር  ናቡቴን ከመናፍቃን ድረ-ገጽ ጋር በመደመር ይዘጋልን ማለታቸውን ጨምሮ በጠቅላላው ባለ ስምንት ነጥብ ደብዳቤ ጽፈው መፈራረም ለቅዱስ ፓትርያርኩ ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ውስጠ አዋቂ ምንጮች በተለይ ለደጀ ሰላም ገልጸዋል

Tuesday, July 31, 2012

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመም የዋልድባ መነኰሳት ተጠያቂ ተደረጉ • READ THIS ARTICLE IN PDF.
 • ከአብረንታንት እና ማይ ለበጣ ሁለት መነኰሳት ወደ ማይ ፀብሪ ተወስደዋልበዶንዶሮቃ 50 በላይ የመነኰሳት እና መነኰሳዪያት ቤት በፖሊስ ተፈትሿል
 • ከፖሊሶቹ አንዲቱ ከጾታዋ የተነሣ ወደ ዋልድባ ለመግባት የማይፈቀድላት ሴት ናት
 • የአብረንታንቱ አባ ገብረ ሥላሴ ዋለልኝ እንደታሰሩ ናቸው
 • 49 ያላነሱ የቤተ ሚናስ መነኰሳት በፖሊስ ይፈለጋሉ
 • ‹‹እናንት ምታታሞች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታመም ተጠያቂዎች ናችሁ›› /የማይ ፀብሪ ፖሊሶች/
ሙሉ ዘገባውን የወሰድነው ከደጀ ሰላም ብሎግ ነው::  

በዝቋላ ገዳም የወተት ላም እርባታ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡

ለዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የወተት ላም እርባታ ፕሮጀክት ለመተግበር ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ፡፡

በገዳሙ በቅርቡ ከፍተኛ የደን ቃጠሎ ተከስቶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ገዳሙን ለመርዳት በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የሚገኙ ምእመናን የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ማኅበረ ቅዱሳን ምእመናንን በማስተባበር ከ600,000.00 ብር /ስድስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለማሰባሰብ መቻሉን የማኅበሩ ዋና ጸሓፊ ዲ/ን ሙሉጌታ ኃይለ ማርያም ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ አብዛኛው በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማእከል አስተባባሪነት በአሜሪካ የሚገኙ የማኅበረ በዓለወልድ እና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ያሰባሰቡት መሆኑ ታውቋል፡፡

የተገኘውን እርደታ ወደ ተግባር ለመለወጥ በታቀደው መሠረት “ለገዳሙ ቋሚ ፕሮጀክት እንደሚያስፈልገው ስለታመነበት ቦታው ድረስ ባሙያዎች በመላክ የዳሰሳ ጥት የተደረገ ሲሆን ከገዳሙ ሓላፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ በውይይቱም ለገዳሙ ትልቅ ጥቅም የሚሰጠው የትራክተር ግዢ ቢሆንም ለጊዜው የተሰበሰበው ገንዘብ ይህንን ለማስፈጸም የማይበቃ በመሆኑ ከዚህ በፊት ተጀምሮ የነበረው የወተት ላም እርባታ ፕሮጀክት እንዲተገበር ስምምነት ላይ ተደርሷል” በማለት የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሓፊ ዲ/ን ሙሉጌታ ኃይለ ማርያም ገልጸዋል፡፡ በስምምነቱ መሠረት የማኅበሩ የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ፕሮጀክቱን እንደሚያስፈጽም ተናግረዋል፡፡

የገዳሙ ደን በተቃጠለበት ወቅት የቀለብ እጥረት በመከሰቱ ማኅበሩ ምእመናንን በማስተባበር 50 ኩንታል ስንዴ 20 ኩንታል ጤፍ፣ 40 ሺህ ብር የሚገመት መጠጥ ውኃ፣ በሶ፣ ስኳር፣ ዳቦ ድጋፍ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ከማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ የተወሰደ ዘገባ ነው::

Monday, July 30, 2012

የአቡነ ጳውሎስ የማዕረግ ስም ላይ “ዓለም አቀፍ የሰላም አምባሳደር” የሚል ተጨመረ • ስለ አቡነ ጳውሎስ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመት በክራውን ሆቴል ለሦስተኛ ጊዜ ይደገሳል።
 • የመንበረ ፓትርያርኩ ሙስና ለጥቅመኛ የውጭ ቡድኖች ‹መስሕብ› ኾኗል - ራእይ ለትውልድ አንዱ ነው።
 • የጠቅ/ቤ/ክህነቱ “የምግባረ ሠናይ አጠቃላይ ሆስፒታል” ኦዲት ተደርጎ አያውቅም።
 • ሰሞናዊው ድግስ “ለመጨረሻው የአቡነ ጳውሎስ በዓለ ሢመት የቁም ተዝካር” በሚል እየተነገረለት ነው።
 • “የሰውዬው [አባ ጳውሎስ] መታወሻ (legacy) አውዳሚነታቸው ነው። እርሳቸውም፣ እኛም እየበላን ያለነው ቀደምት ፓትርያርኮች ያስቀመጡትን ሀብት ነው።” (የቤተ ክህነቱ ታዛቢዎች)
 • ሐምሌ 22ን - እንደ አቡነ ጳውሎስ ወይስ እንደ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ አቡነ ጴጥሮስ?

ሙሉ ዘገባው የደጀ ሰላም ብሎግ ነው::

Monday, July 23, 2012

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የፓትርያርክነት ማዕርግ የተቀዳጀችበት የነጻነት በዓል - በዓለ ሢመተ ፓትርያርክ - አከባበር የመንፈሳዊ ውርደትና የምዝበራ መንገድ ኾኗል  ሙሉ ዘገባው የደጀ ሰላም ነው::
 በሙስና፣ ብኵንነት፣ ኑፋቄ እና ዐምባገነናዊ አሠራር የነቀዘው የአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና 20 ዓመት በዓለ ሢመት ዛሬ ምሽት ለሁለተኛ ጊዜ በሼራተን አዲስ ይከበራል። የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት እና ራእይ ለትውልድ /Vision for Generation/ የተባለው አካል የጥቅም ትስስር የፈጠሩበት የሼራተኑ በዓለ ሢመት ዝግጅት በቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ይኹን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት አይታወቅም።

 
 

Wednesday, July 18, 2012

የሲያትል ምእመናን አቡነ ፋኑኤልን በይፋ ተቃወሙ፤ እንዳይመጡም ተስማሙ

ሙሉ ዘገባው የደጀ ሰላም ነው::
በሰሜን ምዕራብ አሜሪካ በዋሺንግተን ሲያትል በሚገኙት  በደብረ ሰላም ቅ/ሚካኤል እና በደብረ መድኃኒት ቅ/አማኑኤል አብያተ ክርስቲያናት በድብቅ ሊመጡ ያሸመቁትን አቡነ ፋኑኤልን ሕዝቡ በይፋ ተቃወመ፡፡ እሑድ ከቅዳሴ በኋላ ምእመናን በይፋ ባቀረቡት ጥያቄ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ሕገ ወጡ ሊቀ ጳጳስ አባ ፋኑኤል ወደ አብያተ ክርስቲያናቱ እንዳይመጡ በብርቱ ተቃውሞ ቀርቧል። በሌሎች አካባቢዎች የተጀመረው “ቤተ ክርስቲያንን ከነአባ ፋኑኤል እና ከፕሮቴስታንቱ አጋራቸው ከኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን የመታደግ” እንቅስቃሴ በሲያትልም ተጀምሯል። “ምንም አያውቅም” እየተባለ የሚናቀው ምእመን ለቤተ ክርስቲያኑ የክፉ ቀን ደራሽ መሆኑን እና በሐዋሳ ያለው ሕዝበ ክርስቲያን እንባውና በተጋድሎው ቅ/ሲኖዶስ ኡኡታውን ሰምቶ ያገኘውን ድል በአሜሪካ የሚገኘውም ምእመን እንደሚደግመው አረጋግጧል።

Friday, July 13, 2012

የላስ ቬጋስ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን ከአቡነ ፋኑኤል ጋር እንደማይሠራ በድጋሚ አረጋገጠ • የደብሩ ማኅበረ ካህናት የፈረሙበትን ደብዳቤ ተመልከቱ

(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 14/2004 ዓ.ም፤ ጁን 21/ 2012/ READ THISARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በምዕራብ አሜሪካ የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ሥር የሚገኘው የላስ ቬጋስ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን “ከብፁዕ አቡነ ፋኔኡል ጋር እንደማንሠራ እና የሸቱትንም ሾመት የማንቀበል መሆኑን” እንገልጻለን ባለበት መግለጫው አቡነ ፋኑኤል “ከዚህ በፊት ለአህጉረ ስብከቱ ተመድበው አባታዊ መመሪያ እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩት አባቶች በተለየ መልኩ በመጓዝ ካህናት እና ምዕመናንንን በማሳዘን ለመናፍቃን በር የሚከፍት የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ሥርዓት ባልጠበቀ እና ባልተከተለ መንገድ መመሪያ በመስጠት እና በተግባርም በመፈፀም የግል ጥቅምን ብቻ በሚያስጠብቅ አካሄደ በመጓዛቸው በሚሠጡት የተሣሣተ እና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የወጣ አመራር ጋር አብሮ መጓዝ ተገቢ ባለመሆኑ ከዚህ በፊት ያለንን አቋም/ አቋማችንን እንገልጻለን” ብሏል።

Wednesday, July 11, 2012

ጠቅ/ቤተ ክህነት “ጉባኤ አርድእት” ነን ባዮች በመንበረ ፓትርያርኩ እንዳይሰበሰቡ አገደ

·         እገዳው የተላለፈው መንግሥት ለአባ ጳውሎስ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ ነው ተብሏል።
·         በአባ ጳውሎስ ቀጥተኛ ይኹንታ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ለቀናት በኅቡእ ሲሰበሰብ የቆየው ቡድኑ÷ ከፊል መሥራች አባላቱ ከሸሹትና የስብሰባ እገዳ ከተጣለበት በኋላ÷ ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት የ‹ዕወቀኝ› ጥያቄ ማቅረቡ ተነግሯል።
·   የቅ/ሲኖዶስ እና የጠቅ/ቤ/ክህነት ጽ/ቤቶች÷ ቤተ ክርስቲያን “ጉባኤ አርድእት” የተሰኘውን ኅቡእ ቡድን እንደማታውቀው ገልጸዋል።
·     የኅቡእ ቡድኑ አስተባባሪ ፕሮቴስታንታዊው ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን በአባ ጳውሎስ ትእዛዝ የያዘውን የጠ/ቤ/ክህነቱን መኪና እንዲያስረክብ ተደርጓል።
·   አባ ጳውሎስ የእምነት ንጽሕናቸውን በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ያላረጋገጡትንና ከቡድኑ ቀንደኛ አስተባባሪዎች አንዱ የኾኑትን አባ ሰረቀን በመንፈሳዊ ዘርፍ ም/ሥ/አስኪያጅነት ለመሾም ማሰባቸው ተሰምቷል።
·    “ለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ሲባል የቡድኑን ኅቡእ እንቅስቃሴ በጥብቅ እየተከታተልነው ነው” /የጠ/ቤ/ክ መመሪያ ሓላፊዎች/።
·     “ከጉባኤው አስተባባሪዎች አብዛኞቹ በሚሠሩባቸው ቦታዎች ተቀባይነት ያጡ ግለሰቦች ናቸው” /የቋሚ ሲኖዶስ ምንጮች/።
 ሙሉ ዘገባው  የደጀ ሰላም ነው::
 የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ራሱን “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” በሚል መጠሪያ ሰይሞ ከቤተ ክርስቲያን ማእከላዊ አስተዳደር ዕውቅናና ፈቃድ ውጭ ከፓትርያርኩ ባገኘው ቀጥተኛ ይኹንታ የአባ ጳውሎስን ዐምባገነንት ለማጠናከር፣ መንፈሳውያን ማኅበራትን ለማፈራረስ፣ የግል እና የቡድን ጥቅሞቹን ለማስጠበቅ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ መሽጎ ሲዶልት የቆየው ቡድን በየትኛውም የመንበረ ፓትርያርኩ አዳራሾች እና ቢሮዎች ለመሰብሰብ እንደማይፈቀድለት አስታወቀ፡፡

Thursday, July 5, 2012

የታሰሩት የዋልድባ መነኰሳት በነዋሪው ተቃውሞ ለተቃጠለው የፕሮጀክቱ ዶዘር እና ለተጎዱት ሠራተኞች ሓላፊነት እንዲወሰዱ እየተገደዱ ነው

·         የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ሠራተኞች በአካባቢው ሕዝብ እየተሳደዱ ነው::
·         ነዋሪው ሠራተኞቹን እስከ ማይ ገባ ከተማ ድረስ እንዳሳደዳቸው ተነግሯል::
·         የዓዲ አርቃይና ማይ ፀብሪ ወረዳዎች ሓላፊዎች በታሰሩት መነኰሳት እየተወዛገቡ ነው::
·         ከዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም የተወሰዱት አምስት መነኰሳት በዓዲ አርቃይ ፖሊስ ጣቢያ እንደታሰሩ ናቸው::
(ሙሉዘገባውን የወሰድነው ከደጀ ሰላም ነው::
ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ሰኔ 23 ቀን 2004 ዓ.ም÷ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ከዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም የተወሰዱት አምስት መነኰሳት በዓዲ አርቃይ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ በአንድ ቆርቆሮ ቤት ውስጥ እንደታሰሩ መኾናቸውን የስፍራው ምንጮች ለደጀ ሰላም ገለጹ፡፡