Monday, February 6, 2012

የዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቦርድ ሦስት የደብሩ ካህናት ከአገልግሎት አገደ

 READ IN PDF
የአሜሪካ ርዕሰ ከታማ  በሆነችው በዋሽንግተ ዲሲ የምትገኘው ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በአካባቢው ከሚገኘት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በገለልተኛ አስተዳደር የምትመደብ ናት:: ባለው የአባላት ቁጥር ብዛት፣ በአገልጋይ ካህናት ብዛት እና የአገልግሎት ተሳትፎ በዚህ አካባቢ ከሚገኝት ትላልቅ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የመሪነትን ቦታ ትይዛለች :: እንዲሁም ደግሞ በአካባቢው ከሚገኙት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በተለየ ሁኔታ ሰባቱንም ቀን ሙሉ ለምእመናን ክፍት ናት:: ሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚደረገው ሁሉ የደብሩ ቄሰ ገበዝ ሳምንት ሙሉ ቢሮዋቸው ክፍት አድርገው የምእመናኑን ችግር ይሰማሉ::

በዚህ አጥቢያ ሰሞኑን ለመስማት የሚዘገንን ክስተት ተፈጽሞዋል:: ደብረ ሰላም ቅድስ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከተመሰረተችበት ግዜ አንስቶ ለሁለት አስርተ ዓመታት ያልታዩ ክስተቶች ተፈጽሞዋል:: በወርሃዊ ደሞዝ የትፍፍ ግዜ አገልጋይ ርዕሰ ደብር የሚል የማዕረግ ስም ከዚህ አጥቢያ ያገኙት ቀሲስ አብራሃም ኀ/ሥላሴ እና ለረጅም ግዜ የአጥቢያው ሊቀ ዲያቆን ኤልያስ ለሦስት ወር ያህል በማንኛውም አገልግሎት እንዳይሳተፉ ታግደዋል:: ሌላው ደሞዝ እየተከፈላቸው በትርፍ ግዜያቸው በአጥቢያው የሚያገለግሉት ቀሲስ መጠኑ ያለምንም ግዜ ገደብ በምንም ዓይነት አገልግሎት እንዳይሳተፉ ከቦርዱ የስንብት ደብዳቤ እንደደረሳቸው የውስጥ ምንጮቻችን ገልጸውልናል::

በዚህ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ላይ የስልጣን ሽኩቻ መኖሩን ከዚህ በፊት መዘገባችን ይታወሳል:: ምንም እንኳ የቆየ ሽኩቻ ቢኖርም የካህናቱ መባረር ምክንያት የሆነው ግን ዘንድሮ ተከብሮ የዋለው በዓለ ጥምቀት ላይ ከአገልግሎት በመቅረታቸው መሆኑን በተጻፈላለቸው ደብዳቤ ተገልጾዋል::

የጥምቀት በዓል ለረጅም ዓመታት በአካባቢው በገለልተኛ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በአንድ ላይ ሆነው ያከብሩ ነበረ:: ለዘንድሮው የጥምቀት በዓል ተረኞች ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ነበሩ:: ነገር ግን እንደቀደሙት ዓመታት ሳይሆን አጥቢያዎቹ ተከፋፍለው በተለያዩ ቦታዎች በልዩነት ስምምነት አክብረው ውለዋል:: ለክፍፍሉም ምክንያት የሆኑት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ናቸው::

ለዚሁ በዓል አከባበር ምክንያት በማድረግ ከጥምቀት በዓል ሁለት ሳምትት ቀደም ተብሎ በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የተጠራው ስብሰባ ላይ ከደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ መምእራን ቀሲስ ዶክተር አማረ ካሰይ እና የደብሩ ቄሰ ገበዝ ቀሲስ ኃይሉ ተገኝተው ነበረ:: ከደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ደግሞ አስተዳዳሪው ቀሲስ ዘበነ ለማ እና ሌላ አንድ ተወካይ ተገኝተው ነበረ:: በዚሁ ስብሰባ ላይ የደብረ ገነት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን እና የደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን ተወካዮች ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አድረገው በዓሉን አንድ ላይ አብረው ሊያከብሩ እንደማይችሉ በአንድ አቋም ተስማሙ:: እንዲሁም ደግሞ እነዚሁ ሁለቱ በአካባቢው አንጋፋ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የወክሉ አስተዳዳሪዎች ገለልተኛ አስተዳደር ሆነው ሳለ የአጥቢያቸው ምእመናን ማታለል እንደማይፈልጉ በስብሰባው ላይ ገልጸው ነበረ:: ተወካዮቹም በስብሰባው ላይ “ከዚህ በፊት እዚህ አካባቢ ሦስት ጳጳሳት በተለየዩ ግዜያት ከቅዱስ ሲኖዶስ  ተመድው መጥተው ነበረ፤ ነገር ግን እኛ ገለልተኛ አስተዳደር ውስጥ በመሆናችን አንድም የተቀበልነው ሊቀ ጳጳስ የለም:: ሥለዚህ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከበፊተኞቹ ሊቃነ ጳጳሳት በምን በልጠው ነው የምንቀበላቸ?” በማለት ተናግረው ነበረ:: በዚህም ምክንያት ስብሰባው በልዩነት ሥምምነት በዓሉ ሁሉም በያሉበት እንዲያከብሩ ተስማምተው ተበትኖ ነበረ::

ይህ የጥምቀት በዓል አከባበር ምክንያንት በማድረግ የተጠራ ስብሰባ ላይ የተገኙት የደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሊቀ ማእምራን ዶ/ር አማረ ካሣዬ “እኛን ሳያስፈቅዱ ውሳኔ ወስነው መጡ” በማለት ርዕሰ ደብር ቀሲስ አብረሃም፤ ቀሲስ መጠኑ እና ሌሎችም የአጥቢያው ካህናት በማሳመጽ በጥምቀት በዓል ዕለት እና በከተራ ላይ ሳይገኙ ቀሩ:: በዚህም የተባሳጨው የደብሩ ቦርድ የአጥቢያው ማኅበረ ካህናት ለስብሰባ ጠራ:: አስተዳዳሪው ቀሲስ ዶክተር አማረ ካሳዬ አቡነ ፋኑኤል በጠሩት ስብሰባ ላይ ስለተወሰነ ውሳኔ እናዲያብራሩ ተጠየቁ:: አስተዳዳሪውም የአጥቢያው መተዳደርያ ደንብ ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጋር አብረው በዓሉን ሊያከብሩ ስለማይፈቅድላቸው “በዓሉም ከሊቀ ጳጳሱ ጋር አብረን ማክበር እንደማንልችል ወስነናል” በማለት ለቦርዱ አስረዱ:: እንዲሁም አስተዳዳሪው ለቦርዱ ሲያስረዱ “ከዚህ በኋላ ሊቀ ጳጳሱ የምንቀበል ከሆነ መተዳደርያ ደንባችን እንቀይር፥ ካልሆነ ግን ክብረ በዓልም አብረን ልናከብር አንችልም” አሉ::

በዚህም ምክንያት የአጥቢያው ቦርድ በዝግ ስብሰባ የራሱ መረጃ አሰባስቦ ለተፈጠረው አመጽ ተዋናይ ናቸው የተባሉት ቀሲስ መጠኑ በማባረር የስንብት ደብዳቤ ተጻፈላቸው:: ለሁለቱ ማለትም ለሊቀ ዲያቆን ኤልያስ እና ለርዕሰ ደብር ቀሲስ አብረሃም ኀ/ሥላሴ  ደግሞ ለሦስት ወር ከአገልግሎት የሚያግድት ደብዳቤ ተጻፈላቸው:: 

ርዕሰ ደብር ቀስሲ አብረሃም ከዚህ በፊት በአጥቢው ላይ ቦርዱ ከሌሎች ሁለት ካህናት ጋር የክብር ወንበር/መንበር ተሰጥቶዋቸው ነበረ::  ከቀሲስ አብረሃም በተጨማሪ ሌሎች የክብር መንበር ተካፋዮች ቀሲስ ዶክተር አማረ ካሰይ እና ሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ኃይሌ ናቸው:: የክብር መንበራቸው በቤተ ክርስቲያኑ ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ይገኛል:: ማስቀደሻ ቦታቸው/መንበራቸው ነው:: መንበራቸው ማንም ምንም ሊነካው እንደማይችል በሽልማቱ ስነ ሥርዓት ዕለት ተገልጾ ነበረ:: በዚህ አጥቢያ ውስጥ በሥርዓተ ቅዳሴው የሦስቱንም የቦርዱ የክብር መንበር ተሸላሚዎች ስማቸው ይጠራል:: በዛሬው በዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን ርዕሰ ደብር ቀሲስ አብረሃም እንደተለመደው በክብር መንበራቸው ሳይሆን ከምዕመናን ጋራ በቅኔ ማሕሌት ሆነው አስቀድሰዋል:: ቡድኖቻቸው ዲያቆናት እና ሌሎቹም ካህናት ወደ መቅደሱ ሳይገቡ እንደ ምእመን ውጪ አስቀድሰው ተመልሰዋል:: በሥርዓተ ቅዳሴው ላይ ግን እንደተለመደው ስማቸው ተጠርቶዋል ቦርዱ ይህንን ያነሳባቸው አይመስለንም::

የቦርዱ ውሳኔ የተቃወሙት የደብሩ የመንፈሳዊ ጉዳዮች መምርያ ሓላፊ ሊቀ መዘምራን ሞገስ እገዳ ለተጣለባቸው ካህናት የአገልግሎት እገዳው እንዲነሳላቸው ነገር ግን ቅጣቱ በደሞዝ ቅጣት ብቻ እስከተባለው ግዜ ድረስ እንዲቀልላቸው የሚገልጽ ደብዳቤ ለቦርዱ አስገብተዋል:: ይህ በሊቀ መዘምራን ሞገስ የተጻፈው ደብዳቤ በደብሩ ማኅበረ ካህናት ተቃውሞ አስነስቶዋል:: ማኅበረ ካህናቱ በቦርዱ የተጣለው እግድ ትክክል ነው በማለት ደግፈውታል::

ይህ የተፈጠረው ችግር በሽምግልና እነዲፈታ የአጥቢያው ምእመናን ጉዳዩን እንዳይሰሙ ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ እየጣረ መሆኑን የውስጥ ምንጮቻችን ገልጸውልናል::

አሐቲ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ የአስተዳደ መዋቅሯ ቢጠበቅ ኖሮ ለተፈጠረው ችግር አፈታት ዘዴው ቀላል ነበረ ብላ ታምናለች:: የቤተ ክርስቲያናችን አንድነት አምላከ ይጠብቅልን:::

10 comments:

Anonymous said...

I don't think so!

Because, your talk evry day as long as you are under EOTC heade offece; but, the true is opposite.

If all churches in the USA be under EOTC, the problem will be the worst. the main problem our church is Aba Paulos and Meles Zenawi. If they stil are in the top, the problem will be contunue for ever.............

Dillu Zegeye said...

A body without head is lifeless ! Neutralism is Lutheralism not Orthodoxy !

Anonymous said...

@Anonymous, you are still in poletical box... please make yourself free from this box. You should think EOTC, out of your poletical view.

EOTC is not for aba paulos or Meles Zenawi...

I hope that God will give you the light; peace and unity to our church.

Anonymous said...

አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች በማታውቁት ነገር ገብታችሁ የምትፈተፍቱ፤
አንዳንዶቻችሁ ደግሞ በጭፍን ቲፎዞነት እንጂ ነገሩን በፅሞና ያላያችሁ፤
አንዳዶቻችሁ ደግሞ በጭፍን ጥላቻ እንጂ ነገሩን በደንብ ሳታውቁ፤
ሌላው ደግሞ በተለይ በተለይ ጥቅሙ የተነካበትና ከሁዋላው ጉድና ጎድጎዳ የሞላበት፤
በመጨረሻ ደግሞ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለራሱ የንግድ ድርጅትና የፖለቲካ ሥራ
እንደበፊቱ መሥራትና ማጭበርበር ያልቻለው የማህበረ ሰይጣን ድርጅት የሚሰጠው
የሞት የሽረት የመሰሪነትና የቅናት አስተያየቱን ነው የሚያስነብበን። የሆነው ሆኖ
ግን ሁልጊዜ አሸናፊው የእግዚአብሔር ሃሳብ ያለው ነው። እስኪ አሁን ማ ይሙት
በእውነት ለቤተክርስቲያን የምናስብ ከሆነና አላማችን የእግዚአብሔርን መልካም
አገልግሎት ለማገልገል ከሆነ ምን ያጣላናል \ በእውነትስ ክርስቲያን ከሆንን
ክርስቲያን መጣላት አለበት\ ይህንን ደግሜ እላለሁ አላማችን አንድ \ክርስትና\
ከሆነ ምንድን ነው የሚያባላን\ በእውነት አቡነ ፋኑኤል ምን አደረጉ\ ተመድበው
መጡ፣ ሥራቸውን መሥራት ጀመሩ የሥራ ሰው እንጅ የወሬና የአሉባልታ ካህን
አይደሉም። ደግሞስ እኛ ማነንና ነው በስነሥርአት ሲኖዶሱ መድቡአቸው ለክርስትና
አገልግሎት እንዳይሰጡ የምንፈራገጠው፣ አረ ተው መቼም ክርስቲያኖች እንኩአን
አይደላችሁም ፤ ስለ እግዚአብሔር ብትባሉም አልሰማችሁምና አለቃችሁም የቀደመው
ጠላታችን ያ ዲያብሎስ በመሆኑ ነው መሰለኝ እርሱን በማስደሰትና ቤተክርስቲያንን
በመበጥበጥ ላይ ትገኛላችሁ። ነገር ግን እግዚአብሔር ተዋጊ ነው አታውቁም እንዴ\
ምንም አላችሁ ምንም አሁን ጊዜው የእግዚአብሔር ሰዎች የሚፈተኑበት ጊዜ ስለሆነ
እስከመጨረሻው የሚፀና እርሱ ይድናልና፤ አባታችን እስከመጨረሻይቱ ሰአት ድረስ እውነተኛ
ሥራን መሰራት ብቻ ነው፣ ከእናንተ ጋር አፍ መካፈትም አያስፈልግም። ጨው ለራስህ
ብትል ጣፍጥ ያለዚያ ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሃል ነውና፣ ማቅ መንፈሳዊ ድንቁርናችሁ
የትም አያደርሳችሁም፣ ለቤተክርስቲያን ጠላት ማቅ ይገባዋል ሞት፣ ለቤተክርስቲያናችን
ግን አንድነት፣ እድገትና ፍቅር ለዘለአለሙ ይሁን። አሜን።ሰላምንና ፍቅርን የማይወደው ማቅ
ይግባ መቀመቅ። ባታወጡትም ካነበባችሁት ይበቃል።ሳትሰሩ የህዝቡን ገንዘብ እየበላችሁ
አየር ላይ ለቀራችሁት ህገ ወጥ የድርጅቱ ኮሚቴ ነን ባዮች፣ እናንተ ማለት ደግሞ ማንም ናችሁና
ካአቅማችሁ በላይ አትዘለሉ ወደ ላይ። ይቆየን።

Anonymous said...

Abune fanuel done great job , for reason he appointed very real lekawonet as leke kahinat. Others mk elememts please find job that close match to ur profile. You guys no idea about to manage and to serve thechurch just leave ourchurch now. Bc you mk come wrong, place to find job go to employment agency I hope you can be hire not in eotc.

Anonymous said...

if any thing happen to abune fanuel it should be the last age of mk to burried forever.

Anonymous said...

Ahat Tewahedo Thank you very mach yezegebachihut neger tikikil mehonun bebotaw temelkchalehu yesewn kibir alnekachihum melemed yalebet neger melkam yehonewn memezigeb new ahun Papasun-kahinun-sebakiwin- Bordun sim lematsifat almokerachihum wedefitim melkam were akiribu DC Mariam yetebetsebetsew Be 3 negeroch new
1 Bordu alastewlem
2 riese Debiru tiebitega new
3 zemarit Tsdale Gobeze were tamelalsalechbeteley kesis Metsenu bitsenekeku melkam new beterefe debiru selam new Abune Fanueil Melkam sira Jemrewl bertu

Anonymous said...

Abune Fanueil Kekahinat gar mesratachew yasmeseginal Abune Abirham melkam yeseru bihonim Mahibere Kidusan & Mahibere Balewold bemalet norewal Gudachew hulu yeteshefenew Mahiberun sileyazu new Abune Fanueilm Bihonu Mahibere Kidusann makireb alebachew Man yakerarbachew ? hulum meleyayetu yitsekmal yemil new Astaraki yelem -Mekar yelem Beterefe hulunim lemakireb yewsedut ermija melkam new geleltega -wesentega mebabalu altekemem Ahat Tewahedom Ahun melkam tengarol bertu

Anonymous said...

mahibere kidusai melkam mehonun awkalehu

Anonymous said...
This comment has been removed by a blog administrator.