Tuesday, February 7, 2012

“ቤተ ክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አይደለችም፤ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ናት” ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል

 READ IN PDF
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ጋዜጠኛ ከአቶ አዲሱ አበበ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በሀገረ አሜሪካን ስለምትገኘው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ግንዛቤ ለሌላቸው አድማጮች እውነት የሚመስሉ፤ ነገር ግን በመሬት ላይ ካለው እውነት ጋር ፍጹም የማይገናኙ  ትንታኔዎችን ሰጥተዋል:: “የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጵጵስና በተቀበሉበት ወቅት ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዳስረከቡ መረጃዎች አሉን የሚሉ ወገኖች አሉ፤ ነገር ግን አሁንም ድረስ  ቤተ ክርስቲያኑ በእርሶ እጅ እንዳለ ይወራል” በማለት አቶ አዲሱ አበበ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “ቤተ ክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አይደለችም፤ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ናት” ብለው ነበር:: ይህ አነጋገር በሰሜን አሪሜካ ስላለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናን በቂ መረጃ ለሌላቸው ሰዎች እውነት ቢመስልም ሐቁ ግን ከዚህ የራቀ ነው::
 ለብፁዕ አባታችን አሁን ደግሞ እኛ አንድ ጥያቄ እናቅርብ እስኪ፤ እውነት በሰሜን አሜሪካን ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ናትን? 

የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና እንደሚያስረዳው ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተች ተመሠረተች እንጂ አትዘጋም:: በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ የቤተ ክርስቲያን መሠረቷ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑንም ከእውነተኞቹ አባቶቻችን ተምረናል:: ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ስም እዚህ ሀገር ውስጥ የውንብድና ሥራዎች ሲሰሩ እናያለን እንሰማለን:: ብፁዕትዎ እንዳሉት ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ብትሆንማ የተለያዩ ግለሰቦዎች እንደፈለጉ ከፍተው አይዘጓትም ነበር:: እውነታው ግን ይህ አይደለም:: በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ልክ እንደ ፕሮቴስታንቶቹ  አዳራሾች የግለሰቦች ንብረት ናት:: ለምሳሌ ያህል የዛሬ አራት ወር በሜሪላንድ ሲልቨር እስፕሪንግ አካባቢ የተከሰተው ድርጊት በቂ ማስረጃ ነው:: የተከሰተውን ድርጊት በዝርዝር እንየው፣ እንዲህ ነው::

አሁን ለሜሪላንድ ስቴት ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል እና የሰንበት ት/ቤቶች ኃላፊ አድርገው ብፁዕነትዎ የሾሟቸው መልአከ ሰላም ቀሲስ ሰብስቤ ጸጋዬ ኪዳነ ምሕረት ወአማኑኤል የሚል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ነበራቸው:: ይህ አጥቢያ “የተከፈተው” ወይም ደግሞ በቤተ ክርስቲያናችን ቋንቋ የተመሠረተው በቀሲስ ሰብስቤ ነበር:: “ተከፍቶ” ለአንድ ዓመት ያህል አገልግሎት ከሰጠ በኋላ ከቀሲስ ሰብስቤ ጋር አብረዋቸው የነበሩ ሰዎች በጥቅም ተጣልተው ሌላ ኪዳነ ምሕረት ወአማኑኤል በማለት እዛው አጠገብ ሌላ አጥቢያ ከፈቱ:: የቀሲስ ሰብስቤ ኪዳነ ምሕረት ወአማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ለሦስት ዓመታት ያህል ከቆየ በኋላ በዘንድሮ ጥቅምት ወር ላይ ተዘግቶ ቀሲስ ሰብስቤ ወደ ሌላ ስቴት ኮብልለው ነበር:: የመዘጋቱም ምክንያት ቀሲስ ሰብስቤ  ከቤተ ክርስቲያኑ የባንክ አካውንት ያለ ሒሳብ ሹም ፈቃድ ለሁለት ዓመታት ያህል ገንዘብ እያወጡ ለግላቸው ሲያውሉ በመቆየታቸው ነው:: በመጨረሻ የነቁት የአጥቢያው ምእመናን አስተዳዳሪው ቀሲስ ሰብስቤ ላይ አጥቢያውን በተመለከተ አንዳንድ ጥያቄ አነሱ:: ቀሲስ ሰብስቤ መልሳቸው “ቤተ ክርስቲያኑ የእኔ ነው፣ እናንተ ምን አገባችሁ” የሚል ነበር:: ምእመናኑም አስተዳዳሪውን ለመክሰስ የሕግ አማካሪ ጋር ሲሄዱ የቤተ ክርስቲያኑ ፈቃድ የተመዘገበው በቀሲስ ሰብስቤ ስም ብቻ መሆኑን ተረዱ:: እንዲሁም የአጥቢያው የባንክ አካውንት በቀሲስ ሰብስቤ ስም ነበር፥ ምእመናኑ ቢከሱም የትም ሊደርሱ እንደማይችሉ ተረዱ:: በመጨረሻም ቀሲስ ሰብስቤ ቤተ ክርስቲያኑ ዘግተው ጠፉ:: አንባቢያን “ታቦቱንስ የት አደረጉት” ትሉ ይሆናል፤ ይህ ደግሞ የእኛም ጥያቄ ስለሆነ መልስ ልንሰጣችሁ አንችልም::

ከዚህ በፊትም ቀሲስ ሰብስቤ በተመሳሳይ ሁኔታ በዳላስ ቴክሳስ የከፈቱትን ቤተ ክርስቲያን ዘግተው ነበር ወደ ሜሪላንድ ስቴት የመጡት:: የሜሪላንዱም ሆነ የቴክሳሱ አጥቢያዎች “የተባረኩት” በራሳቸው በቀሲስ ሰብስቤ ነበር:: አስተዳዳሪውም ራሳቸው ነበሩ:: ሁለቱንም አጥቢያዎች ከፍተው የዘጓቸው ቀሲስ ሰብስቤ ናቸው:: እና ታድያ በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አባባል እነዚህ የቀሲስ ሰብስቤ አጥቢያዎች የክርስቶስ ነበሩ ማለት ነውን? እውነተኛ አባት የተሰበሰቡ በጎቹን በትኖ ይጠፋልን? እኒህ ግለሰብ አሁን በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የተሰጣቸው ሹመትስ ይገባቸዋልን? መልሱን ለአንባቢ እንተወው::

በሀገረ አሜሪካ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እንዴት እና በማን ይመሠረታሉ? የአጥቢያዎች አመሠራረት የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ቀኖና የጠበቀ ነውን? የአጥቢያዎቹ የይዞታ ባለቤነት የማን ነው? እንግዲህ የእነዚህን ጥያቄዎች መልስ ሊሰጡ የሚችሉ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱን የመሠረቱት ሰዎች ብቻ ናቸው:: በዚህ ሀገር እንደየስቴቶች ሕግ አጥቢያዎች ሲከፈቱ ሁለት ዓይነት ሕጎች ይኖሯቸዋል:: የመጀመርያው ሕግ መተዳደርያ ደንብ የሚባለው ሁሉም ምእመን የሚያውቀው ሲሆን አንዳንድ አጥቢያዎችም በድረ ገጾቻቸው ላይ ያስቀምጡታል:: ሁለተኛው ሕግ ደግሞ ከመሥራች ግለሰቦች ውጪ ማንም የማያውቀው፤ ይህም ሕግ “አርቲክል ኦፍ ኢንኮርፖሬሽን (article of incorporation) ላይ የሚቀመጥ ነው:: በአርቲክል ኦፍ ኢንኮርፖሬሽን የሚቀመጡ ሰዎች በዚህ ሀገር ሕግ ኢንኮርፖሬተር ይባላሉ:: እንደየስቴቱ የሰዎቹ ቁጥር ብዛት ይለያያል:: አርቲክል ኦፍ ኢንኮርፖሬሽን ላይ የሚቀመጠው  “ኢንኮርፖሬተሮቹ” (መሥራቾቹ) እንደሚፈልጉት አድርገው የሚያስቀምጡት ገዢ ሕግ ነው።: በአጥቢያው አባላት መካከል አለመግባባት ሲመጣ (ልክ እንደ ቀሲስ ሰብስቤ) ዘግተው እስከመጥፋት ሊደርሱ ይችላሉ። ምክንያቱም አርቲክል ኦፍ ኢንኮርፖሬሽን ላይ የሚቀመጠው ሕግ ባለቤት ስለሚያደርጋቸው:: ታድያ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ይህንን ሁሉ እያወቁ (እርሳቸውም የግላቸው የሆነው የቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንዳላቸው  ያስታውሷል) አሜሪካን አገር ያለችው ቤተ ክርስቲያን እንዴት የክርስቶስ ናት አሉ?? ግለ ሰቦች እንደ ፈለጉ ከፍተው ሲበቃቸው የሚዘጓት ቤተ ክርስቲያን እንዴት የክርስቶስ ልትሆን ቻለች?

የዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በባለቤትነት ወይም “article of incorporation” ከተመዘገቡት ሦስት ግለሰቦች መካከል አንዱ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ናቸው:: የዚህ አጥቢያ እስከ አሁን (Feb 15, 2011 ዓ/ም) የተሠራው የቤተ ክርስቲያኑ ታክስ መታወቂያ እንደሚያመለክተው ባለቤትነቱ በአባ መላኩ ጌታነህ ስም ነው፤ ነገር ግን ለይስሙላ አስተዳዳሪው አባ እስጢፋኖስ ናቸው:: ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል  አሁንም ለየስቴቱ ሹመት የሰጧቸው ሰዎች አንዳንዶቹ እንደ ብፁዕነታቸው በስማቸው የራሳቸው አጥቢያ ያላቸው፣ አንዳንዶቾ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ከፍተው የዘጉ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ አጥቢያ እንኳን የሌላቸው ተዘዋዋሪ ካህናት ናቸው:: እንግዲህ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በሰሜን አሜካሪካ ከቀጣፊዎች ጋር በመተባበረ ቤተ ክርስቲያናችን የበለጠ ውስብስብ የሆነ ችግር ውስጥ ሊያስገቧት እንዳቀዱ ይህ ሹመት ምስክር አይሆንምን?

በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢ ያሉ አጥቢያዎች ዝርዝር ለማየት ይህንን ይጫኑ::

ይቆየን::

4 comments:

Anonymous said...

« ማኅበሩ አያንቀላፋም»

እንቅልፍ ለሰዎች የተሰጠ የሥጋ እረፍት ነው። «ቀን ለሰራዊት፣ሌሊት ለአራዊት»እንዲሉ! ዛሬ ግን ዓለማችን ቀንና ሌሊቱን አቀላቅላው ሰውም አራዊቱም ጉዞአቸው ባንድ ሆኗል። በሌሊት! ከነዚህ ቀኑንም ሌሊቱንም ከማያንቀላፋው ሀገርኛ ድርጅት አንዱ ራሱን በራሱ የቅዱሳን ማኅበር ነኝ የሚለው «ማኅበረ ቅዱሳን» በቁልምጫ ስሙ «ማቅ» የተባለው ድርጅት ነው። በቤተክርስቲያን ውስጥ ስፍራውና ድርሻው ለጊዜው ባይገባንም ረጅምና ስውር እጁ የሌለበት ቦታ የለም በሚባል ደረጃ ያለእረፍት ይንቀሳቀሳል። ለዚህም ነው የጽሁፋችንን ርእስ «ማኅበሩ አያንቀላፋም» ያልነው። አዎ! ማኅበረ ቅዱሳን አያንቀላፋም። የማያንቀላፋው ራሱን የቤተክርስቲያን ተጠሪ በማድረግና ሲኖዶሱ ባልሰጠው ውክልና በቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ ስውር እጁን እንደአባጨጓሬ እያርመሰመሰ በመገኘቱ ነው። ማኅበሩ በሲኖዶስ መሃል ቁጭ ብሎ በስውር እጁ ጳጳስ ሆኖ ይወስናል፣ ያስወስናል፣ይከራከራል፣ይሞግታል። ለሲኖዶሱ አጀንዳ ይቀርጻል፣ የማይስማማውን ይጥላል፣ የፓትርያርኩ የራስ ህመም እስኪነሳ ያሳብዳል። ምክንያቱም ማኅበሩ ጳጳስ ስለሆነ አያንቀላፋም። በአምሳለ ጳጳስ «ማኅበረ ቅዱሳን ባይኖር ቤተክርስቲያን ምን ተስፋ አላት» ያሰኛል። በአድባራትና ገዳማትም መካከል ሳያንቀላፋ በአለቃነት ወይም በሀገረ ስብከት ደረጃ በሥራ አስኪያጅነት ወይም በመምሪያ ኃላፊነት ውስጥም ኅቡእ መንፈስ ሆኖ ይንቀሳቀሳል። የሰባኪዎችን፣የሰንበት ት/ቤቶችን ወይም የምእመናንን ማንነት ይቆጣጠራል፣ ይመረምራል፣ ይሰልላል። ማኅበረ ቅዱሳን አያንቀላፋምና እዚህም ቦታ አለ። ንግዱ ውስጥ! ይነግዳል፣ያስነግዳል። ግብርና ታክስ የማይከፍል የንግድ ተቋም ሆኖ በሆቴሎች፣ በሱቆች፣ በንዋያተ ቅድሳት መሸጫዎች፣በኢንኮርፖሬትድ ድርጅቶች፣ በህትመት፣ በሚዲያ ውጤቶች ውስጥ ሁሉ አለ።


ስለማያንቀላፋ ለቤተክርስቲያኒቱ ጥናት የሚያጠናላት እሱ ነው። ማኅበሩ እንደቀንድ አውጣ ባንቀላፋ ሲኖዶስ መካከል የተገኘ ንቁ በመሆኑ ሰዶ በማሳደድ ፖሊሳዊ ሥራ ውስጥም እጁ አለ። ግለሰቦችን በግለሰቦች በኩል ሙልጭ አድርጎ ያሰድባል።(ዘመድኩንን ልብ ይሏል?) ከኋላ ሆኖ ጠበቃ ያቆማል፣ዜና ይሰራል፣ ሲሞቀው ወሬውን ያራግባል።(በደጀ ሰላም) ይመሰክራል፣ ያስመሰክራል፣ ሲጠላ ይጥላል፣ ሲወድ ደግሞ ይወዳጃል።(ዘሪሁን ሙላቱን የመሰሉ) ኃጢአት ለእርሱ ዋጋ የሚኖረው ተመንዝሮ በሚያስገኘው ውጤት እንጂ ኃጢአትን ከመጸየፍ አንጻር አይደለም። እንደቤተክርስቲያኒቱ ሕግ ነውራሞች እስከተስማሙት ድረስ ለእርሱ ቅዱሳን ናቸው፣ የማይስማሙት ደግሞ ወደሲኦል መወርወር አለባቸው ብሎ ይዋጋቸዋል፣ ያዋጋቸዋል፣ ከፊት ቀድሞ ወጥመድ ያኖርባቸዋል። ከኋላ ሆኖ ጀርባቸው ላይ ጥላት ይቀባቸዋል። (አባ ፋኑኤልን ልብ ይሏል?) ማኅበሩ እጁ የሌለበት ቦታ የለም። መንፈሱ ሁሉ ገብ ነው። ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን አያንቀላፋም። ሲኖዶስ በስም ጠቅሶ እነእገሌ ተሐድሶ ስለሆኑ ቢችሉ በንስሃ እንዲመለሱ፣ ፈቃደኛ ካልሆኑ ተወግዘው እንዲለዩ ሳይል ማኅበሩ ራሱ ስም ጠርቶ ያወግዛል፣ያባርራል፣ በር ይዘጋል፣ ደብዳቤ ይጽፋል፣ ያጽፋል። ስለማያንቀላፋ ሁሉ ቦታ መንፈሱ ይሰራል። በየመድረኩ ማስተማርና መስበክ የሚችሉት ፈቃድ የተሰጣቸው ብቻ መሆን እንዳለበት ሲኖዶስ ከተናገረ እሱ ቃሉን መንዝሮና ተርጉሞ እነእገሌ ይከልከሉ፣ እነእገሌም ይሰቀሉ ሲል ኢትዮጵያዊ ኢንተርፖል ሆኖ ይቆጣጠራል፣መግለጫ ይሰጣል፣ ያሰጣል። ኦርቶዶክሳዊነታቸው ባልተገፈፈና ውግዘት ባልተሰጠበት ወገን መታገዝ በራሱ ብቻውን በቂ ባለመሆኑ የማኅበሩ ፈቃድ በየትኛውም ቦታ የግድ መሆኑን ሰውር አዋጅ ያውጃል። ያለበለዚያ ሁሉም ቦታ በሚገኘው በስውር መንፈስ እጁ ያግዳል፣ ያሳግዳል።(የልብ ህሙም የእንዳለ ገብሬን ጉዳይ ልብ ይሏል?) ሌላው ቀርቶ ማኅበሩ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ወይም ያለሲኖዶስ ሕጋዊ መግለጫ ራሱ መግለጫ ይሰጣል፣ ለፖሊስ፣ለደህንነት ይወነጅላል፣ያስወነጅላል። በግለሰቦች ነጻነት ውስጥ ጣልቃ ይገባል። በደብዳቤ ስም ጠርቶ መብት ይገፋል። ስም ያጠፋል። የመንቀሳቀስን መብት ለማገድ ይደክማል፣ ይወነጅላል። በሕግ ከሚያስጠይቁ የመብት ገፈፋ ተግባራቱ መካከል አንዱ አባ ድሜጥሮስ በተባለ ጳጳስ እጅ ማኅበሩ የጻፈውና ስም እየጠራ ከሀገር ያለመውጣት የውንጀላ ደብዳቤውን ከደጀሰላም ስውር አፉ አግኝተናልና ለእናንተም ሆነ መብታቸው ለተገፈፈ ወገኖች እንዲደርስ አውጥተነዋል።The rest of the letter, see on Dejebirhanblogspot

Anonymous said...

Abune fanuel done great job , for reason he appointed very real lekawonet as leke kahinat. Others mk elememts please find job that close match to ur profile. You guys no idea about to manage and to serve thechurch just leave ourchurch now. Bc you mk come wrong, place to find job go to employment agency I hope you can be hire not in eotc.

Anonymous said...

Ahat Tewahedo Kesis Sebisiben Bemimeleket Yezegebachihut neger Asazinog yale erefit adire nebere yih sew ( Kesis Sebsibe ) balmoya -yetemare-dimtsaw-Digiri yalew sew new Amerca hager mekera yetekebele yetegefa sew new lezih hulu mekera yederesew lemin endehone bedenb tawkalachuhu 10 amtati mulu bichawn new mistuna lijoch ethiopia nachew yasazinal Abune Fanueil Kemersuwachew Abatoch hulu yeteshale yihonal enj ayansim yemiyasansew yeteregaga hiyiwot yelewm bemoyaw yaltetsekem sew new
Ahat Tewahedo Kesis Sebsiben bemimeleket yezegebachihutim fetsinachihu mansatachihu melkam new yih sew mekari keageg nege yitsekmal hod bisot -yemredaw techegro endaytsefa esegalehu Amercan hager enkan kahinu setoch yekefetut church ale Kesis Sebsibe Abune Abirhamn Barkulig eyale silemin noroal Abune Abirham besime Adirgna libarkilih bilewt new yekerew Cilemnachew menorun enawkalen ebakachihu Ahunm sile egiziabher bilacheh meleyayetun -metsefafatun yemiyasker mekerareb yemiyametsa neger mezigibu hulum yalfal beteley yesewn sim fetsino lematsifat atimokiru simin matsfat kemegidel yeteleye Ayidelem beteley yePapasaten yekahinatin -yesebakiwochin -yezemariwochin-yediyakonochin ye Mahibere Kidusann -yetawaki sewochin sim mansat yikir yemisenakelew bizu sew nena tesasche kehone yikirta lehulachinim lib yisitsen

Anonymous said...

For anonymous who wrote in the title " ማህበሩ አያንቀላፋም" ትክክለኛ አባባል ነው!! አዎ ማህበሩ አጽራረ ቤተክርስቲያኖችነ በመዋጋት ረገድ አያንቀላፋም ይህችን ተዋህዶ እምነታችንን ለመጠበቅ ዘብ የቆመ ጠበቃችን ነው አዎ ምንግዜም ለዘህ ለተቀደሰ ተግባሩ አያንቀላፋም!! አቤት ይህ ማህበር ባይኖር ኖሮ ይህቺ እምነታችን ምን ልትሆን እንደምትችል ሳስብ እንዴት ይዘገንነኛል!! ቤተክርስቲያናችን በመናፍቃን በተሃድሶዎች እንዴት እንደምትበከል ብዙ የተዋህዶ ልጆች በተኩላዎች እንደሚወሰዱ ሳስበው ይዘግንነኛል!! ማህበሩ እስካሁን በመልካም ተጋድሎው ለመናፍቃን ህመም ሆኖ 20 ዓመታትነ ተጉዟል አሁንም እድሜ ይስጥልን!!አሁን በመንግስትም ሆነ በቤተክህነት በላው ሁኔታ(መናፍቃን ወደቤተክርስቲያናችን ዘልቀው ለመግባት በሩ ክፍት በሆነበት ዘመን) መናፍቃኖች ወደዘህች እመነታችን ሰተት ብለው ገበተው ምዕመኗን መንጠቅ እነዳይችሉ ስላደርጋቸው ተቃጠሉ ተንገበገቡ!! መሃበሩን ለማጥፋት የማይፈነቅሉት ድነጋይ የለመ በምዕመኑ ዘንድ እንዲጠላ አንዴ ነጋዴ ነው አንዴ ምንድነው...እያሉ የተለያዩ ስም ለጠፉለት ነግር ግን ምዕመኑ ወሬ ሳይሆን ተግባር ስለሆነ የሚየምነው ሰሚ ሊያገኙ አልቻሉም(ማሀበሩ በተጨባጭ የሚሰራው ይታወቃልና) ይህም እንዳልተሳካከላቸው ሲያውቁ ደሞ በመንግስት በኩል ማህበሩ እንዲፈርስላቸው አንዴ ተቃዋሚ ነው አንዴ የአማራውን መንግስት ሊመልስ የሚጥር ነው (እብዛኞቹ የመንግስት ባለስልጣኖች ትግሬዎች እንደሆኑ ስለሚያውቁ) ምን የማይሉት አለ ማህበሩ ግን ለወሬ ጊዜ የለውም ስንት የሚያከናውናቸው መልካም ተግባራት አሉና!! ለቤተክርስቲያናችን የቆምነውን የተዋህዶ ልጆች መናፍቃንን እና ስራቸውን ከተቃወምን ማህበረ ቅዱሳን ነን ለነሱ! ተሃድሶ/መናፍቃንን የሚቃወም ቤተክርስቲያናችን ቀኖናዋ ተጠብቆ እንዲቆይ የተቻለውን ሁሉ የሚሰራ ድረገጽም ይሁን ብሎግ ለነሱ የማህበረ ቅዱሳን ነው!! አዎ ለተዋህዶ እምነታችን ከምንም በላይ ማህበሩ ትልቅ ስራ እየሰራ ነው ነገር ግን የመሃበሩ አባል ያልሆኑ በጣም በጣም ብዙ የዚች ቤተክርስቲያን ተቀርቋሪ ልጆች አሉ ድምጻቸውንም በተለያየ መንገድም እያሰሙ ነው እናም መናፍቃኖች ለ20 አመታት ሙከራችሁ ሁሉ እንዳልተሳካለችሁ አውቃችሁ እባካችሁን እጃችሁን ከማህበሩ አንሱ!! እግዚያብሄር ቤተክርስቲያናችንን የጠብቅልን!!