Thursday, March 29, 2012

ማስታወቂያ


በዋልድባ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሕዝባዊ ውይይቶች ቀጥለዋል

 •   ሰላማዊ ሰልፎች ማድረጉ ይቀጥላል።
 •  “ሥር ነቀል የምእመናን እንቅስቃሴ ነው የሚያስፈልገው” ከተሳታፊ ምእመን
 •  ምእመናን ለቤተ ክርስቲያናቸው መቆም ያለባቸው ጊዜ ላይ መደረሱ ተወስቷል፡፡
 • “ሁላችሁንም በእግዚአብሔር ስም አንድ ነገር እለምናችኋለሁ። ከዘረኝነት ራሳችንን እናጽዳ። ዘር ለዱባና ለድንች እንጂ ሁላችን ከአንድ ከክርስቶስ ከማይጠፋው ዘር የተወለድን ነን”
ዘገባው የደጀ ሰላም ነው::
 በዋልድባ እና በጠቅላላው የቤተ ክርስቲያን ህልውና ጉዳይ የተቀሰቀሰው ቁጣ በሕዝባዊ ውይይቶች ታጅቦ እየቀጠለ መሆኑን የሰሜን አሜሪካ ምንጮቻችን ገልጸዋል። በመላው የአሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በስልክ ኮንፈረንስ ሐሳባቸውን እንዲሰጡ እያደረገ ባለው በዚህ ሕዝባዊ ስብሰባ የምእመናን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን ተሳታፊዎቹም ስለ ዋልድባ ይዞታ መደፈር ወይም ስለ ዝቋላ እና አሰቦት ገዳማት የእሳት አደጋ ብቻ ሳይሆን “በጠቅላላው ስለ ቤተ ክርስቲያን ህልውና ነው መነጋገር ያለብን” ወደሚለው ገዢ ሐሳብ በመምጣት ላይ ናቸው ተብሏል።

Wednesday, March 28, 2012

“የዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመንፈሳዊ አስተዳደር ከእናት ቤተ ክርስቲያን ጋራ አንድነት መስርቷዋል” ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል የጵጵስና ማዕረግ ለማግኘት እጅ መንሻ ያደረጉ ንግግር

በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ ስብሰባ ጠራ

 • የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የገዳመ ዋልድባ ችግር ከተሰማበት ዕለት አንሥቶ ጸሎተ እንዲያዝ ዐውጀው እንደነበር ተሰምቷል
 • ‹‹ለቋርፍ ተለዋጭ መሬትና በጠፋውም የቋርፍ ተክል ምትክ በስድስት ወር የሚደርስ የሙዝ ዘር እንሰጣችኋለን፤››
 
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 19/2004 ዓ.ም፤ ማርች 28/2012 READ THIS ARTICLE IN PDF)፦
·         ከሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት፣ ከዋልድባ ገዳም ተወክለዋል የተባሉ መነኰሳት፣ ከጎንደር ከተማ የተመረጡ ምእመናንና በማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማእከል ሥራ አስፈጻሚ አባላት ነገ፣ መጋቢት 19 ቀን 2004 ዓ.ም፣ የመንግሥት ‹‹የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት›› በዋልድባ ገዳም ህልውናና ክብር ላይ ስለ ደቀነው ስጋት፣ በተጨባጭም ስለታየው መጋፋት ውይይት እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ ስብሰባውን የጠራውን ብአዴን/ኢሕአዴግ ሲሆን የሚካሄደውም በጎንደር ከተማ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

Tuesday, March 27, 2012

የዋልድባ ገዳም ይዞታን መደፈር የተቃወመ ሰላማዊ ሰልፍ በዲሲ ተካሄደ

·         ኤምባሲው ለሙስሊም ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊ ወገኖቻችን ያሳየውን ከበሬታ ለክርስቲያኖቹ አለማሰየቱ ግርምት ፈጥሯል፤
·         “መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱን ይንቃታል፤ ክርስቲያኑንም ይንቃል” (ሕዝብ)

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 18/2004 ዓ.ም፤ ማርች 27/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የኢሕአዴግ መንግሥት በዋልድባ እና አካባቢው  በግድብ ሥራ፣ በፓርክ እና በስኳር ፋብሪካ ግንባታ ስም የሚያካሒደውን ገዳሙን ድንበር፣ ትውፊት እና መንፈሳዊ ይዞታ የመግፋት መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ በመቃወም ላይ ላሉ ገዳማውያን አበው እና እመው ያላቸውን አለኝታነት ለመግለጽ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ትናንት በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመሰለፍ ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።

Ethiopian Christians Protest in Washington DC (VOA 3/26/2012)

Monday, March 26, 2012

የዋልድባ ገዳም መብት ለማስከበረ በዋሽንግተን ዲሲ የአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

“የአባቶቻችን ርስት እና ቅርስ ተጠብቆ ለትውልድ ይተላለፍ” የሚል መሪ ቃል ያለው የአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፍ የአሜሪካን መንግስት መቀመጫ በሆነችው በዋሽንግተን ዲሲ በኢትዮጵያ ኤምባሲ ዛሬ መጋቢት 17፣2004 ዓ/ም በአካባቢው የሰዓት አቆጣጠር 9am ላይ ተካሄዶዋል:: በአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፉ ላይ በቦታው የተገኙ አባቶች በጸሎት አስጀምረዋል:: በሰልፉም ከአንድ ሺህ በላይ ክርስቲያኖች እንደተገኙ በአካባቢው የነበሩ ዘጋቢዎቻችን ገልጸውልናል:: በአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፉም በአስተዳደር ምክንያት የተለያዩ ወገኖች በአንድነት የቤተ ክርስቲያን ህልውና የሚፈታተኑን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል:: ለአራት ሰዓታት ያህል የቆየው የአቤቶታው ሰልፍ በተለያዩ መዝሙራት የታጀበ ነበረ:: ተሳታፊዎቹም ጥያቄዎቻቸውን በእንባ እና በጩኸት ለኤምባሲው አሰምተዋል::

Saturday, March 24, 2012

ይድረስ ለአባ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፣ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዝዳንት


 •  ከገብር ኄር ድረ ገጽ የተወሰደ ነው:: 
 •   አባታችን ይህቺን ትንሽዬ ጦማር እከትብሎ ዘንድ ያነሳሳኝ “ሰሞኑን” በተከሰቱ ሁለት ዓበይት ጉዳዮች ዙሪያ ጥያቄዎች ስላሉኝ ጥያቄ ለመጠየቅና በጉዳዮቹ ዙሪያ የተሰማኝንና የታዘብኩትን ነገር ልነግሮት በመፈለጌ ነው:: ይህቺን ጦማር ስከትብሎ እርሶ ጋር ላይደርስ ይችላል የሚል ጥርጣሬና ሀሳብ አላደረብኝም:: እናም በአንድም ሆነ በሌላ እንደሚድርስዎት እርግጠኛ ስለሆንኩ የተሰማኝን ነገር ሳላስቀር እንዲህ ከትቤዋለሁ::ጉዳዮቹም ሰሞኑን ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ተብሎ ስለሚነገረው ስለሶስቱ ታላላቅ ገዳማት: ማለትም ስለአሰቦት: ዝቋላ እና ዋልድባ ገዳማት በረከታቸው ይደርብንና ስለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ ሺኖዳ 3ኛ ዜና እረፍት ናቸው::
 • አቢይ ጉዳይ አንድ

Friday, March 23, 2012

"በደኖቹ መቃጠል ማን ብዙ ይጎዳል”? ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ

 READ IN PDF
“የገዳማቱ የተፈጥሮ  ደን  መጠበቅ ተጠቃሚው ማን ነው”? በሚል በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ የቀረበ ጦማር አግኝተናል:: ይህ ጽሑፍ ዲ/ን ብርሃኑ  በፌስ ቡካቸው  ላይ አስቀምጠውታል::  እኛም እንደሚከተለው አቅርበነዋል:: መልካም ንባብ!!!
+++
በዚህ በሰሞኑ የገዳማቱ ደኖች መቃጠል አንድ ያስገረመኝ ነገር ቢኖር ኦርቶዶክሳዊ ከሆኑት ዉጭ ከሌሎቹም ብዙም ጉዳዩን ጉዳይ የማድረግ ነገር አለማየቴ ነዉ፡፡ ሁኔታዉን ደጋሜ ሳስብበት ቢያንስ ሁለት ችግሮች እንዳሉብን ገመትኩኝ፡፡ አንደኛዉ እንደ ዜጋና ሀገር የደኖችን ጠቀሜታ በዉል አለማወቃችን ይመስለኛል፡፡ ሁለተኛዉም ራሳችን ተቆርቋሪዎች ነን የምንለዉም ብንሆን ቦታዉ የእኛ መሆኑ የጣለብን ሓላፊነት አድርገን ስለቆጠርነዉ እንጂ ከዚህ ያለፈ ምን ያህል ጉዳት እንደሚያመጣ ማስረዳት የቻልን አልመሰለኝም፡፡ ይህንን ማድረግ አለብን ወይም ነበረብን የምለዉ ዛሬዉን ማለቴ አይደለም፤ ቀደም ብለን፡፡ እንማን? እኛ፡፡ በቃ እኛ የሚለዉ የሚበቃ መሰለኝ፡፡ ምን አልባትም በየገዳማቱ ዙሪያ ያሉ ነዋሪዎች እሳቱን ለማጥፋት ሲረዱ የማይታዩት እንዲያዉም እሳቱን የሚያስሰነሱት ከሰል በማክሰል ለመጠቀም ሲሉ ነዉ ተብለዉ የሚነሱት በርግጥም አድርገዉት ከሆነ የሚወቀሱት ይህን እንዲረዱ ባለማድረጋችን ይመስለኛል፡፡ በአካባቢዉ ያለዉ ሰዉ ስለደኑ ጥቅም በደንብ የሚረዳዉ ነገር ከሌለ ለምን ይጠብቀዋል? በርግጥም በማቃጠሉ በቀላሉ ከሰሉን ስለሚያገኝና ስለሚሸጥ ራሱኝ የተሻለ ተጠቃሚ አድርጎ ሊያስብ ይችላል፡፡ ለመሆኑ ደኖቹ በመቃጠላቸዉ ከፍተኛ ተጎጂዎች አነማን ናቸዉ? እስኪ ከዛፉ በፊት ከእያንዳንዱ ፍጥረት መጠበቅ ምን ያህል ልንጠቀም እንደምንችል የሚያሳይ አንድ ምሳሌ ላቅርብና ወደ ደናችን ልምለስ፡፡

“እሳት በመንደርም ይነሣል፤ በቤተ ክርስቲያን ሲሆን ለምን ይገናል?” (የጠ/ ቤተ ክህነቱ መግለጫ)

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 14/2004 ዓ.ም፤ ማርች 23/2012. READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ሁሉም ሓላፊዎች በዋልድባ ገዳማት፣ በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ ወአባ ሳሙኤል ገዳም እና በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ከተፈጠረው ችግር ጋራ በተያያዘ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምላሽ ተመጣጣኝና ፈጣን እንዳልሆነ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ላይ የሚሰነዘረውን ወቀሳ በማጣጣል አስተባብለዋል፡፡

ገዳመ ዋልድባን ለመታደግ የፖለቲካ እና የብሔር ልዩነቶቻችን ሊያግዱን አይገባም!!!

 READ IN PDF
እምነት የለሹ ትውልደ ኮሚኒስት  ቤተ ክርስቲያናችን ማሳደድ አሁንም አላበቃም:: አለመታደል ሆነና በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የሚገኙ አባቶቻችን ሐዋርያዊ አደራቸውን ተቀብለው ቤተ ክርስቲያን ከመጠበቅ እና ከማስጠበቅ ይልቅ ትውልደ ኮሚኒስትን በመተባበር ቤተ ክርስቲንን እየተዋጓት ነው:: የሀገር ቤቶቹ አባቶች ከዘመነኛው መንግስት ጋር ተሰልፈው የቤተ ክርስቲያንን መብት ማስከበር አቅቶዋቸዋል:: በውጪ ሀገር የሚኖሩት አባቶች ደግሞ ለቤተ ክርስቲያን ህልውና ከመቆም ይልቅ ለፖለቲከኞች ህልውና በመቆም ቤተ ክርስቲያንን ለተሐድሶ መናፍቃን አሳልፈው ሰጥተዋል::  ከዚህ በፊት ኮሚኒስታዊው ኢትዮጵያዊ ትውልድ እና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በሚል አንድ ጽሑፍ አቅርበን ነበረ:: ጽሑፉን ይህንን በመጫን ያንብቡ::

አሁን በገዳመ ዋልድባ እየተካሄደ ያለው የዚሁ የኮሚኒስቱ እምነት የለሹ ትውልድ ውጤት ነው:: እንግዲህ “የአባቶቼን ርስት አሳልፌ አልሰጥህም” በማለት የተነሳው ይሄኛው ወጣቱ ትውልድ የቤተ ክርስቲያን እሴቶች ጠብቆ ለማቆየት ከኮሚኒስቶቹ ጋር ትግል ገጥሞዋል:: በቀደሙት አባቶቻችን አምላክ ረዳትነት የቤተ ክርስቲያንን መብት ለማስጠበቅ የተሰለፈው ትውልድ ያሸንፋል ብለን እናምለን:: እውነት ሁሌም አሸናፊ ናትና::

Ziquala Fire Report (2012) by VOA Radio

Waldiba 3rd Reportage by VOA Radio

Wednesday, March 21, 2012

“ጥያቄው ከስኳር እና ከዋልድባ መምረጥ አይደለም” አቶ መስፍን ነጋሽ

 READ IN PDF
መንግስት በዋልድባ ገዳም አካባቢ የስኳር ፋብሪካ እያቋቋመ መሆኑን በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ተገልጾዋል:: በዚህ ልማት እና የቅርስ ጥበቃ አስመልክቶ አቶ መስፍን ነጋሽ የሚከተለውን ጽሑፍ በአዲስ ነገር ኦንላይ(addis neger online) ላይ አውጥተዋል:: እኛም ጽሑፉን ለውይይት እንዲሆነን እንደሚከተለው አቅርበነዋል:: መልካም ንባብ!!!
+++
ሰሞኑን በዋልድባ ገዳም አካባቢ ከተጀመረው የስኳር ፋብሪካ ልማት ጋራ ተያይዞ የተነሣው ውዝግብ በመሠረቱ መሬት ከማረስ ወይም የአንዱን ይዞታው ሌላው ከመንካቱ ጋራ የተያያዘ ብቻ አድርጌ አልተመለከትኩትም። ጥያቄው “ለልማት” (በጠባቡ በአቶ መለስ ትርጉም) እና ከቁሳዊ ዋጋቸው ይልቅ ረቂቅ/መንፈሳዊ ዋጋቸው እንደሚበልጥ ለሚታሰቡ እሴቶች ከሚሰጠው ዋጋ ጋራ የተያያዘ ነው። እንዳለመታደል ሆኖ አገራችን እንዲህ ያሉ አገራዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ፋይዳቸው ላቅ ያሉ ጉዳዮችን አደባባይ አውጥቶ ለመከራከር የሚቻልባት አገር አልሆነችም፤ በብዙ ምክንያቶች። አለበለዚያ በጉዳዩ ላይ ሕዝባዊና ምሁራዊ ክርክሮች በኖሩን፣ ሚዲያውም ዜና ከማተም አልፎ ጉዳዩን በጥልቀት ለመመርመር በሞከረ ነበር።

ጥያቄው “ልማት ያስፈልጋል አያስፈልግም?” የሚል አይደለም፤ “መንፈሳዊ/ታሪካዊ/ማኅበራዊ እሴቶች መጠበቅና መዳበር አለባቸው የለባቸውም?” የሚልም አይደለም። ለዚህ ነው “ጸረ ልማት ሃይሎች የስኳር ፋብሪካውን ተቃወሙ” (አይነት) የሚለው የኢቲቪ ቀፋፊ ዜና የሚያስጠላውን ያህል “ጸረ መንፈሳዊ/ማኅበራዊ እሴት የሆነው የአቶ መለስ መንግስት ሆን ብሎ ገዳሙን…..ስኳር ፋብሪካ…አደረገ” የሚለው አይነቱ ክርክርም ትርጉም የሚያጣው።

ሰበር ዜና:- በአሰቦት ገዳም የአብነት ተማሪው በታጣቂዎች ተገደለ

 READ IN PDF
 ዘገባውን ያገኘነው ከማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ነው::
በምዕራብ ሐረርጌ ሜኤሶ ወረዳ በአሰቦት ሥላሴና አባ ሳሙኤል ዘደብረ ወገግ ገዳም የአብነት ተማሪ የሆነው የ7 ዓመቱ ሕፃን ናታን አንበስ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በ3 ጥይት ተመትቶ መገደሉን የገዳሙ ዋና መጋቢና ምክትል አበምኔት አባ ዘወልደ ማርያም ገለጹ፡፡ ከአባ ሳሙኤል ገዳም በተወሰኑ ሜትሮች ርቀት ላይ ከእናቱ ጋር ወደ ገዳሙ በመውጣት ላይ እያለ ከእናቱ እጅ ቀምተው በመውሰድ ፊት ለፊቷ በሦስት ጥይት ገድለውት ሊያመልጡ ችለዋል፡፡ በእናትየው ጩኸትና በጥይት ድምጽ የተደናገጡት መነኮሳት ገዳዮቹን ለመያዝ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

የገዳሙ መነኮሳት እንደገለጹት ጉዳዩን ለፖሊስ በስልክ ያሳወቁ ሲሆን ፖሊስ “መኪና አግኝተን እስክንመጣ ድረስ ሟቹን  ቅበሩት” በማለታቸው ከቀኑ 8፡00 አካባቢ ሊቀበር ችሏል፡፡ ባቲ በተባለው አካባቢ በአሰቦት ቅድስት ከሥላሴ ገዳም ጀርባ ከሚገኘው አካባቢ ታጣቂ አርብቶ አደሮች ተሰባስበው ወደ ገዳሙ በመቃረብ ላይ መሆናቸውንና መነኮሳቱ ስጋት ላይ እንደሚገኙ ጨምረው ገልጸውልናል፡፡

መጋቢት 1 ቀን ባቀረብነው ዘገባ መሣሪያ የታጠቁ ሰዎች እሳቱን በሚያጠፉት ምእመናን ላይ ተኩስ ከፍተው እንደነበርና የፌደራል ፖሊስ አባላት ምላሽ ሰጥተው ከአካባቢው እንዳራቋቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የዝቋላን ገዳም ለመታደግ አስተዋጾ ያድርጉ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::
በዝቋላ ገዳም እና በአካባቢው ደን ላይ የተነሣውን እሳት ለማጥፋት ለሚደረገው ጥረት ለማድረግ የግል ልገሳዎን ይስጡ በሚል ሐሳብ በማ/ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል፣ በሰንበት /ቤቶች አንድነት ጉባኤ እና በማኅበረ በዓለ ወልድ አስተባባሪነት በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ ኦርቶዶክሳውያን አስቸኳይ የገንዘብ ማሰባሰብ ሒደት ላይ እንገኛለን። ዓላማው በአሁኑ ወቅት እሳቱን ለማጥፋት ከየአካባቢው በነቂስ ለወጣው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ጉሮሮውን ማርጠቢያ ውኃ፣ ጉልበቱን መደገፊያ ዳቦ ማቅረቢያ እንዲሆን የታሰበ ነው። በባዶ እጁ፣ በቅጠል እና በአፈር ቋያ እሳት ለማጥፋት እየታገለ ላለው ወገን አለኝታነታችንን ለመግለጽ ነው። ስለዚህም በሚከተለው አድራሻ እየገባችሁ የግላችሁን ልገሳ መስጠት የምትችሉ መሆኑን በትህትና እናስታውቃለን።

በሰሜን አሜሪካን በወቅታዊው የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ ለመወያየት ለሁለተኛ ግዜ አስቸኳይ ስብሰባ ተካሄደ

 •  “ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጩኸታችን ባይሰማንም ከመጮህ ወደ ኋላ አንልም” የስብሰባው አስተባባሪ
ዛሬ በ03/20/2012 ዓ/ም በዋሽንግተን ዲሲ ሰዓት አቆጣጠር 10pm በመላው አሜሪካን ግዛት የሚገኙት የቤተ ክርስቲያን ልጆች ለሁለተኛ ግዜ አስቸኳይ ስብሰባ በስልክ ኮንፈረንስ አካሄዶዋል:: የስብሰባው አጀንዳ በወቅቱ በቤተ ክርስቲያናችን እየተካሄደ ያለው ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ አደጋ ለመታደግ “እኛ ምን እናድርግ” የሚል ነበረ:: በስብሰባው አስተባባሪዎች እንደተገለጸው በተለያዩ ጥንታውያን ገዳማት ላይ እየደረሰ ያለው የእሳት ቃጠሎ ምክንያት እንዲታወቅ እና ለወደፊትም አደጋው እንዳይከሰት መከላከል የሚቻልበት ሁኔታ እንዲፈጠር ማድረግ ነው::
 
ይህ በአጽራረ ቤተ ክርስቲያን እና በተባባሪዎቻቸው እየደረሰ ያለው አደጋ ለመከላከል የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች በአንድነት እንዲሰለፉ በስብሰባው የተሳተፉ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል:: ቤተ ክርስቲያናች እውነተኛ ተቆሪቋሪ መሪ እስክታገኝ ድረስ እያንዳንዱ የእምነቱ ተከታይ መሪ ሆኖ ቤተ ክርስቲያን በወቅቱ ከገጠማት ፈተና እንድንታደጋት የስብሰባው አስተባባሪዎች አደራቸውን አስተላልፈዋል::

Tuesday, March 20, 2012

በፖሊስ ጥይት የቆሰሉት ተማሪዎች ሦስት ደርሰዋል

 •   ወደ ደብረ ዘይት ለሕክምና ተወስደዋል  
 • በፖሊስ ጥይት የቆሰሉት ተማሪዎች ሦስት ደርሰዋል

 •     አጋጣሚው ቃጠሎውን ከመከላከል ሊያዘናጋን አይገባም!!!

  READ IN PDF

ዘገባው የደጀ ሰላም ነው:: 
 በዝቋላ ገዳም የተነሣውን ቃጠሎ ለመከላከል ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ስፍራው ከተነቃነቁት አዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል በፖሊስ ጥይት የቆሰሉት ተማሪዎች ሦስት መሆናቸው ተዘገበ፡፡ በተማሪዎቹ ላይ የደረሰው ጉዳት መንሥኤ በተማሪዎቹ እና በአንድ የኦሮሚያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ መካከል የተፈጠረ አለመግባባት መሆኑን መዘገባችን ይታወቃል፡፡

በሰሜን አሜሪካን የሚኖሩ ምእመናን በእሳት እየጋየ ያለውን የዝቋላ አቦ ገዳም በተመለከተ አስቸኳይ ስብሰባ አካሄደዋል::

 READ IN PDF
ለስብሰባው መንሥኤ በወቅቱ ጉዳይ በተለይም የዝቋላ አቦ ገዳም የእሳት ቃጠሎ የሚታደጉ ወገኖቻችንን ለመርዳት ነው:: ይህ ስብሰባ የተጠራው በፌስ ቡክ እና በስልክ መልእክት በመለዋወጥ ነው:: ስብሰባውም የተካሄደው በኮንፈረንስ ስልክ ነው:: በዋሽንግተን ዲሲ ሠዓት አቆጣጠር 2pm ላይ የተካሄደ ሲሆን ስብሰባው ያዘጋጁት በሰሜን አሜሪካን የሚገኙት ሦስት ማኅበራት ማኅበረ ቅዱሳን፣ ማኅበረ ወልድ እና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ማኅበር ናቸው:: እንደ ሚታወቀው በሰሜን አሜሪካን ቤተ ክርስቲያነችን አንድ አድርጎ የሚመራ የተጠናከረ ማእከላዊ አስተዳደር የላትም:: ነገር ግን የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች ገዳማቱ አደጋ ላይ ሲወድቁ ለመርዳት በግልም በማኅበርም እየተደራጁ በማጣር ላይ ናቸው:: 

በስብሰባው ላይ እንደተገለጸው ኢትቶጵያ ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችን እሳቱን ለማጥፋት ከትምህርት እና ከሥራ ገበታቸው ተለይተው በጉልበታቸው እየታገሉ ናቸው::  ከእሳቱ ጋር የሚታገሉ ወገኖቻችን የሚቀምሱት እህል ውሃ እንደሌላቸው ተነግሮዋል:: ስለዚህ እነዚህ ከትምህርት እና ከሥራ ገበታቸው ተለይተው እንዲሁም ውጪ እያደሩ የሚገኙት ወገኖቻችን የሚጠጡት ውሃ እና ምግብ የማቅረብ ግዴታ እንዳለብን የስብሰባው ተሳታፊዎች ገልጸዋል::

በአካባቢው አንድ ጄሪካን ውሃ በአህያ ወደ ቦታ ለማድረስ አርባ ብር ለሁለቱ ደግሞ 80 ብር እንደሚያወጣ ተገልጾዋል:: በሀገር ቤት የሚኖሩ ወገኖቻችን ግዜያዊ አደጋ የተጋረጠባቸው ገዳማትን ለመርዳት ሕይወታቸውም ጭምር ሰጥተው እየታገሉ እንደሆነም የስብሰባው አስተባባሪ ዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ ገልጸዋል::  እዚህ ሀገር የምንኖር ምእመናን የምንችለው ነገር ሁሉ እንድናደርግ በስብሰባው የተገኙት አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል::

በስብሰባው ማጠቃለያ እንደተነገረው ለዚህ ተብሎ አዲስ የባንክ አካውንት ተከፍቶዋል:: የባንኩ አካውንት በማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካን ማዕከል ድረ ገጽ ላይ እንደሚገኝ ተገልጾዋል:: ስለዚህ በውጪ ዓለም የምንኖር ወገኖች በዚህ በገጠመን ፈተና በአንድነት ቆመን ገዳማቱን ከወደቁበት አደጋ እንድንታደጋቸው፣ ከእሳት እና ከረሀብ ጋር ጦርነት የገጠሙት የሀገር ቤት ወገኖቻችንን እንድንደርስላቸው አሐቲ ተዋሕዶ አደራ ትላለች::

እግዚአብሔር አሐቲ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን!!!

(ሰበር ዜና) በዝቋላ ገዳም ፖሊስ አንድ ተማሪ አቆሰለ

·         ትኩረታችን ወደ መከላከሉ - መዘናጋት አይገባም!!
READ THE ARTICLE
ዘገባው የደጀ ሰላም ነው::
በዝቋላ ገዳም ቃጠሎውን ለማጥፋት በተሰበሰቡ ወጣቶች እና በኦሮሚያ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ መካከል በተቀሰቀሰው አለመግባባት ከአዳማ ዩኒቨርስቲ ከተጓዙት መካከል አንድ ተማሪ ከፖሊስ በተተኰሰ ጥይት እግሩ ላይ ቆስሎ ወደ ሕክምና በመወሰድ ላይ መሆኑ ተሰማ፡፡
የአለመግባባቱ መንሥኤ ወጣቶቹ ቃጠሎውን አስመልክቶ በቀጥታ ስርጭት ዘገባ ማስተላለፍ ሥራ ላይ የነበረውን ጋዜጠኛ መቃወማቸው ነው ተብሏል፡፡ የዐይን እማኞች እንደተናገሩት ጋዜጠኛው እሳቱ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ የሚገልጽ ዘገባ በማስተላለፍ ላይ ነበር፡፡

በተማሪው ላይ ከደረሰው የመቍሰል አደጋ ውጭ ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ ቃጠሎውን ለመከላከል በየሸጣሸጡ፣ በየገደሉ ሲጥሩ ጥቂት የማይባሉ ወጣቶች በመውደቅ፣ በመሰበር እና በመላላጥ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተዘግቧል፡፡ ይሁንና አሁን በተማሪው ላይ ያጋጠመው የመቁሰል አደጋ ትኩረታችንን ሳይቀለብሰው ኀይላችን ሁሉ የቃጠሎውን አደጋ በመከላከል ላይ እንዲወሰን መልእክት ተላልፏል፡፡
በሌላ በኩል ወደ ዝቋላ ገዳም ከተለያዩ ከተሞች የሚሄዱ መኪኖች ድሬ በተባለችው መዳረሻ ከተማ ላይ በፖሊስ መታገዳቸው ተሰምቷል፡፡ የተሰጠው ምክንያትም የሰዉ አለመጠን መብዛትና ‹‹አንዳንዶች በዚህ ተጠቅመው የሚያደርሱትን ጉዳት ለመከላከል ነው፤›› ተብሏል፡፡ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኀይለ ግብር የሆኑና በስፍራው የሚገኙ ባለሞያዎች እሳቱ እንዳይዛመት አሁን ባለው የመከላከል አቅም ግንድ እየተቆረጠ መሠራት ለሚገባው አርፍተ እሳት(fire break) ከፍተኛ የሰው ጉልበት በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡
 አየር ኀይል በሄሊኮፕተር እገዛ እንዲያደርግ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል እንዲያመለክት ለመጠየቅ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የተገኙትን ወጣቶች ያነጋገሩት በቅጽረ ግቢው ጥበቃ እያደረገ የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኀይል ሓላፊ ናቸው፡፡
ትላንት ከዋልድባ ገዳም የተመለሱት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ እና የሕዝብ ግንኙነት መምሪያው ሓላፊ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ ጥያቄውን ለማቅረብ በደብረ ዘይት አየር ኀይል እንደሚገኙ የተነገራቸው ወጣቶቹ፣ የቃጠሎ መከላከሉን ጥረት የሚከታተል ስድስት አባላት ያሉት ኮሚቴ አቋቁመዋል፡፡ ወጣቶቹ ትላንት በሁለት የሕዝብ ማመላሻ እና በአራት ሚኒባሶች ወደ ዝቋላ አምርተው የነበረ ሲሆን ምሽት ላይና በውድቅት የተቀሰቀሰውን እሳት እስከ ንጋት ድረስ ግንድ እየቆረጡ የቃጠሎውን መዛመት የሚያግድ እሳተ ከላ ሲሠሩ አድረዋል፡፡
የቃጠሎውን መዛመት ለመግታት እየተቆረጠ የሚሠራው ማገጃ (አረፍተ እሳተ) ለጊዜውም ቢሆን ከቃጠሎ ተርፎ ለሚታየው የደኑ ክፍል መራቆት ምክንያት እየሆነ ነው፡፡ ‹‹ይህ ሁሉ በአየር መከላከል ቢታገዝ የግማሽ ሰዓት ሥራ ይሆን ነበር፤›› ያለው አንድ ወጣት እንደገለጸው መነኰሳቱ አረፍተ እሳቱን ለመሥራት ዛፉን የሚቆርጡት እያነቡ ጭምር ነው - ገዳማችንን አራቆትነው እያሉ!!
ዓርብ ረቡዕ፣ አጣብቂኝ እና በጋራው ሥር በርትቶ የሚታየው ቃጠሎው ሰዓት የገዳሙ ከብቶች በሚገኙበት ማደሪያ በኩል እንደ አዲስ ተቀስቅሷል፡፡ ሌሊት ሌሊት የሚነሣው ከባድ ነፋስ፣ እርጥበት አጠር የሆነው የቀኑ ዋዕይ እና ቀን ቀን ተዳፍኖ ሌሊት በነፋሱ የሚቀጣጠለው ክምችት የሠራው ፍሕም (በአብዛኛው የጥድ ነው) ለቃጠሎው ማየል አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ የገዳሙ አበምኔት አባ ዮሐንስ አሁን ማምሻውን ለሸገር ኤፍ፣ኤም 102.1 ሬዲዮ እንደተናገሩት ቅዳሜ ከሰባት ሰዓት ጀምሮ የተነሣው እሳት ምንም ዐይነት መገታት አይታይበትም፤ ሕዝቡ ውኃ ወደ ገዳሙ እያመጣ ያለው በሃይላንድ ጠርሙስ ጭምር ነው፡፡ የምሥራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ጫላ ሆርዶፋም ይህንኑ በማጠናከር እሳቱ በአንድ ቦታ ጠፋ ሲባል በሌላ ስለሚቀሰቀስ የማጥፋቱን ሥራ አስቸጋሪ አደርጎታል፡፡ ሸገር የጠየቃቸው ምእመናንም በጣም ተመራጭ የሆነው መንገድ የአየር መከላከል (ሄሊኮፕተር መጠቀም) መሆኑን እንደተናገሩ ዘግቧል፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን

አሜን

ተጨማሪ መረጃዎች:- የዝቋላ ገዳም አሁን ያለበት ደረጃ

ሙሉ ዘገባ የደጀ ሰላም ነው:: READ IN PDF

Monday, March 19, 2012

የዝቋላ የሰኞ መጋቢት 10 ቀን 2004 ዓ.ም. ውሎ "ቃጠሎው እጅግ አሳሳቢ ሆኗል" የማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ

 READ IN PDF
ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ነው:: ከጧት ጀምሮ ምእመናን ከደብረ ዘይት፣ ከአዲስ አበባ ከተለያዩ መሥሪያ ቤቶች የተውጣጡ የቤተ ክርስቲያን ልጆች፣ በማኅበረ ቅዱሳን የሚመራው የዩኒቨርሲቲዎች የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አባላት ቃጠሎውን ለማጥፋት ቦታው ድረስ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ከገዳሙ በደረሰን መረጃ መሠረት እስከ ቀኑ 12፡00 ሰዓት ድረስ ቃጠሎው በፀሐይና በንፋስ በመታገዝ ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ ይገኛል፡፡ መነኮሳቱ ለኦሮሚያ ፖሊስ፣ ለፌደራል ፖሊስና ለአየር ኀይል እንዲሁም ለምእመናን የድረሱልን ጥሪ በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡ በተለይም ቦታው እጅግ አስቸጋሪ በመሆኑ ውኃ ማግኘት ባለመቻሉ የደኑን ውድመት እያባባሰው ስለሚገኝ ውኃ የሚያመላልሱ ቦቴ መኪናዎች ያሏቸው ምእመናን ውኃ በማመላለስ እንዲደርሱላቸው በመማጸን ላይ ናቸው፡፡

ከተለያዩ አካባቢዎች የተንቀሳቀሱት ምእመናን ከአስቸጋሪ ጉዞ በኋላ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ቦታው የደረሰ ሲሆን ለማጥፋት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህንን ዜና እስካጠናቀርንበት 12፡00 ሰዓት ድረስ ቃጠሎው እንዳልጠፋና ከሌላ አቅጣጫ ሌላ አዲስ ቃጠሎ መቀስቀሱን በቦታው ከሚገኙ ምእመናን ለመረዳት ችለናል፡፡ ቃጠሎው በዚሁ ከቀጠለ ከፍተኛ የደን ሀብት ያለበት ቦታ መያዙ እንደማይቀር ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡

በቃጠሎ ጉዳት የደረሰባቸው ምእመናን እንደሚገኙ ከቦታው የደረሰን መረጃ የሚያመለክት ሲሆን በከፍተኛ ጥምና ረሃብ ላይ ለሚገኙ ምእመናን ውኃና ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው ጭምር ገልጸዋል፡፡

የዝቋላ ገዳም ደን ቃጠሎ ማምሻውን በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ገለጸ

 READ IN PDF
ለሁለተ ተከታታይ ቀናት እየተቃጠለ የሚገኘው የዝቋላ ገዳም ደን በቁጥጥ ስር እንደዋለ የመንግስት መገናኛ ብዙኃን( ሚድያ) ማምሻውን ገልጾዋል:: ከጉዳዩ ባለቤት ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ግን ምንም የተባለ ነገር የለም:: ያው እንደሚታወቀው ጠቅላይ ቤተ ክህነት አለቆቻቸው የመንግስት ባለ ስልጣናት እስኪተነፍሱ ድረስ እየጠበቁ ናቸው::

ኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛው በመንግስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት የመገናኛ ብዙኃን የኢትዮጵያ ሬድዮ እና ቴሌቭዢን ናቸው:: በ21 አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሃምሳ ሚሊዮን አባላታ ያላት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ግን ድምጿን ለልጆቿ የምታሰማበት ምንም አይነት የተጠናከረ የመገናኛ ብዙኃን(ሚድያ) የላትም::

ዛሬ ማምሻው በመላው ኢትዮጵያ የፌስ ቡክ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦዋል:: ገዳማቱ በእሳት ሲወድሙ እና ሌላ አደጋ ሲደርስባቸው መረጃ የመለዋወጫ መንገድ ፌስ ቡክ ብቻ ነበረ:: ዛሬ እሱንም ቆረጡት::

በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ አራት ታላላቅ የገዳማት ይዞታዎች ምክንያቱን ባልታወቀ ሁኔታ በእሳት ጋይተዋል:: አንዱ ታላቁ ገዳም ደግሞ በፈርጣማው መንግስታችን በመታረስ ላይ ይገኛል:: ታድያ ይህ ጥፋት በእኛ ዘመን ላይ ሲከሰት በዝምታ ማለፋችን ከታሪክ ተወቃሽነት የምንድን አይመስለንም:: ዝምታችንስ እስከ ምን ድረስ ነው? ይህ እያንዳዳችን የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች መመለስ ያለብን ጥያቄ ነው:: ማኅበራቱ ለምሳሌ ማኅበረ ቅዱሳን ቢሆኑ ቃጠሎ ከደረሰ በኋላ ለማጥፋት ተገኛተዋል ብሎ ዜና ከመዘገብ ይልቅ የመፍትሄ አቅጣጫ ቢሰጡ መልካም ነው::

Monday, March 12, 2012

የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ለወረዳው መስተዳድር ደብዳቤ ጻፈ

  ሙሉ ዘገባው የደጀ ሰላም ነው:: ዘገባውን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ READ IN PDF::
  •  ገዳሙ በውሳኔው ጸንቷል፤ 
  •  “በእኛ በኩል በዚህ ቦታ ላይ ልማት ይሰራ ብሎ መወሰን ፈጽሞ የማይታሰብና የማይታለም ነው። ቦታውም በቅዱሳን መካነ መቃብር የታጠረና የተከለለ ነው” (ገዳሙ)፤ 
  •   በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ሊደረግ ነው፤
  Thursday, March 8, 2012

  ጥንታዊው ገዳመ ዋልድባ ለመታደግ የአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፍ ማርች 26, 2012 ይደረጋል

   READ IN PDF
  አጽራረ ቤተ ክርስቲያን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለማዳከም በተጠና እቅድ ይንቀሳቀሳሉ:: ከእቅዶቻቸውም መካከል ለቤተ ክርስቲያኒቱ የትምህርት እና የጸሎት ማዕከል በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት ታላላቅ ገዳማትን የሚጠፉበት ሁኔታ ማመቻቸት ነው:: ከእነዚህ ታላላቅ የቤተ ክርስቲያኒቷ የአስተምህሮ ማዕከላት መካከል አንዱ ገዳመ ዋልድባ ነው:: እነዚህን የትምህርት ማዕከላት ገዳማት ለማጥፋት በተለያየ ግዜ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ሞክረው ነበረ:: ነገረ ግን በቀደሙት አባቶቻችን ፍጹም ተጋድሎ ለዚህኛው ትውልድ አስተላልፈው አልፈዋል::
  ከጥንታውያን ታላላቅ ገዳምት ውስጥ የምትመደበው የዋልድባ ገዳም ህልውና አስገጊ ደረጃ ላይ መሆኑን የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል:: አሁን በእኛ ዘመን መንግስ ልማት ተገን በድረግ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን እቅድ እውን እያደረገላቸው ይገኛል:: ዋልድባ  ለብዙ ዘመናት በአባቶቻችን ተጋድሎ ተከብሮ  እኛ በአደራ እንደተረከብነው ሁሉ ለሚቀጥለው ትውልድ እስከነ ሙሉ ይዘቱ በአደራ የማስተላለፍ ግዴታ አለብን::

  ገዳሞቻችን የማፍረስ የአጽራረ ቤተ ክርስቲያን እቅድ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በታላላቅ ገዳማት አካባቢ የሚደረጉ ተግባራት ገዳማቱን ያማከለ ጥናት ሳይጠና መከናወን የለበትም:: መንግስት የገዳማቱ አስተዳደር ሳያማክል ያጠናው ጥናት ተገቢ አይደለም:: በገዳማቱ አካባቢ የሚደረጉ ልማቶች ለገዳማቱ ህልውና አስጊ እንዳይሆን መንግስት መከላከል አለበት::

  አሁን በዋልድባ ገዳም እየተደረገ ያለው የልማት እንቅስቃሴ ለገዳሙ ህልውና አስጊ መሆኑን የገዳማቱ አባቶች የአቤቶታ ጥሪ ማስተላለፋቸው በመገናኛ ብዙኃን ተገልጾልናል:: መንግስት የአባቶች አቤቶታ ችላ በማለት እንቅስቃሴውን ቀጥሎበታል::

  ይህንን የገዳማቱ አባቶች አቤቶታ የሰሙ ቅናተ ቤተ ክርስቲያን ያደረባቸው/የበላቸው ወንድሞች የአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ የዓለማችን ከተሞች ለማድረግ እቅድ ይዘዋል:: የመጀመርያው ሰላማዊ ሰልፍ የአሜሪካ መንግስት መቀመጫ በሆነችው በዋሽንግተን ዲሲ ማርች 26፣2012 ወይም መጋቢት 17፣2004 ከጠዋቱ 3 ሰዓት፤ በዚህ ሀገር አቆጣጠር 9am ይደረጋል::  በአቤቶታ ሰልፉ ላይ ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን አማኝ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ልዩነት ሳይገታቸው በአንድነት ድምጻቸውን እንዲያሰሙ አዘጋጆቹ የአደራ ጥሪ አስተላልፈዋል::

  የታላላቅ ገዳማት ህልውና መጠበቅ ለቤተ ክርስቲያናችን ህልውና መጠበቅ ስለሆነ በተለያየ ዘርፍ የተከፋፈሉት የቤተ ክርስቲያኒቷ ልጆች በዚህ እንዲተባበሩ አሐቲ ተዋሕዶ ጥሪዋን ታስተላልፋለች::

  እግዚአብሔር አሐቲ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን!!!


  Wednesday, March 7, 2012

  ሰበር ዜና - ፍ/ቤቱ በመ/ር ዘመድኩን ላይ ፈረደ

  በመምህር ዘመድኩን ላይ ኢ-ፍትሐዊ የቅጣት ውሳኔ ተላልፎበታል:: ሙሉ ዘገባ ከደጀ ሰላም ደርሶናል::
  ዘገባውን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ PDF::

  Tuesday, March 6, 2012

  በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየተደረገው ያለውን በደል ለመቃወም የተጠራ ሕዝባዊ የአቤቶታ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ

   READ IN PDF
  ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ቤተ ክርስቲያናችን ቀድሞ የነበራት ክብር እያጣች የዘመኑ ተሿሚዎች ከጠቅላ ቤተ ክህነቱ እና ከቤተ መንግስቱ በደል እየደረሰባት መሆኑ የአደባባይ ላይ ሚስጥር እየሆነ ነው:: በዚህ የተማረሩ የቤተ ክርስቲያኒቷ አማኞች በደሉ በቃን፣ የቤተ ክርስቲናችን የቀደመ ክብሯ ይመለስ፣ መንግስት ከቤተ ክርስቲያናችን ላይ እጁን ያንሳ፣ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የቤተ ክርስቲያናችን መብት ያስጠብቅ በማለት ሕዝባዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ እና በመላው ዓለም ታላላቅ ከተሞች ላይ ተጠርቶዋል::
  የሕዝባዊ ሰልፉ ዓላማ በአዘጋጆቹ እንደሚከተለው ቀርቦዋል:-


  •  የኢትዮጵያ መንግስት በልማት ሰበብ በዋልድባ ገዳም የሚያደርሰውን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ባስቸኳይ እንዲያቆም ለመጠየቅ
  •  በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እና የሀገርን ቅርስ ለማጥፋት እና ለማውደም የሚሯሯጡትን የውጪ ቅጥረኞች  መንግስት፣ እንደ መንግስትነቱ ሊከታተል እና ለፍርድ እንዲያበቃ ለመጠየቅ
  • በተለያዩ የኢትዮጵያ ገዳማት፣ አድባራት፣ ቤተ-እምነቶቻችን ላይ በተለይ በአክራሪ ሙስሊሞች እየደረሰ ያለውን እንግልት፣ ጠባጫሪነት፣ ስደት፣ እና የሰው ነፍስ የማጥፋት ዘመቻ እንዲያስቆም እና ፍትህ እንዲሰፍን ለመጠቆም
  •  በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ ተንሰራፍቶ ስላለው የሙስና፣ የዘመድተኝነት፣ እና የተንኮል ሥራዎችን እንዲያስቆም እና አስፈላጊውን ምርመራ አድርጎ፣ ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርቡ
  የሚሉ ናቸው::   

  ይህንን ዓላማ የሚደግፉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ዓማኞች እና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መብት እንዲጠበቅ የሚደግፉ ሁሉ ሰልፉ በሚደረግባቸው ከተማዎች እንዲገኙ አዘጋጆቹ ጋብዘዋል::

  እግዚአብሔር አሐቲ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን!!!