Monday, April 30, 2012

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተማላጅ እንጂ አማላጅ አይደለም::

የተሐድሶ መናፍቃኑ አንደበት ደጀ ብርሃን ድረ ገጽ “ክርስቶስ አማላጅ ነው” በማለት በዛሬው ዕለት የእምነት አቋሙን የገለጹበት ጽሑፍ አውጥቶዋል:: ደጀ ብርሃን፣ አባ ሰላም እና ሌሎችም በስም እኛን መስለው የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎች በጎቹን ከበረት ለማስወጣት እጀ ለእጅ በመያያዝ የምንፍቅና ትምህርታቸው በማስተላለፍ ላይ ይገኛሉ:: በጣም በሚያዛዝን ሁኔታ የቤተ ክርስቲያኒቷን ደሞዝ እየበሉ በጠቅላይ ቤተ ክህነት እነ አባ ሠረቀ ወልደ ሳሙኤል እና ዲ/ን ኃይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን ለእነዚህ የመናፍቃን ብሎጎች መረጃ በማቀበል ተባባሪ እንደሆኑ በቂ መረጃዎች አሉን::
          የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክ ወልደ አምላክ ብላ ታምናለች፤ ታስተምራለችም:: ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  ተማላጅ እንጂ አማላጅ እንዳልሆነ ቅዱሳን መጻሕፍ ይናገራሉ:: በዚህ በተሐድሶ መናፍቃን ደጀ ብርሃን ድረ ገጽ ለወጣው የምንፍቅና ትምህርት ምላሽ ይሆን ዘንድ የሚከተለውን የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ የሚገልጽ ጽሑፍ አቅርበንላችኋል:: ጽሑፉን የወሰድነው ከቤተ ደጀኔ ብሎግ ነው:: 
+++

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእርሱን ማንነት ገልጦ ያስተማረበት ትምህርት ነው። በዚህም ትምህርቱ፥ እርሱ የበጎች እረኛ እንደሆነ፥ የበረቱም በር እርሱ መሆኑን ተናግሯል። እውነት የባህርይ ገንዘቡ ስለሆነም፥ ትምህርቱን «እውነት እውነት እላችኋለሁ፤» በማለት ጀምሯል። በዚህም አማናዊ በሆነ ትምህርቱ «ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ፥ በሌላም በኲል የሚገባ ሌባ፣ ወንበዴም ነው፤» ብሏል። ይኽንንም ስለ ሦስት ነገር ተናግሮታል።

Sunday, April 29, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን እና ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮሰ ካልዕ በዓላማ አንድ ናቸው፤ይተዋወቃሉም

አሐቲ ተዋሕዶ ብሎግ  የማኅበረ ቅዱሳን አይደለችም:: ማኅበረ ቅዱሳን የሚያስተዳድራቸው የራሱ የሆኑ በተለያዩ ማዕከላት ብዙ ድረ ገጾች እንዳሉት እናውቃለን::
ማኅበረ ቅዱሳን ለሚያከናውናቸው በጎ ሥራዎች ደጋፊዎች ነን:: በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በጠቅላላው ዓለም ማኅበሩ የሚያከናውናቸው ማሕበራዊ እና መንፈሳዊ ሥራዎች እናዳሉት የዐይን ምስክሮች ነን:: ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያናችን ብሎም ለሀገራችን ኢትዮጵያ የተማረውን ሀይል አስተባብሮ በመያዝ እግዚአብሐርን የሚፈራ እና ከሙስና የጸዳ ትውልድ እንደፈጠረም በሙሉ ልብ እንመሰክራለን:: እንዲሁም ደግሞ ምሁራኑ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በጉልበታቸው፣ በእውቀታቸው እና በገንዘባቸው በነጻ ቤተ ክርስቲያናቸውን ለማገልገል ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ደፋ ቀና ሲሉ በተለያዪ ቦታዎች እናውቃቸዋለን:: የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በብሔር፣ በፖለቲካ እና በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች ሳይከፋፈሉ በአንድነት ሆነው ስለ እውነት ሲሰሩ አይተናል ሰምተናልም:: ስለዚህ ይህ ማኅበር ፍጹም የአገልግሎት ማኅበር ነው ብለን ብንናገር ማጋነን አይሆንብንም::

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ማናቸው? በዲያቆን ዳንኤል ክብረት

READ IN PDF
የተሐ መናፍቃን አቀንቃኝ አደበት/ሚድያ የሆነው “አባ ሰላማ” ብሎግ በማያፍር አንደበቱ እግዚአብሔር ያከበራቸውን ቅዱሳን መሳደብ ቀጥሎዋል:: ይህ ብሎግ በስሙ የተዋሕዶ በማስመሰል ነገር ግን የሚያወጣቸው ጽሑፎች ከቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ የሚቃረኑ የምዕራባውያኑ የፕሮቴስታንቶች አንደበት እንደሆነ በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወቃል:: ቤተ ክርስቲያናችን ለሚያውቃት ምልዑ ናት:: ለሁሉም መልስ አላት:: የቀደሙት አባቶቻችን ብራና ፍቀው በደማቸው ቀለም በጥብጠው ሁሉንም ነገር አሟልተው መጽሐፍት አስቀምጠውልናል:: በየ ጊዜው ለተነሱት መናፍቃን ተገቢውን ምላሽ እየሰጡ አሳፍረ መልሰዋቸዋል:: አሁን እነደ አዲስ የተነሱት የተሐድሶ መናፍቃን አቀንኞች የቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት/መድረክ ሲያጡ የቅሰፋ ትምህርታቸውን በኢንተርኔት ማሰራጨት ጀምረዋል:: አባ ሰላማ የተሰኘው ይኸው የመናፍቃኑ ብሎግ ሰሞኑን ባስነበበው አሳፋሪ ጽሑፍ ማኅበረ ቅዱሳን የኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባት የተክለ ሃይማኖትን አስተምህሮ ይከተላል በማለት ክስ አቅርቦዋል:: ቅዱሱ አባታችንን ለዘለፉበት ምላሽ ይሆን ዘንድ ከዚህ በፊት በዲያቆን ዳንኤል ክብረት ቅዱሳን መጻሕፍትን መሠረት በማድረግ ያቀረበው ጽሑፍ እንደ ሚከተለው አቅርበነዋል::
ሙሉ ጽሑፉን ያገኘነው ከዳንኤል ክብረትእይታዎች ድረ ገጽ ላይ ነው::
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ማናቸው?
አቡነ ተክለ ሃይማኖት 1186 ዓም በሰሜን ሸዋ ቡልጋ ጽላልሽ ተወለዱ፡፡ አባታቸው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሲያስተምሯቸው አካባበቢያቸው ደግሞ በዘመኑ የነበሩ ልጆች ይማሩ የነበረውን ፈረስ መጋለን፣ ቀስት መወርወርን፣ እርሻን እና አደንን አስተምረዋቸዋል፡፡

Thursday, April 26, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤትን በ4.6 ሚሊዮን ብር ለመገንባት ውል መፈረሙን ገለጸ

ሙሉ ዘገባውን የወሰድነው ከማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ  ላይ ነው::


Gedamate 3ማኅበረ ቅዱሳን በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የሚገኘውን የደብረ ኀይል ወደብረ ጥበባት በዓታ ለማርያም የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤትን በ4.6 ሚሊዮን ብር ለመገንባት ሚያዚያ 12 ቀን 2004 ዓ.ም. የግንባታ ውል ስምምነት ከአስማማው አያሌው ሕንጻ ሥራ ተቋራጭ ጋር ተፈራረመ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ልማት ዋና ክፍል አስተባባሪነት የሚከናወነው ይኸው ፕሮጀክት ማኅበረ ቅዱሳንን በመወከል የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ዲ/ን ሙሉጌታ ኀ/ማርያምና የሕንፃ ሥራ ተቋራጩ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ አስማማው አያሌው አማካይነት የፊርማ መርሐ ግብሩ ተፈጽሟል፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጽ/ቤት በተከናወነው የፊርማ መርሐ ግብር ላይ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ዲ/ን ሙሉጌታ ኀ/ማርያም ባደረጉት ንግግር ‹‹ 4.6 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ፕሮጀክት ቀርጾ የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤት ለመገንባት ከዚህ በፊት አድርገነው አናውቅም፡፡ ይህ ትልቅ እድገት ነው፡፡ ምእመናንም ማኅበረ ቅዱሳንን ማመን የቻሉበት ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አውጥቶ ማኅበረ ቅዱሳን ይሥራው ለማለት መቻል ሙሉ ለሙሉ በማኅበሩ ላይ እምነት እንዳሳደሩ ነው የሚያሳየው፡፡ እኛም በታማኝነት ትኩረት ሰጥተን እንድንሠራ የሚያደርገን ነው፡፡ ጨረታውን ከብዙዎቹ የሕንጻ ሥራ ተቋራጮች ጋር ተወዳድሮ ያሸነፈው ድርጅት በማኅበሩ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገና አብሮ የኖረ ነው፡፡ ሥራውንም በጥራትና ከተያዘለት ጊዜ ቀደም ብሎ በማጠናቀቅ ያስረክባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን በኩልም ሥራውን ለማፋጠን አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጣለሁ›› በማለት ገልጸዋል፡፡

Tuesday, April 24, 2012

አቡነ ፋኑኤል አዲስ አበባ ናቸው

  • በጉጉት የሚጠብቁትን ደብዳቤ ከፓትርያርኩ አግኝተዋል፤ 
  • ብፁዓን አባቶች በቅ/ሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ በጥብዓት ሐሳባቸውን ከሰጡ የአሜሪካ ምእመናን ከገቡበት የሐዋሳ ዓይነት ፈተና እና መከራ ይታደጓቸዋል ተብሎዋል
  ሙሉውን ዘገባ የወሰድነው ከደጀ ሰላም ነው:: 
አወዛጋቢው የአሜሪካ ሁለት አህገሩ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቅዳሜ አዲስ አበባ ገብተዋል፤ በመላው አሜሪካ የተነሣባቸውን ተቃውሞ ለማድበስበስ እና ከአሜሪካ እንዳይነሡ ለማድረግ እንደተዘጋጁ የደጀ ሰላም ምንጮች አስታወቁ። በአሜሪካ የተቀሰቀሰባቸውን ተቃውሞ የሚያበርድ ደብዳቤ ከፓትርያርኩ አግኝተዋል።

Monday, April 23, 2012

“እኛ «አክራሪ» የሚለውን ቃል በጥንቃቄ ነው የምንመረምረው” የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ

የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም በአጠቃላይ የማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎት አስመልክቶ ከዚህ በፊት ከስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ አድረገው ነበረ:: በዚህ ቃለ ምልልሳቸው አክራሪነትን እና የማኅበሩ የፖለቲካ ተሳትፎ በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ የማኅበሩን አቋም በመንተራስ ምላሽ ሰጥተው ነበረ:: ይህ አስቀድሞ ምላሽ የተሰጠበት አሁን ወቅታዊ ሆኖ ስላገኘነው ከቃለ ምልልሱ ቀንጨብ አድርገን በአክራሪነት እና የፓለቲካ ጉዳይ የሰጡት ቃል እንደሚከተለው አቅርበነዋል:: ሙሉ ቃለ ምልልሱን የወሰድነው ከማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ላይ ነው::
 
ስምዐ ጽድቅ፡- ማኅበሩ አክራሪ ነው ስለሚባለውስ?
ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ፡- እኛ «አክራሪ» የሚለውን ቃል በጥንቃቄ ነው የምንመረምረው::  አክራሪ ማለት የሃይማኖቱን ሕግ አክብሮ የሚኖር ተግቶ የሚጾም፣ የሚጸልይ በሃይማኖቱ ላይ ለሚነሡ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ፣ ታሪኩን፣ ቤተክርስቲያኑን የሚወድ፣ ለሃይማኖቱ የሚቀና የማይዋሽ ወይም ወደ ከፍተኛ ሥነ ምግባራዊ ሕይወት ራሱንም የሃይማኖት ወገኑን ሁሉ ለማድረስ የሚተጋ ከሆነ የማኅበራችንን አባላት ሊገልጽ ይችላል፡፡ ሰዎች ምናልባት በልማድ በዚህ ብያኔ ለመጥራት ፈልገው ከሆነ ችግር ላይኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን በዚህ ሁኔታ የሚመላለሱትን ክርስቲያኖች «አክራሪ» ተብለው ከሚጠሩ አጥባቂ፣ ዐቃቤ ሃይማኖት ቢባሉ የተሻለ ነው፡፡

Saturday, April 21, 2012

“ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት አልስማማም” ኤፍሬም እሸቴ

ዲያቆን ኤፍሬም እሸቴ የተባሉ የማኅበረ ቅዱሳን አባል ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር አቶ መለስ ዜናዊ ማኅበረ ቅዱሳንን  ከአሸባሪዎች ጋር ፈርጀው በተወካዮች ምክር ቤት የተናገሩትን በግል እንደማይቀበሉት ገለጹ:: ዲ/ን ኤፍሬም እሸቴ የጠቅላይ ሚኒስተሩ እውነታን ያላገናዘበ የሰጡት ቃል እጀግ በጣም ከባድ እንደሆነ የግል አቋማቸውን በገለጹበት ጡመራ ላይ ገልጸዋል::  እንዲሁም ደግሞ “ሰለፊዎች(አልቃይዳዎች) አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱት ግልባጭ ሲያራምዱ ታይተዋል” በማለት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ የተናገሩት አስቀድሞ የተሐድሶ መናፍቃን ማኅበሩን ለመወንጀል ይጠቀሙበት የነበረ ቃል ነው:: አሁን በመንግስት በኩል የጠ/ሚኒስትሩ አጭርና ብዙ መልእክት የተሸከመች ዐረፍተ ነገር “እነዚያ መንግሥትን ተገን አድርገው ቤተ ክርስቲያኒቱን ፕሮቴስታንታዊ ለማድረግ የሚሞክሩ ሰዎች/ ተሐድሶዎች መንግሥትን ለዓላማቸው መጠቀሚያ ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት ተሳካላቸው ማለት ነው?” የሚል ስሜት ያጭራል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል::

ሙሉ ጽሑፉን ያገኘነው ከአደባባይ ነው::

(READ IN PDF)

ማክሰኞ ሚያዚያ 9/2004 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ እንደተለመደው የምክር ቤቱ ክቡራን አባላት በንባብ ላቀረቡላቸው ጥያቄዎቻቸው መልስ ሲሰጡ ተከታትያለኹ። ከጥያቄዎቹ አንዱ ወቅታዊው የሙስሊሞች ጉዳይ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምሻቸው “መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ አልገባም” የሚለውን በሰፊው ሲያብራሩ ቆዩ። አንዱ ማብራሪያቸው ስለ ሰላፊያዎች (አል-ሰላፊያ ወይም ወሐቢያዎች) ነው። ራሳቸውን “አል-ሰላፊዩን” የሚሉትና ትክክለኛውን የቁርዓን ትምህርት እንከተላለን የሚሉት የሙስሊም ክፍል የሆኑትና መሠረታቸውን በሳዑዲት አረቢያ ያደረጉት ጽንፈኛ ወገኖች በተቃዋሚዎቻቸው ደግሞ “ወሐቢያዎች” ይባላሉ። የዚህ ጽሑፍ ዓላማ ስለ ወሐቢያዎች እና ስለአክራሪነታቸው ማተት ስላልሆነ የዚህን ቡድን አስተምህሮ እና በኢትዮጵያ ላይ ስለ ጋረጠው ከፍ ያለ አደጋ “አክራሪ እስልምና በኢትዮጵያ” (ኤፍሬም እሸቴ፣ በ2000 ዓ.ም/ 2008 የታተመ) የሚለውን መጽሐ ማንበብ እንደሚቻል በመጠቆም አልፋለኹ 

Thursday, April 19, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን ከሰለፊ/ከአልቃይዳ ጋር ፈጽሞ ሊመሳሰል አይችልም::

  • “ኢትዮጵያ ውስጥ አልቃይዳዎች በሙሉ ሰለፊ ናቸው:: ሰለፊዎች(አልቃይዳዎች) አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱት ግልባጭ ሲያራምዱ ታይተዋል” ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ የተናገሩት  


የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ”ማኅበረ ቅዱሳን  ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ግኑኝመት አለው” በማለት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ እና የዛኔው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር አቶ አባይ ፀሐዬ ማስጠንቀቂያ ሰጥተውት እንደነበረ ይታወሳል:: አቶ ስብሃት ነጋ(ኦቦይ ስብሃት) እለተ አርብ ሰኔ 30፣2003 ዓ/ም ለፍትሕ ጋዜጣ በሰጡት ቃል ”ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክህነት እዳ ነው:: የቤተ ክህነት አስተዳደር ለማሻሻል መጠነኛ እንቅስቃሴ ሲጀመር ገንቢ ተራ ከመጫወት አፍራሽነት ይበዛበታል፣ ብልሽት እያየ ዝምታ ያበዛል፣ ማኅበረ ቅዱሳን የፖለቲካ መድረክ ይታይበታል፣ማኅበረ ቅዱሳን በሕገ መንግሥት ክህደት ወንጀል ይጠረጠራል” በማለት ተናግረው ነበረ::

ማክሰኞ ሚያዝያ 9፣2004 ዓ/ም ክቡር ጠቅላይ ሚኒተር መለስ ዜናዊ በፓርላማ ንግግራቸው ላይ ማኅበረ ቅዱሳንን ከዓለም አቀፍ አሸባሪ ድርጅት ከአልቃይዳ ጋር አመሳስለውታል:: ክቡርነታቸው ከምን አይነት መረጃ እና ማስረጃ ተነስተው ማኅበረ ቅዱሳን ከአሸባሪ ድርጅት ጋር እንዳመሳሰሉት ሰፋ ያለ ገለጻ አልሰጡም:: በደፈናው ግን “አልቃይዳ/ሰለፊ አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱት ግልባጭ ያራምዳል” አሉ::

Wednesday, April 11, 2012

ጸሎተ ሐሙስ

ነቢያት በሀብተ ትንቢት በመንፈሰ ትንቢት ‹‹እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት›› /መዝ. 117፥24/ በማለት ትንቢት የተናገሩላት በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ትላልቅ የተባሉ ምሥጢራት የተፈጸሙባት ዕለት ናት፡፡

“እግዚአብሔርም በግብጽ አገር ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው ይህ ወር የወሮች የመጀመሪያ ይሁናችሁ የዓመቱም የመጀመሪያ ወር ይሁናችሁ፡፡ ለእስራኤል  ልጆች ሁሉ ተናገሩ፥ በሉአቸውም በዚህ ወር በአሥረኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአባቱ ቤት አንድ ጠቦት ለአንድ ቤትም አንድ ጠቦት ይውሰድ፡፡ የቤቱ ሰዎች ቁጥርም ለጠቦቱ የማይበቃ ቢሆን እርሱና ለቤቱ የቀረበው ጎረቤቱ እንደነፍሶቻቸው ቁጥር አንድ ጠቦት ይውሰድ እያንዳንዱም እንደሚበላው መጠን ከጠቦቱ ይካፈሉ፡፡ የእናንተ ጠቦት ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ይሁን ከበጎች ወይም ከፍየሎች ውሰዱ በዚህም ወር እስከ አሥራ አራተኛ ቀን ድረስ ጠብቁት፡፡ የእስራኤልም ጉባኤ ሁሉ ሲመሽ ይረዱት፡፡ ከደሙም ወስደው በሚበሉበት ቤት ሁለቱን መቃንና ጉበኑን ይቀቡት፡፡ በእሳት የተጠበሰውን ሥጋውንና ቂጣውን እንጀራ በዚያች ሌሊት ይብሉ ከመራራው ቅጠል ጋር ይበሉታል ጥሬውን በውኃ የበሰለውን አትብሉ ነገር ግን ከራሱ ከጭኑ ከሆድ ዕቃው ጋር በእሳት የተጠበሰውን ብሉት ከእርሱም እስከ ጧት አንዳች አታስቀሩ እስከ ጧትም የቀረውን በእሳት አቃጥሉት ወገቦቻችሁን ታጥቃችሁ፥ ጫማችሁን በእግራችሁ በትራችሁንም በእጃችሁ አድርጋችሁ እንዲህ ብሉት፡፡ ፈጥናችሁም ትበሉታላችሁ እርሱ የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው፡፡ እኔም በዚያች ሌሊት በግብጽ አገር አልፋለሁ… ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁንላችሁ፥ ለእግዚአብሔርም በዓል ታደርጉታላችሁ ለልጅ ልጃችሁም ሥርዓት ሆኖ ለዘላለም ታደርጉታላችሁ /ዘዳ.12፥1-15/፡፡

Tuesday, April 10, 2012

ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በአጸደ ሕወት እያሉ በገናን አስመልክቶ ያስተማሩት

የቃለ ዓዋዲው ክለሳ በውጭ ያለውን አገልግሎት ያካትት/የሰሜን አሜሪካን ቤተ ክርስቲያን ልዩ ትኩረት ቢሰጣት

ሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በርካታ ለውጦች የተስተናገዱበት ነበር፡፡ ከለውጦቹ ውስጥ ደግሞ ዋና ዋናዎቹ ሁለት ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ የመጀመሪያው ለውጥ በውድ የመጣ ይልቁንም ለውጡ እውን ይኾን ዘንድ ከ0ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ነገሥታትና ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት የተጋደሉለት ለውጥ ነው፡፡ ይኸውም የቤተ ክርሰቲያኗን አስተዳደር ለ1600 ዘመናት በቅብጥ ቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር እንዲቆይ ያደረገው ሊቃውንት መንበረ ጵጵስናውን ትንሽ ቆይቶም መንበረ ፕትርክናውን ተረክበው ዕውቀት መንፈሳዊ እየመገበች ያሳደገቻቸውን ቤተ ክርስቲያን መምራት የጀመሩበት የለውጥ ምዕራፍ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ቤተ ክርስቲያኗ ለሀገር ለሕዝብ ለምትሰጠው አገልግሎት ዋጋ ይኾናት ዘንድ ከነገሥታት ተሰጥቷት የነበረው ርስት ጉልት ተነጥቆ «ራስሽን ቻይ» የተባለችበት የግድ ለውጥ ነው፡፡

ሰሙነ ሕማማት (ማክሰኞ)

በዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡ ጥያቄውም “በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?” የሚል ነበር፡፡ የካህናት አለቆች ያቀረቡት ጥያቄ ነበር፡፡ ጌታችን ሰኞ ዕለት ሁለት ነገሮችን ማድረጉን ተያይዞ የተነሣ ጥያቄ ነው፡፡ ሰኞ ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ ያላገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፤ በማስከተል ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ ማቴ.21÷23-25፤ ማር.11÷27፣ ሉቃ.20÷1-8፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩት ተአምራትና የኃይል ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀናቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀየሱት ስልት ነው፡፡

Monday, April 9, 2012

ሰሙነ ሕማማት /ሰኞ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከትንሣኤ በፊት ያለውን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት /የሕማማት ሳምንት/ በማለት ትዘክረዋለች፡፡ ሕማማት የሚለው ቃል “ሐመ፤ ታመመ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን የጌታችንና የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማምና ሞቱ የሚዘከርበት ሳምንት ነው፡፡ በሌላም በኩል ይህ ሳምንት ከአዳም እስከ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ የነበሩ ነፍሳት በሲኦል የቆዩበት የአምስት ሺህ አምስት መቶ የመከራ፣ የፍዳና የኩነኔ ዘመን መታሰቢያ ስለሆነ የሕማማት ሳምንት የሚለውን ስያሜ አግኝቷል፡፡ እንደዚሁም ይህ ሳምንት “ቅዱስ ሳምንት” ይባላል” ከሌሎች ሳምንቶች ሁሉ የተለየ የከበረ ነውና፡፡ ምክንያቱም በዚህ ሳምንት በእያንዳንዱ ዕለት ስለ ፍጹም ፍቅር የተከፈለ የመሥዋዕትነት ሥራ ስለ ተሠራበት፣ የሰው ልጆች ደኅንነት ስለ ተፈጸመበት፣ መድኀኔዓለም ስለ እኛ ቤዛ ሆኖ ለመስቀል ሞት ታዛዥ ሆኖ ነፍሱን ስለ ካሠልን “ቅዱስ ሳምንት” ተብሏል፡፡ በተጨማሪም “የመጨረሻ ሳምንት” ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በሙዓለ ሥጋዌው ለፈጸማቸው የቤዛነትና የአርአያነት ተግባራት ፍጻሜ በመሆኑ ነው፡፡

Friday, April 6, 2012

ዲያቆን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን “የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት” ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ተሾመ

READ IN PDF
በተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ የሆነው እና ከዚህ በፊት በነበረው የሃይማኖት ችግር ከማኅበረ ቅዱሳን ተባሮ   የወጣው ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን በቅዱስ ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሁለተኛ ሹመት ተሰጠው:: በማኅበረ ቅዱሳን ታሪክ በሕጋዊ ደብዳቤ ከአገልግሎት በመታገድ ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን የመጀመርያ ሰው መሆኑን ከማኅበሩ ጋር ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ገልጸውልናል:: በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ተፈርመው ለሚወጡ ደብዳቤዎች ዋና አዘጋጅ እና አማካሪ ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን “የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት” ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ተሹሞዋል::

Thursday, April 5, 2012

ከክህነት ስለሚያስሽሩ ምክንያቶች አንዳንድ ነጥቦች ከፍትሐ ነገሥት

ካህናትን ከክህነታቸው ስለሚያሽሩ ምክንያቶች
አንዳንድ ነጥቦች ከፍትሐ ነገሥት
ከደጀ ሰላም ያገኘነው ዘገባ ነው::
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ሀ/ስብከት አዲስ ሊቀ ጳጳስ ተሹሞ ተልኳል ከተባለበት ከጥቅምት ወር 2004 ዓ.ም ጀምሮ በችግር ላይ ይገኛል። ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በሀ/ስብከቱ ውስጥ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በቃለ ዓዋዲው መሠረት የመረጡትን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አልቀበልም ከማለት አልፈው ካህናቱን በሙሉ ማስፈራራት እና አንዳንዶቹንም “አውግዣለሁ” ማለት ጀምረዋል። ይህም መነሻ ሆኖን “ካህናትን ከክህነታቸው ስለሚያስሽሩ ምክንያቶች”፣ በደፈናው ከመሬት ተነሥተው “ክህነት ይዣለሁ” ስለሚሉ አቡነ ፋኑኤልን ስለመሳሰሉ ጳጳሳት አስቀድመው በቅዱሳን አበው የተሠራውን ሕግ በተመለከተ ፍትሐ ነገሥቱ የሚለውን ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን።

የአቡነ ፋኑኤል ድርጊት ተወገዘ ፤ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላትም ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቀሷል

     READ IN PDF
  በቂ እውቀት እና ምስክርነት ሳይኖራቸው ወደ ጵጵስና ሥልጣን የወጡት አቡነ ፋኑኤል ፤ በአሜሪካ ውስጥ እያደረጉ ባሉት ቤተ ክርስቲያንን የማዳከም እንቅስቃሴ  የተነሳ የአባትነት ክብራቸውን በከፍተኛ ፍጥነት በማጣት ላይ ይገኛሉ ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር መዋቅር ሥር የሚገኙት በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ  ስብከተ፣ እና የካሊፎርኒያንና የምእራብ እስቴቶች  ሀገረ ስብከት አብዘኛዎቹ አብያተ ክርስቲያናት  ዘንድ ተቀባይነትን አጥተዋል:: የተሰጠን የክህነት ተግባር በማቃለል ላይ የሚገኙት አቡነ ፋኑኤል አባትነታቸውን የሚቀበላቸው በማጣት ላይ ናቸው:: በተያያዘ ዜና ብጹዕነታቸው ከ250, 000 ዶላር በላይ የአሜሪካ መንግሥት ሳያውቀው በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ይዘው በመውጣታቸው ዙሪያ  ሕጋዊ  ጥያቄ እየቀረበላቸው መሆኑን ለአሐቲ ተዋሕዶ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል።

የሰሜን አሜሪካ እና የካናዳ ምእመናን ለሦስተኛ ጊዜ በዋልድባ ገዳም ጉዳይ በተመለከተ ስብሰባ አካሄዱ

  •    “ከእንግዲህ ወዲህ በቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ላይ አባቶችን አንጠብቅም” ተሳታፊ
  •   ቤተ ክህነት ለቤተ ክህነት ሰዎች፤ ቤተ መንግስቱም ለፖለቲከኞች መንግስት በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ አይግባ፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከፖለቲካ ወገንተኝነት ይጽዱ” የስብሰባው ተሳታፊዎች
ዛሬ መጋቢት 26 ፣2004 ዓ/ም ለሦስተኛ ጊዜ በዋልባ ገዳም ጉዳይ እና በቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመወያየት በካናዳ እና በአሜሪካን እስቴቶች የሚኖሩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች በኮንፈረንስ ስልክ ተሰባስበዋል:: በዋሽንግተን ዲሲ የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 9pm በዊስስት ኮስስት አቆጣጠር  ደግሞ 6pm ላይ ከአራት መቶ ሃምሳ(450) በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት ስብሰባው ተካሄዶዋል:: የስብስባው አስተባባሪ በጸሎት ካስጀመሩ በኋላ አክራሪው የእስልምና ቡድን በቤተ ክርስቲያናችን እያደረሰ ያለውን ጥፋት በተመለከት ከተለያዩ የአክራሪዎቹ ሚድያ የተቀረጹ ከአክራሪዎቹ አንደበት በድምጽ ተሰምቶዋል:: በተለይ በዚህ በሃያ ዓመታት ጊዜ ውስጥ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ያደረሱት ጥፋቶች እንደ መግቢያ በስብሰባው አስተባባሪ ለተሳታፊዎች ቀርቦዋል:: የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ቸልተኝነት ለደረሰው ጥፋት እና ለጥፋቱ መባባስ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳበረከተ ተገልጾዋል::

Tuesday, April 3, 2012

“ጥይት እንደሌለው ጠመንጃ፣ ሥልጣን የሌለው ‘ውግዘት’” ከአንባብያን ለብጹዕ አቡነ ፋኑኤል የተላለፈ መልዕክት

 READ IN PDF
 የሚከተለውን መልዕክት ከአንድ አስታያየት ሰጪ ምዕመን የደረሰን ነው:: 
በቤተ ክርስቲያን ውግዘት ሁለት ዓይነት ነው። በክህነት የሚተላለፍ ውግዘት እና አስቀድሞ የተወገዘ ድርጊት። በርዕሱ “ጥይት እንደሌለው ጠመንጃ ሥልጣን የሌለው ውግዘት” ያልኩት በተወገዘ ድርጊት የተሠማሩ ባለሥልጣን ነን ባዮች የሚያስተላልፉትን ‘ውግዘት’ ነው።
በሕገ ቤተ ክርስቲያናችን የተወገዙ ድርጊቶችን የሚያደርግ ውጉዝ ወይም የተወገዘ ነው። በፍትሐ ነገስት ከሥልጣነ ክህነት የሚያሽሩ ወይም የተወገዙ ድርጊቶችን ከምዕመናን እሰከ ጳጳሳት ያሉትን ይመለከታል። በተለይ ካህናትን እና መነኮሳትን አስመልክቶ፦
1. መነኩሴ በገዳም ተወስኖ እንዲኖር
2. ካህን ያለ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ያለ ጳጳስ ፈቃድ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንደፈለገ እንዳይዘዋወር
3. ጳጳስ ከሀገረ ስብከቱ ውጪ በሌላው ሀገረ ስብከት ያለፈቃድ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን በተለይም ሢመተ ክህነትን እንዳይፈጽም
ያዛል።

በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ዘገባ (ክፍል ሁለት)  •   በዋልድባ ጉዳይ የጎንደር ወጣቶች ሊቀ ጳጳሱን አነጋገሩ::
  •   በዋልድባ ጉዳይ የጎንደር ወጣቶች ሊቀ ጳጳሱን አነጋገሩ::
  • በዋልድባ ወጣቶች ወደ ፕሮጀክቱ አካባቢ እንዳይደርሱ በፖሊስ ታግደዋል::
  • የማኅበረ ቅዱሳን አጥኚ ቡድን ነገ ወደ ዋልድባ ያመራል::   
    ሙሉ ዘገባውን ያገኘነው ከደጀ ሰላም ነው:: READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የጎንደር ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች ጥምረትና የጥምቀት በዓል አከባበር ወጣቶች ማኅበራት ጥምረት ኮሚቴዎች፣ በማኅበረ ቅዱሳን የስድስቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያት ሥራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም የጎንደር ማእከል ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ጋራ መነጋገራቸው ተሰማ፡፡