Friday, April 6, 2012

ዲያቆን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን “የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት” ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ተሾመ

READ IN PDF
በተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ የሆነው እና ከዚህ በፊት በነበረው የሃይማኖት ችግር ከማኅበረ ቅዱሳን ተባሮ   የወጣው ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን በቅዱስ ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሁለተኛ ሹመት ተሰጠው:: በማኅበረ ቅዱሳን ታሪክ በሕጋዊ ደብዳቤ ከአገልግሎት በመታገድ ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን የመጀመርያ ሰው መሆኑን ከማኅበሩ ጋር ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ገልጸውልናል:: በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ተፈርመው ለሚወጡ ደብዳቤዎች ዋና አዘጋጅ እና አማካሪ ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን “የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት” ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ተሹሞዋል::
        
  

ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን በቅዱስ ፓትርያርኩ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ለሰሜን አሜሪካ ውጪ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት ሓላፊ ተብሎ መሾሙ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል:: ይህ የውጪ ጉዳይ ተጠሪ ጽ/ቤት በጥቅምት ወር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ህልውና እዳይኖረው ተሽሮ ነበረ፤ አሁን ግን ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል ጽ/ቤቱን እውቅና ሰጥተውት ደብዳቤ ሲጽፉ ግላባጭ ብለው ይገልጹታል:: ነገር ግን ብፁዕነታቸው በሚጽፋቸው ደብዳቤዎች ሁሉ ግልባጭ ለቅዱስ ሲኖዶ ጽ/ቤት አይገልጹም:: የሚጻፉ ደብዳቤዎቹም በቀጥታ በተሐድሶ መናፍቃን ብሎግ “አባ ሰላማ” ላይ እንደሚወጡ ዘግበን ነበረ:: ይህም የሆነበት ምክንያት የብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አማካሪያቸው ኃ/ጊዮርጊስ ከተሐድሶ መናፍቃን ብሎግ ጋር ባለው ግኑኝነት ደብዳቤዎቹም በእርሱ አማካኝነት ይደርሳቸዋል የሚሉ አስተያየቶች እንደደረሱን ዘግበናል::
        ሌላው የሹመት ደብዳቤ የሚያሳየው መልአከ ሰላም ቀሲስ ሰብስቤ ጸጋዬ ናቸው:: ቀሲስ ሰብስቤ ጸጋዬ በተመለከተ የሚከተለውን ዘገባ ከዚህ በፊት አቅርበን ነበረ:: መልአከ ሰላም ቀሲስ ሰብስቤ ጸጋዬ ኪዳነ ምሕረት ወአማኑኤል የሚል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ነበራቸው:: ይህ አጥቢያ “የተከፈተው” ወይም ደግሞ በቤተ ክርስቲያናችን ቋንቋ የተመሠረተው በቀሲስ ሰብስቤ ነበር:: “ተከፍቶ” ለአንድ ዓመት ያህል አገልግሎት ከሰጠ በኋላ ከቀሲስ ሰብስቤ ጋር አብረዋቸው የነበሩ ሰዎች በጥቅም ተጣልተው ሌላ ኪዳነ ምሕረት ወአማኑኤል በማለት እዛው አጠገብ ሌላ አጥቢያ ከፈቱ:: የቀሲስ ሰብስቤ ኪዳነ ምሕረት ወአማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ለሦስት ዓመታት ያህል ከቆየ በኋላ በዘንድሮ ጥቅምት ወር ላይ ተዘግቶ ቀሲስ ሰብስቤ ወደ ሌላ ስቴት ኮብልለው ነበር:: የመዘጋቱም ምክንያት ቀሲስ ሰብስቤ  ከቤተ ክርስቲያኑ የባንክ አካውንት ያለ ሒሳብ ሹም ፈቃድ ለሁለት ዓመታት ያህል ገንዘብ እያወጡ ለግላቸው ሲያውሉ በመቆየታቸው ነው:: በመጨረሻ የነቁት የአጥቢያው ምእመናን አስተዳዳሪው ቀሲስ ሰብስቤ ላይ አጥቢያውን በተመለከተ አንዳንድ ጥያቄ አነሱ:: ቀሲስ ሰብስቤ መልሳቸው “ቤተ ክርስቲያኑ የእኔ ነው፣ እናንተ ምን አገባችሁ” የሚል ነበር:: ምእመናኑም አስተዳዳሪውን ለመክሰስ የሕግ አማካሪ ጋር ሲሄዱ የቤተ ክርስቲያኑ ፈቃድ የተመዘገበው በቀሲስ ሰብስቤ ስም ብቻ መሆኑን ተረዱ:: እንዲሁም የአጥቢያው የባንክ አካውንት በቀሲስ ሰብስቤ ስም ነበር፥ ምእመናኑ ቢከሱም የትም ሊደርሱ እንደማይችሉ ተረዱ:: በመጨረሻም ቀሲስ ሰብስቤ ቤተ ክርስቲያኑ ዘግተው ጠፉ:: አንባቢያን “ታቦቱንስ የት አደረጉት” ትሉ ይሆናል፤ ይህ ደግሞ የእኛም ጥያቄ ስለሆነ ልንሰጣች ልንሰጣችሁ አንችልም::
       ከዚህ በፊትም ቀሲስ ሰብስቤ በተመሳሳይ ሁኔታ በዳላስ ቴክሳስ የከፈቱትን ቤተ ክርስቲያን ዘግተው ነበር ወደ ሜሪላንድ ስቴት የመጡት:: የሜሪላንዱም ሆነ የቴክሳሱ አጥቢያዎች “የተባረኩት” በራሳቸው በቀሲስ ሰብስቤ ነበር:: አስተዳዳሪውም ራሳቸው ነበሩ:: ሁለቱንም አጥቢያዎች ከፍተው የዘጓቸው ቀሲስ ሰብስቤ ናቸው:: እና ታድያ በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል አባባል እነዚህ የቀሲስ ሰብስቤ አጥቢያዎች የክርስቶስ ነበሩ ማለት ነውን? እውነተኛ አባት የተሰበሰቡ በጎቹን በትኖ ይጠፋልን? እኒህ ግለሰብ አሁን በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የተሰጣቸው ሹመትስ ይገባቸዋልን? መልሱን ለአንባቢ እንተወው:: ይህንን ዘገባ ሊንኩን በመጫን ያንብቡ http://www.ahatitewahedo.com/2012/02/blog-post_07.html
        ሌላኛው ተሿሚ ደግሞ በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው  ሲያወዛግቡ የኖሩት መልአከ ኪዳን ቀሲስ ታደሰ ሲሳይ ናቸው:: ቀሲስ ታደሰ በቨርጂንያ አሌክሳንደርያ ግዛት ውስጥ በስማቸው ያቋቋሙት ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ብቻቸውን ቤተ ክርስቲያኑን በባለቤትነት የሚያስተዳድሩ ካህን ናቸው:: እኚህ ካህን በደብሩ ምእመናን በተደጋጋሚ ተከሰው ፍርድ ቤት ቆመዋል:: በመጨረሻም “ቤተ ክርስቲያኑ የግል ንብረቴ ነው” በማለታቸው ምእመናኑ ከቤተ ክርስቲያኑ ለቀው ወጥተዋል:: ይህንን በተመለከተ ከዚህ በፊት ዘግበን ነበረ:: ዘገባውን የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ያንብቡ:: http://www.ahatitewahedo.com/2010/09/blog-post.html
         እንግዲህ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በሰሜን አሜካሪካ ከቀጣፊዎች ጋር በመተባበረ ቤተ ክርስቲያናችን የበለጠ ውስብስብ የሆነ ችግር ውስጥ ሊያስገቧት እንዳቀዱ ይህ ሹመት ምስክር አይሆንምን?
 

6 comments:

Anonymous said...

Kutara Bicha, Mahibere kidusanin anketikito yegeza. Zare alun yemitilutin astemariwoch Betimihirt kifil astemiro lezih yabeka talak menfesawi wondim mehonun mahiberum yawikal. Mahiberu yalewin yepolitica agenda ena abatochin yemekises hidet yetekawomew ke 1988 ethiopian calander jemiro endeneber senior MK members yawikal ke 14 ametat befit.

Zare Mahiberu ye kutara mechawech sayihon Le betekihinet ena le mahiberat yesera wondim endehone hulum Yawikal.

Wondimoch, Meftihew wode nisiha memeles enji yesidib afi LEZENDOW NEW YETESETEW. MK HULUM ALKUAL....hahahaha

Anonymous said...

"Perhaps it would be good to stop listening out for, and holding fast to, the things that make us individual and different. Perhaps we need to focus on the things that we all have in common, that bind us and make us human; the things that make co-operation both crucial and sensible, beneficial to all involved." Mahlet

" Even if I didn't know the orgional or main issue, what u said is absolutly perfect. There is always difference in individual. If we handel our diferences properly it would be a potential for growth otherwise it is a disaster for life and/or progress".Fisseha

Anonymous said...

Negeru Melkam New D Hayile Giyorgis
Awaki mehonu enawkalen enamnalenim
gin hayimanotega sew newy ? alawkim
Degimo sew yemilekaw beewketuna behayimanotu new Mahibere Kidusan Asenabitotal yetebalew kemahiber new eng ketewahedo haymanot aydelem ebakachihu sile dingil Maeiam Mahibere Kidusann kebete kirsitiyan gar atatsalu Mahiberu berkata melkam sira yesera new Ahun mesmerun yelekeke yimeslal D Hayile Giyorgis Sira Askiyag mehon yichilal Kifat Yalebet sew yimesilal Abune Fanueiln masasat yelebetim Ahun Abune Fanueil & Mahibere kIdusann mastarek yigebawal

Anonymous said...

Sew Yemimezenew 1 Be Hayimanotu 2 Beewketu 3 bekum negeru new Ahun washingiton Dc Sira Askyag hono yeteshomew D Hayile Giyorgis Zemenaw timhirt alew Amelekaketum Melkam new Nigigirim yawkal Mahibere Kidusann Gin Ayidegifim Lemhonu yeminfelgew sew Tewahido hayimanotin-Ethiopia Hageru kewedede Ayibekam wey Mahibere Kidusann Degefe aldegefe mebtu new Wedefit bemiseraw sira memezen yigebanal enj gena tesshome bilo mekawem yehayimanot sew liyadergew ayigebam ebakachihu wedefet besiraw enmelketew Abune Fanueilm memekakr alebachew minew sew hulu kifu hone ?mekawem bicha -Adima bicha Melkam newger enasib

Anonymous said...

enanet woregnoch yepoliticaw albeka belachu mahibhere kidusan men yadirgachu le bete kiristian siltekorekore new esu baynorma noro endenant tehadeso betesefafa neber!!

Anonymous said...

አይ... ግብዞች፣ በእናንተ የሰይጣን ማህበር ካልተደገፉ ወይም እርኩስ አላማችሁን ካልደገፉ የወንጌልን ስራ
አይሰሩም ማለትህ ነው አይ አለማወቅ እነርሱ እንደሆነ ትክክለኛ የእግዚአብሔርን መንግስት ሥራ
ነው እያከናወኑ ያሉት ስለዚህ የናንተን አስመሳይ ምክር አይቀበሉምም፤ አያስፈልጋቸወምም። መንፈስ ቅዱስ
ነው መሪያቸው። በማያገባችሁ ገብታችሁ አትፈትፍቱ። የማይታይ የተሰወረ የለምና፣ የተከደነ የማይገለጥ
የለምና። ማቅ ስውር የኦርቶዶክስ ካባችሁን እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ ገልጦ እያሳየን ነውና አታወናብዱ።
ምንም አላችሁ ምንም ከሰይጣን ጋር ህብረት የለንም። ለእናንተ ግን እውነቱን እንዲገልጥላችሁ ዘወትር አጥብቀን
እንፀልያለን። በመጋቢ ሐዲስ ዲያቆን በጋሻው ደሳለኝና በሌሎች የተዋህዶ ክርስቲያኖች ላይ የሰራችሁት ግፍ ገና
ብዙ ብዙ ያሳየናል። ነገር ግን መጋቢ ሐዲስ በጋሻው የጌታን ፆም ምክንያት በማድረግ ወደ ገዳም የሄደው ለምን
ይመስላችሁአል ለእናንተ የምታደርጉትን ለማታውቁት ሊፀልይላችሁ እኮ ነው ሱባኤ የገባው። እርሱማ እንግዲያው
ጌታ እግዚአብሔር የሚወደውና ፀጋውን የሰጠው ልጁ ነው። እናንተም እንደርሱ ፍቅር ቢኖራችሁ የፀጋ ስጦታ
ትቀበሉ ነበር እንጂ፣ በእርሱ የፀጋ ስጦታ ቀንታችሁ ከዲያቢሎስ ጋር አትተባበሩም ነበር። ያም ሆነ ይህ ምንጊዜም
ክርስቲያን ለመሆን ከፈለጋችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ እንድናደርግ ያስተማረንን ማድረግ
እንጂ በተቃራኒው ያላስተማረንን ነገር ማድረግ ለመንግስተ ሰማይ አያበቃም፤ ለገሃነብ እንጂ።
በተረፈ እናስተውል ይግባን፤ ካልገባን ብዙ ጥፋት እናጠፋለን። ገብቶን ደግሞ የምናጠፋ ከሆነ ክርስቲያን የሚለውን
ሥም ለባለቤቱና ለሚገባው እንመልስ።
ምስጋና ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።