Thursday, April 19, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን ከሰለፊ/ከአልቃይዳ ጋር ፈጽሞ ሊመሳሰል አይችልም::

  • “ኢትዮጵያ ውስጥ አልቃይዳዎች በሙሉ ሰለፊ ናቸው:: ሰለፊዎች(አልቃይዳዎች) አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱት ግልባጭ ሲያራምዱ ታይተዋል” ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ የተናገሩት  


የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ”ማኅበረ ቅዱሳን  ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ግኑኝመት አለው” በማለት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ እና የዛኔው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር አቶ አባይ ፀሐዬ ማስጠንቀቂያ ሰጥተውት እንደነበረ ይታወሳል:: አቶ ስብሃት ነጋ(ኦቦይ ስብሃት) እለተ አርብ ሰኔ 30፣2003 ዓ/ም ለፍትሕ ጋዜጣ በሰጡት ቃል ”ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክህነት እዳ ነው:: የቤተ ክህነት አስተዳደር ለማሻሻል መጠነኛ እንቅስቃሴ ሲጀመር ገንቢ ተራ ከመጫወት አፍራሽነት ይበዛበታል፣ ብልሽት እያየ ዝምታ ያበዛል፣ ማኅበረ ቅዱሳን የፖለቲካ መድረክ ይታይበታል፣ማኅበረ ቅዱሳን በሕገ መንግሥት ክህደት ወንጀል ይጠረጠራል” በማለት ተናግረው ነበረ::

ማክሰኞ ሚያዝያ 9፣2004 ዓ/ም ክቡር ጠቅላይ ሚኒተር መለስ ዜናዊ በፓርላማ ንግግራቸው ላይ ማኅበረ ቅዱሳንን ከዓለም አቀፍ አሸባሪ ድርጅት ከአልቃይዳ ጋር አመሳስለውታል:: ክቡርነታቸው ከምን አይነት መረጃ እና ማስረጃ ተነስተው ማኅበረ ቅዱሳን ከአሸባሪ ድርጅት ጋር እንዳመሳሰሉት ሰፋ ያለ ገለጻ አልሰጡም:: በደፈናው ግን “አልቃይዳ/ሰለፊ አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱት ግልባጭ ያራምዳል” አሉ::

አልቃይዳ/ሰለፊ ባሳለፍናቸው በሃያ ዓመታት ጊዜ በሀገራችን ውስጥ ብዙ ጥፋቶችን አድርሶዋል:: ለዚህም በቂ መረጃ እና ማስረጃዎች አሉ:: ክርስቲያኖች አርደዋል፣ አብያተ ክርስቲያናት አቃጥለዋል እንዲሁም ኢትዮጵያ መተዳደር ያለባት በሸርያ ሕግ መሆን አለበት በማለት አስተምረዋል እያስተማሩም ናቸው:: ሰለፊዎች በቁጥር በዛ ብለው በሚኖሩበት ዞኖች እና ክልሎች ብቻ ገንጥለው የሸርያ ሕግ ተግባር ላይ ለማዋል እየሰሩ ናቸው:: ለምሳሌ የስልጢ ዞን እና የሐረሪ ክልል መጥቀስ ይቻላል:: ታድያ ማኅበረ ቅዱሳን የትኛው መስጅድ/መስጊድ አቃጠለ? የትኛው የፕሮቴስታን ማምለኪያ ቦታዎች አቃጠለ? ማኅበረ ቅዱሳን የትኛው ዞን ወይም ክልል በክርስትና ሕግ ይተዳደር ብሎ አስተማረ? አባላቱን ከፍለው ከአልቃይዳ ጋር እንዴት አመሳሰሏቸው? የአልቃይዳ ዓላማ ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰተር ጠንቅቀው ያወቁት ይመስለናል:: ጠቅላይ ሚኒስተሩ የአልቃይዳ ዓላማ  ጠንቅቀው ስላወቁ ይመስለናል ወታደራቸውን ወደ ሶማልያ የላኩት::

የማኅበረ ቅዱሳን ዓላማ ሆነ ግብ ከአልቃይዳ ዓላማ እና ግብ ጋር ፈጽሞ አይገናኝም:: ሁለቱ ተቋማት ፍጹም ተቃራኒ ናቸው:: ምንም ሊያመሳስላቸው የሚችል ነገር የለም:: የእኔን ሃይማኖት ካልተቀበልክ ትታረዳለህ ብሎ የሚያስምረው አልቃይዳ እና የአባቶችን ሃይማኖት ተጠብቆ ለትውልድ ይተላለፍ ብሎ የሚስተምረው ማኅበረ ቅዱሳን ጋር እንዴት ሊመሳሰሉ ይችላሉ? ስለዚህ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ተሳስተዋል:: ክቡርነታቸው በማኅበሩ ላይ ከፍተኛ የሥም ማጥፋት ወንጀል ነው የተናገሩት:: አንድ የአሸባሪ ድርጅት ለመምታት ግዴታ ሌላው አብሮ መመታት የለበትም:: በእስልምናው አልቃይዳ የአሸባሪ ድርጅት ነው፤ይህም ዓለም ያወቀው እውነት ነው:: የአንድ እምነት አክራሪ/አሸባሪን ለመቅጣት ግዴታ የሌላው እምነት ማኅበር መወንጀል ለምን አስፈለገ? ማስረጃ እና መረጃ ሳይኖር ዝም ብሎ በአንድ ድርጀት ወይም ግለሰብ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ማካሄድ ወንጀል መሆኑን ክቡርነታቸው የሰሩልን ሕግጋት ይናገራሉ:: ስለስዚህ ክቡርነታቸው “ሰለፊዎች(አልቃይዳዎች) አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱት ግልባጭ ሲያራምዱ ታይተዋል” ብለው ማኅበረ ቅዱሳንን ከአልቃይዳ ጋር ያመሳሰሉበት ንግግር ፍጹም የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው:: ለዚህም ይቅርታ ሊጠይቁበት ይገባል::

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ያሉዋቸው እነማን ናቸው? አባ ሠረቀ ብርሃን 10% አሸባሪ ያላቸው የማኅበሩ የሥራ አመራር አባላት ይሆኑ? ወይስ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ስውር የማኅበረ ቅዱሳን አመራር ያላቸው? ማብራርያ የሚያስፈልገው ጥያቄ ነው:: የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ቅዱስ ሲኖዶስ ያጸደቀላቸው መተዳደርያ ደንብ ይዘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ  ክርስቲያን ዶግማ እና ቀኖና ለትውልድ እዲተላለፍ የድርሻቸው እየተወጡ መሆኑን የአይን ምስክሮች ነን:: አባላቱ በሙሉ አንድ አይነት ዓላማ ይዘው እንደሚጓዙ እናውቃለን:: ነገር ግን አባ ሠረቀ እና መሰሎቻቸው አንዳንድ  የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰዎች “ማኅበረ ቅዱሳን ድብቅ ዓላማ አለው” በማለት በተደጋጋሚ ሲከሱት ሰምተናል:: መንግሥት ተጨባጭ መረጃ እና ማስረጃ ሳይዝ የእነዚህን ሰዎች ውንጀላ የሚቀበል ከሆነ  ክሱ መሰረተ ቢስ ይሆናል:: ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ይህንን የተሳሳተ የአባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የተሳሳተ መረጃ ይዘው በአደባባይ ማኅበረ ቅዱሳን ከአልቃይዳ ጋር ማመሳሰላቸው ከመስመረ የወጣ ክስ በእርሳቸው አገላለጽ ደግሞ የፈንጂ ወረዳ የረገጡ ይመስለናል::

የማኅበረ ቅዱሳን አባላትን አንዳንድ፣ 10%፣ ስውር አመራር እያሉ ቢከፋፍሉዋቸውም ከእውነታ የራቀ ውንጀላ በመሆኑ የማኅበሩ አባላት ግን ፈጽሞ ሊከፋፍሉ አልቻሉም፤ አይችሉምም ምክንያቱም የማኅበሩ አባላት ያሰባሰባቸው የቤተ ክርስቲያን ዓላማ እንጂ የዓለም መንግሥት የፖለቲከኞች ዓላማ እናዳልሆነ ምስክሮች ነን:: ዓላማቸው የተሰቀለውን ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ መስበክ እንደሆነ እኛ እንመሰክርላቸዋለን:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት፣ ሥርዓት፣ ታሪክ፣ቅርስ ሳይፋለሱ እና ሳይበረዙ ለትውልድ እንዲተላለፍ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በአንድነት ሆነው እንደሚሰሩ እናውቃለን::

ከተመሠረተ ሃያ ዓመታትን ያስቆጠረው ማኅበረ ቅዱሳን በጉዞው ብዙ ፈተናዎችን እንደገጠሙት የማኅበሩ አባላት በተለያየ ጊዜ ይናገራሉ:: ማኅበሩ በእግዚአብሔር ቸርነት በቅዱሳን አበው እና እመው ጸሎት እስከ ዛሬ ድረስ ቢቆይም አሁንም እየተፈተነ መሆኑን አባላቱ ሲናገሩ ሰምተናል:: ስለዚህ አሁንም ቢሆን የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በዚህ ሳትደነግጡ እና የተሰባሰባችሁበትን ዓላማ ሳትስቱ ሰዎችን ለማስደሰት ሳይሆን ሰለ እውነት ብላችሁ እግዚአብሔርን ለማስደሰተ ሥራችሁን ከበፊቱ ይልቅ ተግታችሁ እንድትቀጥሉ በዚሁ አጋጣሚ አሐቲ ተዋሕዶ አደራዋን ታስተላልፋለች:: 
          እግዚአብሔር አሐቲ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን!!!


29 comments:

Anonymous said...

Why did the prime minster made this statement this time:

1) To threaten Mahibere Kidusan top leadership and divert the report of the MK mission deployed to Waldiba area towards the interest of EPRDF.

2) To implement the unwritten law of EPRDF " No independent organized body of any kind " in the country.

As to me if MK is going to be made political tool of EPRDF and of no use to the church, I suggest it better not exist.

Kinfe Michael said...

The darkest part of the night is the one just before dawn. Let God make it that way for our country and our religion. Let God give us the strength to continue with our good deeds even during times of tests and sufferings.
"Esme Be'Entiahu yiketilune kulo amire, wekone keme abag'e zeyiteb'u, nikah Egzio lemint tinewim."
Even though we have not yet passed through a tiny fraction of the sufferings that our fathers have, we need to pray a lot so that God shows His presence for those showing contempt to our faith.
"Fenu Edeke em'ariyam!!"

Anonymous said...

MK has to make its at most effort to ‘ force the prime minster reconsider its statement and publicise otherwise the issue must be take to court to compel him avert his baseless accusation.
In addition, though, mk is well known for its good deeds among orthodox christains and true church fathers, the insiders and outsiders of the tehadiso are likely to exploit this opportunity. Hence, strong public relation work has to be done to reach the innocent majority christains who can be twisted ....

Anonymous said...

i don't agree to post here that Dn.danei talked about Mk.This is not the making a peace between Mk and our beloved brother dani.

Anonymous said...

It's a sorrow. Where r we heading as a country? I believe our PM made a huge mistake. And Dn Daniel Kibret should never be mentioned here in zis article. Coz he is working for z church and if he made mistake he had publicly asked for pardon. If u didnt accept it, that is ur problem. Anyway MK is under huge pressure. MK is not and will never be a terrorist group!!!

Anonymous said...

It will be Ato Meles, z only leader to label anti-terrorists as terrorist. He is shameless & will be till he dies! But we all ethiopians r suffering from his evil mind products. Don expect him to apologize, Meles has never been polite. Pray to z Almighty God, z solution for this is from heaven not from flesh and bone.

Anonymous said...

Why PM talked about MK ? Cose he cann't get it any poletica party to destroy .THAT'Y DONE

Anonymous said...

I think this person in particular is a terrorist. I mean the writter. What in the world would he/she need to mention Dn. Daniel Kibret's name???!!! Isnt it a dead deal. Poeple please teach us love. Forgive and move on. There's Meles Zenawi to worry about. "Ahiyawun Tito dawlawin"

Anonymous said...

ወይስ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ስውር የማኅበረ ቅዱሳን አመራር ያላቸው? Tsehafiw yih min lemalet new , betam tiyake silecharebign bitabiraraw !!!!!! Dn. Daniel kibhret ye MKn siwr ????????

Anonymous said...

ወይስ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ስውር የማኅበረ ቅዱሳን አመራር ያላቸው? what??????????? please explain this . does he has another mission?...............

tizita. e said...

defintly.

abdi said...

it may be to divert the waldiba monastery report, but be faithful and loyal to truth all things will pass. rather than corrupt the fact it is better the life of mk to be end.

ወደፊትም ከዚህ የበለጠ ፈተና ቢመጣም የሀይማኖት ጉዳይ ስለሆነ እስክንሞት ድረስ እውነትን መናገር አለብን፡፡ እውነትን ሸራርፎ ከመኖር ከእውነት ጋር መሞት ይሻላል፡፡

Anonymous said...

ምን ማለት እንደሆነ እኮ ይገባናል?

Anonymous said...

Ahat Tewahedo Tebareku (thank You )
Mahibere Kidusan Fetenaw Beztal
1 America yalew sinodos Wyane alew
2 ethiopia yalew sinodos tekawami
3 Geleltegaw Ferisaw Mahiber alew
4 Hizibu kesashi asadaj new alew
5 Tehadiso Asasach new alew

Ahun yemitaye neger hulu melkam ayidelem Mahibere Kidusanim rega bilo maseb alebet Biogge hulu Melkam were memezige alebachew Piray minstiru ( Meles Zenaw )yetenagerut D Daneil Kibret -Aba Sereke - D Begashaw Yenegerutn yizo new
degimom Washingto DC betederege selamaw self lay Mahibere kidusan Ke ehapa & ke ginbot 7 Gar taytal Mengistm Mereja alew beyegizew yemderegewn yesilk wiyiyit yisemal
Ahunm Astewlu Rega Belu Mahibere Kidusan semonun alamawn restal behulum neger yagebagal malet jemroal Kifu neger atimezgibu wede ( Deje Selam -Ahat Tewahido -Gebir her- And adirgen ) yeman endehonu
azegajochu hulu limezegebuna letaweku yichilal tetsenkeku
Ahun Abune Pawlosin Mekawem Abune Merkorewsin Medegef Ehadegin Mekawem Gibot 7 medegef yimeslal erfu yemlachihu wede tsornet eyamera new sew yalkaml Mengisit bemenngistu bal bemistu Amlak bemelkotu simetubet aywedim
yesewn sim mansat memezgeb yikrbachihu wede fetsaryachihu alkisu wede emebetachin alkisu melis tametsalachihu beterefe Waldiba teneka _Aebot teneka zikala teneka Mahibere Kidusann Sayihon yemimeleketew Sinodos ale semonun yetenesawn ye esilmna guday tayalachu enersu le ega asbew ayimselachhu eslamaw mengist yinuren new negeru kirstiyan yilkek new neger Ahunim Tetsenkeku ( wede fetena endatgebu tegtachihu tselyu )Kesinodos belay nen atbelu Ahun yemisemaw neger hulu Kebad new Mahibere Kidusan America Honu Papas awgeze- Kihinet setse-Kihinetu Yetyazebetn Kahin Degefe
Poletkega Hone- selamaw self kesekese Abune Fanueiln Asadede Abune Elsan Kesese- Kahinatin Hulu simachewn atsefa yemil new Mahibere Kidusan yemserawn berkata yehone melkam sira yayelet yelem ahun rega belu
Ahat Tewahedo 04 20 2012 yemezegebachit melkaw new yesewn kibir alnkam letseklay ministiru masredat yigebal Aba Samueil

Anonymous said...

Dear Editor,

First of all I would like to thank that you post this article timely on important moment.
Despite your strong side I want to note on some weak side of this article so far I saw:

1. To my view this article did not issue after review and approved by the higher hierarchic of the legislative body (MK yesira amerar)may be due to short of time, and I believe that the below mistakes are due to this problem.
2. This article again make the same mistake as the PM does, to blame Selefia first he should start from EOTC and its affiliates, this is always what PM and his political party EPRDF do, they always start blaming from the blue EOTC and give any wrong doing of the past to the church. Here also this article to get some ground or support he added Dn. Daniel from no where.
3. Why the need to talk about our brothers Islam peoples, if there is wrong the government is the one to take responsibility for what keeping silent and doing nothing before when those individuals making some links with middle east institute or individuals. As in previous time and now they will be brother of us nothing should not be changed, despite peoples from the ruling party and from opposition and some individuals try to put some classification among us (Ethiopian Christians and Islam).
4. The very surprising to me and some what out of moral to read "....ወንጀል መሆኑን ክቡርነቶ የሰሩልን ሕግጋት ይናገራሉ:". I don't have words to explain my mind. Thats why I write the above no.1
5. At the first part of the article it seemed that the article is from the committee as it describes with First person plural but at the end it addresses to the committee.

I would like to address to MK to issue the stand of the Church and to demand further clarification from the government, whether it will happen or not.
But above all Prayer will make us most powerful and will guide us the right way and discussing with fathers shall be the priority.

God may be with us!!!

Anonymous said...

በዳላስ ያለነውን የተዋህዶ ልጆች በኢትዮጵያ ሲኖዶስ ስር እያመለከ ያለውን ህዝብ የማህበረ ቅዱሳን አባል የሆኑት አንድ ቄስ አንዳንድ የማህበሩን አባላትን ይዘው የራሳቸውን ርካሽ ጥም ለማርካት ለመሳሪያነት ዘርና ፖለቲካ እያራገቡ ቤተክርስቲያናችንን ሊከፍሉ ህዝቡን ሊለያዩ ነው።

Anonymous said...

ሊበሉዋት ያሰቧትን አሞራ ጅግራ ናት ይሏታል!!! የሚያሳዝነው ነገር ማሕበሩ ከውስጥም ከውጭም የትዕቢት ፆር የበዛባቸው ሰዎች ኢላማ መሆኑ ነው፤ ይህ ግን ማሕበሩ ከክርስቶስ ጋር ለመሆኑ ትልቁ ምስክር ነው። ሰይጣን ይህንን ማሕበር እንዴት እንደሚፈራው ነው የሚያመለክተው፤ በየአቅጣጫው ፈተና አበዛበት።

ለመሆኑ ከክርስቶስ የሆነና እንደዚህ አይነት ዋጋ ሳይከፍል ወደ እግዚአብሔር መንግስት የገባ ማን አለ? ረስተነው ነው እንጅ ዛሬ የምንከራከርላት ቤተ ክርስቲያንም እኰ ለዚህ የበቃችው በልጆቿ ደም ነበር። ሰይጣን ያደረበት ግፈኛው ዲዮቅልጥያኖስ ክርስቲያኖችን ለመግደል ሲል በሮም ከተማ እሳት ለቆ፣ "ሮምን ያቃጠሏት ክርስቲያኖች ናቸው" የሚል ወሬ በየግዛቱ እንዲወራ አስደረገ። ከዚያ ግማሾቹን በሰይፍ፣ ሌሎቹን በአንበሳ . . . ወዘተ አስፈጃቸው።

ከወጣትነታቸው ደም መጠጣት የለመዱት የኛዎቹ ቄሳሮች ደግሞ አሁን በዲዮቅልጥያኖስ የገባው ሰይጣን ገባባቸው መሰለኝ አንድ ጊዜ መካነ መቃብር ማረስ፣ ሌላ ጊዜ ገዳም መቀማት፣ ሲብስም "አንድ ጌታ፣ አንዲት ጥምቀት፣ አንዲት ሐይማኖት፣" የሚለውን ጥቅስ ስሕተት እንደሆነ መዘብዘብ . . . ወዘተ ጀምረዋል። ምን ቀረ. . . አንገት መቅላቱማ ድሮ በአርባ ጉጉ ተደርጓል!!! እግዚአብሔር ልቡናውን ይስጣቸው እንጅ ምን እንላለን!!!!

Anonymous said...

እህቴ እሱ ወንድ ወኖ በእኔ ያሳብባል አለች።

የሁሉም የባለስልጣኖቻችን አላማ በማህበረ ቅዱሳን ላይ፤ ክርስቲያኑ ሲገደልና በሃይል እንዲሰልም ሲደረግ ማህበሩ ለምን ዝም አይልም ለምን ለህዝቡ መረጃ ይሰጣል ነው ዋናው ጉዳይ፤ እንጂ ከተቃዎሚ ፖለቲካም ወነ ከሰለፊ/ከአልቃይዳ በምንም እንደማይገናኝ ያውቁታል።
በምእራቡ አለም ያሉ ተቃዋሚዎች ማህበሩን ወያኔ፤ የወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚ ይሉታል፤ በአገር ቤት ያሉ ባለስልጣናት ደጎሞ በዚህ ተቃራኒ ይከሱታል። እኔ የማበህበሩ አባል አይደለሁም፡ ሁሉቱም ከሳሾች ለእኔ የሚያውቁ የሚመስሉ አያላዋቂዎች ናቸው።

Anonymous said...

ለምን ከፋህ? ሌላ ቤተ ክርስቲያን ይኖርላችኋል:: ሁሌ በየትም ስቴት ሰዎች ስርዓት ይከበር ሲሉ ነገሩን ከማቅ ጋር ለማያያዝ የሚሞክሩ እንዳንተ አይነት ጥቅም የሚቀርባቸው ሰዎች ሞልተዋል::

Anonymous said...

ከ 3-5 ያለችው እንኩዋን ያንቺ የተሀድሶዎቹ አባባል ነች:: የሚገርመው ግን ተሀድሶዎቹ ሁሉንም መሆናችሁ ነው::
ፈሪሳዊ አሳዳጅ እና ከሳሽ እና አሳሳች::
➠ ጌታቸው ዶኒ ሰረቀ እና በጋሻውን ተመልከት::
እነዚህ ካለ ማህበር በህቡዕ ስለሚንቀሳቀሱ ነው?

Anonymous said...

actually this group which called ማኅበረ ቅዱሳን ... is worst than alQaida their objectives are to eliminate Ethiopian Muslims , always barking about one country one religion , Ethiopia ye christian desate ... so PM Meles Z describe about the current situation well .. we should fight those groups from both side otherwise we will end up like Nigerian kind of mess .

Anonymous said...

መለስ፡ቀበጡ፡ወጥ፡ረገጡ፡
ለይቅርታ፡ይምጡ፡
ተራ፡ወሬ፡አይምሮዋቸው፡ለይ፡አያስቀምጡ
በራሳቸው፡ላይ፡ጉድ፡እንዳያመጡ

Anonymous said...

እኔ እንደገባኝ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አባባል በግልጽ እንደሠማነው ማህበረ ቅዱሳን የሰለፊዎች ግልባጭ /ተቃራኒ/ ነው እንጂ ሁለቱ ተመሳሳይ ናቸው ለማለት አይደለም፡፡ ለመሆኑ ለመናገር ቢፈልጉ እንኳን ዲሞክራሲያዊ መብታቸው አይደለም እንዴ በሚገባ ቋንቋ ማህበረ ቅዱሳንና ሰለፊ ተመሳሳይ ባሕሪያት አላቸው ቢሉ፡፡ በግልጽ መናገር አይችሉም ነበር? ሰለፊዎችን ያውም ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ በከፈተኛ እገዛ ውስጥ ያሉትን ሰለፊዎች በግልጽ አክራሪ ሲሉስ ተደምጠው የለ እንዴ ስለዚህ የመሪውን ቃላት ማጣመማችሁን ትታችሁ የክርስቲያን ሥራ ብትሠሩ ይሻላል፡፡

Anonymous said...

It is always a mystery why the MK considers itself as doing no mistakes. rather than barking here and there it would be wise to think why the PM would say such accusations and improve all the malpractices in the association. I don't think the PM said such statement out of nowhere. Even if i believe that the association as a hole is not Extremist but i suspect that some would be involved in such activities. Hence, you guys stop your scape gloating and cleanup your house.

Anonymous said...

It is always a mystery why the MK considers itself as doing no mistakes. rather than barking here and there it would be wise to think why the PM would say such accusations and improve all the malpractices in the association. I don't think the PM said such statement out of nowhere. Even if i believe that the association as a hole is not Extremist but i suspect that some would be involved in such activities. Hence, you guys stop your scape gloating and cleanup your house.

Anonymous said...

PM Meles.... take time to speak about religion... we really apreciate yours' leadership, but if you come to the religion... I feel it will be too diffucult for you to handle it. if you wanted to live long, better you...

Anonymous said...

Anonymous said...

ወንድሞቻችን ለቤተ ክርስትያን መቆርቆራችን የሚያስደስት ሆኖ ሳለ የምናገለግለው ግን ትምህርቱን አስቀድመን ምስጢርን አደላድለን ቢሆን የተሻለ ይመስለኛል፤ምክንያቱም የተፃፉትን ሁሉ ለቤተ ክርስትያን የወጉ ይመስሉንና በውስጠ ዘ ግን የሚየስተላልፉት ተቀራኒ መልዕክት ያላቸው ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ አልቃይዳዎች በሙሉ ሰለፊ ናቸው:: ሰለፊዎች (አልቃይዳዎች) አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱት ግልባጭ ሲያራምዱ ታይተዋል” ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ የተናገሩት
ይህ ማለት ምን ማለት ነው ማህበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ፈቅዶላቸው ቤተ ክርስትያን ሲንከባከቡ ምዕመናን ሲያጽናኑ ያልታደሉ ደግሞ የዚህን ግብር ግልባጭ ቤተ ክርስትያንን ለመናድ ሕገ ቤተ ክርስትያንን ለማፍረሰ ምዕመናን እምነታቸውን እንዳያፁ መዓልትና ሌሊት ሰዓትና ደቂቃ የማያንቃላፋ የዲያብሎስ እስትንፋስ የሰይጣን ተገዢ የአጋንንት መልዕክተኞችና አስፈፃማች አሉና እግዚአብሔር ለኛም ደካማ ጎናችን ይሙላልን ለእነሱም ቆም በለው የሚስቡበትን አእምሮ ጠባይዕ ሰጥቶ ለንስሀና የሚፀፁቱበት አዕይንት አእምሮ ይስጣቸው፡፡
አሜን!!
እግዚአብሄር አምላካችን ቤተ ክርስትያናችን ይጠብቅልን!!
ህዝበ ክርስትያንን ከምላሳቸው መርዝ ከሚረጩ ተኩላዎች የጠብቀን!!!
በእንት እግዝእትነ ማርያም
በእንተ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል
በእንተ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል
በእንተ ሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ
በእንተ ሊቀ ነብያት ሙሴ
በእንተ ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ
ብሎ ቤተ ክርስትያናችን ይጠብቅልን!!!

Anonymous said...

ሰለፊዎች ፡( ኢትዮጵያ ውስጥ ሙስሊም ይበዛል ስለዚህ እስላማዊ መንግስት መመስረት አለበት ብለው ይናገራሉ)፡፡
ማህበረ ቅዱሳን፡ (አንዲት ሀገር አንዲት ሀይማኖት ይላሉ)፡፡
ስለዚህ ሰለፊዎችና ማህበረ ቅዱሳን ህገመንግስቱን እየተቃወሙ ስለሆነ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር /ማስጠንቀቂያ/ ተገቢ ነው እላለሁ፡፡