Thursday, April 5, 2012

የአቡነ ፋኑኤል ድርጊት ተወገዘ ፤ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላትም ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ ቀስቀሷል

     READ IN PDF
  በቂ እውቀት እና ምስክርነት ሳይኖራቸው ወደ ጵጵስና ሥልጣን የወጡት አቡነ ፋኑኤል ፤ በአሜሪካ ውስጥ እያደረጉ ባሉት ቤተ ክርስቲያንን የማዳከም እንቅስቃሴ  የተነሳ የአባትነት ክብራቸውን በከፍተኛ ፍጥነት በማጣት ላይ ይገኛሉ ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር መዋቅር ሥር የሚገኙት በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ  ስብከተ፣ እና የካሊፎርኒያንና የምእራብ እስቴቶች  ሀገረ ስብከት አብዘኛዎቹ አብያተ ክርስቲያናት  ዘንድ ተቀባይነትን አጥተዋል:: የተሰጠን የክህነት ተግባር በማቃለል ላይ የሚገኙት አቡነ ፋኑኤል አባትነታቸውን የሚቀበላቸው በማጣት ላይ ናቸው:: በተያያዘ ዜና ብጹዕነታቸው ከ250, 000 ዶላር በላይ የአሜሪካ መንግሥት ሳያውቀው በሕገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ይዘው በመውጣታቸው ዙሪያ  ሕጋዊ  ጥያቄ እየቀረበላቸው መሆኑን ለአሐቲ ተዋሕዶ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፍ እየተደረገባቸው ሲሆን መቆሚያና መቀመጫ በማጣታቸው በቅርቡ ለዳግማዊ ትንሳኤ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ምንጮጫችን ገልጸውልናል:: ብጽዕነታቸው የጵጵስና ማዕረግ ለማግኘት ከእጅ መንሻ ገጸ በረከት በተጨማሪ ያላደረጉትን አድርጌያለሁ በማለት ቅዱስ ሲኖዶስን በመዋሸት “የዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ወደ ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር መዋቅር ስር አስገብቻለሁ” ማለታቸው ይታወሳል:: አሁንም በድጋሚ ከያዙት  ገንዘብ ላይ እጅ መንሻ በመስጠት እና የተለመደው የሐሰት ሪፖርት በማቅረብ በሰሜን አሜሪካ ለመቆየት ያላቸውን እድሜ ለማራዘም ጥረት ለማድረግ ከግንቦት ወር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀደም ብለው ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ::  
      
በተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ ላይ ተሳታፊ የሆነው እና ከዚህ በፊት በነበረው የሃይማኖት ችግር ከማኅበረ ቅዱሳን ተባሮ   የወጣው ዲ/ን ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን በአቡነ ፋኑኤል ተፈርመው ለሚወጡ ደብዳቤዎች ዋና አዘጋጅ መሆኑ ፤ አቅምና እውቀት ላነሳቸው አቡነ ፋኑኤል ዋና አማካሪ መሆኑ የውስጥ ምንጮቻችን ገልጸውልናል:: ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን በቅዱስ ፓትርያርኩ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ለሰሜን አሜሪካ ውጪ ጉዳይ ጽ/ቤት ሓላፊ ተብሎ መሾሙ ይታወሳል:: ይህ የውጪ ጉዳይ ጽ/ቤት በጥቅምት ወር የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ህልውና እዳይኖረው ተሽሮ ነበረ፤ አሁን ግን ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል ጽ/ቤቱን እውቅና ሰጥተውት ደብዳቤ ሲጽፉ ግላባጭ ብለው ይገልጹታል፤ ነገር ግን በሚጽፋቸው ደብዳቤዎ ግልባጭ ለቅዱስ ሲኖዶ ጽ/ቤት አይገልጹም:: ደብዳቤዎቹም በቀጥታ በተሐድሶ መናፍቃን ብሎግ “አባ ሰላማ” ላይ ይወጣል:: ይህም አማካሪያቸው ኃ/ጊዮርጊስ ከተሐድሶ መናፍቃን ብሎግ ጋር ባለው ግኑኝነት ደብዳቤዎቹም በእርሱ አማካኝነት ይደርሳቸዋል የሚሉ አስተያየቶች ደርሶናል::    

ከዚህ በፊት በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የዋልድባን ጉዳይ ለማሳሰብ  በተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ በተመለከተ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአባ ፋኑኤል ተፈርሞ ለሄደው ደብዳቤ “ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን አይወክሉም’ በማለት ለማስፈጸም ይሯሯጥ የነበረው ይሄው ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን መሆኑ ታውቋል። አሁንም ከቅዱስ ፓትርያኩ ጋር ባለው የጥቅም ወዳጅነት አቡነ ፋኑኤልን በሰሜን አሜሪካ ለማቆየት ቅዱስ ፓትርያርኩን ለማግባባት በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓዝ ምንጮጫችን ገልጸውልናል::  

አቡነ ፋኑኤል የሚያደርጉትን ድርጊት ብዙዎች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብጹዐን አባቶች በሰጡት አስተያየት “ ካልተማረ ሰው የሚጠበቅ ይሄው ነው፣ በገንዘብ ከመስከር የመጣ እብደት ነው፣ የመጨነቅና እውነትን ፊት ለፊት የመጋፈጥ ፍርሃት ነው” በማለት የሚያደርጉት ሁሉ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን መግለጻቸውን ከተለያዩ ምንጮቻችን ተገልጾልናል::
በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ባወጡት የአቋም መግለጫ እስከ መጨረሻው ድረስ የቤተ ክርስቲያንን አቋም በመያዝ እንደሚጓዙ ገልጸዋል ። 

4 comments:

Anonymous said...

all of you not represent our church only fighting for personal interste.

Anonymous said...

So are you represent our church or you start fighting for your own interest too, brother?
Why you blame both side? You could see many flaws of the bishop unless you don't want to.

Anonymous said...

Thank you very much that you calling me as your Orthodox brother's. Firstly, I would like to mention about myself I am not a part of personal interste from church. However, I deeply concerned the situation as an individual follower. This is with regards to recent issues that done by Aba Fanuel and his irrseponsible group to take away the most important intelectual priest from our church. We need dual qualified priest and deacon other wise we not out useless speculation. It is the master key point all of us understand that Ethiopian Orthodox church in longest and richest history has been a big contribution to Ethiopian Independence, social progress and unity. So, today is our time unite together to save our church instead of fight each others. Furthermore, I am not a part of Abune Fanuel or Mahiber Kidussan, eventhough I strongly againest of Abune Fanuel action. His action is emotional, non spritual, and revengable of his owen conflict. I knew Mahiber Kidussan since 1985 Ethiopian calander which provides an extenssive spritual, social, and economical services for Ethiopian Orthodox church and the countary. Finaly, as responsible father Abune Fanuel has undestand the enemy of Ethiopia alawys attack Ethiopian orthodox church so open your door for dicussion to resolve any problem of our church here in USA, other wise your spritual qualification not enough to lead this annicient church in the world.

Thank you for all and Peace of God stay on true Orthodox brothers and sisters, I am one of Deacon in USA.

Anonymous said...

Fanuel indih karege aba sereke paps bihon min yemiyaderg yimelachihual? Chigiru yetefeterew zare sayhon yetwshomu llet new... It is vey wise to ..... his grace to avoid further damages. it's also important to consider upcoming candidency of arcbishops for the church