- "ሁለት ነጮች ተገድለዋል ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል” ብሏል የኢሳት ዜና፤
(ደጀ ሰላም፤ ሚያዚያ 23/2004 ዓ.ም፤
April 30/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦፦ “በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ ዋልድባ
መትመማቸውን
እንዲሁም ሁለት ነጮች መገደላቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች አካባቢውን
ለቀው መውጣታቸውን”
ኢሳት የተባለው ብቸኛው ከአገር ውጪ የሚገኝ ነጻ የዜና ተቋም በሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት)
ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ዘገባው አስታወቀ። “የገዳሙ አባቶች
ለሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ባቀረቡት ጥሪ መሰረት እስከ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት
የሚገኙ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ወደ አካባቢው መትመማቸውን ተከትሎ ሁለት ነጮች መሞታቸውን፣ ሌሎች ሰራተኞች ደግሞ እኛ ከህዝብ
ጋር አንጣላም በማለት አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል” ያለው ዜና ተቋሙ “የሟቾቹ እና
አካባቢውን ለቀው የወጡት ነጮች ምዕራባውያን ይሁኑ
የቻይና ዜጎች አልታወቀም” ሲል አክሏል።
ዘገባው ቀጥሎም “ከ5ሺ ያላነሱ
የአካባቢው ነዋሪዎች በዋልድባ ተገኝተው ተቃውሞ እያሰሙ ሲሆን፣ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላትም ርምጃ ለመውሰድ ፈርተዋል።
ሁኔታው እጅግ አስፈሪ ነው፣ መንግሥትና ሕዝቡ ተፋጠዋል፣
የአካባቢው ወጣቶችም ወደ አካባቢው ለመጓዝ እየተመካከሩ ነው ሲል አንድ ጉዳዩን በቅርብ ሆኖ የሚከታተል ሰው ለኢሳት” መግለጡን አብራርቷል።
“ሰራተኞቹ
እኛ ለሕዝብ ልማት
ይውላል ተብሎ ነው የመጣነው፣ እናንተማ ካልፈለጋችሁት እኛ እዚህ ምን እናደርጋለን?” በማለት አካባቢውን ለቀው በመውጣታቸው፣ በአሁኑ
ጊዜ ሥራው ሙሉ በሙሉ
ቆሟል።” ያለው ኢሳት
“መንግሥት ሥራው ተቋርጧል
በማለት ለአካባቢው ነዋሪዎች ቢናገርም፣ ሕዝቡ ግን ሚጢቆ በሚባል ቦታ ላይ የተተከሉት ሁለቱ የኤሌክትሪክ
ጄኔሬተሮች ካልተነሱ ሥራው መቋረጡን
ከልብ አምነን ለመቀበል አንችልም የሚል መልስ ሰጥቷል” ብሏል።
“የአካባቢው ሕዝብ አሁንም ጄኔሬተሮቹ እስኪነሱ ድረስ በትዕግስት በአካባቢው ተገኝቶ እየጠበቀ ነው። ሕዝቡ በስንቅ እጦት እንዳይቸገር እርስ በርሱ እየተተካካ እንደሚጠብቅ ለማወቅ ተችሏል” ሲል ኢሳት አብራርቷል። የገዳሙ አባቶች “ከሃይማኖት ወዲያ ምን አለ፣ ለሃይማኖት መሞት ጽድቅ ነው።” በማለት ሰሞኑን ሕዝቡን እየዞሩ ሲያስተምሩ ነበር። ያለው ኢሳት “መንግሥት የተወሰኑ መነኮሳትን አፍኖ መውሰዱም ታውቋል” ብሏል። “አሁን በሚታየው ስሜት የዋልድባ የስኳር ግንባታ ተፈጻሚ ሊሆን እንደማይችል አንድ የአካባቢው ሰው ለኢሳት ተናግረዋል። የሕዝቡ ቁጣ ከመጠን እያለፈ ነው ያሉት እኝህ ሰው፣ መንግሥት ከሕዝቡ ጋር እልህ ውስጥ የሚጋባ ከሆነ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ ይችላል ሲሉ” ማስጠንቀቃቸውን ጠቅሶ “የመንግሥት ባለስልጣናት በግንባታው ዙሪያ የሀይማኖት አባቶች ስምምነታቸውን ሰጥተዋል ቢሉም፣ ሕዝቡ ግን የሚቀበለው አልሆነም” ብሏል።
2 comments:
“ከሃይማኖት ወዲያ ምን አለ፣ ለሃይማኖት መሞት ጽድቅ ነው።”
የአባቶቺእን ርስት አልሰጥህም
ኢሳት የራሳችሁ ሚድያ ሰለ ሆነ ነፃ ሚዲያ ኣላችሁት ኣይደለም?
ነገሩ መጣፉም በዚያን ግዜ በስሜ የሚነግዱ ይመጣሉ ብሎዋል
Post a Comment