Sunday, May 13, 2012

(ሰበር ዜና) ቅ/ሲኖዶስ ሌላ ሰብሳቢ መርጦ ጉባኤውን ለመቀጠል ወሰነ

  •     የሃይማኖት ሕጸጽ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል 
  •     ለምልአተ ጉባኤው ሐሳብ ተገዥ ባልኾነው የፓትርያ አቋም ስብሰባው እግዳት ውስጥ ገብቷል 
  •     ከእርስዎ ጋራ ንትርክ ሰልችቶናል፤ ሦስተኛ አካል (መንግሥት) ጣልቃ ይግባ” (አንድ አባት) 
  • ሦስተኛ አካል ጣልቃ አይገባም፤ በተለይም የሃይማኖት ሕጸጽ ጉዳይ ሳናጠራ እርስዎ ያነሷቸውን አጀንዳዎች አናይም፤ ሲኖዶሱ በራሱ ወስኖ ኹኔታውን ለሚዲያና ለሕዝቡ ይፋ ያደርጋል” (ሌላ አባት)
ሙሉ ዘገባው የደጀ ሰላም ነው:: 
 ንት ዐርብ፣ ግንቦት 3 ቀን 2004 . ጠዋት በርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ መነጋገርያ አጀንዳዎች ላይ የተጀመረው ውዝግብ ከቀትር በኋላም ቀጥሎ የዋለ ሲኾን ዛሬ፣ ግንቦት 4 ቀን 2004 . ከቀትር በፊት በነበረው የምልአተ ጉባኤው ውሎም እንደቀጠለ መኾኑ ተሰምቷል፡፡


በዛሬ ጠዋቱ ስብሰባየእርስዎ ዕውቀት ይህ ስብሰባ የገጠመውን ችግር እንደምን መፍታት ይሳነዋልበሚል ተማኅፅኖ ሳይቀር በብፁዓን አባቶች እየተለመኑ ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስየእኔን አጀንዳ ካልተቀበላችኹ የእናንተንም አልቀበለምእስከ ማለት መድረሳቸው ተገልጧል፡፡ ይልቁንም በሰሜን አሜሪካው ዕርቀ ሰላም ሂደት ቀጣይነት፣ በተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመትና በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻ አጀንዳዎች መካተት ላይ የያዙትን አቋም እያከረሩና አልፎ አልፎም እያለሳለሱ የስብሰባን ሂደት እግዳት ውስጥ አስገብተውታል፤ እያደር በሚታየው አሰላለፍም ፓትርያርኩ በአንድ ወገን የተቀሩት የምልአተ ጉባኤ አባላት በሌላ ወገን ጎራ ለይተው መቆማቸው ነው እየተነገረ ያለው፡፡

ዛሬ ቀትር ላይ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው÷ ከፓትርያርኩ በቀር ብዙኀኑ የምልአተ ጉባኤው አባላት ሌላ ሰብሳቢ በመምረጥ መደበኛ ስብሰባውን ከቀትር በኋላ ለመቀጠል ወስነው ለምሳ ዕረፍት ተነሥተው ነበር፡፡ ምልአተ ጉባኤው እዚህ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ከዚህ ቀደም መንግሥት ወይም ሌላ ሦስተኛ ወገን ጣልቃ እንዲገባ የቀረበውን ሐሳብ የሚያስታውሱ አስተያየቶች ተነሥተው እንደነበር የጉባኤው ምንጮች ተናግረዋል፤ ከእርስዎ ጋራ መነጋገር አልቻልንም፤ ወደ አጀንዳ ሳንገባ በየቀኑ ከእርስዎ ጋራ ንትርክ ሰልችቶናል፤ ሦስተኛ አካል ይግባ፤ ከዚህ በፊትም መንግሥት ይግባ ብለናል ብለዋል አንድ በፓትርያርኩ ግትርነት የተማረሩ አንድ አባት፡፡ ይኹንና ሐሳቡ ወዲያው ነበር ተቃውሞ የገጠመው፡፡

አሁን ጎራ ለይቷል፤ በአንድ በኩል ቅዱስነትዎ በኩል የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ፤ ስለዚህ የቀረቡትን አጀንዳዎች ለተቀበሉት አብዛኛው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ድም ተገዥ እየኾኑ አይደለም፤ ያሉት ሌላ ብፁዕ አባት ሦስተኛ ወገን የሚባል አካል አይገባም፤ አያስፈልገንም፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ አውጭ፣ ሕግ ተርጓሚ፣ ሕግ አስፈጻሚ ነው፤ ስለዚህ አጀንዳዎቹን አጽድቆ መወያየቱን መቀጠል ይኖርበታል፤በማለት አንገብጋቢ የኾኑ አጀንዳዎችን በመለየት ዘርዝረዋል፡፡ በእኚህ ብፁዕ አባት ሐሳብ መሠረት ቅዱስ ሲኖዶሱ ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ሀገረ ስብከት አላቸው፤ በአባትነት የሚመሩት ምእመን አላቸው፤ ስብሰባውን አቋርጠን ወደየ አህጉረ ስብከታችን ተመልሰን የእርስዎን እንቢታ እናስረዳለን፤በማለት አቋማቸውን ግልጽ አድርገዋል፡፡ ከዚህ ሐሳብ ጋራ የሚጣጣም ተጨማሪ አስተያየት የሰጡ ሌላ አባ ስብሰባውን ማቋረጥ ብቻ ሳይኾን ይህ ምልአተ ጉባኤ የሚለያየው ስለ ኹኔታው ለሚዲያ መግለጫ በመስጠት ጭምር ነው ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

የስብሰባው ምንጮች እንደሚያስረዱት ፓትርያርኩ የኋላ ኋላ በአቡነ ፋኑኤል በድጋሚ መጠቀሱ የተነገረውን ሦስተኛ ወገን (የመንግሥት አካል) ጣልቃ ገብቶ ያነጋግረን የሚለውን ሐሳብ የተቀበሉ ቢኾንም ከዚህ በፊት ተደብድበን ምን የመጣ ነገር አለ፤ በሃይማኖት፣ በአስተዳደር ጉዳይ ሲኖዶሱ የመወሰን ሙሉ ሥልጣን አለው፤ በሚል ተቃውሞ ሐሳቡ ተቀባይነት ገኝ ቀርቷል፡፡ በመጨረሻም ከፓትርያርኩ በቀር የምልአተ ጉባኤው አባላትስብሰባውን አናቋርጥም፤ ወደየ ሀገረ ስብከታችንም አንሄድም፤ ሌላ ሰብሳቢ መርጠን እንቀጥላለንበሚል ውሳኔ ከቀትር በኋላ ለመገናኘት ቆርጠው መነሣታቸው ተመልክቷል፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ በየጊዜው በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች የሚቀርቡትን አጀንዳዎች የማጽደቅና እንደ አስፈላጊነቱም የማሻሻል፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዮች ላይ ሁሉ የመወሰን ሥልጣን እንዳለው ተደንግጓል፡፡

ፓትርያርኩ በብቸኝነት ከሚሟገቱላቸው ሦስቱ አጀንዳዎች ይልቅ ለስብሰባው ከተቀረጹት መነጋገርያ አጀንዳዎች መካከል በተ. (2) ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ዓመታዊ ሪፖርት፣ በተ. (6) ማእከልን ጠብቆ አለመሥራት ስላስከተለው ችግር፣ በተ. (10) ስለ ልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን፣ በተ. (13) ስለ ሃይማኖት ሕጸጽ በኮሚቴው የሚቀርበውን ሪፖርት መስማትና መወሰን፣ በተ. (18) በሰሜን አሜሪካው ዕርቅ ጉዳይ ሪፖርት ስለ መስማት የሚሉት አጀንዳዎች ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጧቸው እንደ ኾኑ ብዙኀኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከሚያንጸባርቋቸው አቋሞች ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከእኒህም ሁሉ በላይና በፊት ደግሞ በዛሬው የቀትር በፊት የስብሰባው ውሎ ስለ ሃይማኖት ሕጸጽ የተጠናቀረው ሪፖርት አጀንዳ አንገብጋቢ እንደኾነ በብዙዎቹ የስብሰባው ተሳታፊዎች አጽንዖት የተሰጠበት ጉዳይ ነው ተብሏል፡፡

ይልቁንም በሃይማኖት ሕጸጽ ጉዳይ ማስረጃ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በሊቃውንት ጉባኤና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ኮሚቴ ከታየ በኋላ ሪፖርቱ ገና ወደ ምልዓተ ጉባኤው ቀርቦ ውሳኔ ሳይሰጠበት የተወሰኑ ግለሰቦች ከሕጸጽ ነጻ መኾናቸው እንደተረጋገጠ በመፍቀሬ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎጎች የተነዛው አሉባልታ ብዙዎቹን አባቶች ክፉኛ አስቆጥቷ የሚቀርበውን ሪፖርት በጥንቃቄ እንዲመለከቱትም ከወዲሁ አነቃቅቷቸዋል፡፡ አሉባልታውን ከሚያናፍሱት ብሎጎች የአንዳንዶቹ ጸሐፊዎች ሃይማኖታቸው እንዲመረመር ውሳኔ ከተላለፈባቸው ግለሰቦች መካከል እንደሚገኙበት ጉዳዩን በቅርበት ከሚከታተለው የፀረ - ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መርበብ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ስለ ቅዱሳን ሲኖዶስ ቀጣይ ውይይቶች እና የዛሬ ፍጻሜ የምናዘጋጀውን ሪፖርታዥ እንተጠናቀቀልን እናቀርባለን፤ ተከታተሉን።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን

4 comments:

Anonymous said...

ውድ ደጀ ሰላማውያንና የአሐቲ ተዋሕዶ አዘጋጆች
ይህንን የመሰለ ትኩስ የቤተክርስቲያናችን ዜና እንድንሠማ የምታደርጉትን ልፋት አምላከ ቅዱሳን ይቀበልላችሁ፡፡ ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ግልጽነትና ተጠያቂነት በጎደለበት በአሁኑ ወቅት የቅድስት ቤተክርስቲያን አለኝታና የመረጃ ምንጭ እንዲሁም ቤተክርስቲያን በማንም ፖለቲከኛ እና መንፍቅ እንዳትወረስ እያደረጋችሁ ያለው አገልግሎት እጅግ የሚመሰገን የሚበረታታና የሚደገፍ ነው፡፡ ስለተሐድሶ መናፍቃን መጋለጥ ያደረጋችሁት ሁሉ በቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ሳላመሰግናችሁ አላልፍም፡፡
በቅዱስ ሲኖዶስ ለሚገኙ ቁርጥ የቤተክርስቲያን አባቶች ጳጳሳት በርቱ አዋልደ ንስጥሮስን በአፍ በመጽሐፍ ብለው መርታቱ ከአባቶቻችሁ የወረሳችሁት ስለሆነ ስለ ዱላውና ስድቡ እንዲሁም መከራ አትፍሩ፡፡ እርሱ ባለቤቱ የምትችሉበትን ኃይል ይሰጣችኋል፡፡ በዚህ ዘመን ታሪክን ሥሩ፡፡
1. ለዚህ ትውልድ ከ3 የተከፈለች ቤተክርስቲያንን እንዳታስረክቡ ( የታሪክ ተወቃሽ ትሆናላችሁ)
2. የቅድስት ቤተክርስቲያን ዶግማዋን ቀኖናን ሥርዓቷን ለመጪው ትውልድ ሳይበረዝ እንድታስረክቡ
3. የቅድስት ቤተክርስቲያን ገዳማቷ የአብነት ት/ቤቶቿ ሳይፈቱ መምህራነ ቤተክርስቲያን እየተቸገሩ የቅድስት ቤተክርስቲያን ሀብትና ገንዘብ በአንድ ፖለቲከኛና መናፍቅ ፓትርያርክና ተባባሪ ጳጳሳትና መናፍቃን ሲመዘበር ተባባሪ እንዳትሆኑና እስከመቸውም በአባቶቻችን ስናዝን እንዳንኖር እንድታደርጉ በእኔና በቤተሰቤ እየተማጸንኩ ለልጆቼ የማስተላልፋት ኃይማኖት ከጥንት የወረደች እውነተኛ መሆኗን እየመሰከርኩ እንድኖር መጋደልን እንድታስተምሩን ዝምታው እንዲበቃና ነገሮች እንዲቋጩ እንድታደርጉ እማጸናችኋለሁ፡፡
ይህን ባታደርጉ ግን ለራሳችሁ ይብስባችኋል፡፡ ሕዝበ ክርስቲያኑ ከመቸውም ጊዜ በላይ የቅድስት ቤተክርስቲያን ነገር እያቃጠለው ይገኛል፡፡ የእናንተ ውሳኔ የሾማችሁን አምላክና ሕዝበክርሰቲያኑን የሚያስደስት እንደሚሆን እንጠባበቃለን፡፡
የቅዱሳን አምላክ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን መናፍቃንን ከቤቱ ጠራርጎ ያጽዳልን፡፡ አሜን፡፡

Anonymous said...

washo.
http://www.awdemihret.blogspot.com/2012/05/blog-post_8654.html

Anonymous said...

አረ የአቡነ ጳውሎስ ነገር ግራ አጋብቶኛል የሳቸው ሃይማኖትም ቢመረመር ጥሩ ነው ባይ ነኝ ውይ ውይ ውይ ሰለቹኝ …………….. አረ ብፁዓን አባቶች በርቱልን ከውጭ ጠላት ከውስጥ ደግሞ አባ ጳውሎስ፤በጋሻው፤ሠረቀ………. ግብረ አበሮቻቸው አስቸግረውናል ለሚቀጥለው ትውልድ ምን ልታስረክቡት አስባቿል??

ዲ/ን ዮሴፍ

Anonymous said...

አረ የአቡነ ጳውሎስ ነገር ግራ አጋብቶኛል የሳቸው ሃይማኖትም ቢመረመር ጥሩ ነው ባይ ነኝ ውይ ውይ ውይ ሰለቹኝ …………….. አረ ብፁዓን አባቶች በርቱልን ከውጭ ጠላት ከውስጥ ደግሞ አባ ጳውሎስ፤በጋሻው፤ሠረቀ………. ግብረ አበሮቻቸው አስቸግረውናል ለሚቀጥለው ትውልድ ምን ልታስረክቡት አስባቿል??
ዲ/ን ዮሴፍ