Thursday, May 17, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ስድስተኛ ቀን ውሎ (አርእስተ ጉዳይ)

/ ሲኖዶስ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ላይ የተዘጋጀውን ሪፖርት አዳመጠ
 (ደጀሰላም፤ ግንቦት 8/2004 ዓ.ም፤ May 16/ 2012/ READ this news IN PDF)፦
·        ኮሚቴው ፍጹም ውግዘት የሚገባቸውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች ለይቷል - ማኅበረ ሰላማ፣ ማኅበረ በኵር፣ የምሥራች አገልግሎት፣ አንቀጸ ብርሃን፣ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት፣ አሸናፊ መኰንን፣ አግዛቸው ተፈራ፣ ጽጌ ስጦታው እና ግርማ በቀለ ይገኙባቸዋል

·        “ሃይማኖቴ እንደ አባቶቼ ነው” ያሉት የአባ ሰረቀ እና “የቅን ልቦና የመንፈሳዊና የፈውስ አገልግሎትን ያቋቋምኹት ልጆቼን የማበላቸው ስለተቸገርኹ ነው” ያሉት የ‹ሊቀ ካህናት› ጌታቸው ዶኒ ጉዳይ ያለውሳኔ ሐሳብ ለምልአተ ጉባኤው ውሳኔ ቀርቧል
·        አባ ጳውሎስ ከጥንተ አብሶ ጋራ በተያያዘ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕና እንዲመሰክሩ ሊጠየቁ ይችላሉ
·        ሊቃውንት ጉባኤው ተደጋጋሚ ጥሪ አድርጎለት ያልቀረበው በጋሻው ደሳለኝ ዛሬ ጠዋት የሊቃውንት ጉባኤውን ሰብሳቢ በእጅጋየሁ በየነ አማላጅነት ሲለማመጥ ታይቷል፤ ሊቃውንት ጉባኤው “በአንድ ወቅት በራስ ቅል ኮረብታ ላይ ኢየሱስና ዲያቢሎስ ቁማር ተጫወቱ . . . ዲያቢሎስም በጨበጣ ገባ” የሚለውና ሌሎቹም ጥንቃቄ የጎደላቸው ንግግሮቹ ፍጹም ውግዘት የሚገባቸው እንደኾኑ አመልክቷል
·        የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን አመራርና መዋቅር ይሻሻላል፤ በጠቅላላ ጉባኤና በቦርድ ይመራል፤ የኮሚሽኑ ሊቀ ጳጳስ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር እንደሚኾኑ ተጠቁሟል
·        የማኅበራት መመሪያ ረቂቅ ለውይይት ቀርቧል፤ አሁን ባሉበት አኳኋን ከቀጠሉ “ሌላ ሲኖዶስ ይኾናሉ፤ የፖቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ ይኾናሉ፤ በቀኝ ዘመምና ግራ ዘመም አቋም ቤተ ክርስቲያኒቷን ይውጣሉ/ይከፍላሉ” የሚል ስጋት የቀረበባቸው ማኅበራት ንብረት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን መዋቅር ውስጥ ተጠቃልሎ እንዲተዳደር ሐሳብ ቀርቧል፤ የመመሪያውን ረቂቅ በጥንቃቄ የተመለከቱት የምልአተ ጉባኤው አባላት ጉዳዩ በይደር እንዲታይ አድርገዋል
ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን

2 comments:

Anonymous said...

እንኳን ማኅበረ ቅዱሳን ሃይማኖተ አበውም ታግዷል

አንደኛ ማኅበረ ቅዱሳን ተቋቋመው ልክ እንደ ሃይማኖተ አበው የኢትጵያ ተማሪዎች ማኅበር ነው፡፡ በቀጥታ ትናንሽ ለውጦችና የስም መተካት ብቻ ነው የተደረገበት፡፡ ሃይማኖተ አበው ከዐርባ ሽህ በላይ አባላት ነበሩት፡፡ ግን ደርግ ወጣቱ ሃይማኖተኛ እንዲሆን ስለማይፈልግና አን ሀገራ የወጣቶች ማኅበር ስላቋቋመ በአንድ ደብዳቤ ማኅበሩ ታገደ አባቶችም ወጣቶች አባላት እንዳይበተኑ በማለት ወደ ሰንበት ትምህርት ቤት እንዲታቀፉ አደረጉ፡፡ ማኅበሩም ለማደራጃ መምሪያውና ለሰንበት ትምህርት ቤት እድገት ከፍተኛ ስተዋጽኦ አደረገ፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ ማኅበረ ቅዱሳንን ያቋቋመችበት ሕግ ዶግማ አይደለም፡፡ እንደዚህ ዓይነት አመለካከት ያቸው አባቶች ካሉ እንኳን ካህናት ገና ክርስቲያን አይደሉም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ተባለው ማኅበር ከአእማደ ምስጢር ስድስተኛው የሃይማኖት መገለጫ ወይም ስምንተኛው የቤተ ክርስቲያን ምስጢር ነው ብለው ከሚያምኑ ሰዋች ይሠውረን፡፡ ለእኔ ማኅበረ ቅዱሳን ፕሮጀክት ነው እስከ አሁን በጣም የተወሰ ስኬታማ ውጤት አምጥቷል የጣሩትን አመስግኖና የምስክር ወረቀት ሰጥቶ ፕሮጀክት ማጠናቀቂያ መሠራት አለበት፡፡ አሁነ ማኅበረ ቅዱሳን ወጥ ረግጧል፣ የፖለቲካ፣ የንግድ፣ የመንደር፣ የኑፋቄ ማኅበር ሆኗል ማመን ካልፈለጋቸውሁ በብቁ ማስረጃ በሂደት ሁሉንም እናጋልጣለን እኛ የሰው ገመና ለምን ይጋለጥ ብለን ነው እንጅ፡፡

አሁንም የምንጠብቀው ምንም እንኳ መደራጀት መብት በሕገ መንግሥት የተሰጠን ቢሆንም እንኳን ማኅበረ ቅዱሳንና ንጉሠ ነገሥቱ ሳይቀሩ የክብር አባል የነበሩበት፣ ፓትርያርኩ የሚመሩት፣ በሲኖዶስ ታወቀ፣ ከቤተ ክህነት በጀት የነበረው፣ ታላቁ ሃይማኖተ አበውም በዓለማዊውና ደርግ በሾመው ሥራ አስኪያጅ በአንድ ደብዳቤ ታግዷል፡፡

Anonymous said...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
ቅዱስ ሲኖዶስ ውይይት አጀንዳዎች ይዘት ከወቅታዊ ጉዳዮች አንጻር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሃኛው ክፍለ ዘመን ከደረሰችባቸው አበይት ስኬቶች አንዱ በራስዋ መንበር በራሳዋ ፓትርያርክ በራስዋ ሊቃውንት ጳጳሳት መመሪት መጀመርዋ ነው፡፡ ይህም በሊቃውንቷ ብርታት በሦስት ነገሥታት ዘመን በዮሐንስ አራተኛ፣ በዘውዲቱ፣ እና በኃይለ ሥላሴ ዘመናት ነገሥታቱን መሣሪያ አድርገው የተቀዳጁት ድል ነበር፡፡ አሁን የሚያሰጋት የቀደሙት አባቶች የደረሱበትን ስኬት በየቦታው በሚሱልከለኩ የድሞው መንግሥት አስተሳሰብና አመራር ቅሬት አካሎችና የወቅታዊ አጥፊ ፖለቲካ አራማጆች፣ እንዲሁም የልዩ ጥቅም ተጋሪ ቡድኖች ጉዳይ አስፈጻሚ ባለአደራ ጳጳሳት እንዳይፈርስ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን በልዩ ልዩ ከፍተኛ ለውጥና ውጥረት ላይ ትገኛለች፡፡ ለውጦቹ ለምሳሌ ፈጣን ልማት፣ የድኅነት ቅነሳ፣ ለሞት የሚዳርጉ በሽታዎችን መቆጣጣር፣ የትምሀርትና የመረጃ ጥራት ማጠበቅ፣ የሰለጠነ የማኅበራዊ አደረጃጀት፣ የቱሪዝምና የባሕል ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ ዓለም አቀፍ ግንኙነት፣ የሕጻትና የእናቶች ደህንነት፣ የፍትሕና የሰላም ትግበራ፣ የመሳሰሉት ሲሆኑ ውጥረቶቹ ከምራስቅ አፍሪካ መልከዓምድራዊ አቀማመጥ፣ በተያያዘ፣ የአክራሪዎች በሀገሮች ፖለቲካዊና ማኅበራ ደኅንነት ላይ የፈጠሩት ጫና፣ የተረጋጋ ሀገራዊ አደረጃጀት ከሌላቸው ሀገሮች የሚሰነዘሩ ጥፋቶች መከላከል፣ የተፈጥሮ ሀብት መራቆትና የኢነደስትሪ ጥሬ ዕቃ አቅርቦትን ማደራጀት፣ የመንግሥት ተቋማት ለሕዝቡ ብቁ አገልግሎት ስለሚሰጡበትና ሚዛናዊ የገበያ ሥርጭት ስለሚኖርበት ሁኔታ፣ በመሳሰሉት ከፍተኛ ተጠያቂነት ያለባቸው ጉዳዮች ላይ መንግሥት ሌሊት ከቀን እየሠራ ይገኛል፡፡ የዚህም ጥረት ዋና ምክንያት ምን ዓይነት ሀገርና አካባቢ ለተከታዩ ትውልድ ማስረከብ ይገባናል ከሚል ከፍተኛ የሀላፊነት ስሜት የመነጨ ልዩ የአስተሳሰብ ደረጃ ነው፡፡

ከዚህ አንጻር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከዓርባ ሚሊየን ሕዝብ የሀገሪቱን አጠቃላይ ሕዝብ ከ60 በመቶ በላይ የምትመራ መለኮታዊ (የመለኮት እገዛ የማይለያት) ተቋም ስትሆን አባቶች ደግሞ መለኮትን ፈቃድ የሚፈጽሙ ለከፍኛው መንፈሳዊ ተልዕኮ የተጠሩና የተሸሙ በዚሁ በተጠሩበትና በተሸሙበት የሥራ መስክ መክበርና መከበር የሚገባቸው ሊቃውንትና ቅዱሳን ናቸው፡፡ ይህ የሚሆነው ግን በዓመት አንድ ጊዜ ሲገኛኙ ሊያነሱ የሚገባቸው ጉዳዩች ቤተ ክርስያኒቱ ካላት ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሕልውና፣ ሀገራዊና ሰብዓዊ ኃፊነት ጋር ሲገናኙና ሲታረቁ ነው፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ከፍተኛ ከበሬታና ኃፊነት በሚሰጣቸው አባቶች የተዋቀረ ከላይ በመንፈስ ቅዱስ ከታች በሕዝብ እምነትና ጸሎት፣ ከላይ በመለኮት ፈቃድ ከታች ከኛ ይሻላሉ ተብለው በተሸሙ ቅዱስ አባት እየተመራ አጀንዳዊቹ ምን መሆን አለባቸው ሚለው ነገር በቅጡ ካልተመለከትነው በርግጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ያለው የት ነው? የማንን ጉዳይ ነው የሚያፈጽመው? ለማን ሕልውና ነው የቆመው?የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡

የሀገርን ጉዳይ ጉዳየ ማለት ይቅርና የቤተ ክርስያኒቱን ጉዳይ እንኳ እኮ በቅጡ እየተመለከቱ ነው ወይ፡፡ ዋናዎቹ የጳጳሳቱ መገኛ፣ የቅርስ ባለቤት፣ የታሪክ መዛግብት የሆኑት ገዳማት በከፍተኛ ደረጃ ተጉሳቁለው የተወሰኑ ቡድኖች በስማቸው አሮጌ ጨርቅ ሳይቀር እየለመኑባቸው፣ ኪስ መሙያ ሆነዋል፡፡ መነኰሳቱ የኮሙኒዝም ሥርዓት ካደረሰባቸው ግፍ በበለጠ ለልማትና ለእድገት እንቅፋት እንዲሆነ እስከመቀስቀስ በመድረስ የሁለት ዓለም ስደተኞች ሆነዋል፡፡ ጳጳሳቱ ከገዳማቱ ጋር ያላቸው ግንኙነት ላልቶ የከተማ ወጣቶች አለንላችሁ በማለት የሚነግዱባቸው፣ የዓለማውያን ጊዜ ማሳለፊያ ሆነዋል፡፡ ለመሆኑ ለገዳማቱ ጉዳይ ማነው ተጠያቂ፣ የከተማ ወጣቶች ወይስ የገዳማት መመሪያ፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር መገኛ የነበሩት የአብነት ትምህርት ቤቶች እንደገዳማት መነገጃ ሆነዋል ትምህርት መመሪያን በብቃት ማጠናከር ሳይቻል ቀርቶ ነው ወይስ አሁንም የጥቅም ጉዳይ አለበት

የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ፣ የቅርስና ቱሪዝም ፣ የወጣቶች፣ የልማት ጉዳይ እኮ ለማንም ተላልፎ ሊሰጥ የማይችል የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ብቻ በዋናነት ሊሠራ ሚገባ ማንም ጣልቃ ሊገባበት የማይችል አስተዳደራዊ ተግባር ነው፡፡ ይህንን ከመለኮት ለቤተ ክርስቲያኒቱ የተሰጠ አደራ በቤተ ክርስያኒቱ ስም ለተዋቀሩ ቡድኖች አሳልፎ ከሰቱ በኋላ ይስተካከል ሲባል ቆቤን አወልቃለሁ ማለት ትርጉሙ ምንድን ነው፡፡

ዛሬ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያሠጓት ዋና ዋና ጉዳዮች ስብከተ ወንጌል በተረት መዳከም፣ የቅርስ ዝርፊያና ውድመት፣ ወጣቶችን የሚመለከት ማዕከላዊ የሆነ አሠራር አለመኖር ወይም የማደራጃው ድክመት፣ በካህናት መካከል የሚፈጠሩ ጉዳዮችን የሚፈታ የፍትሕ መታጣት፣ ለቁጥር አዳጋች የሆኑ ደቃቅና የተደራጁ ማኅበራት ክፍፍልና የርስ በርስ ግጭት፣ የገዳማት አስተዳደር መዳከም፣ የገንዘብ ብክነትና ውደመት፣ ለራሳቸው ጥቅም ብቻ የሚተጉ ሀገረ ስብከት የለሽ የድርጅትና የቢሮ ሐዋርያት (ጳጳሳት)፣ ማዕከሉን ያልጠበቀ የውጭ ግንኙነት፣ ፍጹም ፖለቲከኞች ሆኑ ጳጳሳት፣ የአብነት ትምህርት ቤቶች በከፍተኛ ፍጥነት እየተዳከሙ መምጣት፣ ወጣቶች ከሰንበት ትምህርት ቤት ውጭ፣ ከወጣትነት በኋ ያሉት ምእመናን ከሰበካ ጉባኤ ውጭ በመደራጀት መከፋፈል፣ የሌሎች ሃይማኖቶች እየበረቱ መምጣት፣ የመሳሰሉት ናቸው…

ታዲያ አባቶች ጊዜያቸውን እያጠፉ ያሉት በምን ላይ ነው፡፡ እርስ በርስ በመወነጃጀል፣ በማደም፣ ከመዋቅራቸው ይልቅ ለቡድኖችና ዶግማና ቀኖና ላፈረሱ ሁሉም ማኅበራት ጠበቃ መቆም፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሥራ እንቅፋት በመሆን፣ እኔ እስከማምነው ድረስ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያዳከማት ሁሉም ራሱን ሥራ ባለመሥራቱ ነው፡፡ ተሐድሶ ለም ማለት አይደለም ግን ቤተ ክርስያኒቱ ከተደዳከመች ለምን አይገቡ ዓላማቸው እኮ ነው፡፡ መጡብን ብሎ በመረበሽ፣ ወይም የረብሻ ወሬ ላመጡት ከመሟገት መዋቅሩን አጠናክሮ ሥራ መሥራት፣ ማኅበራቸው ሥርዓትና መዋቅር እንዳይዝ ሚታገሉት ቡድነኞች ለምን መዋቅሩ ውስጥ ገብተው ሥራ አይሠሩም ተሀድሶን አይከላከሉም፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤት ገብተው እንዳይማሩ ማን ከለከላቸው፣ በሰበካ ጉባኤ ታቅፈው እንዳያገለግሉ ማን አገዳቸው ልማትን በልማት ኮሜቴ ገብተው እንዳያለሙ ማን አገደ በፖለቲካዊ ማኅበር ተገንጥለው ከመዋቅር ውጭ ሆነው ለመሥራት ለምን ፈለጉ፡፡

ይህንን የመንግሥት አካላት ሳይቀሩ ሊታዘቡት የሚገባ ሐቅ ነው እንላለን፡፡