Monday, May 21, 2012

ሐሙስ ማታ

ቅጣው የተባሉ የተዋሕዶ አርበኛ የሚከተለውን መልዕክት አድርሰውናል::  መልካም  ንባብ::
+++
መቼም ሁሉ ዕለት የየራሱ የሆነ ታሪክ አለው፡፡ ጠቅልሎ መጥቶ መጥፎ ያረገፈውን አራግፎ ሲሄድ ብዙ የሚተውልን ወይም የሚተውብን ጉዳይ አይጠፋም፡፡ የሰሞኑ /ከዚህ በቅርቡ ጊዜያት አንስቶ/ የምናየው ፍጥጫና ጡጫም ከዚህ የታሪክ ሂደት የተለየ አይደለም፡፡ ዮዲት መጣች ጊዜዋን ጠብቃ ሄደች:: ግራኝም መጣና ሄደ:: ጣልያንም ተከሰተና በራሱ ጊዜ አገሩ ገባ፡፡ ተዋሕዶ ግን ወልድ ዋሕድ እያለች ነበረች:: አለች:: ትኖራለች፡፡


ሐሙስ ማታ ይሁዳ ትንቢቱን በተግባር ሲያረጋግጥ፣ አይሁድ ሊቃነ ካህናትን አስከትሎ ብቅ ያለባት፣ ኋላ ላይ ታንቆ ለመሞት እንኳ ቢመኝ ያልሆነለትን ብርቱ መከራ ሊቀበል ጌታውን ለሽያጭ ያቀረበት፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ጥብአት ገድሎት በጭራሽ አላየሁም አልሰማሁም ያለበት፣ በጌታው የፍቅር ዓይን ወዴት አለህ የተባለበት የግፈኞቹ አይሁድ ጭካኔ የጅማሬው ጅማሬ የታየበት ዕለት ነው፡፡ ሁሉ ለበጎ ሊሆን ክርስቶስም ስለዓለሙ መዳን በፈቃዱ ሲሰቀል በዙሪያው ግን ስንት ትርምስ ነበር:: ስንቱስ ራሱን ለትዝብት ጣለ፡፡
 ሐሙስ ማታ በድጋሚ ከሁለት ሺህ ዓመታት በኋላ እንደ አዲስ እያየነው ነው፡፡ የተዋሕዶ ሥርዓት፣ ቀኖና፣ ዶግማ ይከበር ያሉ ሃይማኖታቸውን ለመጠበቅ የፀኑ የበረቱ ለሽያጭ ቀርበዋል፡፡ ይሁዳዎች በውስጥ በአፍአ  በዝተዋል፡፡ ሁለት ደመወዝ የሚበሉ የመናፍቃንን ሃሳብ እውን ለማድረግ ሌትና ቀን የሚሠሩ ይሁዳዎች በዝተዋል፡፡ በየ ድረ ገጾች (አባ ሰላማ፣ደጀ ብርሃን፣አውደ ምሕረት...) የምናያቸው እነዚህ “ቆናጽል ንዑሳን” ጥቃቅን ቀበሮዎች የይሁዳ የግብር ልጆች ናቸው፡፡
 
ያን ጊዜ የነበረው ይሁዳ ገንዘቡን ሳይበላው እንዳለፈ የዛሬዎቹም የሰበሰቡትን ሀብትና ንብረት ሳይጠቀሙበት ያልፋሉ፡፡ ለብሰው ሳይሞቃቸው፣ ጐርሰው ሳይጠጋቸው ጥለውት ይሄዳሉ:: ተዋሕዶን አሳልፎ ሰጥቶ በሃይማኖት ጉዳይ ቁማር ተጫውቶ የተመቸው እንደሌለ ግልጽ ነው፡፡ ዛሬ ይሁዳን ጠቅላይ ቤተ ክህነት አፀድ ልናገኘው እንችላለን፡፡ በአጥቢያ እና በወረዳ ቤተ ክህነት የቤተ ክርስቲያን ሥራ ለመስራት አስመስሎ ያለ ቦታው ተቀምጦ፤ ያለ ሥፍራው ተንሰራፍቶ ልናገኘው እንችላለን፡፡ ልቡ በገንዘብ ተነድፎ ወንድሙን ሊሸጥ ተስማምቶ ይሁዳ ዛሬው በየ ሥፍራው አለ፡፡
 
በዚህ በሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት እንኳን ስንቱን ይሁዳ አየን፡፡ ያልጠበቅናቸው ይሁዳዎች ሐሙስ ማታ ሆነና ተከሰቱ፡፡ ሊሸጡ ሲያስማሙ ስንቶቹን አየናቸው፡፡ ዲሲ የጦርነት አውድማ ያደረገ፣ ምእመኑን ግራ አጋብቶ ሀገረ ስብከቱን በታትኖ፣ ንጹሐንን አሳዝኖ፣ የተሠራውን በጎ ሥራ ሁሉ በአፍጢሙ የደፉ ይሁዳን አየን፡፡ የአዋሳ ትርምስ የንጹሐን እንባ ሳይታበስ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ሌላ ዕንባ ሌላ ሐዘን ተደገመ፡፡ ኑፋቄ ይዞ ማኅበረ ቅዱሳንን የተቀላቀለ፣ ኋላም ተነቅቶበት የተባረረ ኃይለጊዮርጊስን የመሰለ ይሁዳንም አይተናል፡፡ የሚሠራው ክፉ ሥራ ፍጻሜውን ምን እንደሚያደርግለት የይሁዳን ታሪክ ካነበበ ይረዳዋል፡፡ ንጹሃንን ሸጦ፣ ተዋሕዶን “ከእነ አባ ሰላማ” ብሎግ ጋር አስማምቶ እንቅልፍ ወስዶት ከቀጠለ መልካም ነው፡፡ ግን አይመስለንም፡፡ እኛ ብንተወው ጉዳዩን /ወንጀሉን/ ዐቃቤ ሕግ አይተወውም፡፡ የእኛ ዐቃቤ ሕግ /ዐቃቤ ተዋሕዶ/ የቅዱሳን ጸሎት፣ አጽማቸው፣ ዕንባቸው፣ ተጋድሎቸው ነው፡፡ በደሙ በመሠረታት ቤተ ክርስቲያን ተቀልዶ ተኝቶ ማደር አይኖርምና የቅዱሳን ዕንባ ይሁዳን ዛሬም ይፋረዳል፡፡
 
ደግሞ መካከለኛ አለ፤ አላየሁም አልሰማሁም የሚል፡፡ ይሄ ተጸጽቶ ንስሐ ሊገባ ለጊዜው ግን ዝምታን የሚመርጥ፡፡ አሁን በእውነት እንዲህ ያለው መስሎ አዳሪ ቢበዛ እንጂ የቤተ ክርስቲያን ችግር የሚያስተኛ ነበር ወዳጄ፡፡ መናፍቃን ገድላቱን ሲያብጠለጥሉ አላየሁም፤ አልሰማሁም የሚለው የየአጥቢያው ካህን ምን ይሉታል፡፡ አንዳንዱማ በተዋሕዶ ልጆችና በቆናጽሉ /በቀበሮዎቹ/ መካከል የሚካሄደውን ጦርነት እንደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እየተከታተሉ ይዝናናል፡፡ ዛሬ ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህ አለ፣ ይኼኛው የመናፍቃን ድረ ገጽ ይኼን መለሰ እያለ ይስቃል::
 
ወዳጄ ወንድምህ ተናንቆ እየሞተ ያለው አንተን ጡት አጥብታ ላሳደገችህ ቤተ ክርስቲያን እንደሆነ ዘነጋኸው ይሆን፡፡ ስማቸው በየ ድረ ገጽ እየተጠቀሰ የሚዘለፉ ወንድሞችህ አንተን ለማኖር ሃይማኖትህን ለመጠበቅ እየሞቱ ነው፡፡ አንተ ግን ከጀርባ ሆነህ ትዝዝናለህ፡፡ የግል አስተያየትህን በመስጠት ትረቃለህ፤ ትመጥቃለህ፡፡ የአንተ አስተያየት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምንም ካልጠቀማት በእጅህ ካለው ጠጠር አንዱንም ካልወረወርኸው የጓዳው ውይይት ምን ፋይዳ አለው ብለህ ነው፡፡
ሐሙስ ማታ ግፈኞች ሰይፍና ጎመድ ይዘውም የቀረቡበት ነው:: እንግዲህ ሰይፍ ሲነሳ ባለ ሰጥፍ ራሱን ይመርምር፡፡ ከይሁዳ ተነጋግሮ፣ ጴጥሮስን አሸብሮ ሰይፍ ወድሮ ለመያዝ፣ ለመጨበጥ፣ ግፍ ለመሥራት፣ የቀረቡ ሁሉ ራሱን ይመርምር፡፡ ሰይፍን የሚያነሳ በሰይፍ ይጠፋል፡፡ ከዚህ ይልቅ “እኔ ከደሙ ንጹህ ነኝ” ማለት ይሻላል፡፡
 
መንፈሳዊ ሰው በበትር አይመለስም፡፡ በርቀት ያለው ሰማያዊ ተስፋ ስለሚያጸናው፡፡ ሰይፍ አያሸሸውም፡፡ “ሰማዕትነት አያምልጥህ” እያለ ሳይጠራራ እየሞተ ለማሸነፍ ሳይዘጋጁ ሰይፋችሁን ወደ ሰገባው መልሱ፡፡ እውነትን የምታጠፉ መስሏችሁ ከገፋችሁበት ግን ፍርዱን ለሰማያዊው ንጉሥ ትተናል፡፡ ሐሙስ ማታ ሲያልፍ አርብ ላይ መድኃኔዓለም በድጋሚ አይሰቀልም፡፡ ተዋሕዶም ምንም አትሆንም አርብ የክፉዎች የእናንተ የመከራ ቀን እንዳትሆን አስቡበት፡፡

4 comments:

Anonymous said...

AMEN WEGENOCHE ENGANEM BE HAYEMANOT YTESENAN.

well said...

እግዚአብሔር ይስጥህ ወንድሜ የልቤን ነው የተናገርከው ለሁሉም ጊዜ አለው ለመንቀልም ለመትከልም አለው ጊዜ የቅዱሳን አባቶቻችን ጸሎት ዘወትር አምላካቸው ፊት ነው ንስሐ ቢገባና ከጌታ ጋር ቢታረቅ አሁን ጊዜው ተሰጥቶ ነበር ይጠቀምበት ካልሆነ ተቀምጦ ኦርቶዶክስን ከሚተችበት ወንበር ላይ እግዚአብሔር እንስቶ እንደ ናቡከደነፆር ወደ ጫካ ይሰደዋል አንደበቱም ይዘጋል "አለሁ አለሁ" ሲል እንደ ዳታንና አቤሮን ምድር ተከፍታ ትውጠዋለች መስሎት ነው ካንዱ ወደ አንዱ እንደ አበደ ውሻ እየተሯሯጠ የሚለክፈው እውቀት የለም በገንዘቡና በአድና የሚያምን ስለሆነ እሱም አድመኞቹም ይበተናሉ ገና ጉድ እንሰማለን አጥብቀን ብቻ " አምላከ ቅዱሳን እርዳን እያልን መጸለይ ነው

YIMERAYENEW said...

ቃልወትን ያሰማልን!
ምን ይሆን....................???
ሳጥናኤል ወደ ሲጥንና ስሙን ቀየረ
ወደ እንጦርጦስ ተወረወረ
አዳምን አሳስቶ ከክብሩ አዋረደው ግን ይሕ አድመኝነቱ በክርስቶስ መስቀል ተሻረበት... ዛሬም ተንኮሉን አልተው ብሎ መልኩን እየቀያየረ በክርስቶስ ደም የተመሰረተሽ ቤተክርስቲያንን እየተፈታተናት ይገኛል!!!
ሰውም በሰውነቱ ትናንትን ዘንግቷል አላስተዋለም ነገን በራሱ ቁጥጥር ስር እንዳደረገ ብቻ ነው የሚታየው የስጋ ሞቱንም ፈጽሞ የረሳ ይመስላል ምክንያቱም ጥበቡ ስጋተኮር ብቻ ስላደረገ በውነት ሰው የከንቱ ከንቱ ስጋው ምንም የማይጠቅም መሆኑን ያስተውል !!! ለምን የፍርድ ቀን ከኛ ትሰወራለሽ በውነት ክርስቶስ በፊቱ አቁሞ ይታዘበናል........

Anonymous said...

Tebarek