Wednesday, May 16, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ የዋልድባ ልማት ፕሮጀክት ጠቀሜታን ያልዘገቡበት ምክንያት እንዲያቀርቡ ተጠየቁ

READ IN PDF
ለማኅበረ ቅዱሳን ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምርያ “በዋልባ ገዳም አካባቢ  የሚካሄደውን ግዙፍ የስኳር ልማት ፕሮጀክት በተመለከተ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ያወጣው መግለጫ በማኅበሩ ልሳናት ላይ ለምን እንዳልተዘገበ” የሚል ክስ ያዘለ ደብዳቤ ተጻፈለት:: የደብዳቤው ይዘት በዋልድባ አካባቢ እየተካሄደ ያለው የስኳር የልማት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ያወጣው የፕሮጀክቱን ጠቀሜታ መግለጫ በማኅበሩ ሚድያ ያልተዘገበበትን ምክንያት ማኅበሩ በጽሑፍ እንዲያስረዳ የሚጠይቅ ነው:: ማኅበሩ ፕሮጀክቱን በተመለከተ አጥኚ ባለሙያዎች ወደ ዋልድባ ገዳም አካባቢ እንደላከ እና በሪፖርቱም ዙርያ የማኅበሩ የሥራ  አስፈጻሚ እና አመራር አካላት ውይይት እንዳደረጉበት ደጀ ሰላም ታማኝ ምንጮን ጠቅሶ መዘገቡን ይታወሳል:: 

 
በጠቅላይ ቤተ ክህነት ውስጥ የተሰገሰጉት የውስጥ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ከምንም ጊዜ በላይ ቤተ ክርስቲያኒቷን ለማድከም የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ላይ ናቸው:: ለዚህም የተሐድሶ መናፍቃን ብሎጎችን ማየት በቂ ምስክር ነው:: ቅዱሳን መላእክትን፣ ቅዱሳን አባቶችን፣ እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ወላዲተ አምላክን፣ ጻድቃን ሰማእታትን እና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን የሚሳደበው “አባ ሰላማ” ብሎግ በቀጥታ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የወጣው ደብዳቤ በአስቸኳይ በብሎጋቸው  እንዲለጥፉት ተብሎ ተልኮላቸዋል:: ለዚህም በቂ ማስረጃ እና መረጃ ደርሶናል:: በጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምርያ ሥም የተጻፈው ደብዳቤ ጸሐፊዎቹ ወይም ከጀርባ ሆነው ደብዳቤውን የሚያጽፉት ሰዎች ተልኮዋቸው ቤተ ክርሲቲያኒቷን ማድከም መሆንን ከተሐድሶ መናፍቃን ብሎጎች ጋር ያላቸውን ግኑኝነት ያስረዳል:: ጌታችንና መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶ “አማላጅ” በማለት የሚጽፉት “ደጀ ብርሃን” ብሎግ እንዲሁም ደግሞ በአጠቃላይ “የቤተ ክርሲያናችን አስተምህሮ ትክክል አይደለም” በማለት የኑፋቄ ትምህርት የሚያሰራጨው “አባ ሰላማ” ብሎግ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እየተደረገላቸው ያለው ትብብር የቤተ ክርስቲያንናችን የውስጥ ጠላቶች በአሁን ወቅት አካሄዳቸውን ጥርት ባለ መልኩ እየታየ ነው:: እነዚህ የኑፋቄ ብሎጎች “ልማታዊ” ናቸው በማለት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲነበቡ ተፈቅዶላቸዋል:: በተቃራኒው ግን እነ ደጀ ሰላም እና አንድ አድርገን “ጸረ ልማት ናቸው” በማለት  ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይነበቡ እየተደረገ ነው::
ጠቅላይ ቤተ ክህነት “ጸረ ልማት” ናቸውና “ይዘጉልኝ” በማለት ለዘጊው አካል ጥያቄ ሲያቀርብ ኑፋቄ የሚያሰራጩት እነ “አባ ሰላማ” እና “ደጀ ብርሃን” ብሎጎች እንዲዘጉ ግን ጥያቄ አልቀረበም:: ጸረ ልማት የተባሉት እንዲዘጉ ተፈረደባቸው:: ልማታዊ የተባሉት የኑፋቄ ብሎጎች ግን ከጠቅላይ ቤተ ክህነት መረጃ እየተሰጣቸው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲነበቡ ተፈቅዶላቸዋል::
 የማኅበረ ቅዱሳን ልሳናት/ሚድያ የዋልድባን የስኳር ልማት ፕሮጀክት ያለው ጠቀሜታ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የተሰጠው መግለጫ ባለመዘገባቸው የተነሳ በጸረ ልማት ተፈርጀው ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምርያ የተጻፈበትን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ  ደርሶናል::

7 comments:

ደምሴ ማሙየ said...

በስጋዊ አስተሳሰብ የሚኖሩ አይሁዶች ምንም ሃጢያት እና በደል የሌለበትን መድህን አለም ኢየሱስ ክርስቶስን ስቀለው ስቀለው ስቀለው....ስቀለው,ሲሉ ሽፍታ ወንበዴና ዘራፊ የሆነውን በርባንንን ይፈታ ሲሉ ጮሁ አሁንም ደግሞ ተረፈ አይሁዶች አጽራረ ቤተክርስቲያ ልማታዊ, እውነተኛ የቤተክርስቲያ ልጆች ደግሞ ጸረ ልማት ተብለው በተሃድሶ አራማጆች ቤተክርስቲያን ተፈርዶባታል.
ነገር ግን እግዚአብሄር ይህን የሚያስታግስበት ጊዜአለውና በጸሎት ሁላችንም እንትጋ.........

ደምሴ ማሙየ said...

በስጋዊ አስተሳሰብ የሚኖሩ አይሁዶች ምንም ሃጢያት እና በደል የሌለበትን መድህን አለም ኢየሱስ ክርስቶስን ስቀለው ስቀለው ስቀለው....ስቀለው,ሲሉ ሽፍታ ወንበዴና ዘራፊ የሆነውን በርባንንን ይፈታ ሲሉ ጮሁ አሁንም ደግሞ ተረፈ አይሁዶች አጽራረ ቤተክርስቲያ ልማታዊ, እውነተኛ የቤተክርስቲያ ልጆች ደግሞ ጸረ ልማት ተብለው በተሃድሶ አራማጆች ቤተክርስቲያን ተፈርዶባታል.
ነገር ግን እግዚአብሄር ይህን የሚያስታግስበት ጊዜአለውና በጸሎት ሁላችንም እንትጋ.........

Anonymous said...

Is there a regulation that forces any newspaper or magazine to publish some thing on it if it does not want to do so? Are they trying to force Tsimea tsidik and Hamer to publish about waldiba? Any one who knows some thing, please tell what you know about this.

Anonymous said...

yetetseyekew Tsekaminetun Sayihon Yederesubetin New Debdabew yemayilewn ale atibelun temelkachi yitazebal belu Ahunim Waldiba dires yehedew Ye Mahibere Kidusan Budin Min Derese ?Menager neberebet Ebakachihu sew Mahiberun enditselana enditseratser atadirgut Mahibere Kidusan Lebete Kiristyan yasfelgal

Anonymous said...

melkam neger neber

Anonymous said...

የቤተክርስቲያናችንና የሐገራችን የካንሰር በሽታ የሆነው እራሱን ማህበረ ቅዱሳን እያለ የሚጠራው የማፊያ፣ የወሮበላ፣ የአሸባሪ፣ የመሰሪ ድርጅት የተሰጠው ደብዳቤ ብጣም አስፈላጊ መሆኑ ፍፁም ጥርጥር የለውም። ሆኖም ግን ቤተክርስቲያናችንን ሐያ አመት ሙሉ የገዘገዛትና ምዕመኑን በእምነትና በቤተክርስቲያን ሥም ሲዘርፍ ለኖረ የሠይጣን ድርጅት በአሁኑ ጊዜ ግን በቃህ ሊባል ይገባው ነበር እንጂ የማስተካከል ደብዳቤ ብቻ መቀበል የለበትም። ማህበሩ ባጠቃላይ ለቤተክርስቲያናችንና ለሐገራችን ፈፅሞ አስፈላጊ አይደለም። ማቅ ካልተዘጋ በቀር በየጊዜው የማፊያ ስትራቴጁን እየቀያየረ የቤተክርስቲያንን ደምና የክርስቲያኖችን ደም ሲመጥ ለመኖር አላማ ስላለው እባካችሁ የቤተክህነትና የሲኖደስ አባቶች ይህንን መሰሪ የሰይጣን ማህበር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከካንሰሩ እንድትታደጉት በህያው እግዚአብሔር ሥም እንለምናችኁለን።

Shambelie said...

Shambelie from Haramaya University

It is real a shameful activity what is done by our the so called fathers who are educated. There are so many fathers of us in our church who only follow an agent that has a bread for them.
Ohhhh....GOD please, please......don't extend your silence more than this......
Abatoch alikewubin
Yal abata eyenorin
Egnam teteratary ena eminete godolo honin
ABIETU ...ANTE HUNEN