Wednesday, May 23, 2012

አባቶቻችን በተሐድሶ መናፍቃን የወሰዱት የማያዳግም ውሳኔ አስደስቶናል::እንኳን ደስ አለን ተዋሕዶያውያን!!!

በዘንድሮው የግንቦት ወር የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ብፁዓን አባቶቻችን ሐዋርያዊት ለሆነችው ቤተ ክርስቲያናችን ሐዋርያዊ እና ታሪካዊ  ውሳኔዎች በማስተላለፍ ጉባኤው ተጠናቋዋል:: ተመክረው አልመለስ ያሉት ውስጠ አርዮሳውያን እና ንስጥሮሳውያን የተሐድሶ መናፍቃን ተወግዘው እንዲለዩ ተወስኖዋል:: አምላከ ቅዱሳን የማይለያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ብዙ ፈተናዎች እንዳሳለፈች የቤተ ክርስቲያንናችን የታሪክ መዛግብት ያትታሉ:: ፈታኞቿ በመከራው ዘመን ውስጥ ቤተ ክርስቲያንን ያሸነፉ ቢመስላቸውም የመከራው ዘመን ሲያልፍ ቤተ ክርስቲያን በድጋሚ እያበበች እና እየተሰፋፋች ኖራለች:: ትኖራለችም:: ዮዲት ጉዲት ጥንታውያን መጻሕፍ አቃጥላ ቤተ ክርስቲያንን ታሪክ አልባ ለማድረግ ሞክራ ነበረ:: ነገር ግን እነ  አባ ሰላማ መተርጉም ተነስተው ቅዱሳት መጽሐፍት በድጋሚ እንዲጻፍ አደረጉ:: እናም ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ ተሸንፋ አታውቅም:: አትሸነፍምም::


በዚህ ዘመን የተነሱት “ቤተ ክርስቲያን መታደስ አለባት” እያሉ የሚያቀነቅኑት የተሐድሶ መፍፍቃንን ብፁዓን አባቶቻችን አሳፍረዋቸዋል:: ጸረ ተዋሕዶ የተሐድሶ መናፍቃን አቀንቃኝ ብሎጎች “አባ ሰላማ፣ ደጀ ብርሃን፣ አውደ ምሕረ....) በሬ ወለደ የሐሰት ዘገባዎቻቸው ሲገለጥባቸው አፍረዋል:: ወደፊትም ያፍራሉ:: ለጊዜው ብትደበቅም እውነት አሸናፊ ናትና:: እውነት ተሸናፊ ልትሆን አትችልም::

እንደ ቀደሙት የተዋሕዶ አርበኞች አበው የአሁኖቹም አባቶቻችን ለእውነት እንዲቆሙ ያደረገልን አምላክ ክብርና ምስጋና ይድረሰው:: ለብፁዓን አባቶቻችን እና ከእነሱ ጋር ለለፉት የሊቃውንት ጉባኤ አባላት ረዥም እዕሜ ከሙሉ ጤንነት ጋር ይስጥልን እንላለን:: እኛ የአሐቲ ተዋሕዶ አዘጋጆች እውነት በመገለጡ በጣም ደስ ብሎናል:: መላው የተዋሕዶ ልጆች እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን::

 አሐቲ ተዋሕዶ የቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ ሁኔታዎች እየተከታተለች የምትዘግበው ደጀ ሰላም ብሎግ ጋር እየተናበበች እውነትን ለምእመናን ለማድረስ የአቅሟን ሞክራለች:: ለወደፊትም የተሐድሶ መናፍቃን ለማጋለጥ እና ለሚያስተላልፏቸው የኑፋቄ ትምህርቶች የሊቃውንት ጉባኤው ምላሽ ተከታትለን ለማቅረብ ቃል እንገባለን::

የተሐድሶ መናፍቃን አቀንቃኝ ብሎጎች በብፁዓን አባቶች ላይ እንደተለመደው የስም ማጥፋት ዘመቻ ጀምረዋል:: በዚህ ምልዓተ ጉባኤ ላይ የተሐድሶ መናፍቃንን በመታገል መዶሻ ሆነው ሲደክሙ የቆዩት አባቶቻችን መካከል ብፁዕ አቡነ አብረሃም ላይ የፈጠራ ድርሰት አዘጋጅተው እያናፈሱ ነው:: አባቶችችን በፈጠራ ወሬ እንደማይሸማቀቁ ምንም ጥርጥር የለንም:: እንኳን በፈጠራ ድርሰት ቀርቶ ሰይፍ እንኳን ቢመጣ ወደ ኋላ እንደማይሉ በዚህ ምልዓተ ጉባኤ በያዙት አቋም አስይተዋል:: በብፁዓን አባቶቻችን ላይ ከተሐድሶ መናፍቃን እና ከደጋፊዎቻቸው የአካል ጉዳት እንዳያደርሱባቸው መከላከል ተገቢ ነው እንላለን:: 
አምላከ ቅዱሳን አሐቲ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጥብቅልን!!!
  

6 comments:

Anonymous said...

For me it is prepature end ! Many decisions are made but, their implementaion is not always there as long as the stambling block the so called patriarch and his advisor Elizabel are there. Hence, I feel that the holy synod must have discussed about implementaion problem encountered so far including demolition of the statue, reckless involvement of the guy on every church affair beyond his mandate. And the cover he gives to the so called " tehadiso".He had to be given a warning letter/statent.

The holy synod has underweighed the role of "aba" Serqe in his role as a pivot or axis of " Tahadiso" in the church.

Most of the people who are condemened us Menafiq and declared to be outcasted are already known and that is not a big success unless the gain in making it official. The holy synod had to give due attentions to the mites 'qinqin' who windowdress like memebrs of the church but are brain children of the decayed protestant.

The north America dioces and the gang group memeber " Aba Fanuel" and his accessory " Hailegiorgis" had to be discussed. And I feel that the north American christains must stand firmer than before against this guy and his club. The church has no place for these kinds of pigs and blood sucking leeches.

I am not clear if the holy synod has decided to reinstate Aba Hiruy or not !? I know there was an idea but I could not understand the final.

If enqubahir is there, I take it as the holy synod rescued MK but made the vast sunday schools vulnerable to weak leadership of the guy. And I suggest the sunday school youth must unite and defend the fact that the sunday school department is not waste bin or garbage spot for incapable and corupt menafiks like enqubahiri.And mk must not stop struggling for the betterment of the sunday scholl department that is expected to lead millions of church youth.

I am sorry that the holy synod never discussed about waldiba while it is the at most church monastry and is under difficult situation !!!

Thanks to the information you provided to us, if you ask me if about the success of the holy synod meeting.

The most important thing is that the Our fathers have demonstrated their unity on the church affairs except Guys like " patriarch, aba Gerima, aba fanuel" the latter two blind supporters and corrupt members of the gang club led by the former.

I was wondering why "Aba Gerima" was in every committee established !Just as informer of the " Patriarch " on what shall go in each committee. If I were " aba gerima" I prefer death rather than playing this role.


Finally, I thank you dear brothers/sisters. And please keep it up. God be with u.

Anonymous said...

እግዚአብሔር ቅዱሳን አባቶቻችን ዪተብቅልን.

Anonymous said...

እግዚአብሔር ቅዱሳን አባቶቻችን ዪተብቅልን.

Anonymous said...

God bless u all Ahati tewahedo, Andadrgen, dejeselam

Elelelelelele Menafikan Chinkilatu temeta , Setyan tewarede.

Tehadeso please go to your own hall with protestant and do ur dance song.

melaku meharie said...

ye abraham amlak ke egna ga nwe ahaiewoch bertu be informationachehu tetekmenal

Anonymous said...

በዘንድሮው የርክበ ካህናት ሲኖዶስ ስብሰባ በቤ/ክ ውስጥ የፈለጉትን ያህል እንክርዳዳቸውን ሲዘሩ ኖረው ሲበቃቸው እነሱን የመሰሉትን ቤ/ክ ውስጥ ተክተው በገዛ ፍቃዳቸው ከቤ/ክ ከወጡ ብዙ ኣመት ያስቆጠሩ መናፍቃን ስለተወገዙ ሲኖዶስ ትልቅ ስራ የሰራ ሊመስል ይችላል:: ለመሆኑ ከቤ/ክ ውስጥም ሆኑ ከውጪ ያሉ መናፍቃን መመሪያ ሰጫቸው ኣባ ጳውሎስ በስልጣን ላይ እያሉ የቤ/ክ ችግር መፍትሄ ያገኛል ወይ? ኣባ ጳውሎስ ሶስት መለኮት ብለው ስለጻፉት መጽሃፍና እመቤታችንን በተመለከተ የጻፉትን ኣጸያፊ ኣባባላቸውን ለውይይት ከቀረበ በኋላ ውሳኔ ሳይሰጥበት መታለፉ ትክክል ነው ወይ? የቤተክርስቲያን መሪዎች በራሳቸውና በቤ/ክ እየቀለዱ የሚኖሩት እስከመቼ ነው? ሁሉንም እግዚኣብሔር ይፍታው::