Tuesday, July 31, 2012

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመም የዋልድባ መነኰሳት ተጠያቂ ተደረጉ • READ THIS ARTICLE IN PDF.
 • ከአብረንታንት እና ማይ ለበጣ ሁለት መነኰሳት ወደ ማይ ፀብሪ ተወስደዋልበዶንዶሮቃ 50 በላይ የመነኰሳት እና መነኰሳዪያት ቤት በፖሊስ ተፈትሿል
 • ከፖሊሶቹ አንዲቱ ከጾታዋ የተነሣ ወደ ዋልድባ ለመግባት የማይፈቀድላት ሴት ናት
 • የአብረንታንቱ አባ ገብረ ሥላሴ ዋለልኝ እንደታሰሩ ናቸው
 • 49 ያላነሱ የቤተ ሚናስ መነኰሳት በፖሊስ ይፈለጋሉ
 • ‹‹እናንት ምታታሞች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ መታመም ተጠያቂዎች ናችሁ›› /የማይ ፀብሪ ፖሊሶች/
ሙሉ ዘገባውን የወሰድነው ከደጀ ሰላም ብሎግ ነው::  

በዝቋላ ገዳም የወተት ላም እርባታ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሊደረግ ነው፡፡

ለዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የወተት ላም እርባታ ፕሮጀክት ለመተግበር ስምምነት ላይ መደረሱ ተገለጸ፡፡

በገዳሙ በቅርቡ ከፍተኛ የደን ቃጠሎ ተከስቶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ገዳሙን ለመርዳት በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የሚገኙ ምእመናን የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ማኅበረ ቅዱሳን ምእመናንን በማስተባበር ከ600,000.00 ብር /ስድስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለማሰባሰብ መቻሉን የማኅበሩ ዋና ጸሓፊ ዲ/ን ሙሉጌታ ኃይለ ማርያም ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ አብዛኛው በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማእከል አስተባባሪነት በአሜሪካ የሚገኙ የማኅበረ በዓለወልድ እና የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ያሰባሰቡት መሆኑ ታውቋል፡፡

የተገኘውን እርደታ ወደ ተግባር ለመለወጥ በታቀደው መሠረት “ለገዳሙ ቋሚ ፕሮጀክት እንደሚያስፈልገው ስለታመነበት ቦታው ድረስ ባሙያዎች በመላክ የዳሰሳ ጥት የተደረገ ሲሆን ከገዳሙ ሓላፊዎች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ በውይይቱም ለገዳሙ ትልቅ ጥቅም የሚሰጠው የትራክተር ግዢ ቢሆንም ለጊዜው የተሰበሰበው ገንዘብ ይህንን ለማስፈጸም የማይበቃ በመሆኑ ከዚህ በፊት ተጀምሮ የነበረው የወተት ላም እርባታ ፕሮጀክት እንዲተገበር ስምምነት ላይ ተደርሷል” በማለት የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጸሓፊ ዲ/ን ሙሉጌታ ኃይለ ማርያም ገልጸዋል፡፡ በስምምነቱ መሠረት የማኅበሩ የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል ፕሮጀክቱን እንደሚያስፈጽም ተናግረዋል፡፡

የገዳሙ ደን በተቃጠለበት ወቅት የቀለብ እጥረት በመከሰቱ ማኅበሩ ምእመናንን በማስተባበር 50 ኩንታል ስንዴ 20 ኩንታል ጤፍ፣ 40 ሺህ ብር የሚገመት መጠጥ ውኃ፣ በሶ፣ ስኳር፣ ዳቦ ድጋፍ ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ከማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ የተወሰደ ዘገባ ነው::

Monday, July 30, 2012

የአቡነ ጳውሎስ የማዕረግ ስም ላይ “ዓለም አቀፍ የሰላም አምባሳደር” የሚል ተጨመረ • ስለ አቡነ ጳውሎስ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመት በክራውን ሆቴል ለሦስተኛ ጊዜ ይደገሳል።
 • የመንበረ ፓትርያርኩ ሙስና ለጥቅመኛ የውጭ ቡድኖች ‹መስሕብ› ኾኗል - ራእይ ለትውልድ አንዱ ነው።
 • የጠቅ/ቤ/ክህነቱ “የምግባረ ሠናይ አጠቃላይ ሆስፒታል” ኦዲት ተደርጎ አያውቅም።
 • ሰሞናዊው ድግስ “ለመጨረሻው የአቡነ ጳውሎስ በዓለ ሢመት የቁም ተዝካር” በሚል እየተነገረለት ነው።
 • “የሰውዬው [አባ ጳውሎስ] መታወሻ (legacy) አውዳሚነታቸው ነው። እርሳቸውም፣ እኛም እየበላን ያለነው ቀደምት ፓትርያርኮች ያስቀመጡትን ሀብት ነው።” (የቤተ ክህነቱ ታዛቢዎች)
 • ሐምሌ 22ን - እንደ አቡነ ጳውሎስ ወይስ እንደ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ አቡነ ጴጥሮስ?

ሙሉ ዘገባው የደጀ ሰላም ብሎግ ነው::

Monday, July 23, 2012

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የፓትርያርክነት ማዕርግ የተቀዳጀችበት የነጻነት በዓል - በዓለ ሢመተ ፓትርያርክ - አከባበር የመንፈሳዊ ውርደትና የምዝበራ መንገድ ኾኗል  ሙሉ ዘገባው የደጀ ሰላም ነው::
 በሙስና፣ ብኵንነት፣ ኑፋቄ እና ዐምባገነናዊ አሠራር የነቀዘው የአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና 20 ዓመት በዓለ ሢመት ዛሬ ምሽት ለሁለተኛ ጊዜ በሼራተን አዲስ ይከበራል። የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት እና ራእይ ለትውልድ /Vision for Generation/ የተባለው አካል የጥቅም ትስስር የፈጠሩበት የሼራተኑ በዓለ ሢመት ዝግጅት በቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ይኹን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት አይታወቅም።

 
 

Wednesday, July 18, 2012

የሲያትል ምእመናን አቡነ ፋኑኤልን በይፋ ተቃወሙ፤ እንዳይመጡም ተስማሙ

ሙሉ ዘገባው የደጀ ሰላም ነው::
በሰሜን ምዕራብ አሜሪካ በዋሺንግተን ሲያትል በሚገኙት  በደብረ ሰላም ቅ/ሚካኤል እና በደብረ መድኃኒት ቅ/አማኑኤል አብያተ ክርስቲያናት በድብቅ ሊመጡ ያሸመቁትን አቡነ ፋኑኤልን ሕዝቡ በይፋ ተቃወመ፡፡ እሑድ ከቅዳሴ በኋላ ምእመናን በይፋ ባቀረቡት ጥያቄ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ሕገ ወጡ ሊቀ ጳጳስ አባ ፋኑኤል ወደ አብያተ ክርስቲያናቱ እንዳይመጡ በብርቱ ተቃውሞ ቀርቧል። በሌሎች አካባቢዎች የተጀመረው “ቤተ ክርስቲያንን ከነአባ ፋኑኤል እና ከፕሮቴስታንቱ አጋራቸው ከኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን የመታደግ” እንቅስቃሴ በሲያትልም ተጀምሯል። “ምንም አያውቅም” እየተባለ የሚናቀው ምእመን ለቤተ ክርስቲያኑ የክፉ ቀን ደራሽ መሆኑን እና በሐዋሳ ያለው ሕዝበ ክርስቲያን እንባውና በተጋድሎው ቅ/ሲኖዶስ ኡኡታውን ሰምቶ ያገኘውን ድል በአሜሪካ የሚገኘውም ምእመን እንደሚደግመው አረጋግጧል።

Friday, July 13, 2012

የላስ ቬጋስ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን ከአቡነ ፋኑኤል ጋር እንደማይሠራ በድጋሚ አረጋገጠ • የደብሩ ማኅበረ ካህናት የፈረሙበትን ደብዳቤ ተመልከቱ

(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 14/2004 ዓ.ም፤ ጁን 21/ 2012/ READ THISARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በምዕራብ አሜሪካ የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ሥር የሚገኘው የላስ ቬጋስ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን “ከብፁዕ አቡነ ፋኔኡል ጋር እንደማንሠራ እና የሸቱትንም ሾመት የማንቀበል መሆኑን” እንገልጻለን ባለበት መግለጫው አቡነ ፋኑኤል “ከዚህ በፊት ለአህጉረ ስብከቱ ተመድበው አባታዊ መመሪያ እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩት አባቶች በተለየ መልኩ በመጓዝ ካህናት እና ምዕመናንንን በማሳዘን ለመናፍቃን በር የሚከፍት የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ሥርዓት ባልጠበቀ እና ባልተከተለ መንገድ መመሪያ በመስጠት እና በተግባርም በመፈፀም የግል ጥቅምን ብቻ በሚያስጠብቅ አካሄደ በመጓዛቸው በሚሠጡት የተሣሣተ እና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የወጣ አመራር ጋር አብሮ መጓዝ ተገቢ ባለመሆኑ ከዚህ በፊት ያለንን አቋም/ አቋማችንን እንገልጻለን” ብሏል።

Wednesday, July 11, 2012

ጠቅ/ቤተ ክህነት “ጉባኤ አርድእት” ነን ባዮች በመንበረ ፓትርያርኩ እንዳይሰበሰቡ አገደ

·         እገዳው የተላለፈው መንግሥት ለአባ ጳውሎስ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ ነው ተብሏል።
·         በአባ ጳውሎስ ቀጥተኛ ይኹንታ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ ለቀናት በኅቡእ ሲሰበሰብ የቆየው ቡድኑ÷ ከፊል መሥራች አባላቱ ከሸሹትና የስብሰባ እገዳ ከተጣለበት በኋላ÷ ለቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት የ‹ዕወቀኝ› ጥያቄ ማቅረቡ ተነግሯል።
·   የቅ/ሲኖዶስ እና የጠቅ/ቤ/ክህነት ጽ/ቤቶች÷ ቤተ ክርስቲያን “ጉባኤ አርድእት” የተሰኘውን ኅቡእ ቡድን እንደማታውቀው ገልጸዋል።
·     የኅቡእ ቡድኑ አስተባባሪ ፕሮቴስታንታዊው ኀይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን በአባ ጳውሎስ ትእዛዝ የያዘውን የጠ/ቤ/ክህነቱን መኪና እንዲያስረክብ ተደርጓል።
·   አባ ጳውሎስ የእምነት ንጽሕናቸውን በቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ያላረጋገጡትንና ከቡድኑ ቀንደኛ አስተባባሪዎች አንዱ የኾኑትን አባ ሰረቀን በመንፈሳዊ ዘርፍ ም/ሥ/አስኪያጅነት ለመሾም ማሰባቸው ተሰምቷል።
·    “ለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ሲባል የቡድኑን ኅቡእ እንቅስቃሴ በጥብቅ እየተከታተልነው ነው” /የጠ/ቤ/ክ መመሪያ ሓላፊዎች/።
·     “ከጉባኤው አስተባባሪዎች አብዛኞቹ በሚሠሩባቸው ቦታዎች ተቀባይነት ያጡ ግለሰቦች ናቸው” /የቋሚ ሲኖዶስ ምንጮች/።
 ሙሉ ዘገባው  የደጀ ሰላም ነው::
 የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ራሱን “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” በሚል መጠሪያ ሰይሞ ከቤተ ክርስቲያን ማእከላዊ አስተዳደር ዕውቅናና ፈቃድ ውጭ ከፓትርያርኩ ባገኘው ቀጥተኛ ይኹንታ የአባ ጳውሎስን ዐምባገነንት ለማጠናከር፣ መንፈሳውያን ማኅበራትን ለማፈራረስ፣ የግል እና የቡድን ጥቅሞቹን ለማስጠበቅ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ መሽጎ ሲዶልት የቆየው ቡድን በየትኛውም የመንበረ ፓትርያርኩ አዳራሾች እና ቢሮዎች ለመሰብሰብ እንደማይፈቀድለት አስታወቀ፡፡

Thursday, July 5, 2012

የታሰሩት የዋልድባ መነኰሳት በነዋሪው ተቃውሞ ለተቃጠለው የፕሮጀክቱ ዶዘር እና ለተጎዱት ሠራተኞች ሓላፊነት እንዲወሰዱ እየተገደዱ ነው

·         የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ሠራተኞች በአካባቢው ሕዝብ እየተሳደዱ ነው::
·         ነዋሪው ሠራተኞቹን እስከ ማይ ገባ ከተማ ድረስ እንዳሳደዳቸው ተነግሯል::
·         የዓዲ አርቃይና ማይ ፀብሪ ወረዳዎች ሓላፊዎች በታሰሩት መነኰሳት እየተወዛገቡ ነው::
·         ከዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም የተወሰዱት አምስት መነኰሳት በዓዲ አርቃይ ፖሊስ ጣቢያ እንደታሰሩ ናቸው::
(ሙሉዘገባውን የወሰድነው ከደጀ ሰላም ነው::
ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ ሰኔ 23 ቀን 2004 ዓ.ም÷ ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ከዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም የተወሰዱት አምስት መነኰሳት በዓዲ አርቃይ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ በአንድ ቆርቆሮ ቤት ውስጥ እንደታሰሩ መኾናቸውን የስፍራው ምንጮች ለደጀ ሰላም ገለጹ፡፡

Monday, July 2, 2012

ሰበር ዜና - የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም በፌዴራል ፖሊስ ተከቧል

·        አራት መነኰሳት በፖሊስ ተይዘው ተወስደዋል፤ ሌሎቹ መነኰሳት እየተደበደቡ ተበታትነዋል።
·        የገዳሙ የሱባኤ ወቅት በፖሊስ የኀይል ርምጃ እየታወከ ነው።
·        በዛሬማ ወንዝ ላይ የሚገነባውን የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት ግድብ የሚሠራው ሱር ኮንስትራክሽን  ለቆ መውጣቱ እየተነገረ ነው፤ በምትኩ የቻይና ተቋራጭ የገባ ቢኾንም በእርሱም ላይ ተቃውሞው መቀጠሉ ተሰምቷል።
ሙሉ ዘገባውን የወሰድነ  ደጀ ሰላም ብሎግ ነው:: ፤
 በሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ዓዲ አርቃይ ወረዳ የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም ከማይ ፀብሪና ዓዲ አርቃይ ወረዳዎች በአምስት መኪና ተጭነው በመጡ የፌዴራል ፖሊስ ኀይሎች ሥምሪት ውስጥ እንደሚገኝ የስፍራው ምንጮች ለደጀ ሰላም ገለጹ፡፡