Friday, September 28, 2012

መጪውን ጊዜ በሃይማኖት “ብሔርተኝነት” መዋጀት

(ማኅበረ ቅዱሳን):-ጊዜ ይመጣል ጊዜ ይሄዳል፡፡ ጊዜ መጥቶ ሲሄድ ግን እንደው ዝም ብሎ አይደለም፡፡ የጊዜውን አሻራ አሳርፎ ነው፡፡ አሻራው ግን አዎንታዊም አሉታዊም ሊሆን ይችላል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ምርጫው በጊዜ መጠነ ክበብ ውስጥ ያለው የሰው ልጅ ነው፡፡

የሰው ልጅ ደግሞ በጊዜያት ውስጥ የረቀቀና የገዘፈ ዓለም ባለቤት ሆኖ የተፈጠረና ጊዜ የማይቆጠሩላቸው የሥሉስ ቅዱስ ፍጡር ነው፡፡ በሕያውነቱ ረቂቁን ዓለም- ዓለመ ነፍስን መስሎና ሆኖ ሲኖር፤ በምድራዊነቱ ግዙፉን ዓለም- ዓለመ ሥጋን በተዋሕዶ ነፍስ መስሎና ሆኖ ይኖራል፡፡ በዚህም የሁለት ዓለም ባለቤት ነው፡፡ የሰማያዊና ምድራዊ ወይም የመንፈሳዊና ዓለማዊ፡፡

እንዲህ ሆኖ ሲፈጠር በነጻ ምርጫው እንዲኖር የሚያስችለው ነጻ አእምሮ የተቸረው ብቻ ሳይሆን የምርጫውን ተገቢነትና ትክክለኛነት የሚያረጋግጥበት አእምሮ የተሰጠውም ባለጸጋ ፍጡር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡

Thursday, September 13, 2012

የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ(የማኅበሩ የሥራ አመራር ጉባኤ ሥም ዝርዝር)

ሪፖርታዥ

TAKLL2004 534(ማኅበረ ቅዱሳን):-የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ የመምሪያ ሓላፊዎች፤ ቀሳውስትና ካህናት፤ የፌደራል ጉዳዮች የሃይማኖት ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም.በድምቀት ተጀመረ፡፡


ነሐሴ 29 ቀን 2004 ዓ.ም.

በዋዜማው ነሐሴ 29 ቀን 2004 ዓ.ም. ከቀኑ ስድስት ስዓት ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ የማኅበሩ አባላት ማኅበሩ እያስገነባው በሚገኘው ሕንጻ ውስጥ በመገኘት የሕንጻው ግንባታና በማኅበሩ የአንዳንድ አገልግሎት ክፍሎችን እንቅስቃሴ በመጎብኘት ማብራሪያ እየተሰጣቸው ቆይተዋል፡፡ ከምሽቱ 12፤00 ስዓት ጀምሮ የጠቅላላ ጉባኤው አስተባባሪ ኮሚቴ ባዘጋጀው ትራንስፖርት ከማኅበሩ ዋናው ማእከል አቧሬ ወደሚገኘው አቡነ ጎርጎርዮስ የትምህርትና ሥልጠና ማእከል በመጓዝ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት፤ የመርሐ ግብር ትውውቅ፤ ሕጽበተ እግርና የእራት መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡

Tuesday, September 4, 2012

ቅዱስ ሲኖዶስ ሱባኤ አወጀ

  • ሱባኤው 
    ከጳጉሜን 1/ 2004 - 
    መስከረም 10/ 
    2005 ዓ.ም ድረስ ነው።
  • ቅ/ሲኖዶሱ የአስታራቂ ኮሚቴውን ሪፖርት አዳምጧል::
  • ሦስት የአስታራቂ ኮሚቴው አባላት አዲስ አበባ ናቸው::
  • ቅ/ሲኖዶሱ አካሄዱን ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ቡድኖችን እንደማይታገሥ አስታውቋል::
ሙሉ ዘገባው የደጀሰላም ብሎግ ነው::
 READTHIS NEWS IN PDF
  ቅዱስ ሲኖዶስ መጪው ዘመን ቤተ ክርስቲያናችን ሰላሟንና አንድነቷን የምታረጋግጥበት፣ ዐበይት ተቋማዊ ችግሮቿን በመፍታት ለአገራችንና ለመላው ዓለም ሐዋርያዊ አገልግሎቷን የምታጠናክርበት ይኾን ዘንድ ካህናትና ምእመናን በአንድነት ወደ እግዚአብሔር የሚያመለክቱበትና ከጳጉሜን 1/2004 - መስከረም 10/2005 ዓ.ም የሚቆይ የሱባኤ ጊዜ ማወጁ ታወቀ፡፡ የሱባኤ ጊዜ እንዲታወጅ የተወሰነው ቅዱስ ሲኖዶሱ ትናንት፣ ነሐሴ 28 ቀን 2004 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ሲሆን ዛሬ ማክሰኞ ባደረገው ስብሰባም ቀናቱን ይፋ አድርጓል። (ዝርዝሩን እንደደረሰልን ለማቅረብ እንሞክራለን።) ሱባኤውን የተመለከተ መግለጫ በተከታዮቹ ቀናት በቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊው በኩል እንደሚሰጥም ተመልክቶ ነበር፡፡ በመንፈሳዊው ትውፊታችን እንደቆየን ወደ አዲሱ ዘመን የምንሸጋገርባትና እንደ 13ኛ ወር የምትቆጠረው ጳጉሜን በበርካታ ክርስቲያኖች ዘንድ የፈቃድ ጾም የሚያዝባት ወቅት እንደኾነች ይታወቃል፡፡