Sunday, December 30, 2012

የኢትዮጵያ መንግሥት ዓላማውን ግልጽ አድርጓል፤ እኛም አውቀናል

 • የመንግሥት ደጋፊ የጡመራ መድረኮች “አስታራቂ ኮሚቴው” ላይ ዘምተዋል፤
 • ከጳጳሰቱ መካከል የዕርቁ እንቅፋት የሆኑት አባቶች በግልጽ ታውቀዋል፤ ስማቸውን ከማውጣታችን በፊት አሁንም ሐሳባቸውን ይቀይሩ እንደሆነ እንጠብቃቸዋለን፤
 • ጉዳዩን ያቀነባበሩት የአዲስ አበባው ልዑክ አባል የሆኑት ን/ዕድ ኤልያስ አብርሃ ናቸው ተብሏል፤
 • የአዲስ አበባው ልዑክ አባቶች ዲሲ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ከተጠሩ በኋላ ተገደው እንዲፈርሙ ተደርገዋል፤
PDF  ሙሉ ዘገባው የደጀ ሰላም ብሎግ ነው::
 በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ አልገባኹም በሚል ሰሞኑን መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ለዕርቁ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ የሄዱትን የሰላምና አንድነት ጉባኤውን አባል ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን አስሮ ወደ አሜሪካ ከላካቸው ወዲህ ለዕርቁ ያለው የተስፋ ደጅ መዘጋቱ እሙን ሆኗል። መንግሥት የዕርቁ ድርድር ለይስሙላ እንጂ “ከምር” እንዲሆን አልፈለገም ነበር።
ነገሩ ከምር ሲሆን ግን “የጭቃ ጅራፉን” መምዘዝ ይዟል። ለዲፕሎማሲ ይጠቅመኛል ብሎ የፈቀደው ዕርቅ መሰካት ሲጀምር ከዲፕሎማሲው ከማገኘው ትርፍ በሩን መዝጋት ይሻለኛል ያለ መስሏል። የራሱን ፓርቲ አባል በፓትርያርክነት ለማስቀመጥ በጠራራ ፀሐይ ወረራውን ቀጥሏል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ሊ/ካ ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁን በግድ ወደ አሜሪካ መለሳቸው

 •   Listen VOA Interview
 •     የኢትዮጵያ መንግስት ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን ከሀገር አባረራቸው
 •     ጉዳዩን ያቀነባበሩት የአዲስ አበባው ልዑክ አባል የሆኑት ን/ዕድ ኤልያስ አብርሃ ናቸው ተብሏል፤
   ዘገባውን የወሰድነው ከደጀ ሰላም ብሎግ ነው::
 በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ አልገባኹም በሚል ሰሞኑን መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ለዕርቁ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ የሄዱትን የሰላምና አንድነት ጉባኤውን አባል ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን አስሮ ወደ አሜሪካ መለሳቸው። እዚያው አስሮ ያላስቀራቸው አሜሪካዊ ዜግነት ስላላቸው ነው ተብሏል። ከእርሳቸው ጋር ለዚሁ ጉዳይ ወደ ኢትዮጵያ የሄደው የሰላምና አንድነት ጉባኤው ሌላ አባል ዲ/ን አንዱዓለም ዳግማዊ ስላለበት ሁኔታ አልታወቀም። ዝርዝሩን እንደደረሰልን እናቀርባለን። 
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።

Saturday, December 29, 2012

ዲ/ን አባይነህ ካሴ በ፲ኛ ዓመት የማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሥራ አመራር ጉባኤ አባል ሆነው አልተመረጡም::

ሐራ ዘተዋሕዶ የጡመራ መድረክ የቤተ ክርስቲያን ትልቁ አጀንዳ በመተው ግለሰብን በማግዘፍ/በማግነን ማኅበረ ቅዱሳንን በማኮምሸሽ  በተከታታይ ጡመራዎቹ  ላይ  አይተናል::  ይህ ሐራ ዘተዋሕዶ የጡመራ መድረክ  ከተሃድሶዎቹ ብሎጎች በተለየ ሁኔታ እና አቀራረብ ማኅበረ ቅዱሳንን በመተቸት “አገልግሎት” ጀምሮዋል::  በእርግጥ ለጡመራ መድረኩ መልስ የመስጠት ስልጣኑ የለንም::  ነገር ግን እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን ማኅበረ ቅዱሳን ለሚሰራቸው ሥራዎች በአይናችን አይተናል:: በጆሮዋችንም ሰምተናል:: ስለዚህ ለማኅበሩ በጎ ሥራ ምስክሮች ነን:: የማኅበሩ ክፍፍል በአይናችን ማየትም ሆነ  በጆሮዋችን መስማት አንፈልግም:: 

ሐራ ዘተዋሕዶ የተሰኘው የጡመራ መድረክ “በ፲ኛ ዓመት የማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ዲ/ን አባይነህ ካሴ የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጉባኤ አባል ሆኖ ተመርጦ ነበረ”  የሚል የፈጠራ/የሐሰት ዘገባ ስላየን  ዝም ብለን ማለፍ አልቻልንም:: በማኅበረ ቅዱሳን ፲ዓመት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ 17 አባላት ያሉት የሥራ አመራ ጉባኤ እንደተመረጡ በማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያዎች ላይ ተዘግቦ ነበረ::  ሙሉ ዘገባውን እኛም እዚሁ ብሎግ ላይ አቅርበነው  ነበረ::  ለማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጉባኤ አባላት ከተመረጡት  17ቱ አባላት ዝርዝር ውስጥ ዲ/ን አባይነህ ካሴ በጠቅላላ ጉባኤ አልተመረጡም ነበረ:: ነግር ግን የኢዲቶሪያል ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተመድበው ነበረ:: መረጃው እንደሚያሳየው የኢዲቶርያል ቦርድ ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር አሸናፊ በየነ ናቸው::

Tuesday, December 25, 2012

የ6ኛ ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴው “የተመረጠ” ሳይሆን “የተሰየመ” ነው

  ሙሉ ዘገባው የደጀ ሰላም ነው::
6ኛውን ፓትርያርክ ለማስመረጥ ተቋቁሟል የተባለው አስመራጭ ኮሚቴ በጥቆማ ስም ዝርዝራቸው የተበተነ እንጂ ብዙዎቹ ይስማሙበት ወይም አይስማሙበት እንዳልተጠየቁ ምንጮቻችን ገልጸዋልይህንን ተከትሎ ማኅበረ ቅዱሳን ምርጫው እንዲካሄድ በሾርኔ እንደተስማማ ተደርጎ በድረ ገጾች መዘገቡ አጀንዳው ከምርጫው ወደ ማኅበሩ እንዲዞር ለሚሹ ጥሩ አጋጣሚ ከመፍጠሩም በላይ ማኅበሩ ከቅ/ሲኖዶሱ ጋር ያለውን መልካም የሥራ ግንኙነት ለማጠልሸት ለሚፈልጉ ሰዎች አስደሳች አጋጣሚ እንደፈጠረ እየተነገረ ነው።

ዝርዝሩ እንደሚያመለክተው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስና ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ እንዲሁም ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መምሪያ ኃላፊዎች መካከል ደግሞ የሰበካ ጉባኤ መምሪያ ዋና ሓላፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ እና የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ዋና ሓላፊው መጋቤ ምስጢር ዓምደ ብርሃን ስማቸው ተጠቅሷል። ታላላቅ ገዳማት እና አድባራትን እንዲወክሉ የተደረጉት ፀባቴ አባ ኀይለ መስቀል ውቤ (የደብረ ሊባኖስ ገዳም አበምኔት) እና ንቡረ እድ አባ ዕዝራ (የአኵስም ጽዮን ንቡረ እድ) ሲሆኑ ዲያቆን ኄኖክ አሥራት - ከአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት፤ አቶ ባያብል ሙላቴ ደግሞ ከማኅበረ ቅዱሳን የተሰየሙ ናቸው። አቶ ዓለማየሁ ተስፋዬ  (ከኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት)፣ ቀኝ አዝማች ኀይሉ ቃለ ወልድ እና አቶ ታቦር ገረሱ ደግሞ ምእመናንን ወክለው የተቀመጡ ናቸው፡፡

Monday, December 24, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ ፮ኛውን ፓትርያርያክ ለመምረጥ የወሰነውን ውሳኔ በድጋሜ እንዲያጤነው ጠየቀ

 •   ቤተክርስቲያን ስድስት ቦታ ብትከፈል አያገባኝም።” አቡነ ቀሌምንጦስ
 •  “ወነአምን በአሐቲ ቤተክርስቲያን” ማኅበረ ቅዱሳን
 •  ቅዱስ ሲኖዶስ ለእርቀ ሰላሙ ቅድሚያ የማይሰጥ ከሆነ ራሳችንን እናገላለን” በአሜሪካ የኢትዮጵያ አብያተክርስቲያናት ምእመናን
 •  ሐራ ተዋህዶ የተሰኘው የጡመራ መድረክ “ማኅበረቅዱሳን አቋሙን ለወጠ።” የሚለው መሰረተ ቢስ ዜና ግቡ ምን እንደሆነ እያነጋገረ ነው።
 •  “መንግሥት በካርድ ነው የሚመርጠው ፣ ስለዚህ መንግሥት ኃጥያተኛ ነው? እኛ ማን ሆነን ነው በዕጣ ካልሆነ የምንለው? ከመንግሥት እኛ እንበልጣለን?” አቡነ ጎርጎርዮስ 
ሙሉ ዘገባውን የወሰድነው ከአንድ አድርገን ብሎግ ነው:: TO READ IN PDF CLICK HERE
ባለፉት ሃያ ዓመታት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት በማበርከት በቅዱስ ሲኖዶስ እና በምእመናን ዘንድ ታማኚነት ያተረፈው ማኅበረ ቅዱሳን ከአቡነ ጳውሎስ እረፍት በኋላ የቤተክርስቲያን አንድነት ቅድሚያ በመስጠት ቅዱስ ሲኖዶስ ለእርቀ ሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲወያይ ለጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በደብዳቤ ማሳወቁ፣ በህትመትና ኤሌክትሮኒክስ ልሳኖቹ ማሳወቁ እንዲሁም የማኅበሩ አመራሮች አባቶችንና ምእመናን መደበኛ በሆኑና ባልሆኑ መንገዶች በማወያየት የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት መጣራቸው ይታወቃል።