Saturday, December 29, 2012

ዲ/ን አባይነህ ካሴ በ፲ኛ ዓመት የማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሥራ አመራር ጉባኤ አባል ሆነው አልተመረጡም::

ሐራ ዘተዋሕዶ የጡመራ መድረክ የቤተ ክርስቲያን ትልቁ አጀንዳ በመተው ግለሰብን በማግዘፍ/በማግነን ማኅበረ ቅዱሳንን በማኮምሸሽ  በተከታታይ ጡመራዎቹ  ላይ  አይተናል::  ይህ ሐራ ዘተዋሕዶ የጡመራ መድረክ  ከተሃድሶዎቹ ብሎጎች በተለየ ሁኔታ እና አቀራረብ ማኅበረ ቅዱሳንን በመተቸት “አገልግሎት” ጀምሮዋል::  በእርግጥ ለጡመራ መድረኩ መልስ የመስጠት ስልጣኑ የለንም::  ነገር ግን እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን ማኅበረ ቅዱሳን ለሚሰራቸው ሥራዎች በአይናችን አይተናል:: በጆሮዋችንም ሰምተናል:: ስለዚህ ለማኅበሩ በጎ ሥራ ምስክሮች ነን:: የማኅበሩ ክፍፍል በአይናችን ማየትም ሆነ  በጆሮዋችን መስማት አንፈልግም:: 

ሐራ ዘተዋሕዶ የተሰኘው የጡመራ መድረክ “በ፲ኛ ዓመት የማኅበረ ቅዱሳን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ዲ/ን አባይነህ ካሴ የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጉባኤ አባል ሆኖ ተመርጦ ነበረ”  የሚል የፈጠራ/የሐሰት ዘገባ ስላየን  ዝም ብለን ማለፍ አልቻልንም:: በማኅበረ ቅዱሳን ፲ዓመት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ 17 አባላት ያሉት የሥራ አመራ ጉባኤ እንደተመረጡ በማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያዎች ላይ ተዘግቦ ነበረ::  ሙሉ ዘገባውን እኛም እዚሁ ብሎግ ላይ አቅርበነው  ነበረ::  ለማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር ጉባኤ አባላት ከተመረጡት  17ቱ አባላት ዝርዝር ውስጥ ዲ/ን አባይነህ ካሴ በጠቅላላ ጉባኤ አልተመረጡም ነበረ:: ነግር ግን የኢዲቶሪያል ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው ተመድበው ነበረ:: መረጃው እንደሚያሳየው የኢዲቶርያል ቦርድ ሰብሳቢ ቀሲስ ዶ/ር አሸናፊ በየነ ናቸው::

የማኅበረ ቅዱሳን መተዳደርያ ደንብ መነሻ በማድረግ  ከማኅበሩ አባላት ጠይቀን ባገኘነው መረጃ መሠረት የኢዲቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢው የሥራ አመራር መደበኛ ስብሰባ ላይ ቢገኝም የውሳኔ ድምጽ ግን የለውም:: እውነታው ይህ ሆኖ እያለ ሐራ ዘተዋሕዶ የጡመራ መደረክ  ዲ/ን አባይነህ ካሴ የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር  እያለ በተከታታይ  አንጃ/ቡድን በመፍጠር የተሳሳተ መረጃ በማስተላለፍ ላይ ይገኛል::

እኚህ ሐራ ዘተዋሕዶ እያገነናቸው ያሉት ግለሰብ ከኢሳት ሬድዮ ጣቢያ ጋር በተደጋጋሚ የማኅበረ ቅዱሳን የሥራ አመራር አባል እየተባሉ እየተጠሩ ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው  “እኔ የሥራ አመራር ጉባኤ አባል አይደለሁም” አላሉም:: ሐራ ዘተዋሕዶ እና ተገናኙ ግለሰብ ዓላማቸው ምን ይሆን??? ጊዜ ይፍታው እንላለን::

በማኅበረ ቅዱሳን ፲ኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተመረጡት የሥራ አመራር ጉባኤ አባላት ዝርዝር የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ:: http://www.ahatitewahedo.com/2012/09/10.html

9 comments:

Anonymous said...

ይልቅስ የናንተ አላማ ምን እንደሆነ አይታወቅም:: ሐራ ዘተዋህዶ ላይ ስለ ዲ/ን አባይነህ ካሴ ይህን ያክል አልተጻፈም:: እናንተ ግን ስለ አባይነህ ካሴ ይህን ያክል መጻፋችሁ ሌላ አጀንዳ ያስመስልባችኋል:: ሐራ ዘተዋህዶ ስለ ማህበሩም ስለ ዲያቆኑም ይህን ያክል አልጻፈም:: ያለውን እውነታ ብቻ ነው የጻፈው:: ''ዲ/ን አባይነህ የስራ አመራር ተብሎ የተነገረላቸው ስህተት ነው የኤዲቶሪያል ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ናቸው'' ማለት ብቻ በቂ ነበር:: እናንተ ግን ያውም ያንንም ክዳችሁ የኤዲቶሪያል ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ነበሩ ነው ብላችሁ የጻፋችሁት:: ስለዚህ አሁን አይደሉም ማለት ነው? ሐራ ዘተዋህዶ ላይ የተጻፈው ከኃላፊነታቸው ተነሱ የተባለው እውነት ነው ማለት ነው? ያ እውነት ከሆነ ታዲያ ምን እውነት ይዛችሁ ነው ሐራ ዘተዋህዶን ለመውቀስ የተነሳችሁት? እናንተ ትክክለኞቹ የማህበሩ ሰዎች ብትሆኑ መጨረሻ ላይ በተጠቀማችሁበት አገላለጽ ንጹህ የተዋህዶ ልጅ የሆኑትንና እውነተኛ የተዋህዶ መምህር የሆኑትን ዲ/ን አባይነህን ባልዘለፋችሁ ነበር:: 'አሐቲ ተዋህዶ' የኛ ትመስይኝ ነበር አሁን ግን ተጠራጠርኩሽ:: ሐራ ዘተዋህዶ የኛ ትሁን የተሐድሶዎች ገና አልታውቀም:: እናንተ ግን እውነትን ስለተናገሩ ከተሐድሶዎቹ ከነ 'አባ ሰላማ' መደባችሁት:: ተሐድሶ መናፍቅ ለማለት አትቸኩሉ:: እኔ በበኩሌ እስካሁን ምንም እንከን አላገኘሁበትም በ'ሐራ ዘተዋህዶ':: 'የማህበሩን ክፍፍል በአይናችን ማየት አንፈልግም....' ላላችሁት ጥሩ ነው:: እውነታችሁን እንዲሆን ከልቤ ተመኘሁ:: ትክክለኛ የተዋህዶ ልጅ አዎ የማህበሩን ክፍፍል ማየት አይፈልግም:: የናንተ አቀራረብ ግን የማህበሩን ክፍፍል የማይፈልግ ቡድን አያስመስልባችሁም:: የማህበሩን ክፍፍል የማይፈልግ ሰው የተከበሩትንና አንጋፋውን የተዋህዶ መምህሩን አያንቋሽሽም:: እናንተ እንዳላችሁት ሐራ ዘተዋህዶ ዲ/ን አባይነህን አላገነናቸውም እሳቸው ግን ለክርስቲያን መግነን/ከፍ ከፍ ማድረግ አይገባም እንጂ ማድረግ ቢገባ ኖሮ ዲ/ን አባይነህ ከፍ ከፍ ሊሉ የሚገባቸው አንጋፋና ንጹህ የተዋህዶ ፍሬ ናቸው:: እባካችሁ መጻፍ ካልቻላችሁ ስለቤተክርስቲያን ጉዳይ አትጻፉ:: መጻፍ ከፈለጋችሁ ደግሞ ከደጀ ሰላም ተማሩ::

Anonymous said...

sorry to hear this news! men alsflege sle deyakon abaynhe kassie metshaf.esu yeserawen kenante weste manem alseram . enante fete ayetachew metamesgenu! asafari nachew. ahun egna nene christian menbalew. bemenem melku hara tewhedo gar atewedaderum. endet mezegeb enkwa endalebaachw matwku.
abetu amlak yeker yeblen.

አንድ አድርገን said...

GREAT

Fisseha Moges said...

Ye Kefa Ye Aplos mebabalu lemn aybekanim wondimoch??? Endet new negeru? manin eyeteketelin manin eyamelekin endehone Lerasachinim yawekinew aymeslegnim!!!

Benefesebet menfes ye tikikilegna christian megelecha aydelemna ebakachihu Qom bilachihu asbu. Kechaln beetselot bemebertat leselam enqum enisra kalchaln degmo arfen enqemet...Ahun afrash were kemanafes yilik zimta rasu agelglot yehonebet gize lay dersenalina!!!

Anonymous said...

Dn Abayineh Kasse has an Exellent personality & religious life. Please You are not allowed to touch him.

Anonymous said...

መንፈሳዊነት የጎደለው ዘገባ ሆኖ አግኝቼዋለሁ:: እስቲ ረጋ ብላችሁ አስተውሉ ከመጻፋችሁ በፊት?? ጎራ ለይታችሁ ሰውን መዝለፍ መንፈሳዊነት አይደለም::ከሐራ ተዋህዶን እርግጥ ነው በጥርጣሬ ነው የማየው:: በዚህ ዘገባችሁ ግን ከ ሐራ ተዋህዶ ነው የባሳችሁት:: እንዲያውም ይህንን ዘገባ ብታወርዱት መልካም ነው::

Anonymous said...

@andeadirgen men malet felgachew new GREAT! lemen new betfozo menaweraw! bakachew arfachew teqemetu! mawrate megebachewen leytachew ewkuuuuuuuuuuuuuuuuuuu! engdhe enantem thadeso lalemebale wastena yelachwem. endeferdachew yeferedbachewal!

Anonymous said...

በመጀመሪያ ደረጃ በክርስቲያኖች መካከል በምንም መልኩ፣ በምንም ደረጃ ይሁን መለያየትን መፈልግ ፍጹም ሴጣናዊ ተግባርና ዓላማ ነው፤ ‹‹ሀራ ተዋህዶ›› የተሰኘው ጀማሪው ብሎግም የክርስቲያኖች መለያየት ፍጹም ስለሚያስደስተው፣ ይህቺን የቤ/ክ የችህር ወቅት እንዴት ልጠቀምባት ብሎ የፈጠረው ትራጀዲ ዘጋባ ገና ከጅምሩ ስሙን አስመስሎ ትግባሩን ከአባቱ ወርሶ ስለመምጣቱ ምንም ጥርጥር የለንም፤ ከማንኛውም ሰው ስህተት ከብረት ዝገት እንዳለ ለሁሉም ግልጽ ነው፤ ደግሞ ስራ እሰካለ ድረስ ስህተት አይጠፋም፣ እንደዚህ አይነት ነገር ሲኖር ደግሞ በቤተክርስቲያናችን የቀድሞ አባቶች፣ ማህበራትና ጉባኤዎች መካከል በመንፈሳዊ አካሄድ መተራርም ያለና የኖረ ምግባር ነው፣ የአሁኑን አያድርገው እንጂ፡፡ ሌላው ይህ ‹‹ሀራ ተዋህዶ›› የተሰኘው ግሎግ ‹‹ድንገት መሀል መሀል ዘገባው የቤ/ክ ተቆርቋሪነትን ለማስመሰል የተጠቀመባቸው ስልቶች አሉ፣ እስከ አሁንም እያደረጋቸው ነው ይህ ግን ‹‹ኮሶን በሙዝ›› እንዲሉ አይነት የጥፋት መረጃ ነው፤ በዚህ ተግባሩም ሀራ ተዋህዶ ብሎገሩም ገና ከጅምሩ ጭራው የት እደሆነ ለአብዛኘው ኦርቶዶክሳዊ ግልጽ ሆኗል፤ ለነገሩማ ድህረ ገጹ አዳራሻ እንኳን የት አለውና፣ እርግጥ ነው መንበረ ፓትርያሪክ አካባቢ የዓላማና የጥቅም አጋሮቹ እንደሚኖሩትና እንዳሉት ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ስለዚህ በወቅቱ ስለ ማኅበረ ቅዱሳንም ይሁን ስሌሎች ጉዳዮች በተቆርቋሪንት አስመስሎ ሲዘግብ የነበረው መከፋፈልን ለመፍጠር ነበር፤ ግን ቅዠት ሆኖበት አልፏል፤ እንዲሁም ዘገባው ሁሉ ከዕውነት የራቀና ፍጹም የጸረ-ኦርቶዶክስ ፕሮፓጋንዳ መሆኑን ለማረጋገጥ እኮ የፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ በቅዱስ ሲኖዶስ ተሰየመ እንጂ ለምርጫ ስለቀረቡት የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት ሃሳብ ተሰጥቶበት የምርጫ አካሄድ የሚመስል አካሄድ አልነበረም፣ ይህ ድህረ ገጽ ግን ሲዘግብ የነበረው ከዚህ በተቃራኒና ፍጹም ከዕውነት የራቀ ነበር፣ የዘገባቸውን ሁሉ እዚህ ጋር ደግሜ መጻፍ ጥሩ ስላልሆነ ልለፈው፤ ከዚያ ውጭ በቤተክርስቲያናችህ ውስጥ መከፋፈልን፣ … ለመፍጠር ‹‹ሀራ ተዋህዶ›› ብሎግም ይሁን ሌሎች እንደ ‹‹አባ ሰላማ፣ አውደ ምህረት፣ ዲ/ን አሸናፊ … ›› ያሉ የሚቃዡትን የጸረ-ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ድህረ ገጾች ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን የክርስቶስን መስቀል አንግበን ፍጹም እንታገላቸዋለን፤ ‹‹አሀቲ ተዋህዶ›› ሆኑ ሌሎች ድህረ ገጾች ይንን ከማድረግ በሚያዘናጉ ቃላት እንዳይታለሉ እምክራለሁ፡፡
ለሁሉም ለቤተክርስቲያናችን ሰላምና እንድነትን ያምጣልን፡፡

Anonymous said...

አሁን የዲያቆን ዓባይነህን መልካም ዝና ያጠፋችሁ መስሎአችሁ ነውን? ማንነታችሁን የበለጠ ግልጽ እያደረጋችሁ መምጣታችሁ ጥሩ ነው። ይሁን እነጂ ይህንን ዕንቁ የሆነ ወንድማችንን ከእናንተ በላይ አውቀዋለሁ። በማኅበሩ ውስጥ ከምስረታው ጀምሮ የነበረ በበጎ ተጽዕኖው የሚታወቅ በየወደቅንበት እየመጣ ከገጠር ገጠር እየተዘዋወረ ባደርንበት እያደረ በዋልንበት እየዋለ ለቤተክርስቲያን ምን መሆን እንዳለብን አቅጣጫ የሰጠን ስምምነታችንንም ጠብቀን በምክሩ እያገለገልን የምነገኝ ብዙዎች ነን። ከብዙዎቹም አንዱ እኔ ነኝ። እናንተ ግን አዲስ ነገር ያመጣችሁ መስላችሁ የጭቃ ጅራፍ ቃጣችሁ። በእርግጥ በአሥረኛው ጠቅላላ ጉባኤ የሥራ አመራር አባል ሆኖ አልተመረጠም። ያልተመረጠበትም ምክንያት ምን እንደሆነ ይታወቃል። ባለመመረጡም አይከፋኝም። ይህችን ሀሳብ ከሐራ ተዋሕዶ ዘገባ ለማረም የተነሡ መስሎ ሌላ ድብቅ አጀንዳ ማምጣት ልታፍሩበት የሚገባ ድርጊት ነው። ነቅተንባችሁአል። ዲያቆን ዓባይነህ ማለት አኮ ብዙ ነገራችን ነው። በማንኛውም ጊዜ ለቅድስት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አድልቶ የሚቆም ጥበዐተ መንፈስቅዱስ ያልተለየው ውድ መምህራችን ነው። በግቢ ጉባኤያት የትምህርት መድረክ ላይ የቀረጻቸው ስንቶች አሉ? በአፍም በመጣፍም አጽራረ ቤተክርሰቲያንን ከሚታገሉ ጥቂቶች መካከል አንዱ መሆኑን የማናውቅ መሰላችሁን? ይህን የምለው ማኅበሬን የምወደውን ያኅል መሥዋዕትነት እየከፈሉ በአግዳሚ ወንበር ላይ እየተኙ ስንት ሥራ የሠሩት ሲነኩ እንባ ስለሚተናነቀኝ ነው። የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ላንተ ይብስብሃል እነዳይሆን ጠንቀቅ በሉ። በሰበብ አስባብ ማኅበሩን ለማዘጋት መድከም አያስፈልጋችሁም። ከነባሮቹ ጥቂት ቢቀሩን እነርሱንም በልዩ ዘመቻ ማሳደዱ ይብቃ። ጭብጦ ይዞ ወደ አሻሮ ጠጋ አትበሉ። ያነሳችሁት ጥቂት እውነት ወደ ውሸት እንዲያድግ ሰለምን ትጣጣራላችሁ?