Friday, March 22, 2013

“የማልስማማባቸው የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሃይማኖታዊ ትንታኔዎች” አዲስ

 READ IN PDF
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የወቅቱ የቤተክርስቲያን ጉዳይን በሚመለከት ከላይፍ መጽሄት የመጋቢት ወር እትም ቁጥር 102 ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ነው:: ቃለ ምልልሱን በመጀመርያ ያነበብኩት አንድ አድርገን የተባለ ብሎግ ካወጣው በኋላ ነበር:: ጋዜጠኛው ያነሳቸውን ጥያቄዎች በቤተ መንግስትና ቤተ ክህነት ላይ ያተኮሩ ነበሩ:: የቀድሞው ፓትርያርክ የአቶ ታምራት ላይኔ እና የአዲሱ ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስንም ጉዳይ ተነስቷል:: የዲያቆን ዳንኤልን መልስ ግን ለኔ አስገራሚ ነበር:: የሰጣቸው በርካታ ምላሾች ሊዋጡልኝ አልቻሉም:: በአንዳንዶቹ አስተያየቶቹ ደግሞ ፈጽሞ አልስማማም:: ጥቂቶቹን በሦስቱ ፓትርያርኮች ዙርያ ላንሳ፦

ፓትርያርክ ጳውሎስ
የላይፍ ጋዜጠኛ ÷ ከአቡነ ጳውሎስ ንብረት ጋር በተያያዘ ላቀረበለት ጥያቄ ዲያቆን ዳንኤል የሰጠው መልስ እንዲህ የሚል ነበር::
"ንብረት በመያዝና በማስቀመጥ ረገድ እሰከ አሁን ብዙ ያልተሰማባቸው አባት አቡነ ጳውሎስ ናቸው፡፡
ምናልባት ዘመዶቻቸው ረድተው ይሆናል ካልተባለ በቀር ብዙ ንብረት የላቸውም፡፡"

Saturday, February 16, 2013

ክርስቲያኑ ኢትዮጵያዊ መብቱን ለማስከበር ያልቻለባቸውና የማይችልባቸው ምክንያቶች

ይህ ጽሑፍ የአቅማቸውን ጥቂት ነገር ለማድረግ የሚተጉትን ላይመለከት ይችላል።
  ከደጀ ሰላም ብሎግ የተወሰደ ሐተታ ነው::  PDF
 ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን በኢትዮጵያ እየተስፋፋ በመጣው እምነትን በነጻ የማራመድ መብት ገፈፋ ዋነኛ ተጠቂ ከሆኑት ኢትዮጵያውያን መካከል ኦርቶዶክሱ ክፍል ዋነኛ ተጠቃሽ ነው። በወታደራዊው የደርግ ዘመን የነበረውን ግፍና መከራ እንኳን ለጊዜው ብናቆየው “የሕዝብ ብሶት ወለደኝ” ያለው የኢሕአዴግ መንግሥት ከተመሠረተ ወዲህ ቤተ ክርስቲያናችን በዓይነ ቁራኛ ከመታየት እስከ የ“ነፍጠኛ ጎሬ” እስከመባል ድረስ ብዙ ዘለፋ አስተናግዳለች። ከዚያም ገፋ ሲል በአንዳንድ አክራሪዎች ምእመናኗ ታርደዋል፣ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ ከየአካባቢው እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል። ለዚህም በስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ የሚያራምደው ፖሊሲ ሁነኛ ምክንያት ነው።

Thursday, January 31, 2013

"እናት ቤተ ክርስቲያናችን አልተከፈለችም" ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ

መግቢያ፤
"ቤተ ክርስቲያናችን ከሁለት ተከፈለች" የሚል ሥጋትና ሐዘን ከብዙ አቅጣጫ ይሰማል። እውነት
ተከፍላ ከሆነ ሥጋቱንና ሐዘኑ የሁላችንም ነው። ግን ለመሥራቿ ክብርና ምስጋና ይግባውና፥
እናት ቤተ ክርስቲያናችን አልተከፈለችም። ከፈሏት የምንላቸው ካህናትም፥ አለመከፈሏን
ደጋግመው ተናግረውታል። ሳትከፈል ተከፈለች ማለት ያሳዝናል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ
ክርስቲያን እንኳን ዛሬ፥ መከፋፈልን የሚያመጡ የነገረ መልኮት ብጥብጦች በተነሡባቸው
የተለያዩ ዘመናት እንኳን፥ ጥቂት ተሞክሮ እንደሆነ ነው እንጂ፥ አልተከፈለችም። ስለዚህ ፥
መዓቱ እስኪያልፍ ድረስ፥ ቅዱስ ገብርኤል "ንቁም፡ በበህላዌነ፡" እንዳለው፥ ባለንበት ነቅተን
እንጽና፤ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ነፃነት ተባብረን በአንድነት እንሥራ።

Friday, January 11, 2013

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ለዕርቀ ሰላሙ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚመክር ታወቀ

abunehizkiel ማኅበረ ቅዱሳን:- የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ጥር 6 ቀን 2005 ዓ.ም. የሚካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ለዕርቀ ሰላሙ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚመክር የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ፣ የደቡብና ምዕራብ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከትና የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በተለይ ለስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ ገለጹ፡፡

ለዕርቀ ሰላሙ ድርድር ወደ አሜሪካ የተላኩት አባቶች ተልእኳቸውን ፈጽመው በሰላም ወደ አገራቸው መመለሳቸውን ያስታወሱት ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የተላኩት አባቶች በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ውሳኔ በመሆኑ እነዚሁ አባቶች በዕርቀ ሰላም ድርድር ወቅት የደረሱበትን የውሳኔ አሳብና ተያያዥ ጉዳዮች ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ጥር 6 ቀን 2005 ዓ.ም. በሪፓርት መልክ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፡፡

Wednesday, January 2, 2013

“ቤተ ክርስቲያንን ለፈተና አጋልጠን ወደ ገዳም አንገባም” (ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ)

  • ከሰሜን አሜሪካ የተመለሱ የሰላም ልዑካን የጉዞ ሪፖርታቸውን ለሚ ሲኖዶስ ቅርበዋል።
  • የሰላም ልዑካኑ  ዕርቀ ሰላሙ መቀጠል እንዳለበት በአት አሳስበዋል፡፡
PDF
ሙሉዘገባውን የወሰድነው ከደጀ ሰላም ብሎግ ነው::
ላለፉት ሦስት ዓመታት  ሁለቱን ሲኖዶስ ለማስታረቅ ደፋ ቀና ሲል የነበረ አስታራቂ ጉባኤ ባወጣው መግለጫ መግለጫው ለሽምግልና ከተቋቋአካል አይጠበቅም በሚል  ተቃውቸውን የገለጡት ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጉባኤው ይቅርታ ካልጠቀ አብረውት ለመሥራት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
ይህንንም አአስቀድመው ይፋ ያደረጉት ወደ ሰሜን አሜሪካ ተላኩት ልዑካን  ሲሆኑ በመግለጫቸው አስታራቂ ስሕተት ፈጽሟል፣ ይቅርታ ካልጠየ አብረነው አንሠራም ማለታቸው የዕርቁ ተስፋ ላይ ጥላ አጥልቶበት ሰንብቷል፡፡ ከሊቃነ ጳጳሳቱ  መካከል ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ አዲስ አበባ  ከገባን  በላ መግለጫ  እናወጣለን  አሁን ምን ያስቸኩለናል ማለታቸውም ተጠቁሟል፡፡

በአሜሪካን ግዛት የላስ ቬጋስ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ለቅ/ሲኖዶስ የተማጽኖ ጥሪ አቀረቡ

  ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
ቤተ ክርስቲያናችንን እንታደግ
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ።

ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ጉዳይ መነሻ በማድረግ በሐመረ ኖኅ ኪዳነምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በላስ ቬጋስ የተሰጠ መግለጫ።
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት አባቶቻችን በቅድሚያ ቡራኬያችሁ ይድረሰን እያልን። እንደሚታወቀው ቤተ ክርስቲያናችን ለሁለት አሥርት ዓመታት በፈተና ውስጥ እንድትቆይ  ያደረገውን የልዩነት ግድግዳ አፍርሶ አንድ ሲኖዶስ አንድ ፓትርያርክ አንድ አስተዳደር እንዲኖራት ለማድረግ የተጀመረውን የእርቀ ሰላም አላማ በመደገፍ ልዑካንን በመሰየም የጀመራችሁት ሂደት አስደስቶናል። እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የራሷ መንበረ ፕትርክና ከማግኘቷ በፊት ለረጅም ዓመታት ከግብፅ በሚመጡ ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ማርቆስ ሥር ስትተዳደር መቆየቷ ይታወሳል። በነዚህ በሳለፈቻቸው ዘመናት የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲጠበቅ በነበራት ጽኑ አቋም ብዙ መስዋዕትነት ከፍላለች። ለብዙ ዘመናትም የነበረውን ችግር በማቃለል የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንደተጠበቀ የራሷን መንበረ ፕትርክና እንዲኖራት እድርገዋል። የቀደሙት አባቶችችን በተግባር ያስተማሩን ትምህርት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለመጠበቅ ሲባል የማይከፈል መሥዋእትነት አለመኖሩን ነው። ዛሬም የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚፈታተኑ መዋቅራዊ አንድነትን የሚያናጉ አለመግባባት እና መለያየት የሚፈጥሩ ችግሮች እየታዩ ምመጣታቸውና ውሳኔ የሚጠይቁ ጉዳዮች መብዛታቸውን ስንመለከት የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊና ሃይማኖታዊ አመራር መዋቅራዊ ተዋረዱን ጠብቆ መጠናከር እንዳለበት የስገነዝበናል።