Wednesday, January 2, 2013

“ቤተ ክርስቲያንን ለፈተና አጋልጠን ወደ ገዳም አንገባም” (ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ)

  • ከሰሜን አሜሪካ የተመለሱ የሰላም ልዑካን የጉዞ ሪፖርታቸውን ለሚ ሲኖዶስ ቅርበዋል።
  • የሰላም ልዑካኑ  ዕርቀ ሰላሙ መቀጠል እንዳለበት በአት አሳስበዋል፡፡
PDF
ሙሉዘገባውን የወሰድነው ከደጀ ሰላም ብሎግ ነው::
ላለፉት ሦስት ዓመታት  ሁለቱን ሲኖዶስ ለማስታረቅ ደፋ ቀና ሲል የነበረ አስታራቂ ጉባኤ ባወጣው መግለጫ መግለጫው ለሽምግልና ከተቋቋአካል አይጠበቅም በሚል  ተቃውቸውን የገለጡት ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጉባኤው ይቅርታ ካልጠቀ አብረውት ለመሥራት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
ይህንንም አአስቀድመው ይፋ ያደረጉት ወደ ሰሜን አሜሪካ ተላኩት ልዑካን  ሲሆኑ በመግለጫቸው አስታራቂ ስሕተት ፈጽሟል፣ ይቅርታ ካልጠየ አብረነው አንሠራም ማለታቸው የዕርቁ ተስፋ ላይ ጥላ አጥልቶበት ሰንብቷል፡፡ ከሊቃነ ጳጳሳቱ  መካከል ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ አዲስ አበባ  ከገባን  በላ መግለጫ  እናወጣለን  አሁን ምን ያስቸኩለናል ማለታቸውም ተጠቁሟል፡፡


ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሰሜን አሜሪካ የድርድር ጉዞ የተመለሱት ልዑካን ትናንት ማክሰኞ  ለቋሚ  ሲኖዶስ  የጉቸውን ሪፓርት በተለየ ቆራጥነት እንዲሁም ለዕርቁ መሰካት ጥረት መደረግ እንዳለበት በሚያሳስብ ብዓ አቅርበዋል፡፡ ልዑካኑ በሰሜን አሜሪካ ቆይታቸው ዕርቀ ሰላሙ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንደነበር ገልጠው እነርሱ በድርድር ላይ እንዳሉ አዲስ አበባ ይ የአስመራጭ ኮሚቴ መመረጡ የአስታራቂ ኮሚቴው መግለጫ እንዲያወጣና ጉዳዩ ወደ ግጭት እንዲያመራ እንዳደረገው አስታውሰዋል፡፡ አንዳንዶች “ስቶ ማሳት” ብለውታል። ልዑካኑ እጅግ እንዳዘኑ በገለጡበት በዚህ የአስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ ምክንያት የዕርቀ ሰላ ሂደ ለጊዜው ቢስተጎልም ሌሎች ሽማግሌዎችን በመጨመር መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

በትናንትናው ስብሰባ ከተገኙት መካከል በተለይም ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ‘’ካልተስማሙ ገዳም መግባት ይችላሉ እንደምትሉ ሰምተናል፡፡ ግን ገዳም አንገባም ቤተ ክርስቶያንን ለመከራ ትተን የትም አንሄድም ሕዝቡን እያናናን እስከ መጨረሻው እንዘልቃለን” ማለታቸው ተነግሯል፡፡ አረጋውያኑን አባቶች ገለል በማድረግ በብልጠት እየተሠራ ያለውን ሥራ  እንደማይቀበሉት የገለጹት ልዑካኑ ጉዳዩ በጥቂት ሊቃነ ጳጳሳት ብቻ የሚታይና የሚወሰን ባለመሆኑ ሁሉም አባቶች የሚገኙበት ስብሰባ እንዲጠራ አሳስበዋል። በመጀመሪያ  ከጥር  አራ ስድስት እስከ አራ ስምንት እንዲሆን ሳብ  የቀረበ ቢሆንም በመጨረሻ  ግን  ምልዓተ ጉዳቤው በጥር ስድስት እንዲደረግ እና ለዚህም በአገር ውስጥም ከአገር ውጪም ያሉት ሁሉም  አባቶች  ተልተው እንዲገኙ  እንዲደረግ ተወስኗል፡፡

ዕርቀ ሰላሙ አጠቃላይ ሁኔታ ላይ እንዲሁም ስለ ፓትርያርክ ምርጫ ጉዳይ ይነጋገራል ተብሎ በሚጠበቀው በጥር ስድስቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ላይ ሁሉም አባቶች የሚገኙ ከሆነ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ገንቢ የሆነ ዘላቂ ውሳኔ ይተላለፋል ተብሎ ከወዲሁ ተስፋ ተጥሎበታል። ምርጫው እንደ አበው ሥርዓት በዕጣ ሳይሆን ካርድ በመጣል የሚለውን ሐሳብ አጥብቀው የሚቃወሙት አባቶች እና በካርድ ይሁን የሚሉትና 6ኛ ፓትርያርክ ለማስቀመጥ ሰፊ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙት አባቶች መካከል ጠንካራ ውይይት መደረጉ እንደማይቀር ምንጮቻችን ገልጸዋል። የቅርቡን የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ምርጫ እንኳን እንደ ተሞክሮ አለመወሰዱ በእጅጉ ግራ ያጋባቸው ምንጮቻችን ከዕርቅ ይልቅ ለምርጫው ሰፊ ትኩረት መሰጠቱም በአባቶች መካከል ለተፈጠረው ልዩነት ዋነኛውም ምክንያት መሆኑን ያብራራሉ።

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃምና ብፁዕ አቡነ ቀለንጦስ የመሳሰሉት ሊቃነ ጳጳሳት ከዕርቀ ሰላሙ በፊት ምርጫውን እናስቀድም፣ አስመራጭ ኮሚቴው ሥራውን ይቀጥል፣ ምርጫው በቶሎ ይፈፀም በማለት ሲገቱ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብፁዕ አቡነ  ሉቃስ፣ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ፣ ብፁዕ አቡነ  ኤልሳዕ እና ሌሎችም ታላላቅ አባቶች በተቃራኒው ዕርቀ ሰላሙ ይቅደም ለምርጫ አንቻኮል በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ና ሌሎች ጥቂ የማይባሉ ሊቃነ ጳጳሳት  ደግሞ  አስመራጭ ኮሚቴ ለመምረጥ የፈረሙ ቢሆንም በችኮላ የተደረገ መሆኑን በመግለጥ ጉዳዩ በድጋሚ መጤን እንዳለበት እየተናገሩ መሆኑን የደጀ ሰላም ምንጮች አስረድተዋል፡፡
     
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።

1 comment:

Anonymous said...

ስለዚህ ዕርቁን በተመለከተ ምን መንገድ አለ?

1. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ለቤተ ክርስቲያን ሳላም ብዕትውናን መርጠው ፣ የፖትርክናን ክብር ንቀው(ለበጎ) ቅዱሳንን ተከትለው ለበለጠ ክብር እራሳቸውን ማጨት
2. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስን ለቤተ ክርስቲያን ሳላም ሲባል ከነሙሉ ክብራቸው ወደ መንበረ ፕትርክናው እንመልሳለ ብሎ መቀበል
3. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትሪያሪክ አድርጎ ሀገሩን እና ሁኔታውን የሚያውቅ ሊቀ ጳጳስ እንደራሴ መሾም
4. ከላይ የተዘረዘሩትን የሚቀበል ቢጠፋ እንኳን ምርጫውን ለእግዚአብሔር መስጠት፡፡ በሃይማኖት ለሚኖር ሰው ሁሉ ቀላል ነው፡፡ ዕርቀ ሰላሙን አድርጎ ፤ ውግዘቱን አንስቶ ሁሉም አባቶች ወደ ሃገር ተመልሰው፤ ሲባኤ ታውጆ አቡነ መርቆሪዎስ በመንበሩ ይቀመጡ ወይስ አዲስ ይመረጥ የሚለውን በዕጣ ለመንፈስ ቅዱስ ምርጫውን መስጠት ይቻላል፡፡ አሊያም እጩ ሆነው በምርጫ ከሚያልፉ ሶስት አዲስ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር አራተኛ የቅዱስነታቸው ስም አምስተኛ የእግዚአብሔር ስም ገብቶ እጣ ሊወጣ ይችላል፡፡ የእግዚአብሔር ስም ቢወጣ ሁሉንም ትቶ አዲስ ሦስት እጩዎች ለማግኘት እንደ አዲስ መስራት ይቻላል፡፡
5. ሰላም ተገኝቶ ይህ ሁሉ ማድረግ ባይቻል እንኳን 4ተኛው ፖትሪያሪክ በህይወት እያሉ ሌላ ፓትሪያሪክ አለመሾም ለምን ቢሉ የተሻለ ሰላም የሚያመጣ ከሆነ በፓትሪያሪክ ከተመራንበት ጥቂት አሥርት ዓመታት ይልቅ በመንበረ ማርቆስ ሊቀ ጳጳሳት የተመራንበት ስለሚበዛ
6. ሌሎችም
....ከማይቀበሉት ፕትርክና የሚቀበሉት ምንኩስና ይበልጣል!