Wednesday, April 23, 2014

በብፁዕ አቡነ ዘካርያስ ሥልጣነ ክህነት የተያዘባቸው መልአከ ኃይል ጌታሁን መኮነን በቀድሞ አቋማቸው


የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ መልአከ ኃይል ጌታሁን መኮነን ብፁዕ አቡነ ዘካርያስ በተገኙበት ውይይት ላይ የቤተ ክርስቲያን አንድነት እንዲመጣ ያስተላፉት መልዕክት ነበረ። መልአከ ኃይል ጌታሁን መኮነን በአሁን አቋማቸው የሚኒያፖሊስ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን "በገለልተኝነት አሥተዳደር ይቀጥል" ከሚሉ ወገኖች በመሰለፋቸው ብፁዕነታቸው ሥልጣነ ክህነትታቸውን አግደውባቸዋል።

Tuesday, April 22, 2014

ብፁዕ አቡነ ዘካሪያስ የአራት ካህናት ሥልጣነ ክህነት አገዱ

በሰሜን አሜሪካን በሚኒያፖሊስ ከተማ በሚኒሶታ ግዛት የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውዝግብ ከአንድ ዓመት በላይ ፈጅቶ በዘንድሮው በዓለ ትንሣኤ ዕለት አባላቱ ለሁለት ተከፍለው በዓሉን በተለያየ ቦታ አክብረው ዋሉ። ይህ ውዝግብ ከመነሻው ጊዜ ጀምሮ ለአሐቲ ተዋሕዶ በቅርበት መረጃዎች ይደርሱ ነበረ። የቤተ ክርስቲያናችን የውስጥ ችግሮች ለውጭ አካላት አሳልፎ ላለመስጠት ጉዳዪን ላለመዘገብ ተቆጥበን ነበረ። የዚህ አጥቢያ ምእመናን እና ካህናት ለሁለት ተከፍለው ሲወዛገቡ ከአንድ ዓመት በላይ ፈጅቶባቸዋል። ሚኒያፖሊስ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በገለልተኛ አሥተዳደር ሥር ቆይቶዋል። ሦስት አስርተ ዓመታት ለማስቆጠር ጥቂት ዓመታትን የቀረው ይህ አጥቢያ በገለልተኛ የቦርድ አስተዳደር ሥር ቆይቶ ነበረ። 

ሆኖም ግን “የገለልተኛ አስተዳደር ይብቃን እና ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደረ መዋቅር ሥር እንቀላለቅል” የሚሉ ወገኖች አማካኝነት የዛሬ አንድ ዓመት ከሦስት ወር አካባቢ ለአስተዳደር ቦርድ ጥያቄ ቀርቦ ነበረ። በዚህም ምክንያት የአስተዳደር ቦርድ ይህንን ጥያቄ ሁለት አመለካከት ያላቸው ማለትም “ወደ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር መዋቅር እንቀላቀል” የሚል አቋም ያላቸው እና “አይ በገለልተኛ የአስተዳደረር እንቆይ” የሚል አቋም ያላቸው ሁለት ቡድኖች ለአስተዳደር ቦርዱ እና ለአባላት ጥናት እንዲቀርብ ኮሚቴ አዋቅሮ ነበረ። ከሁለቱንም ወገኖች ያካሄዱትን ጥናታዊ ጽሑፍ ለአስተዳደር ቦርዱ አቅርበው በመጨረሻም ለቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት በሙሉ በነሐሴ ወር አካባቢ ጥናቱ ቀርቦ ነበረ። ጥናታዊ ጽሑፍ በቀረበት ዕለት “በድምጽ ይወሰን አይወሰን” በማለት አባላቱ ተከራክረው በመጨረሻም ካህናቱ ምእመናን ይከፋፈሉብናል በሚል ፍራቻ “ለጊዜው እንዲሁ እንዳለን በገለልተኝነት እንቆይ” አሉ። የካህናት ሃሳብ ተቀባይነት አግኝቶ ድምጽ ሳይሰጥ በገለልተኛ አስተዳደር ለጊዜው እንዲቆዪ ተስማምተው ለጥናታዊ ጽሑፍ የታደመ አባላት ድምጽ ሳይቆጠር ተበተነ። 

Friday, March 22, 2013

“የማልስማማባቸው የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሃይማኖታዊ ትንታኔዎች” አዲስ

 READ IN PDF
ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የወቅቱ የቤተክርስቲያን ጉዳይን በሚመለከት ከላይፍ መጽሄት የመጋቢት ወር እትም ቁጥር 102 ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ነው:: ቃለ ምልልሱን በመጀመርያ ያነበብኩት አንድ አድርገን የተባለ ብሎግ ካወጣው በኋላ ነበር:: ጋዜጠኛው ያነሳቸውን ጥያቄዎች በቤተ መንግስትና ቤተ ክህነት ላይ ያተኮሩ ነበሩ:: የቀድሞው ፓትርያርክ የአቶ ታምራት ላይኔ እና የአዲሱ ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስንም ጉዳይ ተነስቷል:: የዲያቆን ዳንኤልን መልስ ግን ለኔ አስገራሚ ነበር:: የሰጣቸው በርካታ ምላሾች ሊዋጡልኝ አልቻሉም:: በአንዳንዶቹ አስተያየቶቹ ደግሞ ፈጽሞ አልስማማም:: ጥቂቶቹን በሦስቱ ፓትርያርኮች ዙርያ ላንሳ፦

ፓትርያርክ ጳውሎስ
የላይፍ ጋዜጠኛ ÷ ከአቡነ ጳውሎስ ንብረት ጋር በተያያዘ ላቀረበለት ጥያቄ ዲያቆን ዳንኤል የሰጠው መልስ እንዲህ የሚል ነበር::
"ንብረት በመያዝና በማስቀመጥ ረገድ እሰከ አሁን ብዙ ያልተሰማባቸው አባት አቡነ ጳውሎስ ናቸው፡፡
ምናልባት ዘመዶቻቸው ረድተው ይሆናል ካልተባለ በቀር ብዙ ንብረት የላቸውም፡፡"

Saturday, February 16, 2013

ክርስቲያኑ ኢትዮጵያዊ መብቱን ለማስከበር ያልቻለባቸውና የማይችልባቸው ምክንያቶች

ይህ ጽሑፍ የአቅማቸውን ጥቂት ነገር ለማድረግ የሚተጉትን ላይመለከት ይችላል።
  ከደጀ ሰላም ብሎግ የተወሰደ ሐተታ ነው::  PDF
 ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን በኢትዮጵያ እየተስፋፋ በመጣው እምነትን በነጻ የማራመድ መብት ገፈፋ ዋነኛ ተጠቂ ከሆኑት ኢትዮጵያውያን መካከል ኦርቶዶክሱ ክፍል ዋነኛ ተጠቃሽ ነው። በወታደራዊው የደርግ ዘመን የነበረውን ግፍና መከራ እንኳን ለጊዜው ብናቆየው “የሕዝብ ብሶት ወለደኝ” ያለው የኢሕአዴግ መንግሥት ከተመሠረተ ወዲህ ቤተ ክርስቲያናችን በዓይነ ቁራኛ ከመታየት እስከ የ“ነፍጠኛ ጎሬ” እስከመባል ድረስ ብዙ ዘለፋ አስተናግዳለች። ከዚያም ገፋ ሲል በአንዳንድ አክራሪዎች ምእመናኗ ታርደዋል፣ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ ከየአካባቢው እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል። ለዚህም በስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ የሚያራምደው ፖሊሲ ሁነኛ ምክንያት ነው።